ምርጫ ቦርድ ምርጫ 2012ን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት እያደረገ ሲሆን በምርጫው ጊዜ ሰሌዳ እና አፈፃፀሙ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መነሳታቸውን ቦርዱ ካወጣው መረጃ ለመረዳት ችለናል፡፡
በውይይቱ ላይ የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፣
1) የመራጮች ምዝገባ ጊዜ 30 ቀናት ያንሳል
2) የእጩ ምዝገባ ቀናት አንሷል፣ ቢታሰብበት !
3) ቀኑ ክረምት ላይ በመዋሉ ለማስፈፀም ያስቸግራል፣ ጥቅምት/ህዳር ላይ ለምን አይሆንም?
4) በምርጫ ዘመቻ ወቅት ወከባ እንዳይፈጠር ቦርዱ ዝግጅት ቢያደርግ?
5) የምረጡኝ ቅስቀሳ ቀናት ያንሳሉ፣ ከአሁን ጀምሮ ቅስቀሳ የጀመሩ ፓርቲዎችም አሉ፣ ቦርዱ ምን ይላል?
6) ፓርቲዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ የሚደረደሩበት ቅደም ተከተል በእጣ ይሆናል ማለት ምን ማለት ነው?
#ምላሽ
1)የመራጮች ምዝገባ በህግ የተቀመጠ 30 ቀን ነው።
2)የእጩ ምዝገባ ቀናት በህግ በተቀመጠ መልኩ ይታያል፣ አስፈላጊ ከሆነ ቀናት መጨመሩን ቦርዱ ሊያየው ይችላል ግን በእቅዱ ላይ የተቀመጠው ቀን ለፓርቲዎች አያንስም እንደውም ጫና የሚሆነው ቦርዱ ላይ ነው።
3) ነሃሴ ላይ ምርጫው መካሄዱ ቦርዱ ወዶ የገባበት ሳይሆን ግንቦት ለማድረግ ስላልተቻለ ነው፡፡ ብዙ የተዘረዘሩ ለውጦች እያደረገ እንደሆነ የገለፀው ቦርዱ፣ በዚህም ምክንያት ግንቦት ላይ ማድረግ የሚቻል አይደለም ብሏል፡፡ አፈፃፀሙ ክረምት በመሆኑ ብዙ ችግር እንደሚገጥመው እሙን ነው ከክልል መንግስታት፣ ከፌደራል መንግስትና ሌሎች ተቋማት ቦርዱ የሎጀስቲክስ ድጋፍ ጠይቆ ለማስፈፀም ጥረት ያደርጋል። ከመስከረም ካለፈ ደሞ የህግ ጥሰት ይፈጥራል ስለዚህ ወደፊት መግፋት አልተቻለም ሲል ገልፅዋል ቦርዱ፡፡
4) በምርጫው ዘመቻ ጊዜ ወከባ እና ችግር እንዳይኖር ቦርዱ ጥረት ያደርጋል፣ ከዚህ በፊት ፓርቲዎች ችግር ሲገጥማቸው ቦርዱ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፣ አሁን ይህንን ድጋፍ ለማስፋት በምርጫ ዘመቻ ወቅት የራሱ ዴስክ አዘጋጅቶ ተቋማዊ ድጋፍ ያደርጋል…
5) የምረጡኝ ቅስቅሳ አሁን መጀመር አይቻልም፣ የተሰጠው ከሶስት ወራት በላይ ጊዜ በቂ ነው፣ ከአሁኑ ቅስቀሳ የጀመሩ አሉ ለተባለው ውይይት እና ንግግር ከህዝብ ጋር ማደረግ ይቻላል፣ እኔን ምረጡኝ የሚል ዘመቻ ግን መጀመር አይቻልም፣ ያንን የሚያደርጉ ፓርቲዎች ላይ ቦርዱ ማጣራት ያደርጋል።
6) ፓርቲዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚደረደሩበት ቅደም ተከተል ሲባል የሚደረደሩበት መንገድ በእጣ የሚወሰን ይሆናል እንጂ ከዚህ በፊት እንደነበረው አይሆንም። እጣው ላይ በሚደርሳቸው ቅደም ተከተል መሰረት ፓርቲዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ በቅደም ተከተል ይቀመጣሉ።
ምንጭ፦የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ውይይት ያገኛቸውን ግብዓቶች ያካተተ ይፋዊ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ የሚያሳውቀው የፊታችን ጥር 23 ቀን 2012 በርካታ ተሳታፊዎች በሚገኙበት ኮንፍረንስ ላይ ነው። #ምርጫ2012 #Ethiopia
Via NEBE
@YeneTube @FikerAssefa
Via NEBE
@YeneTube @FikerAssefa
ከዓለማቀፉ የአውቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ በተገኘ ድጋፍ ‹ሳይክሎትሮን› የተሰኘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የካንሰር ምርመራ እንዲሁም ሕክምና ለማድረግ የሚያስችል መሣሪያ ለመግዛት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው መሣሪያው፣ የካንሰር ምርመራን ለማከናወን ከማገዙም በላይ የካንሰር ሕክምና እንዲሁም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያደረጉ ግለሰቦችን የጤና ሁኔታ ለመከታተል እንደሚረዳ ተገልጿል።
Via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa

የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ አመንቴ ገሺ ትናንት መታሰራቸውን ፓርቲያቸው ዐስታወቀ።
ሊቀ መንበሩ በምርጫ ቦርድ ጥር 7 እና 8 ቀን 2012 ዓ.ም ሁሉንም ፓርቲዎች ለማወያየት በተዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ተደርጎላቸው ከአሶሳ ቦሌ አየር ማረፍያ እንደደረሱ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዩች ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለዶቼቬለ ዐስታውቀዋል።
ዶቼቬለ ስለ ጉዳዩ የጠየቃቸው የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጁላን አብዲ ጉዳዩን እናጣራለን ነገር ግን እስካሁን የደረሰን ሪፖርት የለም ብለዋል።
የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታሁን መርጋ እና የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ጌታቸው ወድሻም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ለማግኘት ጽ/ቤት መክፈት አለባችሁ ባላቸው መሰረት ባለፈው ሳምንት በአሶሳ ከተማ ጽ/ቤት ከከፈቱ በኋላ ፖሊስ እንዳሰራቸው አቶ ዮሐንስ አክለው ተናግረዋል። ሁለቱን ፖለቲከኞች ፖሊስ ያሰራቸው ጽሕፈት ቤት መክፍት አትችሉም በማለት ነውም ብለዋል።
ጉዳዩን ለማጣራት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሐመድ አምደኒል ጋር ብንደውልም ስልክ አያነሱም።በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀስ ተቃዋሚው የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የተመሰረተው በመስከረም 2012 ዓ.ም ነው።
ምንጭ:- የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስተዳደር የሚያደርስባቸው የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ሠራተኞች ተናገሩ::
ይሁን እንጂ አየር መንገዱ በበኩሉ ተቋሙ በጥብቅ ሥነ-ምግባር በመመራቱ የተቋሙን ገጽታ ለማጠልሸት ጥረት የሚያደርጉ ሠራተኞች ወቀሳ ነው ሲል ክሱን አስተባብሏል።
ምንጭ:- ኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ / አዲስ ማለደ
@YeneTube @FikerAssefa
ይሁን እንጂ አየር መንገዱ በበኩሉ ተቋሙ በጥብቅ ሥነ-ምግባር በመመራቱ የተቋሙን ገጽታ ለማጠልሸት ጥረት የሚያደርጉ ሠራተኞች ወቀሳ ነው ሲል ክሱን አስተባብሏል።
ምንጭ:- ኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ / አዲስ ማለደ
@YeneTube @FikerAssefa
የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ለመከላከል በሚል አዲስ የተረቀቀው አዋጅ በህገ መንግስቱ መጠነኛ ገደቦች ተጥለውበት ለዜጎች የተፈቀደውን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን ሊገድብ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።
ምንጭ:- ሸገር
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:- ሸገር
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት 121 ወረዳዎች ውስጥ 95 ያህል የሚሆኑት ዲጂታል ነዋሪነት መታወቂያ ለተገልጋዮች መስጠት መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኹነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ምንጭ:- ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
ምንጭ:- ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በስልክ ጥሪ አገልግሎት ላይ ማምሻውን ስለተከሰተው መቋረጥ ያደረሱኝ መረጃ!
"የቴክኒክ ብልሽት አጋጥሞን ነበር፣ ይህም የስልክ ጥሪ መቋረጡ ምክንያት ነበር። ችግሩ ያጋጠመው ከሞባይል ወደ ሞባይል የጥሪ አገልግሎት ላይ ነበር። አሁን ላይ የጥሪ አገልግሎቱ መስራት የጀመረ ሲሆን ችግሩ ምን እንደነበር ለማወቅ ጥረት እያደረግን ነው። ምናልባት ይሄ ዛሬ ይፋ ካደረግነው ስጦታ ጋር ይያያዝ እንደሆነ ሰዎች ከጠየቁ፣ ከሱ ጋር የተገናኘ አይደለም። የኢንተርኔት እና የፅሁፍ መልእክት አገልግሎታችን እየሰሩ ነበር።"
Via Elias Meseret

Joint Statement of Ethiopia, Egypt, Sudan, the United States and the World Bank
January 15, 2020
Washington, DC – The Ministers of Foreign Affairs and Water Resources of Ethiopia, Egypt and Sudan and their delegations met with the Secretary of the Treasury and the President of the World Bank, participating as observers, in Washington, D.C. on January 13-15, 2020. The Ministers noted the progress achieved in the four technical meetings among the Ministers of Water Resources and their two prior meetings in Washington D.C. and the outcomes of those meetings and their joint commitment to reach a comprehensive, cooperative, adaptive, sustainable, and mutually beneficial agreement on the filling and operation of the Grand Ethiopian Renaissance Dam.
Toward that end, the Ministers noted the following points, recognizing that all points are subject to final agreement:
1. The filling of the GERD will be executed in stages and will be undertaken in an adaptive and cooperative manner that takes into consideration the hydrological conditions of the Blue Nile and the potential impact of the filling on downstream reservoirs.
2. Filling will take place during the wet season, generally from July to August, and will continue in September subject to certain conditions.
3. The initial filling stage of the GERD will provide for the rapid achievement of a level of 595 meters above sea level (m.a.s.l.) and the early generation of electricity, while providing appropriate mitigation measures for Egypt and Sudan in case of severe droughts during this stage.
4. The subsequent stages of filling will be done according to a mechanism to be agreed that determines release based upon the hydrological conditions of the Blue Nile and the level of the GERD that addresses the filling goals of Ethiopia and provides electricity generation and appropriate mitigation measures for Egypt and Sudan during prolonged periods of dry years, drought and prolonged drought.
5. During long term operation, the GERD will operate according to a mechanism that determines release based upon the hydrological conditions of the Blue Nile and the level of the GERD that provides electricity generation and appropriate mitigation measures for Egypt and Sudan during prolonged periods of dry years, drought and prolonged drought.
6. An effective coordination mechanism and provisions for the settlement of disputes will be established.
The Ministers agree that there is a shared responsibility of the three countries in managing drought and prolonged drought.
The Ministers agreed to meet again in Washington, D.C. on January 28-29 to finalize a comprehensive agreement on the filling and operation of the GERD, and that there will be technical and legal discussions in the interim period.
The Ministers recognize the significant regional benefits that can result from concluding an agreement on the Grand Ethiopian Renaissance Dam with respect to transboundary cooperation, regional development and economic integration that can result from the operation of the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The Ministers of Foreign Affairs reaffirmed the importance of transboundary cooperation in the development of the Blue Nile to improve the lives of the people of Egypt, Ethiopia, and Sudan, and their shared commitment to concluding an agreement.
Via Spokesperson Of Foreign Affairs

ሻሸመኔ የኤሌክትሪክ ስርጭትን በፈረቃ ልታደርግ ነው፡፡
የሻሸመኔ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ማዕከል በደንበኞች መብዛት ምክንያት ሀይልን በፈረቃ ላስራጭ እገደዳለሁ ብሏል፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በበኩሉ በማሰራጫው ላይ ያለው ችግር እንዲባባስ ያደረገው ዲስትሪክቱ ራሱ ነው ብሏል፡፡በሰብስቴሽኑ ላይ የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ለአዳዲስ ከፍተኛ የሀይል ተጠቃሚ ደንበኞች አገልግሎት እንዳይሰጥ ደብዳቤ ብንጽፍም ይህንን ተግባራዊ ሳያደርግ ቀርቶ ለአዳዲስ ከፍተኛ ሀይል ተጠቃሚ ደንበኞች ሀይል ሲሰጥ ነበር ይላል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሬክ አገልግሎት ሻሸመኔ ዲስትሪክት ስራ አስኬያጅ አቶ ጉልቱማ ቂጣታ በበኩላቸው ከታህሳስ 2011 ጀምሮ ለአዳዲስ ከፍተኛ የሀይል ተጠቃሚዎች የሰጠነው ምንም መስመር የለም ሲሉ መልሰዋል፡፡በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮሚኔኪሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ደግሞ ለአዳዲስ ደንበኞች ሀይል መስጠቱን የሚሳይ አሀዛዊ መረጃን ያቀርባሉ፡፡የተፈጠረውን ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቅረፍ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አቶ ሞገስ ገልጸዋል።
Via Ethio FM

አዋሽ ባንክ በአንድ ጊዜ ሦስት ወለድ አልባ ቅርንጫፎችን ሥራ አስጀመረ!
አዋሽ ባንክ በአዲስ አበባ ሰባተኛ፣ በርበሬ ተራ እንዲሁም በቦሌ ሚካኤል አካባቢ የከፈታቸውን ሦስት ወልድ አልባ የባንክ አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎቹን ሥራ ሲያጀምር የባንኩ አመራሮችና እንግዶች ተሳትፈዋል።በሒሳብ ዓመቱ የሚከፈቱትን ወለድ አልባ ቅርንጫፎች ብዛት 20 ለማድረስ ማቀዱንም አሳውቋል።
ምንጭ: ሪፖርተር

በዩኒቨርሲቲዎች በተፈጠረ የሰላም እጦት 35 ሺህ ተማሪዎች ትምህርት ጥለው መውጣታቸውን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አረጋገጠ።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች ሰላም ባጡባቸው ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ አካላት ጋር ግምገማ እና ምክክር እያደረገ ይገኛል። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የገዥው ፓርቲ አባላት ከዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ አካላት የፀጥታ ችግር በተፈጠረባቸው 22 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ባደረጉት የመስክ ምልከታ ላይ የተዘጋጀ ሪፖርት በመድረኩ ላይ ቀርቧል።በቀረበው ሪፖርትም የዩኒቨርሲቲዎች የሰላም መታወክ የፖለቲካ አመራሮች ትልቅ ሚና እየተጫወቱ እንዳለ ተገልጿል።
በተለያዩ ክልሎች ባሉ የተለያዩ የፖለቲካ አመራሮች የሚወጡ መግለጫዎች እና ከግቢ ውጭ ተማሪዎችን ሰብስቦ ተልእኮ የመስጠት ሥራዎች ለመማር ማስተማሩ መታወክ እንደ አንድ ምክንያት ተጠቁሟል።ተልእኮ የተቀበሉ ተማሪዎች መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች ላይ የሥነ ልቦና፣ አካላዊ፣ የሕይወት እና ንብረት ጉዳት በማድረስ ግጭት እንደሚያነሣሡም ተጠቁሟል።በሚዲያዎች የተጋነኑ እና የተዛቡ መረጃዎች መሰራጨት፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ችግሮችን ውጫዊ ማድረግ ወይም ቸልተኝነትም ሌላው ለዩኒቨርሲቲዎች የሰላም እጦት የተነሣ ተግዳሮት ነው።
በዩኒቨርሲቲዎች ያለው በቤተ ዘመድ የተሳሳበ የሠራተኛ አደረጃጀት እንዲሁ እንደ አንድ ችግር ተጠቅሷል።ችግር የፈጠሩ እና ምንም ዓይነት የሕግ እርምጃ ሳይወሰድባቸው በነፃ የሚለቀቁ እና እንዲማሩ የሚፈቀድላቸው ተማሪዎችም በዩኒቨርሲቲዎች ለሚታየው የሰላም እጦት ሌላው ምክንያት ነው።የትምህርት ተቋማቱ የፀጥታውን ችግር ለመቅረፍ እንዲችሉም ሚኒስቴሩ በደህንነት ስጋት የወጡ ተማሪዎችን የመመለስ ሥራ እንደሚሠራ ገልጿል።
የተማሪዎችን አደረጃጀት በኅብረ ብሔር ለማሰባጠርም ታስቧል።በዩኒቨርሲቲ አመራሩ በኩል ውጫዊ ማስፈራሪያዎችን በመፍራት ውሳኔ ሰጭነት ላይ የሚታየውን ማፈግፈግ እንዲሻሻል እና ጠንካራ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ተገልጿል።ተቋማቱን ለማረጋጋት በ22 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነበሩ ከ640 በላይ ተማሪዎች፣ 40 መምህራን እና ከ240 በላይ የአስተዳደር ሠራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እንደተወሰደ ተገልጿል።
Via EBC

ባላገሩ አይዶል በቅርቡ የኪነ ጥበብ ባለተሰጥዖዎችን ማወዳደር እንደሚጀምር አስታወቀ።
የባላገሩ አይዶል መስራችና ባለቤት አርቲስት አብርሃም ወልዴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኢቲቪ የኪነ ጥበብ ውድድሮችን ስናካሂድ ነበር ለረጅም ጊዜ ከማወዳደር ርቀን የቆየነው ከኢቲቪ ጋር በነበረ አለመግባባት እና በሌሎች ምክንያቶች ነው ብለዋል።አሁን ግን የባላገሩ አይዶል ውድድርን ለመጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀናል ያሉት አርቲስት አብርሃም ውድድሩ በባላገሩ ቴሌቪዥን በኩል በቅርቡ ይጀመራል ብለዋል።
የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላችሁ ሁሉ ባለገሩ አይዶል ሊጀመር በመሆኑ ጠብቁን እንደ ከዚህ በፊቱ አዳዲስ ድምጻዊያንን ለኢትዮጵያዊያን እናስተዋውቃለን ብለዋል አርቲስት አብርሃም።ከዚህ በፊት በባላገሩ አይዶል ወድድር አሸናፊ የነበረው ድምጻዊ ዳዊት ጽጌ የኔዜማ በሚል ያሳተመውን የሙዚቃ አልበም ዛሬ አስመርቋል።
ምንጭ:Ethio FM

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት የሚጀምርበት ቀን.....
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ጥር 6/2012 ዓ፣ም ባካሄደው ስብሰባ የተማሪዎችን መልሶ መግቢያ ቀን ወሰኗል፡፡
ስለሆነም የሁሉም ተማሪዎች መልሶ መግቢያ ቀን ጥር 14 እና 15/2012 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን ጥር 18/2012 ዓ.ም የተቋረጠው ትምህርት ሙሉ በሙሉ የሚጀመር መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡ በቀጣይ ቀናት ጥር 16 እና 17 በሰላም ኮንፈረስ እና በጎ አድራጎት ተግባራት ላይ የምትሳተፉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
ምንጭ:- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ

*በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተፈጠረው የሰላም እጦት ጋር በተያያዘ ከ640 በላይ ተማሪዎች፣ 40 መምህራን እና ከ240 በላይ የአስተዳደር ራተኞች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸው ተገለጸ
*በዩኒቨርሲቲዎች በተፈጠረ የሰላም እጦት 35 ሺህ ተማሪዎች ትምህርት ጥለው መውጣታቸውን የገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ እነዚህን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
*በ22 ዩኒቨርሲቲዎች ተፈጥሮ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለማጣራት የተዋቀረው ኮሚቴ ባደረገው የመስክ ምልከታ ያዘጋጀው ሪፖርት በመድረኩ ላይ ቀርቧል።
https://telegra.ph/YeneTube-01-16

ዳሽን ባንክ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት ዝርፊያ ተፈፅሞበታል!!
ዳሽን ባንክ በመዲናችን አዲስ አበባ ውስጥ በያዝነው አመት ለሁለተኛ ጊዜ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ለባንኩ ቅርብ የሆኑ ግለሰብ ለየኔቲዩብ ጥቆማ አድርሶናል።
ዝርፊያው ባሳለፍነው ሳምንት ዳሽን ባንክ #የረር_ጎሮ_ቅርንጫፍ ላይ የተፈፀመ ሲሆን ፣ እንደምንጫችን ገለፃ በባንኩ ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ሲፈፀም ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው ከሁለት ወር በፊት ዳሽን ባንክ #ኮተቤ ቅርንጫፍ ነበር።

በፍርድ ቤቶች ምርጫ ነክ ክርክሮችን በልዩ ሁኔታ ለመዳኘት የቅድመ ዝግጅት ሰራ ተጀመረ!
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሃገራችን በቅርቡ ከሚካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዞ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለሚቀርቡ የዳኝነት ጥያቄዎች ቀልጣፋና ጥራት ያለው ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት ማድረግ ጀመረ፡፡የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተሰጧቸውን ሃላፊነቶች በህገመንግስቱና በስነ-ስርዓት ህጉ ከተቀመጡት መሰረታዊ ድንጋጌዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ለመወጣት የሚያስችላቸውን አደረጃጀትና አቅም ለመፍጠር በየበኩላቸው የቅድመ ዝግጀት ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
በዚሁ መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከሶስቱም ፌዴራል ፍ/ቤቶች የበላይ አመራሮችና የምድብ ችሎት አስተባባሪዎች ጋር የምርጫና ሌሎች ተያያዥ ህጎችን መሰረት በማድረግ ለፍርድ ቤቶቹ ለሚቀርቡ ጉዳዮች ጥራት ያለው ፈጣን ውሳኔ መስጠት ስለሚችሉበት ሁኔታ መክረዋል፡፡የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሰፊ ውይይት ባደረጉበት በዚህ የምክክር መድረክ ከምርጫ ሂደት ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ ጉዳዮች በአጭር ጊዜ ውሳኔ የሚፈልጉ በመሆናቸው በመደበኛው የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደማይቻል በመግለጽ በቅድመ ምርጫ፤ በምርጫ እና በድህረ ምርጫ ጊዜ ወደ ፍርድ ቤት ለሚቀርቡ አቤቱታዎች ፈጣን፤ ግልጽና ፍትሃዊ ዳኝነት ለመስጠት ፍርድ ቤቶች ሊያከናውኗቸው የሚገቡ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
ምንጭ:የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በተለያዩ ምዕራፎች ለመሙላት እንደተስማማች ሦስቱ ሀገሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ ተገልጧል፡፡ ውሃ ሙሌቱ የታችኛውን ተፋሰስ ሀገሮች ግድቦች እና የወንዙን ፍሰት ግምት ውስጥ ያስገባል፡፡ሙሌቱም ሐምሌ እና ነሐሴ ብቻ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ውሃው ከፍታ 595 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ ግብጽ እና ሱዳን አስከፊ ድርቅ ካጋጠማቸው ማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፡፡ ሀገራቱ ለመጨረሻው ስምምነት ከ12 ቀናት በኋላ ስምምነቱን በሰነድ ለማፅደቅ በዋሽንግተን ይገናኛሉ፡፡ እስከዚያው በዝርዝር ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ይቆያሉ::
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
መቱ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት መስተጓጎል ምክንያት ናቸው የተባሉ 26 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ሴኔት መታገዳቸውን አስታወቀ።
የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በትናንትናው ዕለት ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ ስምንት ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርት እንዲታገዱ መወሰኑን በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ባሰራጨው መረጃ ገልጿል። በመረጃው መሠረት ስድስት ተማሪዎች ለአንድ ዓመት፤ አስራ ሁለት ተማሪዎች ለሁለት ዓመት ከትምህርት እንዲታገዱ ተወስኗል።
"የተስተጓጎለዉን የመማር ማስተማር ስራ ወደ መደበኛ ቦታዉ ለመመለስ የዩኒቨርሲቲዉ አመራር፤ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ፤ የአካባቢዉ ማህበረሰብ አካላትና የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ያላሰለሰ ጥረት ሲያደጉ ቢቆዩም ችግሩን የሚፈጥሩ አካላት ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸዉ ትምህርት ለማስቀጠል የተደረገ ጥረት እስከ ዛሬ ድረስ ሳይሳካ ቆይቷል" ብሏል። የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ባለፉት ጥቂት ወራት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች የበርካታ ተማሪዎች ሕይወት አልፏል፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቶቹን ለመቆጣጠር በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጥበቃ የፌድራል ፖሊስ አባላት ጭምር እንዲሳተፉ አድርጎ ነበር። ግጭት እና ኹከቱን መቆጣጠር የተሳናቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን እስከ ማቋረጥ ደርሰው ነበር።