YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኢዜማ

ትላንት በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ በደረሰው ጥቃት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርስ ጥቃት በምንም ምክንያት ተቀባይነት የሌለው እና ጥቃቱ በየትኛውም የእምነት ተቋም ላይ ሲደርስ ሁሉም ማኅበረሰብ በአንድነት ቆሞ ሊያወግዘው የሚገባ ተግባር ነው።

መንግሥት በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ጨርሶ ሊታገስ አይገባም። በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈፀም ጥቃት የዜጎች የእምነት ነፃነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰፍን የምንፈልገው ሀገራዊ መረጋጋት እና ሰላም ላይ ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር የወንጀል ድርጊት መሆኑን በመረዳት መንግሥት በአጥፊዎች ላይ ተገቢውን የህግ እርምጃ መወሰድ አለበት።

ከእንደዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየሞከሩ የሚገኙ ኃይሎች ከዚህ ኃላፊነት ከጎደለው አካሄድ እንዲታቀቡ አጥብቀን እናሳስባለን።

መንግሥት ትላንት በሞጣ የተፈፀመው ዓይነት ጥቃት በድንገት የሚከሰት አለመሆኑን በመረዳት ለወደፊቱ እንዲህ ዓይነት ጥፋት ከመከሰቱ አስቀድሞ መከላከል የሚቻልበት አቅም መፍጠር ላይ አትኩሮት አድርጎ መሥራት ይገባዋል።

የአጥፊዎቹ ድርጊት በከተማው የሚኖሩ የሁለቱን እምነት ተከታዮች ለዘመናት በሰላም አብሮ በመኖር ያላቸውን ታሪክ በፍጹም የማይገልፅ ቢሆንም፣ በደረሰው ጥፋት ምክንያት ወደፊት በዜጎች መሀከል የሚኖረው ግንኙነት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን መቃቃር የሞጣ ከተማ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች አና የከተማው አስተዳደር የከተማው ሕዝብን በማረጋጋት፣ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀትና እና አጥፊዎችን አጋልጦ በመስጠት የማያዳግም መፍትሄ ሊያስቀመጡ ይገባቸዋል።

የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት
@Yenetube @Fikerassefa
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትግራይ ክልል የተሰጠ መግለጫ

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቻይና ሻንሲ ግዛት ልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኢንቨስትመንት፣ ትምህርት፣ መአድን ልማት እና የሁለትየሽ ግንኝነት ዙርያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማድረግ እየመጣ መሆኑን በግልፅ ደብዳቤ ለክልሉ መንግስት መፃፉ ይታወቃል፡፡

ሆኖም የትግራይ ክልል መንግስት እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ በመጠበቅ ላይ እያለ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ጉዞኣቸው እነዲስተጓጎል እና እንዳይመጡ ተደርጓል፡፡

በመሆኑም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የቻይና ሻንሲ ግዛት ልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ እንዳይመጡ መከልከላቸው አግባብነት የሌለው መሆኑ በመግለፅ ፤ይህ ተግባር በትግራይ ክልል ውስጥ የሚደረጉትን የኢንቨስትመንትና ተዛማጅ የልማት እንቅስቃሴዎች በይፋ የሚገታና የህዝብ ለህዝብ መልካም ግንኙነት እንዳይጠናከር የማድረግ ተግባር የተፈፀመበትን ምክንያት በወቅቱ በቂ ማብራርያ እንዲሰጥበት የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን በይፋ የተሰጠ ማብራርያ ባለመኖሩ በድጋሚ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጠው ይጠይቃል፡፡

የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ
ታህሳስ11 2012 ዓ/ም
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሚገኘው ብራና የባህል እና የኪነጥበብ ማዕከል ነገ እሁድ(ታህሳስ 12) በመቄዶንያ የኪነጥበብ ድግስ አዘጋጅቷል። ዝግጅቱ ከቀኑ 8:00 የሚጀምር ሲሆን መምጣት የምትችሉ ተጋብዛችኋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ከትላንት ምሽቱ የመስጂዶች ቃጠሎ ጋር በተያያዘ አምስት ሰዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አልጀዚራ ዘቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
ትምህርት ተቋረጦ በነበረባቸዉ ት/ት ክፍሎች ዉስጥ ለምትገኙ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

ከቅዳሜ ታህሳስ 11/2012 ዓ.ም. ጀምሮ ሲደረጉ በነበሩት ዉይይቶች መሠረት ከሰኞ 13/2012. ጠዋት 2፡00 ጀምሮ መደበኛዉ ትምህርት ስለሚቀጥል፣ መማር ማስተማር ተቋርጦ በነበረባቸዉ ክፍሎች ዉስጥ የምትገኙ ተማሪዎች በየክፍላችሁ ተገኝታችሁ ትምህርት እንድትቀጥሉ እያሳሰብን፣ ነባር የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ተማሪዎች (2nd year and above) በተያዘላችሁ መርሃ-ግብር መሰረት ሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ በተዘጋጀዉ ዉይይት መድረክ እንድትሳተፉ እናሳዉቃለን፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@Yenetube @Fikerassefa
"ዶ/ር አብይ እና አቶ ለማ መገርሳ ተስማምተዋል " እሸት በቀለ - DW

በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይና የመከላከያ ምኒስትሩ ለማ መገርሳ መካከል የነበረ አለመግባባት "በበሳል የድርጅታችን ስራ አስፈጻሚ አመራሮችና በቀድሞ የትግል ጓዶች" መፈታቱን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ። "በጋራ ለመታገል ተስማምተዋል" ተብሏል።

@Yenetube @fikerassefa
👏OBN በሰበር ዜናው አቶ ለማ መገርሳ በድርድር ከብልፅግና ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጿል ።

@Yenetube @FikerAssefa
ታላቅ ቅናሽ!!!
ወብ የሆኑ የወንዶች አልባሳትን ከRJ FASHION በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ.
ጂንስ ሱሪ,ቱታ,ሸሚዞች አሉን
ለበለጠ መረጃ
:0900628132
TELEGRAMPAGE:-
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
አቶ ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ የነበረቸውን ልዩነት አጥብበው የህዝቡን ትግል ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሻገር መስማማታቸው ተገለጸ

አቶ ለማ መገርሳ ከዚህ ቀደም በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ ያላቸውን ልዩነት በኦሮሞ ባህል መሰረት ስምምነት ከተደረገ በኋላ ልዩነታቸውን አጥበው ከዚህ በኋላ በጠንካራ አንድነት በጋራ በመስራት የህዝቡን ድል ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከስምምነት ተደርሷል፡፡

ይህ ስምምነት የተደረሰው የቀድሞ የODP ስራ አስፈጻሚዎችና ነባር አመራሮች በጋራ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

ፓርቲው የዴሞክራሲ ስርዓትንና በኦሮሞ ባህል መሰረት ውስጣዊ ችግሩን እና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ጠንክሮ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
በፖለቲካ ሂደት ውስጥ በተለይ ደግሞ ሪፎርም በሚደረግበት ወቅት የሀሳብ ልዩነቶች መኖራቸው የተለመደ መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡
የሀሳብ ልዩነት መኖር በራሱ ችግር እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ትልቁ ነገር የሀሳብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via:- OBN
@Yenetube @Fikerassefa
የትራንስፖርት ሚኒስቴር እያስመዘገበ ላለው የተሻለ አፈጻጸምና ላሳየው አጋርነት ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ ከተባለ ተቋም እውቅና ተሰጠው።

መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ፥ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን ትስስር ለማጠናከር ትኩረቱን በትራንስፖርትና ንግድ ዘርፍ ላይ አድርጎ የሚሰራ ነው።

ተቋሙ በየአመቱ በሚያዘጋጀው አመታዊ ጉባዔ ላይ በምስራቅ አፍሪካ በአጋርነት ከሚሰሩ አቻ ተቋማት ውስጥ ለኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር፥ በ2019 ባስመዘገበው የተሻለ አፈጻጸምና ላሳየው አጋርነት እውቅና መስጠቱን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@Yenetube @Fikerassefa
ማስታወቂያ

💥RUTA'S COLLECTION ONLINE SHOPPING"💥

ከልጅ እስከ አዋቂ
-ልብሶች
-የህፃናት ልብሶች
-ጫማዎች
-ቦርሳዎች
- የለም ብቻ ነው የሌለው ቻናላችን ላይ ገብተው የፈለጉትን ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን።
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFe-eZf8qYhlHBBX_g
📌Urgent Notice to all First year Students of Wollega University .
A meeting which was planned to be conducted today at 4:00 LT with Higher Officials of Ministry of Education and WU's Board members is now postponed to tommorow morning to 2:00 LT.Therefore ,you are
kindly invited to attend the meeting in the Auditorium.

☆The University

አስቸኳይ ማስታወቂያ ለወለጋ ዩኒቨርሰቲ አንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ ።
ዛሬ በቀን 13/04/2012 ዓ.ም ጠዋት ከ4:00 ጀምሮ ሊካሄድ የነበረው ስብሰባ ለነገ 14/04/2012 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ስዓት የተላለፈ መሆኑን ኢያሳወቅን ፣በተጠቀሰው ሰዓት በወለጋ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል።

☆ ዩኒቨርሲቲው

@yenetube @Fikerassefa
መረጃ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ታህሳስ 11/2012 ዓ.ም ከክልል፣ ከዞን እና ከከተማ አስተዳደር የሚመለከታቸው አካላት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከተለያዩ አደረጃጀት ተወካዮች፣ከተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

ውይይቱን ተከትሎም ዛሬ ማለትም ታህሳስ 13/2012 ዓ.ም ትምህርት ተቋርጦባቸው በነበሩ ሁሉም ግቢዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ተጀምሯል፡፡

Via:- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
@Yenetube @Fikerassefa
የሳዑዲ አረቢያ ፍርድ ቤት በጀማል ኻሾግጂ ግድያ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ አምስት ሰዎች በሞት እንዲቀጡ መፍረዱን የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

ሌሎች ሶስት ተከሳሾች እስር ተፈርዶባቸዋል። የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሞት የተፈረደባቸው "በኻሾግጂ ግድያ በቀጥታ የተሳተፉ" መሆናቸውን አስታውቋል።

ሞት ከተፈረደባቸው መካከል ከሳዑዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን አጠገብ በብዛት ይታዩ የነበሩት የ47 አመቱ ማኸር አብዱል አዚዝ ሙተርብ ይገኙበታል።

ሳዑዲ አረቢያ በኻሾግጂ ግድያ 31 ሰዎች ተጠርጥረው መመርመራቸውን እና 21 መታሰራቸውን አስታውቃለች። አስሩ በወንጀሉ ለመሳተፋቸው ማረጋገጫ ባለመገኘቱ መለቀቃቸውን የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።

በተቋሙ መግለጫ መሰረት በወቅቱ ጀማል ኻሾግጂን በድርድር አሊያም በኃይል ከቱርክ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመውሰድ በሳዑዲ አረቢያ የስለላ መስሪያ ቤት ምክትል ኃላፊ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር።

ድርድሩ ሳይሳካ ሲቀር የድርድሩ መሪ ጀማል ኻሾግጂ እንዲገደል ትዕዛዝ ማስተላለፉን መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

Via:- እሸት በቀለ
@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ በአርባ ምንጭ እየመጣ የነበረ አይሱዙ መኪና ወዜ ቀበሌ (ልማት ሰፈር) ሲደርስ በአስፓልት ላይ እንዲህ በተዘረጋው ጭቃ ተንሸራቶ ወድቋል!

አርባ ምንጭ በከተማው ዋና መንገድ ውሃ መፍሰሻ/መውረጃ አጥቶ እንዲህ አስፓልቱን ሲያበላሸውና ለተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ በመሆን የቆየው ይህ መንገድ አሁን ደግሞ ለትራፊክ አደጋ ምክንያት እየሆነ ነው።

Via:- Dawit Wasihun Kassa
@YeneTube @FikerAssefa
ገርጂ የሚገኘው ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በርካታ ተማሪዎች ተጠልለዋል!

ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሄድ አዲስ አበባ የገቡ 200 የሚገመቱ ተማሪዎችን ዛሬ በአጋጣሚ በቤተ-ክርስቲያኑ በኩል ሳልፍ ለመመልከት ችያለሁ። ተማሪዎቹን ለመርዳት ጥረት እያደረጉ ያሉ ሰዎች "በየካ ሚካኤል እና ሳህሊተ ምህረት ቤተ-ክርስቲያኖችም ሌሎች ተማሪዎች ይገኛሉ። ገንዘብ አሰባስበን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመላክ እየሞከርን ነው" ብለውኛል።

"ለምን ዩኒቨርሲቲ ለቀው እንደመጡ አጣሩ ተብለን ነው" ያሉ ፖሊሶችም በቤተ-ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ይታዩ ነበር። አስተባባሪዎቹም "እኛ ለምን ለቀው እንደወጡ መመለስ አንችልም፣ ከፈለጋችሁ ተማሪዎቹን አናግሩ" የሚል መልስ ሲሰጡ ነበር።

Via:- ኤልያስ መሰረት
@Yenetube @Fikerassefa
በሞጣ በሀይማኖት ሰበብ በተፈጠረው ግርግር የንግድ ሱቆች ላይ ዘረፋ መፈጸሙን የአማራ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አስታወቀ

በሞጣ ከተማ አስተዳደር አላማውን የእምነት ተቋማት ላይ ያደረገ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት ይርሳው መግለጫ ሰተዋል፡፡

በመግለጫቸውም አጋጣሚውን በመጠቀም ሱቆች እንደተዘረፉና እንደወደሙ እንዲሁም በሰዎችም ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰም ተናግረዋል፡፡

በዚህ ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

የፀጥታ ኃይሎችም ወደ አካባቢው በመግባት የማረጋጋት ስራ እንደተሰራና ከህብረተሰቡም ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሆነ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

አቶ ጌትነት አክለውም በደረሰው ጉዳት የክልሉ መንግስት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልፀው ወንጀለኞችንም ለፍርድ ለማቅረብ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

አሐዱ ሬዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa
የመስጂዶች መቃጠል ምክንያት በማድረግ ዛሬ በሀረር ፣ በባቢሌ፣ በሶማሌ ፣ በአርሲ ቦቴ፣ ባሌ ጊንዲር፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ ነገሌ፣ ኮፈሌ፣ አወዳይ እና ጊኒር ከተሞች የሙስሊም መኃበረሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛል።

@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር መረጃ!

የቦይንግ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴኒስ ሙሊንበርግ ከስራቸው ተነስተዋል። ኒውዮርክ ታይምስ "ተባረሩ" ብሎ የዘገበ ሲሆን ብሉምበርግ ደግሞ "በፍቃዳቸው ከስራቸው ለቀዋል" ብሏል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው የ737 MAX አውሮፕላን በኢንዶኔዥያ እና ኢትዮጵያዊ ተከስክሶ ከ 300 በላይ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈ ጀምሮ በርካታ ትችቶችን ሲያስተናግዱ ነበር።

Via:- Elias Meseret
@Yenetube @Fikerassefa
በሕዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል እና የግድቡ አተገባበር ላይ በካርቱም የተካሄደው የሦስትዮሽ ውሃ ሚንስትሮች ስብሰባ ተጠናቋል፡፡ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ አሁንም ስምምነት አልተደረሰም፡፡ በድርቅ ትርጓሜ እና በድርቅ ጊዜ ግድቡ እንዴት እንደሚያዝ ግን መቀራረብ እንደተፈጠረ የሱዳኑ ውሃ ሚንስትር እንደተናገሩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ቀጣዩ ስብሰባ በአዲስ አበባ ታህሳስ 30 እና ጥር 1 ይካሄዳል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa