YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዛሬ ዋልታ የሰራውን ስህተት ዶ/ር ደብረፂዎን ገብረሚካኤል ከመሸ በትግረኛ ባሰፈሩት አጠር ያለ ጽሑፍ "#በህዝብ_እና_በፓርቲው ላይ ሲካሄድ የቆየው #የስም_ማጥፋት_አካል_ነው" ብለውታል።

ትርጉም :- ቢቢሲ አማርኛ
@YeneTube @Fikerassefa
ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ የቀረበ የሀዘን መግለጫ፡-

በዩኒቨርሲቲው ሻምቡ ካምፓስ በደን ጥናት 2ተኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ኢያየሁ እናኑ ጥላሁን ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጪ በግምት 3ኪሜ. በሚሆን ርቀት ላይ በሚገኘው ሚካኤል ቤተክርስቲያን አከባቢ ከሌሊቱ 8:00 እስከ 9:00 ሰዓት መካከል ባልታወቁ ሰዎች ጥቃት ደርሶበት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ዩኒቨርሲቲው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቹ ፣ ለጓደኞቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

ምንጭ:- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
በተጨማሪ የVOA ዘገባ ያድምጡ

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሻምቡ ግቢ ማንነታቸው ለጊዜው አልታወቀም በተባለ ግለሰቦች ትናንት አንድ ተማሪ መገደሉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀሰን ዩሱፍ አስታውቀዋል። ግድያውን በመፈፀም የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

@Yenetube @fikerassefa
የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ከሚል፣ የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ እንዲሁም የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በፈረንጆቹ ከታህሳስ 14 አስከ 15 በኳታር በሚካሄደው 19ኛው የዶሃ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ዶሃ ገብተዋል።

ከፎረሙ አስቀድሞም የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከሚል እና የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በዛሬው እለት በዶሃ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ዓለም አቀፍ ት/ቤትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ እና የሚሲዮኑ የስራ ባልደረቦች፣ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር አመራሮች፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች መሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ቤተሰቦች፣ እንዲሁም ሕጻናት ተገኝተዋል።

የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቱ እድሳት በፍጥነት እና በጥራት እየተከናወነ ሲሆን፣ የእድሳት ሥራው በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ሥራውን የሚያከናውነው ተቋራጭ ኃላፊዎች በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቱም በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራውን ይጀምራል ነው የተባለው።
የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቱ እንዲቋቋም በ 2010 ዓ.ም ለኳታር መንግስት ጥያቄውን በማቅረብ አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ያደረጉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መሆናቸውን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
‹‹ኢትዮጵያን ለመፍረስ የሚዳርጋት ስጋት የለም››
ጀነራል ብርሃኑ ጁላ :- ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

ሀገራችን ውስጥ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከጀርባ ባሉ ስውር እጆች በሚደገፉ ኃይሎች ወይንም ቡድኖች የሚፈጠሩ ግጭቶች ቢኖሩም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እያለ ኢትዮጵያን የሚበታትን እና ለመፍረስ የሚዳርጋት ስጋት እንደሌለ ተገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፣ ፖለቲከኞች የሚሉትን ሊሉ ይችላሉ፤ የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል የት ሄዶ ነው ኢትዮጵያ የምትፈርሰው? ኢትዮጵያን የሚበታትንና ለመፍረስ የሚዳርጋትም ምንም አይነት ስጋት የለም፡፡

እንደ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ገለጻ፣ አሁን በተጨባጭ በሚታየው ሁኔታ ሀገራችን የዳር ድንበር መደፈርና የውጭ ስጋት የለባትም፡፡ በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በደቡብ፣ በምእራብ ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታም ሰላማዊ ነው፡፡ ሕዝቡ ተረጋግቶና ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ትብብርና ድጋፉን አጠናክሮ መስራት ይጠበቅበታል:: በአጠቃላይ ህዝቡ ሊሸበር አይገባውም፤ በመረጋጋት ሥራውን መስራት አለበትም ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ⬇️
https://telegra.ph/YeneTube-12-14
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶ/ር ደብረፆውን ሰላም መሆናቸው በትላንትና ማታ Facebook live ገብተው ነበር ቪዲዮውን ይመልከቱ።
@Yenetube @FikerAssefa
"የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ" ህግና ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው እና እንዲቋቋም ለካቢኔ የቀረበው ሀሳብ ይሁንታን አግኝተዋል::
@Yenetube @Fikerassefa
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 77ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኞች ማኀበር የአየር መንገዱ አስተዳደር እያደረሰበት ያለው የመብት ጥሰት እና ከፍተኛ ጫና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ገልጾ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠው ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠየቀ፡፡

ሙሉ መግለጫውን አያይዘናል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተማሪዎች የምገባ እና ተያያዥ ጉዳዮች በተቋም ደረጃ እንዲቋቋም ወሰነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የተማሪዎች የምገባ በተቋም ደረጃ እንዲመራ ተወስኗል ።

ኤጀንሲው በየአመቱ ለተማሪዎች የሚደረጉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎችም ይሁን የምግብ አቅርቦቶች በተቀናጀና ወጥ በሆነ መልኩ ሳይቆራረጥ ለተማሪዎች እንዲደርስ የማድረግ ተልእኮን ይዟል፡፡

ለዚህም ኤጀንሲው የከተማ አስትዳደሩ ለተግባሩ የመደበውን በጀት ስራ ላይ ከማዋል ጀምሮ ለጋሽ አካላትንና በጎ ፈቃደኞችን የማስተባበርና አቅርቦቶቹ በትክክል እየተዳረሱ መሆኑን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት፡፡

አስተዳደሩ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ለታዳጊ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ የማሰራጨት እቅድም በኤጀንሲው የሚመራ ይሆናል።
የኤጀንሲው መቋቋም ታዳጊዎች ትኩረታቸውን ትምህርት ላይ ብቻ እንዲሆን በማድረግ የታዳጊዎች የትምህርት አቅም ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡

ኤጀንሲው ተማሪዎች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ነጻ የትምህርት እድል እንዲያገኙ የማድረግ ተግባርም የሚያከናውን ይሆናል።
ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ኤጀንሲው እንዲቋቋም የቀረበውን አዋጅ ለምክርቤት መርቷል፡፡

ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲሆንም ካቢኔው ወስኗል።

ለተያዘው የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ አነሳሽነት ለ600ሺህ ተማሪዎች ዩኒፎርም እና የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ከ300ሺህ በላይ ታዳጊ ተማሪዎች የምገባ መርሀ ግብር ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

Via:- Addis Ababa City Administration
@Yenetube @FikerAssefa
Sport !

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።
ስሁል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ ላይ በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ባህር ዳር ከነማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፥ ወላይታ ድቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሰበታ ከተማ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በተመሳሳይ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ወደ ሀድያ ሆሳዕና አቅንቶ እንግዳውን ወልቂጤ ከተማን የገጠመው ፋሲል ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

በሌላ በኩል ድሬ ዳዋ ከተማ ከሃድያ ሆሳዕና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ድሬ ዳዋ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ጨዋታው ነገ ቀጥሎ ሲካሄድ መቐለ ላይ በትግራይ ዓለማቀፍ ስታዲየም መቀሌ 70 እንደርታ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታል፤ ጅማ አባ ጅፋር እና ሲዳማ ቡና ደግሞ በአደማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።

Via:- FBC
@Yenetube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የደረሱ ሰብሎችን ከሚሰበስቡ አርሶ አደሮች ጋር በአጨዳ ላይ የሚያሳይ ቪዲዮ ።
@Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል መቐለ የሚገኘውን አዋሽ የብረ ታብረት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
በቀጣይ ወር በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በድምቀት ለማክበር አስተዳደሩ ድጋፍ ያደርጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁእ አቡነ ማትያስ ጋር ተወያዩ።

ኢ/ር ታከለ የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ በቅርስት በመምዝገቡ የተሰማቸውን ደስታ ለብፁእ አቡነ ማትያስ ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማዋ በሚገኙ ሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ዩኒፎርምን ጨምሮ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲደረግ እና የምገባ መርሃ ግብር በዘላቂነት እንዲተገበር ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከከተማዋ ወጣቶች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ሽልማቱ የተበረከተላቸው "እናመስግን!" በሚል በከተማው ወጣቶች በተዘጋጀው የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡

የ300 ሺ ተማሪዎች ምገባን ጨምሮ ፣ ለ600 ሺ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች የዩኒፎርም እና የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እንዲሁም በአስሩም ክፍለከተሞች የሚገኙ የአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ቤት እድሳት ላይ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፆኦ ሽልማት እንደተበረከተላቸውም ተገልጿል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ህግ እና ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው እና በዘላቂነት እንዲተገበር ለማስቻል ለካቢኔ የቀረበው ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት በማግኘቱ 'የተማሪዎች የምገባ ኤጀንሲ' እንደሚቋቋም ኢ/ር ታከለ ተናግረዋል፡፡

የኤጀንሲው መቋቋም በተያዘው የበጀት ዓመት የከተማ አስተዳደሩ በስፋት የሰራውን የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራምን ጨምሮ የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት ቀጣይነት እንዲኖረው እና ተቋማዊ እንዲሆን እንደሚረዳ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር እርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የከተማው ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የፋሲል ግንብ በኃላፊዎች ጫና እንዳይጎበኝ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ!

በጎንደር ከተማ ፋሲል ግንብ (የነገሥታት ግቢ) እየተባለ የሚታወቀው ታሪካዊ ቅርስ በኃላፊዎች ክልከላ በአገር ውስጥና በውጪ አገር ጎብኚዎች እንዳይታይና መጉላላት እንዲፈጠር እየተደረገ መሆኑን የአስጎብኚዎች ማህበር አስታወቀ።የጎንደር አስጎብኝዎች ማህበር አባል ወጣት ኑር ሁሴን አጋዥ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፀው፤ በቱሪስት መስህብነቱ በቀዳሚነት የሚታወቀው የፋሲል ግንብ <<በተለያዩ ምክንያቶች>> በቅርብ አመራሮች ትዕዛዝ እንዳይጎበኝ እየተደረገ ነው። በርካታ ጎብኚዎች ገንዘብ ከፍለውና ጊዜያቸውን አባክነው በቦታው ቢገኙም ሰዓት ደርሷል በሚል እንዲወጡ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት እንዲመላለሱና ላልተገባ ወጪም እንዲዳረጉ ሆነዋል። ይህም ሁኔታ ቱሪስቶች እንዲቆዩና ተመልሰው እንዲመጡ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የፊታችን የካቲት ወር የአፍሪካ ሀገራት ምድር ጦር ጉባኤን ታስተናግዳለች!

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ የካቲት ወር 2020 ዓመተ ምህረት የአፍሪካ ሀገራት ምድር ጦር ጉባኤን ታስተናግዳለች። ጉባኤውንም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ጋር በመተባር እንደሚያዘጋጀውም ነው የተመለከተው።በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ላፍቴ ፍሎራ በጉባኤው ዝግጅት ዙሪያ ለመምከር ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸውም ወቅት ለጉባኤው እየተደረገ ባለው ዝግጅት ዙሪያ ከኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በጉብኝታቸውም ወቅት የአሜሪካ ጦር በአህጉሪቱ ዘላቂ ፀጥታ ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት ጥረቶችን ማገዝ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።ለአራት ቀናት በሚካሄደው ጉበኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወታደራዊ አዛዦችን የሚያሰባስብ ነው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የ40/60 የጋራ ቤቶችን ሊዘርፉ በነበሩ ግለሰቦች ጥቃት የደረሰባቸው የጥበቃ ሠራተኛ ሕይወታቸው አለፈ!


በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የከተማ አስተዳደሩ የቁጠባ ቤቶች ግንባታ ልማት ኢንተርፕራይዝ እያስገነባቸው ያሉ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሊዘርፉ በነበሩ ግለሰቦች፣ ጥቃት የደረሰባቸው የጥበቃ ሠራተኛ ሕይወታቸው አለፈ፡፡ ፖሊስ ሁለት ተጠርጣሪዎችን ይዞ በምርመራ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ረቡዕ ታኅሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ሌሊት ቁጥራቸው 30 የሚሆኑ ግለሰቦች ተሽከርካሪ ይዘው ረድኤት ዳግም ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ከኢንትርፕራይዙ ኮንትራት ወስዶ እየገነባው ባለው 160 አባወራዎችን በሚይዘውና ባለ 15 ፎቅ በሆነው ሁለት ብሎክ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመዝረፍ መምጣታቸውን፣ የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳግማዊ ፋሲል ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በውድቅት ሌሊት ለዝርፊያ የመጡት ግለሰቦች በዕለቱ በጥበቃ ላይ በነበሩት አቶ ሹመት ተገኝ የተባሉ የማኅበሩ ሠራተኛ ላይ ከባድ የድብደባ ጥቃት አድርሰውባቸው ለሕክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል የገቡ ቢሆንም፣ ሐሙስ ታኅሳስ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ሌሊት ሕይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል፡፡

የኤልኤች ሴኩዩሪቲ ኤጀንሲ የጥበቃ አባል የነበሩት ሟች የጥበቃ ሠራተኛ፣ በድንጋይና በብረት መደብደባቸውንም አክለዋል፡፡ ለዝርፊያ መጥተው የነበሩ ግለሰቦችን ሌሎች በአጎራባች የነበሩ የጥበቃ ሠራተኞች ጭምር ተረባርበው ያሰቡትን ዘረፋ ሳይፈጽሙ እንዳባረሯቸው፣ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን በተወሰኑት የጥበቃ ሠራተኞች ላይ ጉዳት በመድረሱ፣ ሆስፒታል መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩንም የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ እያጣራው መሆኑን አክለዋል፡፡

በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚገኘው የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ ሳጅን እመቤት ታምራት ስለወንጀል ድርጊቱ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፣ ወንጀሉ መፈጸሙን አረጋግጠዋል፡፡ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው የጥበቃ ሠራተኛ አቶ ሹመት ተገኝም ሕይወት ታኅሳስ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ሌሊት ስምንት ሰዓት አልፏል ብለዋል፡፡ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ መሆናቸውንና ንብረት እንዳልተዘረፈ ገልጸዋል፡፡ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው የጥበቃ ሠራተኞች የነበሩ ቢሆንም፣ ጉዳታቸው መጠነኛ በመሆኑ ሕክምና ተደርጎላቸው ከሆስፒታል መውጣታቸውን ሳጅን እመቤት አስረድተዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa