YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዛሬ በወላይታ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የ2012 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ በወረዳው ዋና አሰተዳደር በሆኑት በአቶ ዘውዱ ሣሙኤል አብሳሪነት በይፋ ተጀምሯል፡፡በእለቱ በቦታው የዞን አመራር አካላት ፡ የሃይማኖት መሪዎች የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ባለሙያዊችና አመራሮች ተገኝተው በጋራ በመሆን የተፋሰስ ሥራውን አሰጀምሯል፡፡

ምንጭ: የዞኑ አስተዳደር
@YeneTube @FikerAssefa
ትናንት ምሽት 22 አካባቢ ስለተፈጠረው ሁኔታ በጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት👇👇

ትናንት ምሽት ከለሊቱ 7 ሰአት አካባቢ ጀምሮ 22፣ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ጀርባ ረብሻ መከሰቱ ይታወቃል! ዛሬ ጠዋት ወደ ስፍራው ሄጄ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ ሀይሎች ይታዩ ነበር። በአካባቢው ያሉ ሱቆች በአብዛኛው ዝግ የነበሩ ሲሆን ህዝቡ ላይ የመደናገጥ ስሜትም ይታያል። ችግር ወደተከሰተበት ቦታ ለማለፍ ግን ክልክል ነበር።ስለነበረው ክስተት የአካባቢውን ነዋሪዎች እና የክፍለ ከተማውን ሀላፊ አናግሬ ነበር።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ "ቤተ ክርስቲያን ተሰራበት የተባለው ቦታ ለአመታት ባዶውን የቆየ እና ምንም አገልግሎት ሳይሰጥ የነበረ ነው። ባለፈው እሁድ ከክፍለ ሀገር የመጡ የሀይማኖት አባቶች ቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራ ብለው ሀሳብ አመጡ። ከዛ ጀምሮ ወከባ ሲደርስባቸው ነበር። ትናንት ጭራሹኑ በጥይት እና አስለቃሽ ጭስ ህዝቡን ሲያሰቃዩት ነው ያደሩት። ቀን ላይ ምንም ሳይሉ በለሊት መጥተው ይህን ሁሉ ማረጋቸው ግራ ገብቶናል። የተተኮሰው ጥይት ብዙ ሰው አቁስሏል፣ ሁለት የሞቱ ሰዎች እንዳሉም እየሰማን ነው" ብሎኛል።ሌላ ማታ የነበረውን ሁኔታ ያየ ግለሰብ ደግሞ "በሰላም ማስለቀቅ ይቻል ነበር። እናቶች፣ አባቶች እና ህፃናት ሲሰቃዩ አድረዋል። ዛሬ ጠዋትም ፖሊሶች አካባቢውን ከበዋል" ብሏል።

የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ፈቃዱ በበኩላቸው ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራ የታሰበው ቦታ ለአረንጓዴ ስፍራ የተተወ ነው ይላሉ። አክለውም "ይህ ሆን ተብሎ ፅላት እንኳን ሳይገባ የተደረገ መሬት የመያዝ ስራ ነው። እነዚህ በቅርቡ በተደጋጋሚ እየታዩ ያሉ ድራማዎች ናቸው" ብለዋል።
አቶ ጥላሁን ጨምረው እንዳሉት "ጉዳዩን ወረዳውም፣ ፖሊስም ከካህናት ጋር ሲወያይ ነበር። ነገር ግን እናነሳለን ብለው እድሜ ከማራዘም ውጪ ምንም አላደረጉም። ከሌላ ቦታ የመጡ ወጣቶች ነገሩን እንዲያባብሱት ተደርጓል። ከዛም የከተማው ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ ህግ እንዲያስከብሩ ተደርጓል። በዚህ ወቅት የፖሊስ መኪና አቃጥለዋል።"

"ለምን ቦታው ላይ የእምነት ተቋም መሰራት አይችልም?" ለሚለው ጥያቄዬ አቶ ጥላሁን ሲመልሱ "እዛው ጋር ቤተ ክርስቲያን አለ። ህጉም አይፈቅድም፣ ተገቢው ቦታም አይደለም" ብለዋል።

"ለምን እርምጃው ለሊት ላይ ተደረገ?" ብዬ ለጠየቅኩት ሲመልሱ ደግሞ "እንደዚህ አይነት ስራዎች ብዙ ግዜ የሚሰሩት ማታ ላይ ነው። ቀን ላይ ከሆነ ቀውሱ ይበዛል። ከዚህ በፊት ሁለት ግዜ ቀን ላይ ተሞክሯል፣ አልሆነም። ሌላ ተአምር የለውም" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ።

ምንጭ: የሚንስትር መ/ቤቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ
@YeneTube @FikerAssefa
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለ33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እንግዶች በሚያልፉበት ወቅት ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረትም ፡-
📌 ከቦሌ አየር መንገድ-በሚሊኒየም አዳራሽ-ወሎ ሰፈር-ኦሎምፒያ መስቀል አደባባይ-ብሄራዊ ቤተመንግስት-ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ-ሸራተን አዲስ-አራት ኪሎ፣
📌 ከቦሌ አየር መንገድ-በሚሊኒየም አዳራሽ-ወሎ ሰፈር-ኦሎምፒያ-ጋዘቦ-በአዲሱ መንገድ-ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ-ቡልጋሪያ ማዞሪያ-አፍሪካ ህብረት፣
📌 ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር-አደባባይ-ብሄራዊ ቤተመንግስት-በፍል ውሃ-ብሄራዊ ትያትር-ሜክሲኮ አደባባይ-አፍሪካ ህብረት፣
📌 ከአራት ኪሎ-ሸራተን ሆቴል-ሀራምቤ ሆቴል-ብሄራዊ ትያትር መብራት ወይም አንድነት መብራት-ሰንጋ ተራ-ዋቢ ሸበሌ-ምክሲኮ አደባባይ-ትምባሆ ሞኖፖል-አፍሪካ ህብረት፣
📌 ከቦሊ አይር መንገድ-በሚሊኒየም አዳራሽ-ወሎ ሰፈር-ኦሎምፒያ-መስቀል አደባባይ-ብሄራዊ ቤተ-መንግስት-ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ-አራት ኪሎ እንግዶች በሚያልፉበት ወቅት ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ናቸው።ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱት መንገዶች ዝግ በሚሆኑበት ሰዓት ህብረተሰቡ የሚከተሉትን ተለዋጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ከጦር ሃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች፦
📌 በኮካ ኮላ ድልድይ-በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ
የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች
📌 በአትላስ-ዘሪሁን ህንጻ-ሲግናል
📌 በቀለበት መንገድ-መገናኛ-ዲያስፖራ አደባባይ-እንግሊዝ ኤምባሲ
📌 በቀለበት መንገድ-መገናኛ-አድዋ ጎዳና-አዋሬ አራት ኪሎ ያትን መንገዶች በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ቻይና በረራ ማቆም ኮሮና ቫይረስን አያስቀርም ተወልደ ገብረማርያም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የተወሰኑ አየር መንገዶች ወደ ቻይና መብረር ቢያቆሙም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መብረሩን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ዋና ስራ አፈጻሚው አያይዘው በረራን ማቋራጡ ቫይረሱን አያስቀረም ፤ ዋስትናም አይሆንም ያሉ ሲሆን በአለም ጤና ድርጅት የተቀመጡ የጥንቃቆዎችን በመተግበር በመነሻ ፤ በመድረሻ እንዲሁም በጉዞ ወቅት በመተግበር በረራውን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

#coronavirus
@YeneTube @Fikerassefa
ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ትናንት ማታ ከተፈጠረው ክስተት ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚድያ ገፃቸው ያሰፈሩት👇👇

"ከየትኛውም ጊዜ በተለየ ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርበን እየሰራን እንገኛለን።ከስራችን ጅማሬ አንስቶ የደከምንበት የሃይማኖት ተቋማት ጥያቄዎች ምክንያት አንድም የሰው ሕይወት ይጠፋል ብለን አስበን አናውቅም።በተለይም የይዞታ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ ረጅም ርቀት ሄደን ጥያቄዎችን ስንመልስ ቆይተናል።ይሁን እንጂ በመንግሥት እና በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ ጥቂት አጥፊዎች ምክንያት በከተማችን ይሆናል ያላልነው ፤እንዳይሆንም የለፋንበት ድርጊት ተፈጽሟል።

ከተማችንን በመለወጥ ሂደት ውስጥ ህይወታቸው ይለወጣል ብዬ ከማስብላቸው ወጣቶች ሁለቱን አጥተናል።እነዚህን ወጣቶች ለማጣት ያበቁንን በየትኛውም ወገን ያሉ የጥፋቱ አካላትን በሕግ እንዲጠየቁ እናደርጋለን።በጥፋቱ ወንድሞቻችንን አጥተናል። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ። እጅግ አዝኛለሁ።"

@YeneTube @FikerAssefa
በዴዴሳ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በቡኖ በደሌ ዞን ዴዴሳ ወረዳ ትላንት ምሽት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።አደጋው የደረሰው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-80032-ኢት የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት ዲቪዥን አስተባባሪ ኢንስፔክተር በኃይሉ ገዛኸኝ ገልጸዋል።

ተሽከርካሪው ሰዎችና እህል ጭኖ ከበደሌ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እንዳለ በወረዳው ርዕሰ ከተማ ደምቢ ሲደርስ በመገልበጡ አደጋው መድረሱ ተገልጿል።በአደጋው ሾፌሩን ጨምሮ ተሳፍረው የነበሩ አራት ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ የሟቾችንም አስከሬን ቤተሰቦች እንዲረከቡ መደረጉን ሃላፊው ገልጸዋል።በወቅቱ በመንገድ ላይ የነበረና በተሽከርካሪው ተገጭቶ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰበት አንድ ታዳጊ ወጣት በወረዳው ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን ኢዜአን ጠቅሶ ፋና ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በረራ ማቆም ዋስትና አይሰጥም - አቶ ተወልደ ገ/ማርያም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተገናኘ ወደ ቻይና በረራ ማቆሙ ዋስትና እንደማይሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ገለፁ።ዋና ስራ አስፈጻሚው አየር መንገዱ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተገናኘ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቋርጥም ለፋና ተናግረዋል።አየር መንገዱ በርካታ ዓለም አቀፍ በረራዎችን እንደማድረጉ ወደ ቻይና ብቻ በረራ ማቆም ዋስትና እንደማይሆንም ነው የተናገሩት።

ወደ ቻይና የሚደረገው በረራ ቢቆም እንኳን የቫይረሱ ተጠርጣሪዎች ወዳሉባቸው ሀገራት በረራ እንደማድረጉ ከስጋቱ ነጻ መሆን አይቻልም ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፥ አየር መንገዱ በትራንዚት ከሌሎች መዳረሻዎቹ በርካታ ቻይናውያንን እንደሚያጓጉዝም ጠቅሰዋል።መፍትሄው ለደንበኞች እና ሰራተኞች ጤንነት ጥንቃቄ ማድረግ ብቻ ነው ሲሉም አስረድተዋል።በመሆኑም ቫይረሱን ለመከላከል አየር መንገዱ በመዳረሻ ሀገራትም ሆነ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከፍተኛ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።አያይዘውም የዓለም ጤና ድርጅት የጉዞ እገዳ ማድረግ እንደማይገባ ያቀረበውን ምክር እናከብራለን ብለዋል።

70 በመቶ ቻይናውያን መንገደኞች በትራንዚት አዲስ አበባን እንደሚረግጡ ያነሱት አቶ ተወልደ፥ በማግለል መፍትሄ እንደማይመጣ መረዳት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።ከዚህ ቀደምም የኢቦላ ወረርሽኝ ባጋጠመ ጊዜ አየር መንገዱ የሚያደርገውን በረራ አለማቆሙን አስታውሰዋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት 35 በረራ ወደ ቻይና ያደርጋል።የብሪታኒያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በረራ ቢያቆምም የቻይና አየር መንገድ ግን በቀን በርካታ በረራዎችን ወደ ብሪታንያ እያደረገ ይገኛል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ቴፒ ከተማ በተነሳ ግጭት 8 ሰዎች ሞቱ፤ ከሃያ በላይ ቆሰሉ!

ከከተማው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግጭቱ ትናንት አመሻሽ አካባቢ የተከሰተው ልዩ ሀይል በሚል የሚጠራው የክልሉ የጸጥታ አባላት በአንድ ግሮሰሪ ውስጥ በመጠጣት ላይ የነበሩና በህግ ይፈለጋሉ ያሏችውን ግለሰቦች ለመያዝ መሞከራቸውን ተከትሎ ነው። በከተማው ከርጫ በር በተባለው ሰፈር በጸጥታ አባላቱና ተጠርጣሪ በተባሉ ግለሰቦች መካከል የተከሰተው አለመግባባት ወደ ሁከት በማምራት ወደ ሌሎች የከተማዋ ክፍሎች መዛመቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በከተማው ለሰዓታት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንና አስከአሁንም ስምንት ሰዎች በጥይት ሲሞቱ ከሃያ በላይ የሚሆኑ መቁሰላቸውን በአካባቢው ነበርን ያሉ የአይን አማኞች ለዶቼ ቨለ ገልጸዋል። ከሟቾቹ መካከል አንዱ የክልሉ ልዩ ሀይል የጸጥታ አባል ሲሆን የተቀሩት ሰባቱ የከተማው ሲቪል ነዋሪዎች ናቸው ያሉት የአይን አማኞቹ << በአሁኑወቅትም በከተማው የግልና የመንግስት ተቋማት ተዝግተዋል ፣ ነዋሪዎች በስጋት በየቤታቸው ተቀምጠው ይገኛሉ ፣የከተማዋ ጎዳናዎችም አሁን ድረስ የህዝብ እንቅስቃሴ አይስተዋልባቸውም >> ብለዋል። ስለጉዳዩ የተጠየቁት የቴፒ ከተማም ሆኑ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊዎች << በከተማው ግጭት መከሰቱ እውነት ነው። የግጭቱ መነሻና የደረሰው ጉዳትም እየተጣራ ይገኛል። መረጃዎች ተሰብስበው ባልተጠናቀቁበት ሁኔታ እንዲህ ነው ለማለት እንቸገራለን >> ብለዋል።

በደቡብ ክልል ሸካ ዞን የምትገኘው የቴፒ ከተማ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በአካባቢው በተነሳው የአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ ይታወቃል። በከተማው በተያዘው ወር ብቻ ሁለት ወንማማቾችን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች < ያልታወቁ > በተባሉ ታጣቂ ቡድኖች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው የሚታወስ ነው። በአካባቢው በሚስተዋለው የፀጥታ ስጋት የተነሳም በአሁኑወቅት ከተማዋን ከሚዛን ፣ ከጅማና ከማሻ ከተሞች የሚያገናኘው መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ ይገኛል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ቤተክርስቲያን ልትፈርስ ነው ብለው ቄሶች ጥሪ አቀረቡ ህዝቡም ወጣ

በነበረውም ተኩስ ሰዎች ሞቱ።” ነዋሪዎች


ወንድሟ በጥይት ተመቶ አቤት ሆስፒታል የተኛባት ቅድስት ሀይሉ ስለነበረው ክስተት እንዲህ ስትል ለፊደል ፓስት ተናግራለች ።” ይሄ 22 ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ጀርባ የሚገኘው ቦታ ለረጅም አመታት ታጥሮ የቆየ ነው። ምን አልባት 17 አመት በላይ። ለቤተክርስቲያንም አገልግሎት እንዲሆነ ከተጠየቀ ቆይቷል። ባለፈው ቅዳሜ የአርሴማ ማርያም እና የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ገብቶበት አገልግሎት ጀመረ።

ፓሊሶች ትናንት እኩለ ለሊት ካለፈ በኋላ ቦታውን ለማፍረስ መጡ ።በሁኔታው የተደናገጡት ቄሶች በማይክራፎን ምእመኑን የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ ። የአካባቢውም ህዝብም ግልብጥ ብሎ ወጣ።

አስለቃስ ጭስ ተተኮሰ ፣ተከታታት ተኩሶች ነበሩ።
የፓሊስም መኪና ተቃጠለ። ጩኸት ለቅሶ ይሰማ ነበር።የፌዴራል ፓሊስም ብዛት ቦታዉን የተወረረ ከተማ አስመሰለው። ህልም እንጂ እውን አይመስልም በዚህ ክስተት ሁለት ሰዎች ሞቱ ።

የእኔን ወንድም የግራ እጅኑ ተመታ ።ወደ 15 ሰውም ቆሰለ። አምቡላንስ ተጎጂዎችን ኮርያ እና አቤት ሆስፒታል እይሰዱ ነበር። ሲነጋ የአካባቢው ሱቆች ተዘግተው ባለቤቶችም ስለተፈጠረው ነገር ግራ ገብቷቸው ስለሞቱት ሰለቆሰሉት ሰዎች በጣም አዝነው እያወሩ ነበር።

ፓሊሶች ማፍረስ ከፈለጉ ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጋር ተማክረው መፍትሄ ማበጀት ይችሉ ነበር ።ለሊት እንደሌባ መጥተው ማፍረሳቸው የሰው ሒወት አሳጥቶናል ።”

የአካባቢው ፓሊስ መምሪያ በሰጠው ምላሽ ህገወጥ ግንባታዋን በቀን ማፍረስ ሁከትን ያባብሳል ተብሎ ነው በማታ ለማፍረስ ታቅዶ የነበረው የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ቦታውን እንዲፈርስ ቢጠይቅም ሰሚ አካል አለማግኘቱን ተናግረዋል።

Via:- fidelpost.com
@Yenetube @Fikerassefa
ወደ ደቡብ አፍሪካ የተላከው የአራቱም ሰዎች ናሙና ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆኑ ተረጋገጠ!

በቅርቡ ለተጨማሪ የላቦራቶሪ ምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ የነበረው የአራቱም ሰዎች ናሙና ከኖቭል ኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆኑ መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ማምሻውን በፌስቡክ ገፁ ባሰራጨው መልዕክት አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል።

ትላንት ምሽት 22 አካባቢ ከቤተክርስቲያን ግንባታ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ወጣቶች ህይወት ማለፉን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ኢ/ር ታከለ ኡማ ክስተቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸው አስተዳደሩ ጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡እስካሁንም ከጥፋቱ ጋር ግኑኝነት አላቸው በሚል የተጠረጠሩ አመራሮችን ጨምሮ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ማጣራቱም እንደቀጠለ ገልጸዋል፡፡ከጥፋቱ ጋር በተያያዘ የተደራጁ መርጃዎች እየተገኙ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ፡፡

አስተዳደሩ ከምንጊዜው በላይ ከኃይማኖት ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት ኢ/ር ታከለ በተለይም ከኃይማኖት ተቋማት ይዞታ ጋር በተያያዘ አፋጣኝ ምላሾች እየተሰጡ እንደሆነ ችግሮች ሲኖሩም በመነጋገር እየተፈቱ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡በትላንትናው ምሽትም የኃይማኖት ተቋሙ የተገነባበት ቦታ ተገቢ ባይሆንም በለሊት ለማፍረስ መኬዱ ተገቢ ባለመሆኑ ትእዛዝ የሰጠው አካል ላይ ማጣራት እየተደረገ እንደሆነና ተገቢው እርምጃም እንደሚወሰድ እንዲሁም ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ኢ/ር ታከለ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ያለው የጠበቀ ግኑኝነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ኢ/ር ታከለ፡፡በጥፋቱ ህይወታቸውን ያጡ ወጣቶች ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን የተመኙት ኢ/ር ታከለ የተጎጂ ቤተሰቦችን የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሰላም ሚኒስቴር 12 የእርሻ ትራክረተሮችን ገዝቶ ለክልሎች አስረከበ። የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም በ28 ሚሊየን ብር የገዛቸውን የእርሻ ትራክተሮች ለጋምቤላና ለቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አስረክቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የውሃ መሰረተ ልማት ላይ ባእድ ነገር የጨመሩ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንች ተያዙ!

ባለቤትነቱ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የሆነ የፍሳሽ መሰረተ ልማት ላይ ባእድ ነገር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለስልጣኑ አስታወቀ፡፡ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፋብሪካ ተረፈ ምርት በቦቴ ተሸከርካሪ በማጓጓዝ በባለስልጣኑ የፍሳሽ መስመር ውስጥ ሲደፉ በመገኘታቸው ነው፡፡ጥር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት በተለምዶ ጠማማው ፎቅ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ባእድ ፍሳሹን ወደ መስመር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች ከነተሸከርካሪው በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ተናግረዋል

ምንጭ:ኢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

ትናንት በቦሌ ክ/ከተማ 24 ቀበሌ አካባቢ ከተከሰተው ክስተት ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ለኢትዮ ኤፍ.ኤም መግለጫ ሰጥተዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ መረጃዎች የሀሰት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገግጿል፡፡ፖሊስ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በቀጣይ በምርመራ የሚያገኘውን ውጤት ለህዝብ የሚገልፅ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት የሚውል የ100 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አድርገዋል።

ምንጭ: ፎርብስ
@YeneTube @FikerAssefa
አንድነት ፓርክ ከቅዳሜ ጥር 30 እስከ ረቡዕ የካቲት 4 ድረስ ለጎብኚዎች ዝግ እንደሚሆን እየገለፅን በእነዚህ ቀናትም ፓርኩን ለመጎብኘት ትኬት አስቀድማችሁ የቆረጣችሁ ጎብኚዎች ከሀሙስ የካቲት 5 ጀምሮ ጉብኝታችሁን ማከናወን የምትችሉ መሆኑን ከፓርኩ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ያለፈው 24 ሰዓት ከእስካሁኑ ከፍተኛ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች የተመዘገቡበት መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት WHO አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ ከ24,500 በላይ ሰዎች የተጠቁ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም 492 ደርሷል።

Photo:Worldwide የቫይረሱ ስርጭት
ምንጭ:CNN
@YeneTube @FikerAssefa