YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በኖቤል ኮሚቴ የተበረከተላቸው አንደኛው ሜዳልያና የምስክር ወረቀት ምስለ ቅርፅ በሰላም ሚኒስቴር ተቀመጠ፡፡

የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚል እና የሚኒስቴሩ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተበረከተው 100ኛው የሰላም ኖቤል ሜዳልያና የምስክር ወረቀት ምስለ ቅርፅ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት የተካሄደው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ በሙፈሪያት ካሚል ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰላም ለሰጡት ዋጋ የተበረከተ መሆኑን ገልፀው በሀገራችን ያላውን የሰላም እና የእርቅ እሴት ልናጎለብተው ይገባል ብለዋል።

ሜዳልያና የምስክር ወረቀት ምስለ ቅርፁ ከሰላም ሚኒስቴር በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚቀመጥ ሲሆን ዋናው ሽልማት ደግሞ በብሄራዊ ሙዝየም ተቀምጦ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል።

Via:- EBC
@Yenetube @FikerAssefa
አሳሳቢው በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ እየደረሰ ያለው ስርቆት!

ታህሳስ 04 ቀን 2012 ዓ.ም በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ (Tower) ላይ በደረሰው ስርቆት ሞጆ ከተማና አካባቢው ኤሌክትሪክ ተቋርጧል።

ይህ የዘረፋ ወንጀል የተፈጸመው ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ አካላት ሲሆን: የዘረፋው ሰለባ የሆነው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለሞጆ ኃይል ማስተላለፊያ ጣቤያ (Distribution Subsstation) ኃይል የሚያስተላልፍ ነው።

ክቡራን የሞጆና አካባቢው ደንበኞቻችን ይን ችግር እስኪቀረፍ በከፊል ኤሌክትሪክ የተቋረጠ መሆኑን እያሳወቅን ይህንን አይነት እኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ዘራፊዎችን በመከታተል ለህግ አስከባሪ አካላት በማሳወቅ ወንጀልን በጋራ በመከላከል በመንግስትና ህዝብ ሀብት ላይ እየረሰ ያለውን ጉዳት እናድን እያልን:
መሠል ተግባራት እንዳይፈጸሙ ህብረተሠቡ መሠረተ ልማቱን እንዲጠብቅ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Via:- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
@Yenetube @Fikerassefa
ትኩረት ለቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ!
በአካባቢው ካሉ በርካታ ሰዎች እየደረሰኝ ያለው መልእክት እንደሚያስረዳው ትናንት ምሽት በማንቡክ ቀበሌ በተነሳ ግጭት ውጥረት ተከስቷል፣ የሰው ህይወትም ሳይጠፋ አልቀረም።

የክልሉን ሀላፊዎች ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ሙከራ ባደርግም እስካሁን አልተሳካም።

Via:- Elias meseret
@Yenetube @Fikerassefa
የቤንሻንጉል ክልል ቃል አቀባይ አቶ መለሰ በየነን በስልክ አግኝቼ በዳንጉር ወረዳ ስለተከሰተው የሰው ህይወት መጥፋት ጠይቄአቸው ይህን መልስ ሰጥተዋል!

"እስካሁን ባለኝ መረጃ በትናንትናው እለት የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል። ሁለቱ ሰዎች የአማራ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ 11 ሰአት ገደማ ምርት እየሰበሰቡ በነበረበት ወቅት በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፎ ተገኝተዋል። ከዛ በሁዋላ አንድ የጉሙዝ ተወላጅ ከገበያ እየተመለሰ በነበረበት ወቅት ጥቃት ደርሶበት ህይወቱ አልፏል። የጥቃቱ ምክንያት እስካሁን ግልፅ አይደለም፣ ግጭት ነበር የሚል መረጃም አልደረሰንም። ሰዎቹ ህይወታቸው አልፎ ነው የተገኙት። አሁን ላይ የተፈጠረው የህይወት ማለፍ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አጣርቼ እነግርሀለው።"

Via:- Elias Meseret
@Yenetube @Fikerassefa
በደብረብርሀን አንድ ካሬ መሬት እሰከ 32,000 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።

- ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት -

የኢንቨስትመንት ፍሰቷ አየጨመረ የመጣው ቀዝቃዛዋ ደብረብርሀን የመሬት ዋጋ ካለፉት ሶስት አመት ጀምሮ እያነር መጥቶ አንድ ካሬ መሬት በሊዝ እስከ 32,000 ብር ድረስ እየተሸጠ እንደሚገኝ ከከተማዋ ባለሀብቶች መረጃ ደርሶኛል።

እንዲሁም የቤት ኪራይ ዋጋም በአራት አመት ውስጥ በመቶ ፐርሰንት ጨምሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
ስፖርት !

ሲዳማ ቡና ከሜዳው ውጭ ጅማ አባጅፋርን ሲያሸንፍ መቀሌና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል ።

ወሎ ኮምቦልቻ በሜዳው ሲያሸንፍ ወልዲያ ከነማና ደሴ ከነማ ተሸንፈዋል ።ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ከነማ ከሜዳው ውጭ ነጥብ ተጋርቷል ።

👉 ከፍተኛ ሊግ

ተጠናቀቀ | ወልዲያ ከነማ 0- 1 ፌደራል ፖሊስ
ተጠናቀቀ | ለገጣፎ ከተማ 4 - 3 ደሴ ከነማ
ተጠናቀቀ | አክሱም ከተማ 1 - 1 ደ/ብርሃን ከነማ
ተጠናቀቀ | ወሎ ኮምቦልቻ 2 - 1 አቃቂ ቃሊቲ

👉 ኘሪምየር ሊግ

ተጠናቀቀ |መቀሌ 70 እ.1 - 1 ኢትዮጵያ ቡና
ተጠናቀቀ | ጅማ አባጅፋር 1 - 2 ሲዳማ ቡና
በአዲስ አበባ የሚገኙ ያረጁ ላዳ ታክሲዎች በአዳዲስ ሊተኩ ነው!

በአዲስ አበባ የሚገኙ ያረጁ አነስተኛ የላዳ ታክሲዎች በአዳዲስ ታክሲዎች ሊተኩ እንደሆነ እና ለዚሁ ሲባል የታክሲ ባለቤቶችን ከባንክ ጋር የማስትሳሰር ስራ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ አስታወቁ።የአዲስ አበባ የታክሲና የሀይገር ባስ ማህበራት ለተገልጋዩ ክብርን በመስጠት ለማገልገል የሚያስችል መርሐ ግብር ይፋ ማድረጊያ መድረክ 13 የታክሲ እና ሶስት የሀይገር ባስ ማህበራት በተገኙበት ተከናውኗል።መርሐ ግብሩ በተለይ ለአረጋውያን፣ ለነፍሰጡሮች እና ለአካል ጉዳተኞች በተሻለ መንገድ ለማገልገል የሚያግዝ ነው ተብሏል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት ኢ/ር ታከለ ኡማ አነስተኛ ታክሲዎችና ሀይገር ባሶች ለነዋሪው እየሰጡ ላሉት አገልግሎት አመስግነዋል።የታክሲ ባለንብረቶች በተለያዩ ጊዜያት ለሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች አስተዳደሩ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑንንም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።በእድሜ ያረጁ አነስተኛ ታክሲዎች አዳዲስና የመጫን እቅማቸው ከፍ ባሉ አነስተኛ ታክሲዎች እንዲተኩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም በበመድረኩ ተነስቷል።የታክሲና የሀይገር ባስ ባለንብረቶች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ሚያከናውናቸው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴዎች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለፃቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የፊታችን የካቲት ወር የአፍሪካ ሀገራት ምድር ጦር ጉባኤን ታስተናግዳለች

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ የካቲት ወር 2020 የአፍሪካ ሀገራት ምድር ጦር ጉባኤን ታስተናግዳለች።

ጉባኤውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ጋር በመተባር ያዘጋጀዋል።

በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ላፍቴ ፍሎራ በጉባኤው ዝግጅት ዙሪያ ለመምከር ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝታቸውም ወቅት ለጉባኤው እየተደረገ ባለው ዝግጅት ዙሪያ ከኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

የአሜሪካ ጦር በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት ጥረቶችን ማገዝ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ለአራት ቀናት የሚካሄደው ጉበኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወታደራዊ አዛዦችን የሚያሰባስብ ነው።

በዚህ ቆይታቸው በሀገራቱ መካከል ወታደራዊ ትብብርን በማጠናከር የአህጉሪቱን ደህንነት መጠበቅ ላይ እንደሚወያዩ በአፍሪካ ከአሜሪካ ጦር እዝ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@Yenetube @Fikerassefa
የነዋሪው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ገለፁ።
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የተመራው የስራ አመራር ቡድን በዛሬው ዕለት እንደ ከተማ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው ከፍተኛ የሆኑና የረዥም ጊዜ የነዋሪዎች ጥያቄ የሆኑ የመሠረተ ልማት ስራዎችን ለማፋጠን ያለመ ምልከታ አድርጓል፡፡
የዛረው ምልከታ በተለይም በከተማዋ ገጠራማ አካበቢዎች የተጀመሩ የመንገድ መሰረተ ልማቶች፣ ሆስፒታል እና የትምህርት ተቋማትን እንዲሁም ሌሎች የካፒታል ፕሮጀክቶችን የካተተ ሲሆን ለዩ.ኤል.ጂ.ዲ.ፒ ልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ የማዘጋጀት ስራው የደረሰበትን ደረጃ መመልከትም የጉብኝቱ አንድ አካል ነበር፡፡
በምልከታው ወቅት የረዥም ጊዜ የነዋሪዎች ጥያቄ የሆኑና ከ2008 ጀምሮ ውል ተገብቶባቸው ነገር ግን አጥጋቢ ስራ ሳይሰራባቸው በእንጥልጥል የቀሩ የመንገድ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ለነዋሪው ጥያቄ ተገቢው ምላሽ ሳይሰጥባቸው የከረሙ የካፒታል ፕሮጀክቶች፣ ተገንብተውም ቢሆን የሚፈለገውን አገልግሎት በሙሉ አቅም መስጠት ያልቻሉ በጅምር የቀሩ ስራዎች ተለይተዋል እነዚህንም ማፋጠን የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
የከተማዋን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት የሚያፋጥኑ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ተንጠልጥለው የቀሩ ተግባራትን ልየታ በማድረግ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ በመስጠት በትክክለኛው ወቅት ተገቢውን ምላሽ መስጠት የአስተዳደሩ የፀና አቋም መሆኑን ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በጉብኝቱ ወቅት ገልፀዋል፡፡

Via:- Hawassa City Administration
@Yenetube @Fikerassefa
ናይጀሪያዊው ነጋዴ ጓደኛው ያገናኘው ሴተኛ አዳሪ የገዛ ልጁ ሆና አገኛት🙊

በናይጀርያ ግዛት ውስጥ ባለች ዴልታ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው አሳባ የሶስት ልጆች አባት ባለትዳርና በንግድ ስራ የተሰማራው ነጋዴ ጓደኛው ለአዳር ከእሱ ጋር እንድታሳልፍ ያገናኘው ሴት ወደሚያገኛት ክለብ ሲያመራ ዛይራ የተባለች 20 አመት ያልሞላት ሴት ልጁ ስትሆን ተጠደናግጦም እንዴት ይሄን ትሰርያለሽ ብሎ የመታት ሲሆን ሰዎችም የልጅቷን ጩኸት ሲሰሙ ልጅቷን ከአባቷ ዱላ ያስጣሏት ሲሆን አባትዬውንም አንተስ ትዳር እያለክ እንዴት ወደ ሴተኛ አዳሪ ትሄዳለክ የስራክን ነው ያገኘኸው በማለት ወቅሰውታል ሲል ኮጂ ዴይሊ የተባለ ድህረገፅ አስነብቧል።

ምንጭ: ኮጂ ዴይሊ / ተስፋዬ ጌትነት
@Yenetube @Fikerassefa
Fastest-growing economies, 2019.

Rwanda: 7.8%
Bangladesh: 7.8%
Ivory Coast: 7.5%
Ghana: 7.5%
#Ethiopia: 7.4%
Nepal: 7.1%
Cambodia: 7%
Benin: 6.6%
Mauritania: 6.6%
Vietnam: 6.5%
Gambia: 6.5%
Maldives: 6.5%
Laos: 6.4%
Niger: 6.3%
Turkmenistan: 6.3%
Myanmar: 6.2%
@Yenetube @Fikerassefa
Ten 'coolest places to go', 2019.

1. Azores, Portugal
2. Eastern Bhutan
3. Cabo, Mexico
4. Colombia
5. #Ethiopia
6. Madagascar
7. Mongolia
8. Pakistan
9. Rwanda
10. Turkish Riviera

(Forbes)
@Yenetube @Fikerassefa
እንደምን አደራችሁ የሀገሬ ልጆች ?
#ውቢቷ_ባህር_ዳራ ከተማ
#Yenetube
ለኢትዮጵያ ህፃናት 100,000 ዶላር እርዳታ ለገሰ
ታዋቂው የግራሚ አዋርድ ተሸላሚ አቤል ተስፋዬ ቶሮንቶ ካናዳ ለሚገኝ ኢትዮጵያ ውስጥ በ ኤች አይ ሺ ወላጅ ያጡ ህፃናትን ለሚረዳው ፒፕል ቱ ፒፕል ካናዳ የ 100,000 ዶላር እርዳታ ለገሰ።

@Yenetube @Fikerassefa
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከ100 የፎርብስ መጽሄት የ2019 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች አንዷ ሆነው ተመረጡ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከ100 የፎርብስ መጽሄት የ2019 የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው ተመረጡ።
መፅሄቱ በየአመቱ በሚያወጣው የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል 93ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ፕሬዚዳንቷ ከአህጉረ አፍሪካ ብቸኛዋ ሴት ተመራጭ ናቸው።
Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa