YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
⬆️⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጅቡቲ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ዝግጅት ላይ በድንገት በመገኘት ንግግር አሰሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 ኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን አስመልክቶ ቅዳሜ ዕለት (ጥቅምት 08፣ 2012ዓ.ም) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የተሰናዳ የደስታ መግለጫ ፕሮግራም ላይ በድንገት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበዓሉ ታዳሚ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ንግግር አሰምተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ‹‹ይሄ ግጥምጥሞሽ ነው… ዳያስፖራው ዝግጅት አለው ስባል ሰላምታ ለማቅረብ ነው የመጣሁት›› ብለዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ አክለውም ‹‹በጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚለዩበት አንድ መለያ በሰላም መኖር፣ የአገሪቱን ህግ ማክበር፣ ስራ መውደድ፣ እርስ በእርስ መግባባት፣ የተቸገረን መርዳት ሲሆን ሁሌ የምትመሰገኑበትን ይሄንን መልካም ስማችሁን እንድታቆዩ አደራ እላችኋለሁ›› ብለዋል፡፡

ጅቡቲ ሁለተኛ ቤታችን ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ጅቡቲያውያኑ እኛን ይወዳሉ፤ እኛም ደግሞ አብዝተን እነሱን እንወዳቸዋለን ብለዋል፡፡ ዶ/ር አብይ መደመር በጅቡቲ እና በኢትዮጵያ በግልጽ መታዩት ጠቅሰው ይሄንን በሁለቱ አገራት መካከል ያለ ጥብቅ ወዳጅነት የምታጠናክሩ ድልድዮች ጀግና ኢትዮጵያውያን ስለሆናችሁ በታማኝነት፣ በጨዋነትና በፍቅር እዚህ ካለው ህዝብ ጋር በመኖር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር እያንዳንዱ ዜጋ እንደ አምባሳደር እንዲሰራ አደራ ብለዋል፡፡ስለ ኖቤል ሽልማቱ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማቱ በአንድ ሰው ስም መነገር ስላለበት እንጂ ሽልማቱ የሁላችሁም ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በኢኮኖሚ ማሻሻያ ሰፋፊ ስራዎች መጀመሩን፣ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ታላላቅ ኢኮኖሚ አንዷ እንድትሆን እየሰራ መሆኑን አክለው ገልጸው- የኢትዮጵያ ዕድገትና ብልጽግና የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳን፣ የኤርትራ ብልጽግና መሆኑን አክለው ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም በውስጣችንም በአጎራባች አገራት ሰላም እንዲኖር እንሰራለን ብለዋል፡፡በሚቀጥለው ምርጫ ከተመረጥን እንሰራለን ካልተመረጥን አቅፈን በማስረከብ አርዓያ የሆነ ስራ እንሰራለን ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ተሸንፎ ስልጣንን በስርዓት ማስረከብ ከዚህ ኖቤል የሚበልጥ እንጂ የሚተናነስ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡በመጨረሻም ስደት እንዲያበቃ ለልጆቻችን የምትበጅ ኢትዮጵያን ሰርተን ማቆየት አለብን በማለት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሐመድ በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንገተኛ መገኘት የተሰማቸውን ደስታና ክብር ገልጸው በጅቡቲ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አምባሳደሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለዚህ ታላቅ ዓለም-አቀፋዊ ሽልማት በመብቃታቸው በጅቡቲ የምንኖር እኛ ኢትዮጵያውያን የተሰማንን ደስታ በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ሽልማቱ መላው ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ከመሆኑም ባሻገር አገራችን በዓለም-አቀፍ መድረኮች ላይ እየተጫወተች ያለውን ሚና የሚያጎላና እውቅናንም የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡በዝግጀቱ የተገኙት ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ደስታና ክብር ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

( በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ )
@YeneTube @FikerAssefa
ከ80 በመቶ በላይ የግል ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸው ተገለፀ።

ከመንግሥት ፖሊሲ ጋር ተናበው ባለመስራታቸው ሰማንያ ነጥብ ሰባት በመቶ የግል ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና፤ ጥራት ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ባለስልጣኑ ትናንት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ እንደገለፁት፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ብዙ ሥራ ቢሠራም አሁንም በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ የሆነ ችግር ይስተዋላል፡፡ ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም በተደረገው የኢንስፔክሽን ሥራ በርካታ የግልና የመንግሥት ተቋሞች ከመንግሥት በወረደ አቅጣጫ ባለመስራታቸው ከደረጃ በታች ናቸው፡፡

ምንጭ:ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ 5ተኛ ዙር የ"ማስ" ስፖርት በመስቀል አደባባይ

