YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሞጣ 33 ሰዎች ቁጥጥር ሥር ዋሉ! (የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ)

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ሰሞኑን በአራት መስጊዶች እና አንድ ቤተክርስቲያን ላይ ከተፈጸመው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ 33 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ አስታወቀ። የምሥራቅ ጎጃም ዞን የፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው እንዳመለከቱት ባሳለፍነው አርብ በሞጣ ከተማ በአንድ ቤተክርስቲያንና በ3 መስጊዶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል። የነበረውን ግርግር በመጠቀምም 111 ሱቆች መዘረፋቸውን 18ቱ ደግሞ ተቃጥለዋል። የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የሀይማኖት አባቶች ዛሬ ከጠዋቱ ጀምሮ ሞጣ ከተማ በመገኘት ቃጠሎና ዝርፊያ የደረሰባቸውን አካባቢዎች መጎብኘታቸውንና ከህብረተሰቡ ጋር ውይት ማድረጋቸውን በሞጣ ከተማ አስተዳደር የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ መንግሥቱ ዓለማየሁ አመልክተዋል፡፡ድርጊቱን በመቃዎም ደግሞ ትናንት በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ከሚሴ ከተማ ድርጊቱን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፋው ትውልደ ኤርትራዊው እና የስዊድን ዜግነት ያለው ኤርሚያስ ተክሌ ምርመራ ቶሎ እንዲጠናቀቅ መመሪያ አስተላልፏል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል፡፡ መመሪያው የተላለፈው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነው፡፡ ኤርሚያስ ከስዊድን አዲስ አበባ እንደገባ ድንገት የጠፋው ግንቦት 2010 ዓ.ም ነበር፡፡ ጠበቆቹ እና ቤተሰቦቹ በቂ ምርመራ እንዲደረግላቸው ባለፈው ጥቅምት አመልክተው ነበር፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በሳኡዲ አረቢያ በቤት ሰራተኝነት ስትሰራ በነበረችው ኢትጵያዊት ሶፍያ እስማኤል በአሰሪዎቿ እገታ ተፈጽሞባት የነበረ ሲሆን ሳኡዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት ማስለቀቅ መቻሉን አስታወቀ።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ስርጭት መቀነስ ካልተቻለ ከ10 ዓመት በኋላ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የክልሉ ሕዝብ ለኩላሊት ሕመም ሊጋለጥ እንደሚችል ጥናቶች አመላከቱ፡፡

(አብመድ)
@YeneTube @FikerAssefa
አድማስ ራዲዮ ከጂጂ ጋር ያደረገውን ቆይታ አቀናብረን አቅርበንላችኃል።

https://www.youtube.com/watch?v=DAKlRkVX7eI&t=99s
የፀዲን | ሰው | ኦብሰሽን የተዘጋጀውን ኮንሰርት ላይ አስገራሚ እንቅስቃሴዎች | አፈትልኮ የወጣ ቪዲዮ ነው ተመልቱት።


📌በሾሻል ሚዲያ ላይ አነጋጋራ ቪዲዮ

youtube.com/watch?v=9YZpV5nNh-4
ትልልቅ የሙስና ወንጀል ተሰርቶባቸዋል ተብለው በተጠረጠሩ ተቋማት ላይ የተደረገው ጥናት ተጠናቋል - ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት

ትልልቅ የሙስና ወንጀል ተሰርቶባቸዋል ተብለው በተጠረጠሩ ተቋማት ላይ የተደረገው ጥናት መጠናቀቁን የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል ባለፉት ስድስት ወራት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጠጣር የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል በማቅረብ የተሳካ ስራ መስራቱን ተናግረዋል።

የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመከላከል በኩል በግብር ስወራ፣ ኮንትሮባንድ እና የጨው ምርት ሽያጭ አሻጥር ላይ አጣርቶ መረጃ ማቅረቡንም ነው የተናገሩት።ከግብር ስወራ እና የመንግስት ሀብት ምዝበራ አንፃር ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ሀብት ለማዳን ያስቻለ ስራ መሰራቱንም ገልጸዋል።የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል በተባሉ የመንግስት ተቋማት ላይ ጥናቶችን አጠናቆ ለመንግስት ማስረከቡንም አስታውቀዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ ነው!

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል፥ ስር ነቀል ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ ላይ ያለው አገልግሎቱ የስያሜ እና አሰራር ለውጥ የሚያደርግበት ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ረቂቅ አዋጁ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ስያሜን ወደ ብሔራዊ መረጃ ማዕከል (ኤን አይ ሲ) እንዲሻሻል ይጠይቃል።

ረቂቅ አዋጁ ከፖለቲካ፣ ብሔር እና ሃይማኖት ጥገኝነት የተላቀቀ ነፃ የመረጃ እና ደህንነት ተቋም የመፍጠር የማሻሻያ ስራ አንዱ አካል መሆኑንም ተናግረዋል። ተቋማዊ ማሻሻያውን ተከትሎ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት በአስር አመት ወስጥ ሊደርስበት የሚችለውን ደረጃ የሚያመላክት የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድም ተዘጋጅቷል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተቀሰቀሰ!

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ቅዳሜ በተማሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የመማር ማሥተማር ሥራው መቋረጡን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 11/2012 ዓ/ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ በተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ድንጋይ መወራወር ያስከተለው ግጭት በቁጥጥር ሥር ቢውልም የመማር ማስተማር ሥራው ለጊዜው መቋረጡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታደሠ ቀነዓ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

«በተማሪዎች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚፈልጉ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ተማሪዎች እያነሳሱ ነው» ያሉት ዶ/ር ታደሠ «የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የሆኑ ጥቂት ተማሪዎች ከሌላ ዩኒቨርሲቲ መጡ የተባሉ ተማሪዎችን አጋርነት ለማሳየት በሚል ግጭት ለመፍጠር ሲሞክሩ ነበር » ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው ግጭት ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራው መቋረጡን ዶ/ር ታደሠ ተናግረዋል።

በተማሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተከሰተ ጉዳት እንደሌለ እና የተፈጠረውን ግጭት ለመቅረፍ ከዛሬ ጀምሮ ከተማሪዎች እና ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት መጀመሩን ፕሬዚዳንቱ አክለው ገልጸዋል።

«ከሌላ ዩኒቨርሲቲ መጡ» ስለተባሉ እና ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር በመሆን ግጭት እንዲቀሰቀስ እያደረጉ ያሉ ተማሪዎች ያሉዋቸውን ሰዎች በሚመለከት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር በመሆን መፍትሄ እያፈላለጉ መሆኑንም ዶ/ር ታደሠ አስታውቀዋል።

በዩኒቨርሲቲው የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ጊቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች ስለመኖራቸው የተጠየቁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጊቢውን የሚያስለቅቅ የጎላ ችግር ባለመኖሩ ጊቢውን ለቆ የወጣ ተማሪ የለም ብለዋል።

Via:-DW Amharic
@Yenetube @Fikerassefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት ወቀሳ መልስ ሰጠ

ሰሞኑን ለሥራ ጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ሊያደርጉ የነበሩ የቻይና የሻንሺ ግዛት ልዑካን አባላት በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይጓዙ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ እገዳ ተደርጎባቸዋል የሚለው የትግራይ ክልል መንግሥት ቅሬታ የመገናኛ ብዙሃን ዓበይት የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቆይቷል።

የተፈጠረውን ክስተት ለማጣራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊዎችን አነጋግሯል:: 
ለመሆኑ የልዑካን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበፌደራል መንግስቱ ዕውቅና እና አስፈላጊውን 
ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነው ?

ለሚለው ጥያቄ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚስትር ሚኒስትር  ´ዴኤታ  አምባሳደር  ዶክተር ማርቆስ ተክሌ የፌደራል መንግስቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤዥያ እና ፓስፊቅ አገራት ጉዳዮች መምሪያ እና ቻይና ፔኪንግ  በሚገኘው የኢትዮጵያሚስዮን አማካኝነት 
ከወራት በላይ  ከግዛቲቱ ሃላፊዎች ጋር የደብዳቤ ልውውጥ እና ውይይት አድርጎ ለትግራይ ክልልም 
በደብዳቤ አሳውቆ በህጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አረጋግጠውልናል::

Via:- ጀርመን ድምፅ
@Yenetube @Fikerassefa
የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አቋርጠው ወደነበረው መደበኛ ትምህርታቸው መመለሳቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለታ ተስፋዬ ገለፁ።

ዶክተር ለታ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ከሌላ አካባቢ ካለው የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው የመጡ ተማሪዎች በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ካልተማሩ በሚል ለተወሰኑ ቀናት ትምህርት ተቋርጦ ቢቆይም መግባባት ላይ በመደረሱ መደበኛ ትምህርት ተጀምሯል።

ዶክተር ለታ እንዳሉት፤ በአማራ ክልል ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የኦሮሞ ተማሪዎች ወደጊቢው ገብተን ትምህርት ካልተማርን በሚል ጥያቄ አንስተው ነበር፣ በግቢው ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ ከሌላ ቦታ የመጡ ተማሪዎችን ተቀብላችሁ ካላስተማራችኋቸው አንማርም የሚል ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተዋል። ‹‹በወቅቱ የእኛ ምላሽ የነበረው፣ ተቋሙ የፌዴ ራል እንደመሆኑ ተቀብለን ማስተማር የምንችለው የተመደበልንን ብቻ እንደሆነ ነው።

ለዚህም ምክንያቱ ዩኒቨርሲቲ የራሱ የሆነ ህግና ደንብ ያለው በመሆኑ ነው።››

ሲሉ ጠቅሰው፤ተማሪዎችንም ሰብስበው ጉዳዩን በአግባቡ እንዳስረዷቸው ገልፀዋል። ጥያቄውንም ላቀረቡ ተማሪዎች መርዳት የሚገባቸው ነገር ካለ በፋይናንስም በኩል ቢሆን ለመርዳት እንደሚቻል ተናግረው፤ እነርሱን ተቀብሎ ለማስተማር ግን የተመደበላቸው በጀት በግቢው ላሉ ተማሪዎች ብቻ መሆኑን በመግለፅ እንደማይችሉ አሳውቀዋቸዋል።

ወደ ነበሩበት ዩኒቨርሲቲ እስኪ መለሱ ድረስ ሊያግዟቸው እንደሚችሉም የነገሯቸው በመሆኑም ለአንድ ሳምንት ያህል ተቋርጦ የነበረው ትምህርት መጀመሩን አመልክተዋል።

Via EPA
@Yenetube @FikerAssefa
በአንበጣ መንጋ የተወረረችው ሶማሊያ አንበጣን ለምግብነት ማዋል ጀምራለች።

የአንበጣ መንጋን ሙሉ በሙሉ በኬሚካል መግደል ስላልተቻለ በሱማሊያና በኢትዮጵያ የሰብል ዝርያዎችን በማውደም ላይ ይገኛል፡፡

ሰብላቸውና ምግባቸው በዚህ መንጋ እየተበላባቸው የሚገኙት ሱማሊያዊያን አንበጣውን እየጠበሱ ወደ መብላት መሸጋገራቸውን ፌስ ኦፍ አፍሪካ የተሰኘው ዌብሳይት ዘግቧል።

አንበጣውን የተመገቡ አንድ አዛውንት ለዚሁ ሚዲያ እንዳሉት የጀርባ ህመም እና የደም ግፊታቸው ህመም እንደቀነሰላቸው ተናግረዋል።

የተለያዩ የማህበረሰብ አንቂዎች ወይም አክትቪስቶች ደግሞ የአገሬው ዜጎች አንበጣን ለምግብነት እንዲያውሉ በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ የተወሰኑት ደግሞ ነዋሪዎች እና አንበጣን እንደ አሳ ጠብሶ በመሸጥ ላይ የሚገኙ ምግብ ቤቶችን ከስራቸው እንዲቆጠቡ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው ተብሏል።

በተበበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ የአለም የምግብ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሣየው ፣ አንድ አንበጣ 170 ሺህ ቶን ሰብል በአመት ይመገባል ይህም 1 ሚሊየን ሰው መመገብ የሚችል ነው ተብሏል፡፡

Via:-Ethio fm
@Yenetube @Fikerassefa
በአሁኑ ሰአት በአማራ ክልል በተቃጠሉት 4 መሰጂዶች በማስመልከት ተቃውሞ #በአፋር ከተማ እየተደረገ ነው።

#ከመስጂዶቻችን_ላይ_እጃችሁን_አንሱ!!
መልክት እያስተጋቡ ይገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናሳወቃለን።
@Yenetube @Fikerssefa
የማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት በውጭ አገር የትምህርትና ስልጠና ዕድል እንዲያገኙ የሚያደርግ አዋጅ ፀደቀ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ባቀረበው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ ላይ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባል በውጭ አገር የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ የሚያመቻች አዋጅ ፀደቀ።

ዛሬ ታኅሳስ 14/2012 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የፌደራል መረሚያ ቤት የረጅም ዓመት ልምድ ያለው ማሰልጠኛ እንዳለው ተጠቅሶ፤ ነገር ግን ተደጋጋሚ ወንጀሎችን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግን ወደ ውጭ አገር ልኮ ማሰልጠን እንደሚቻል ተቀምጧል።

በዚሁ አዋጅ ላይ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በፌደራል መንግስት ከሚመደብለት በጀት በተጨማሪ ከውስጥ የሚያገኘውን ገቢ የገንዘብ ሚኒስቴርን እያስፈቀደ መጠቅም እንደሚችልም ተቀምጧል።

Via :- Addis Maleda
@Yenetube @Fikerassefa
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ በአስከተማ ከተማ 01 ቀበሌ በግብርና ቢሮ እሳት ቃጠሎ ተከስቶ ከፍተኛ ንብረት ወደመ፡፡

በጋ/ወ/ፖ/ጽ/ቤት መርማሪ ፖሊሰ ሳጅን ተቀባ ደሳለኝ እንደተናገሩት ቃጠሎው የተነሳው በግብርና ቢሮ ውስጥ መሆኑን ገልፀው ታህሳስ 13/2012 ዓ.ም ለታህሳስ 14/2012 ዓ.ም ሊነጋ 10፡00 አካባቢ ሲሆን መረጃዎችና ንብረቶች መውደማቸውን ተናግሯል ፡፡

በአጠቃላይ የውሃ ማሰባሰብ ቢሮና ሞተር ሳይክል ፣ የተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ፣ የምግብ ዋስትና ቢሮ ፣ የማህበራት ቢሮ ፣ የውሃና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ፣ የመሬት አስተዳደር አንድ ቢሮና ንብረት ክፍል እንዲሁም የቅየሳ መሳርያዎች እና ፋይሎች በሙሉ መውደማቸውና የእሳቱ ቃጠሎም በህብረተሰቡ ተሳትፎ መቆጣጠር እንደተቻለ ገልጸዋል ፡፡

የእሳቱ መነሻ ምክንያት በውል ባይታወቅም ሆን ተብሎ የተፈፀመ እንደሆነ በመገመት አስፈላጊውን ማጣርያና ክትትል እየተደረገ መሆኑን መርማሪው ተናግሯል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሁለት አዋጆችን መርምሮ አጸደቀ!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን ታኅሣሥ 14 ቀን 2012 ዓ.ም አካሔደ።ም/ቤቱ በቅድሚያ በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ አጽድቋል። በመቀጠልም በሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1174/2012 አጽድቋል።

የተፈጥሮ ሀብት፣ መስኖ እና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል የቀረበውን በኢፌዴሪ መንግሥት እና ጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ ለማስተላለፍ የተፈረመውን ስምምነት ዓለም አቀፍ ደንቦችን መሠረት አድርጎ የተካሔደ መሆኑን መነሻ በማድረግ አዋጅ ቁጥር 1175/2012 ሆኖ እንዲጸድቅ ውሳኔ አሳልፏል።በሌላ በኩል በውጭ አገራት ለተሰጡ የግልግል ዳኝነት የተሰጡ ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ውሳኔዎች መርምሮ ለሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል።

ምንጭ፦የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በጅግጅጋ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሔደ

በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ በመስጊዶች ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ ዛሬ ታኅሳስ 14/2012 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በርካቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ድርጊቱን አውግዘዋል።

አብዲአዚያ አሊ የተባሉ ጸሐፊ (freelance writer) ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በርካታ ቁጥር ያላቸው የጅግጅጋ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ የወጡ ሲሆን ሰላማዊ የነበረውን ሰልፍም ወደ ረብሻ ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩም አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰልፉ መሐል ወደ ግርግር በማምራት አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ እንደተደረገ እና መክሸፉን የአዲስ ማለዳ ምንጮች ተናግረዋል።
የተፈጠረውን ግርግር እና ረብሻ ለማክሸፍም ከፀጥታ አካላት ወገን የተኩስ ድምጾች እንደተሰሙ ምንጮች ከስፍራው ጨምረው ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ አቅራቢያም የተኩስ ድምጽ መሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። በርካታ የጸጥታ አካላት ተሸከርካሪዎችም ወደ ዩኒቨርስቲው አቅጣጫ እያመሩ እንደሆነም ከስፍራው ተገልጿል።

በጅግጅጋ ከተማ ተካሔደውን ሰልፍ በተመለከተ ክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የኮሙኒኬሽን አማካሪ መሐመድ ኦላድ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ሰልፉ መካሔዱንና በሰልፉም መሐል የተኩስ ድምጽ የተሰማ ቢሆንም አስለቃሽ ጭስ ወይም የጥይት ለመሆኑ ግን እርግጠኛ መሆን እንዳልቻሉ እና እየተጣራ እንደሆነም ተናግረዋል።

Via:- አዲስ ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa