YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የበረሃ አንበጣ የኢትዮጵያ ደቡባዊ አካባቢዎች ደርሷል

ለወራት ሰሜን ኢትዮጲያን ሲያስጨንቅ የከረመው የበረሃ አንበጣ አሁን ፊቱን ወደ ደቡብ አካባቢ ያዞረ ይመስላል። የደቡብ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ በክልሉ የአንበጣ መንጋ በስፋት መከሰቱን ለዶቼ ቨለ (DW) አረጋግጠዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
የትንባሆ ዋጋ አሁን ካለበት ዋጋ ሦስት ዕጥፍ ቢጨምር በትንባሆ ምክንያት የሚደርሰውን እና እየደረሰ ያለውን ጉዳት እስከ 40 በመቶ እንደሚቀንሰው የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

Via:- ኢትዮ ኤፍ ኤም /Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2ሽሕ ኹለት መቶ 25 ግብር ከፋዮችን ኦዲት በማድረግ ሊሰወር የነበረ 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማስቀረት እንደተቻለ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርሀኑ አበበ ተናገሩ።

Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ የበረከት ስምዖንን እና ታደሠ ካሳን 2 መከላከያ ምስክሮች መስማቱን የአማራ ብዙኻን መገናኛ ዘግቧል፡፡ በነገው ችሎት ሌሎች ምስክሮች ይቀርባሉ፡፡ ለምስክርነት የተጠሩት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም መቼ እንደሚቀርቡ አልታወቀም፡፡

Via:- wazema
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
 ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
 በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቱን መሸጥ ይችላል።
 ከ2700 በላይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች
@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
 0953707070
Samsung CURVED UHD TV
55 7 SERIES NU7300 SMART TV
BRAND NEW
INBOX 📩 @CloudMultiTrading2 📩
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተፈጠረው ስምምነት በሰላም እጦት ለተቸገሩት እፎይታን የሰጠ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በኩል ክፍፍል ሊኖር አይገባም ሲሉ የቫቲካኑ ጳጳስ ፍራንሲስ ተናገሩ። ጳጳሱ በቫቲካን የሚገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ኮሌጅ 100ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ላይ ተገኝተዋል።

Via:- ኢትዮ ኤፍ ኤም
@YeneTube @Fikerassefa
ሐና ዩሐንስ የጋብቻ ቀለበት በድብቅ አደረገች።

የዘመን ድራማ ተዋንያኗ እና የእንተዋወቃለን የቴቪ ፕሮግራም አዘጋጇ ሐና ዩሃንስ ባሳለፍነው ሳምንት በድብቅ የጋብቻ ቀለበት እንዳረገች ኢትዮፒካሊን ዘግቧል። እንደ ኢትዮፒካሊክ ዘገባ ከሆነ በቀለበት ስነ-ስርዓቱ ላይ ከልጇ በስተቀር የተገኝ ሰው አልነበረም።

ሐና በዘጠነኛው ለዛ ሽልማት ላይ በተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ምርጥ የሴት ተዋናይት ተብላ መሸለሟ ይታወሳል።

Via:- AccessAddis
@YeneTube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ከትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ በየቀኑ በአማካኝ 13 ሰዎች ህይወታቸው እንደሚያለልፍ የኢፌዲሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

Via:- ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አስራ ሰባት የአስተዳደር ሠራተኞችን በግምገማ ከስራቸው አባረረ

የዩኒቨርስቲው የዓለም አቀፍ እና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጋንፉሬ ለዶይቸ ቬለ (DW) በስልክ እንደገለፁት ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር ሥራውን እንዳያከናውን ያጋጠመውን እክል ተከትሎ እያካሄደ ባለው የሠራተኞች ግምገማ ከዲስፕሊን ግድፈት ጋር በተያያዘ አስራ ሰባት የአስተዳደር ሠራተኞች ከሥራቸው እንዲባረሩ ወስኗል።

ኃላፊው እንዳሉት በአስተዳደር ሠተኞች ላይ በተካሄደው ግምገማ አንድ ሠራተኛ ከደረጃው ዝቅ ብሎ እንዲሠራ ተወስኗል። በዩኒቨርሲቲው ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት የተጀመረው ግምገማ ቀጥሎ የአካዳሚክ ክፍሉ ሠራተኞች በመገምገም ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ከሁለት ሳምንት በላይ ያቋረጠውን መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ለማስጀመር ቀደም ሲል በተማሪ ማደርያ ክፍሎች፤ በመመገቢያና ሌሎች አካባቢዎች ነበሩ ያላቸውን ችግሮችን ለመፍታት እና የተቋሙን አገልግሎት ምቹ የማድረግ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም አቶ ደቻሳ አስረድተዋል።

ዩኒቨርስቲው በተቋረጠው ትምህርት ሳቢያ የባከኑ የትምህርት ጊዜያትን ለማካካስ የሚቻልበት ዕቅድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እና በቅርብ ቀናት የተቋረጠው ትምህርት ለማስጀመር እቅድ እንዳለው አስታውቀዋል።

በዩኒቨርሲቲው በትምህርት ዓመቱ በተማሪዎች በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉና ሌሎች ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው። ምክንያቱ በውል አይገለፅ እንጂ ባሳለፍነው ሳምንት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ያሬድ ማሞ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር በተፃፈ ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል።

ምንጭ:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
የሁለት ሳምንት አስክሬን አስነሳለሁ ያለችው 'አማኝ' በገንዘብ ተቀጣች!

በኦሮሚያ ክልል ቦሰት ወረዳ ወለንጪቲ ከተማ ከሞተ ሁለት ሳምንት የሆነውን የሁለት ወር ህፃን "ከሞት እንዳስነሳ ራዕይ ታይቶኛል" በማለት መቃብር ያስቆፈረችው 'አማኝ' በማጭበርበር መቀጣቷን ፖሊስ ለቢቢሲ ገልጿል።
ህጻኑ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከሞተ በኋላ ራዕይ ታይቶኛል ያለችው ሴት፤ የህጻኑን እናት እና አንዲት ሌላ ሴት በመያዝ ወደ መቃብር ሥፍራ በመሄድ ቆፍረው ማውጣታቸውን የቦሰት ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ካሰኝ ደምሴ ገልጸዋል። ''ግለሰቧ እንደ ለቅሶ ደራሽ በመሆን ወደ እናት ቤት በመሄድ ልጅሽ አልሞተም፤ በሕይወት ነው ያለው፤ ከሞት እንዳስነሳውም ራዕይ ታይቶኛል" ትላታለች። መቃብር ሥፍራም ሄዳ ጸሎት ማድረግ እንደምትፈልግ ትነግራታለች። እናትም እውነት መስሏት ተያይዘው ወደ መቃብር ሥፍራው ሄደዋል።

https://telegra.ph/bbc-01-14
🛑 Breaking 🛑

የኦሮሚያ ክልል ከእገታ የተለቀቁ ተማሪዎች #በእጄ ናቸው አለ

ከእገታ ተለቀቁ የተባሉ ተማሪዎችን ዛሬም እንዳላገኙ ቤተሰቦች ቢናገሩም የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች አሁን #በመንግሥት_እጅ መሆናቸውን ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የእገታውን ተግባር የፈፀሙት ራሳቸውን ሸኔ ብለው የሚጠሩ ቡድኖች ናቸው ሲሉ ኮሎኔል አበበ ተናግረዋል።

Via:- Addis Maleda / VOA
@YeneTube @FikerAssefa
በአሶሳ የታሰሩት ጋዜጠኞች በ10 ሺ ብር ዋስ ተለቀቁ፡፡

በትላንትናው አለት በአሶሳ ተይዘው የነበሩት ጋዜጠኛች ዛሬ ማምሻውን በ10 ሺብር ዋስ መለቀቃቸውን ሸገር ታይምስ ከስፍራው አረጋግጣለች፡፡በትላንትናው እለት ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና የካሜራ ባለሙያው በኃይሉ ውቤ ካረፉበት ሆቴል ተወስደው ታስረው እንዳደሩ እና ጠዋት ያሰራቸው አካል ማነው ሲባል መልስ የሚሰጥ እንደጠፋ የገለጹት ምንጮቻችን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንም ሆነ ሌላ አካል የታሰሩት በዚህ ምክንያት ነው የሚል ባለመገኘቱ እና ከሳሽም ባለመኖሩ ቃል እንዲሰጡና በ10 ሺብር ዋስ እንዲፈቱ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

"ሁለቱ ባለሙያዎች ዛሬ ቃል ሰጥተዋል" ያሉት የመረጃ ምንጮቻችን በቃል መስጫው ላይ የእለት ውሎአቸውን እና ምን ሲሰሩ እንደዋሉ ካስመዘገቡ በኋላ ለእያንዳንዳቸው 5ሺ ብር በዋስትና እንዲያስይዙ የተጠየቁ ሲሆን ይህንን የዋስትና ክፍያም ለዘገባ የጠሯቸው አካላት ከፍለው እንዲፈቱ መደረጋቸውን የሸገር ታይምስ ምንጮች አሁን ከስፍራው በስልክ አረጋግጠውልናል፡፡

ባለሙያዎቹ በትናንትናው እለት በአሶሳ ከተማ የሶስት ፓርቲዎችን ውህደት ለመዘገብ የተገኙ ነበሩ፡፡በተያያዘ ዜና የቦሮ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ አመንቴ ገሺም ምርጫ ቦርድ ጥር 7 እና 8 ሁሉንም ፓርቲዎች ለማወያየት ባዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ወደ አሶሳ ሲያመሩ በአሶሳ አየር ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል፡፡

Via Sheger Time Magazine
@YeneTube @FikerAssefa
"እኔ የምገኘው በኦሮሞ ጫካ ውስጥ ነው : በወለጋ ቡና ስር የኦሮሞ ነፃነት ጦር መሪ #ጃል_መሮ"

ከቢቢሲ ጋር ካደረገው ቆይታ ላይ የተቀነጨበ⬆️

በሶሻል ሚዲያ ላይ ጃል መሮ መቐለ እንደሚገኝ በስፋት ሲናፈስ ቢቆይም ጃል መሮ አሁን ላይ ወለጋ ጫካ ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጪውን አገራዊ ምርጫ እና የጊዜ ሰሌዳ አስመልክቶ የምክክር ውይይት እያደረገ ይገኛል። ውይይቱ የቦርዱ የኦፕሬሽን እቅድና የ2012 የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ያተኩራል!

ምንጭ:NEBE
@YeneTube @FikerAssefa
በስራ ማቆም አድማ የተከሰሱት 9 የሲቪል አቪየሸን የበረራ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የጥፋተኛነት ፍርድ ተወሰነባቸው።

የሚከፈለን ደሞዝ አነስተኛ 000 ይጨመርልን በማለት በ2010 ነሀሴ ላይ የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት ሰባት ወንዶች ሁለት ሴት የበረራ ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ከ16 ወራት የክስ ሂደት በኋላ ትላንት ጥር 4, 2012 ሀገርን ስጋት ላይ ጥለዋል በሚል ጥፋተኛ ተብለዋል። ነገ ልደታ ፍርድ ቤት የሚውለው ችሎት የእስር ብይን ያስተላልፍል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሰራተኞቹ ትናንት ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ቦታ ተወስደዋል።አድማ ባደረጉ ሰሞን ከአንድ ወር እስራት በኋላ ተለቀው ከስራም የተባረሩት እነዚህ ሰራተኞች በቅርቡ ተደውሎላቸው ወደ ቀድሞ ስራቸው እንደሚመለሱ ቃል ተገብቶላቸው ነበር።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይህንን ይመስላል፣ ፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተያየትና ግብአት ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል!
#Elections2012

@YeneTube @FikerAssefa
ባህር ዳር ከተማ አንድ ሊትር ቤንዚን በጥቁር ገበያ እስከ 70 ብር እየተሸጠ ነው።

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የነዳጅ እጥረት የተከሰተ ሲሆን በባህር ዳር ከተማ ተባብሶ አንድ ሊትር ቤንዚን በጥቁር ገበያ እስከ 70 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው። የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎቶችም በከፊል ሥራ አቁመዋል።በባህርዳር ከተማ በተከሰተው እጥረት ሳቢያ በሕገወጥ መልኩ በጥቁር ገበያ በተለይም በከተማው ቀበሌ 07 እና 14 ቤንዚን እየተሸጠ ሲሆን፣ ባጃጆችም በዚህ ዋጋ ገዝተን አያወጣንም በሚል የታሪፍ ጭማሪ ማድረጋቸውን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ነዋሪ ይናገራሉ።

ምንጭ:አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም የበጀት አመት አጋማሽ እቅዱን 104% ማሳካቱን አስመልክቶ ለሁለት ቀን የሚቆይ ስጦታ ለደምበኞቹ አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስን ማን ሊያስተዳድረው ይገባል የሚለው ጉዳይ እያወዛገበ ነው!

‹‹ደመወዝ እንከፍላለን እንጂ እኛ የአዲስ አበባ ፖሊስን አናስተዳድርም››

-ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ

‹‹ለሕዝባችን ደኅንነት ሲባል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ተቀራርበን እንድንሠራ ሊደረግ ይገባል››

 -የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ በሆነችው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ አልፎ አልፎ ለሚያደርገው ቁጥጥር የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችን ሰኞ ታኅሳስ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በመጥራት የሥራ ክንውናቸውን ሲገመግም፣ በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ትኩረትን ከሳቡ የውይይት ርዕሶች መካከል ነበር። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ማን ሊያስተዳድረው ይገባል የሚለው ጉዳይም አወዛግቧል፡፡

በምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ሰብሳቢነትና የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ብቻ በተሳተፉበት በዚህ የግምገማ መድረክ፣ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የከተማ አስተዳደር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቅርቧል።

ሙሉ ዝርዝር👇👇👇

https://telegra.ph/addisabaPolice-01-15