Photo: Eng. Takele Uma Banti
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeLetterAlert

የገቢዎች ሚኒስቴር እንደማንኛዉም ባለበጀት መስሪያ ቤት በጀት ተመድቦለት በበጀት የሚንቀሳቀስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ነዉ፡፡

ስለዚህ የበጀት ፍሰቱ ቁጥጥር የሚደረግበትና በስርዓት የሚመራ ነዉ፡፡ ከአሰራርና መመሪያ ዉጪ ከተመደበለት በጀት ዉጪ እንደፈለገዉ ለሚዲያም ሆነ ሌሎች አካላት ድጋፍ ማድረግ አይችልም፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለግል ሚዲያ(ኦኤም ኤን)ድጋፍ አድርጓል ተብሎ የሚናፈሰዉ ወሬ አሉባልታና ሆን ተብሎ ለማደናገሪያነት የተሰራጨ ስለሆነ የፌስ ቡካችን ተከታታዮች በጠየቃችሁን መሰት ወሬዉ ዉሸት መሆኑን እንድታዉቁ እናስታዉቃለን፡፡

በተለይ በዘንድሮዉ ሩብ አመት ያስመዘገብነዉ ዉጤት ሰራተኛና አመራሩን ለተሻለ ዉጤት የሚያነሳሳ እንጂ ለአሉባልታ ቦታ ሰቶ ወደ ኋላ የሚመልስ ስላልሆነ ስኬታማ እንቅስቃሴችንን ለማደናቀፍ የምትጥሩ አካላት ከዚሁ ድርጊታችሁ እንድትታቀቡ እናሳስባለን፡፡ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ወሬ ተሰራጭቶ ዉሸት መሆኑን ምላሽ የሰጠንበት ሲሆን አሁንም እየተሰራ ያለዉን ስራ ለማጠልሸት ሆን ተብሎ የተሰራጨ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

-የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ክፍለ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እያደረጉ ነው፡፡በምክክሩም የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግባቸውም ይጠበቃል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሄደው የቆየውን 5ኛ ዘመን 17ኛው መደበኛ ጉባኤ የ2012 በጀት አመት አመታዊ እቅዶችን፣ የተለያዩ አዋጆችን እና አዳዲስ ሹመቶችን በማፅደቅ አጠናቋል፡፡
በበጀት አመቱ ክልሉ በድህነት ቅነሳ፣ የክልሉ ሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥ እንዲሁም የሴቶች እና ወጣቶችን የልማት ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ላይ በማተኮር በስፋት እንደሚሰራ የክልሉ ም/ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል አስታውቀዋል፡፡የ2011 በጀት አመት ግምገማን ተከትሎ በአመራሩ ለውጥ እንደሚደረግ እና ጥፋት የተገኘበት አመራርም በህግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚሆን ምክትል ርእስ መስተዳድሩ ዶ/ር ደብረፂዮን አስምረውበታል፡፡በህብረተሰቡ ለሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስም ያልተማከለ የመንግስት አሰራር ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።በከተማ እና በገጠር የሚታየውን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት በበጀት አመቱ 258 ሺህ ለሚሆኑ ወገኖች የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

ከስድስት ቢልዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት እንዲኖር ማድረግም አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ዶ/ር ደብረፂዮን አክለው አስረድተዋል። በቅርቡ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ የሆነው የትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋም ድርጅት /ኢፈርት/ በበጀት አመቱ ለሚሰሩ የልማት ተግባራት የሚውል ከ864 ሚልዮን ብር በላይ መመደቡን በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡ምክር ቤቱ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት፣ የዳኝነት የአገልግሎት ክፍያ፣ የዳኞች ጉባኤ ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን ተሻሽለው የወጡ ረቂቅ አዋጆች እና ሌሎች አዋጆችን ጨምሮ 4 የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል፡፡የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ የነበሩ ወ/ሮ የምስራች ብርሃን ለትምህርት በመላካቸው በምትካቸው ወ/ሮ ዘይነብ አብዱልለጢፍን በመሾም ጉባኤውን አጠናቋል፡፡

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን ለሚያገናኘው የአርጆ‐ጉደቱ‐ጅርማ‐ሶጌ መንገድ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በዲጋ ወረዳ የአርጆ ጉደቱ ጅርማ ሶጌ 46 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።የመሰረት ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ነው በጋራ የተቀመጠው መንገዱ 392 ሚሊየን ብር የተመደበለት ሲሆን፥ ወጪውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንደሚሸፍነው ተገልጿል። መንገዱ ሲጠናቀቅ የኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች ይበልጥ ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።መንገዱ በአስፋልት ደረጃ እንደሚገነባም ተገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ልዪ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ከተውጣጡ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስለ አካባቢው ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ውይይት በመደረግ ላይ ነው ፡፡

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት አካባቢው በልማት በተለይም ደግሞ በመስኖና በአካባቢ ልማት ጥበቃ የሚታወቅ እንጂ በጸጥታ መደፍረስ የማይታወቅ አካባቢ መሆኑንና የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት በወንድማማችነትና በቤተሰብነት በጋራ አብሮ በመኖር ልማትን የሚያለማ እንጂ እርስ በራስ የሚጠፋፋ እንዳልሆነ ገልጸው የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች አካባቢው ሰላም እንዲሆንና ለዘመናት የቆየውን ወንድማማችነት እንዲቀጥል ኃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንደገጹት ለዘመናት ተከባብሮና ተቻችሎ የቆየውን ማህበረሰብ ለማለያየትና የፖለቲካ አጀንዳቸውን ለመዘርጋት በሚጥሩ ኃይሎች ተታሎ ለመገዳደል በመድረሱ ማዘናቸውን ገልጸው ይህም ድርጊት የሁለቱን ህዝቦች የማይወክል በመሆኑ ችግሩ እንዲከሰት ያደረጉና የተሳተፉ አካላትን ለህግ አሳልፎ ለመስጠትና የነበረውን ሰላምና በአንድነት ሰርቶ የማደግ ባህል እንዲመለስ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ገልጸው መንግስትም ለጉዳዪ ልዪ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ: ሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር
@YeneTube @FikerAssefa
ግብጽ በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መውሰድ ስላለባት እርምጃ ለማማከር የተቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያውን ስብሰባ እንደሚያደረግ ይጠበቃል።

ግብጽ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ይጋፋል በሚል ነበር ከአንድ ሳምንት በፊት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ብሄራዊ አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሟ የተሰማው።እንደ ግብጹ አልአህራም ዘገባ ከሆነ ይህ አማካሪ ምክር ቤት ከግብጽ ብሄራዊ ደህንነት፣ከህዝብ ተወካዮች፣ከግብርና ሚኒስቴር ፣ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሌሎች ተቋማት የተውጣጣ ቡድን ተቋቁሟል።

የዚህ ቡድን ዋና አላማ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ የሚጎዳ በመሆኑ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ የግብጽን ጥቅም ለማስበር መውሰድ ስለሚኖርባቸው እርምጃዎች ማማከር መሆኑ ተገልጿል።ይህ ቡድን በተቋቋመ በሳምንቱ ማለትም ዛሬ አመሻሽ እንደሚሰበሰብ ዘገባው አመልክቷል።

ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፋ አዲስ አቅድ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሰት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የግብጽን እቅድ እንደማይቀበል ማስታወቁ ይታወሳል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ከአንድ ሳምንት በኋላ በሩሲያ ሱቺ ከተማ በሚካሄደው በአፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ ላይ ተገናኝተው በህዳሴው ግድብ ቀጣይ ድርድር ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ኦፍላ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ሕይወታቸው ካለፉት 6 ሰዎች በተጨማሪ 22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል። አደጋው የደረሰው 28 ሰዎችን አሳፍሮ ከኮረም ከተማ ወደ ፋላ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 06938 ትግ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ትላንት ቀትር ላይ ፍቅረ ወልዳ በተባለ ስፈራ በመገልበጡ መሆኑን የዞኑ ትራፊክ ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር አብርሃ ወረደ ተናግረዋል፡፡

በተሳፋሪዎቹ እና ረዳቱ መካከል ከክፍያ ጋር በተያያዘ የተነሳ ጠብ ለተሽካርካሪው መገልበጥ መንስኤ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ጠብ ሲፈጠር አሽከርካሪው አውቶቡሱን አቁሞ ሲወርድ ታኮ ባለማድረጉ ተሸካርካሪው 150 ሜትር ጥልቀት ካለው ገደል ተንሸራቶ መግባቱን ተናግረዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በመቐሌ፣ማይጨውና ኮረም ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል ።ፖሊስ አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑም አስረድተዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
የሰላም ሚኒስቴር ለክቡር ዶክተር አብይ አህመድ መቶኛው የሰላም የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ " ሰላም መቶ በመቶ ያሸልማል" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የእውቅና ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ በሚሊኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬዉ እለት በአ/ቃ/ክ/ከ/በወረዳ 9 አስተዳደር አካባቢ በወጣቶች መካክል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት በፀጥታ አስከባሪዎች እና በአካባቢው ሀብረተሠብ ትብብር ወደነበረበት ሠላም ተመልሷል፡፡

ምንጭ:በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
የሰላም ሎሬት ከሆኑ ወዲህ ዐቢይ የተሸለሙትን 2ኛ የወርቅ ሐብል ለመከላከያ ምኒስትሩ ለማ መገርሳ አበርክተዋል፣ የኦዴፓን ሐብል ያበረከቱላቸው ለማ ነበሩ። ለማን "በብዙ መከራ በብዙ ደህንነት አብረውኝ ነበሩ" ያሏቸው "መሪ የነበረው" ብለዋቸዋል።

-Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
መረጃ የማይሰጡ ተቋማትና ኃላፊዎች በህግ ይጠየቃሉ ።

በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መረጃ ሲጠየቁ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ የተቋማት ኃላፊዎች በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባ ተጠቆመ። የመረጃ አሰጣጥ ስርዓቱን ለማሳለጥ የሚዲያ ህጉ ላይ ማሻሻያ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።
የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ እንደተናገሩት በየተቋማቱ ያለው መረጃ የህዝብ ሀብት እንጂ የግለሰብ ንብረት አይደለም።በመሆኑም መረጃ ለህዝብ ጥቅም ተብሎ ሲፈለግ ወይም ህዝቡ ማወቅ እፈልጋለሁ ይሰጠኝ ሲል መረጃውን የያዙ ኃላፊዎች የመስጠት ግዴታ አለባቸው።አቶ ዝናቡ ቱኑ እንደሚሉት የመንግሥት ተቋማት ቀዳሚ ተልእኮው ህዝብን ማገልገል፣ የህዝብን ደህንነት መጠበቅ እና የህዝብን ጥያቄ መመለስ በመሆኑ ህዝብ ለሚያቀርበው ጥያቄ ሁሉ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

ምንጭ: ኢ.ፕ.ድ
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ለትግራይ ሚድያ ሃውስ:

"ኢህአዴግ የግድ ለውጥ ማድረግ ነበረበት። ቀድመን የተነጋገርንበት ነበር።"

"ለዉጡ ወደኋላ ተመልሷል ብቻ ሳይሆን መንገዱን ስቶ ለሀገሪቱም አደጋ ጋርጧል።"

"ትግራዋይነት እንርሳ። አማራነት እንርሳ። ኦሮሞነት እንርሳ። ኢትዮጵያውነት ብቻ ነው የምያዋጣን ብለው የምያምኑ የዋሃን ናቸው።"

"ህወሓት አይዋሀድም ይሄ ምንም ይቅርታ አያስፈልገዉም፡፡ ሊቀመንበሩ እንደሚሉት የግድ አደርጋለሁ ካሉ እና ከተሳካላቸዉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸዉ።"

"ትግራይን ለማስተዳደር የሚፈልጉ እና ለመላክ የተዘጋጁ አዲስ አበባ የሚኖሩ ሰዎች አሉ።"

"ኢትዮጵያ ለዉጭ ጨረታ የቀረበች ሀገር መስላለች።"

"የትግራይ ህዝብ ጥቅም በእንደዚህ አይነት ሰርከስ መመለስ አይችልም።"

"ኢትዮጵያን ማዳን ካለብን እዉነት እናዉራ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የምር ለዉጥ ይፈልጋል፡ የመበለቶች ተረት በማዉራት የኢትዮጵያ ችግር ሊፈታ አይችልም።"

"ሌብነት ኢንስቲቱሽናላይዝ እስከሚመስል ድረስ ከፍተኛ ምዝበራ የሚካሄድበት፥ በደም የተጨማለቁ ሰዎች እንደፈለጉ የሚፈነጩበት ሀገር ነዉ የሆነዉ።"

ምንጭ: ድምፂ ወያኔ
@YeneTube @FikerAssefa
የኩላሊት ታማሚዋ ኢትዮጵያዊት በደቡብ አፍሪካ ህክምና እንዳታገኝ ተከለከለች!

ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ ዓለም ኤርሴሎ በደቡብ አፍሪካ በደረሰባት የኩላሊት ህመም በጆሀንስበርግ ሆስፒታል ኩላሊት እጥበት ህክምና ስታገኝ የነበረ ሲሆን የደቡብ አፍሪካዊ ዜግነት ሰለሌላት ሆስፒታሉ ህክምናውን እንዳታገኝ አድርጓታል።ጉዳዩን ለጆሃንስበርግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብታቀርብም ፍርድ ቤቱ ከሔለን ጆንