YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሰበር ዜና ‼️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሀገሪቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች #100_ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ #ለሶማሌ ክልል 35 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር፣ #ለኦሮሚያ ክልል 33 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር፣ #ለደቡብ ክልል 18 ሚሊየን ብር፣ ለአማራ ክልል 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር፣ #ለትግራይ ክልል 3 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር፣ #ለቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር፣ #ለጋምቤላ ክልል 454 ሺህ ብር፣ #ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 387 ሺህ ብር እና #ለሀረሪ ክልል 62 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት ወቀሳ መልስ ሰጠ

ሰሞኑን ለሥራ ጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ሊያደርጉ የነበሩ የቻይና የሻንሺ ግዛት ልዑካን አባላት በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይጓዙ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ እገዳ ተደርጎባቸዋል የሚለው የትግራይ ክልል መንግሥት ቅሬታ የመገናኛ ብዙሃን ዓበይት የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ቆይቷል።

የተፈጠረውን ክስተት ለማጣራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃላፊዎችን አነጋግሯል:: 
ለመሆኑ የልዑካን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበፌደራል መንግስቱ ዕውቅና እና አስፈላጊውን 
ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነው ?

ለሚለው ጥያቄ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚስትር ሚኒስትር  ´ዴኤታ  አምባሳደር  ዶክተር ማርቆስ ተክሌ የፌደራል መንግስቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤዥያ እና ፓስፊቅ አገራት ጉዳዮች መምሪያ እና ቻይና ፔኪንግ  በሚገኘው የኢትዮጵያሚስዮን አማካኝነት 
ከወራት በላይ  ከግዛቲቱ ሃላፊዎች ጋር የደብዳቤ ልውውጥ እና ውይይት አድርጎ ለትግራይ ክልልም 
በደብዳቤ አሳውቆ በህጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አረጋግጠውልናል::

Via:- ጀርመን ድምፅ
@Yenetube @Fikerassefa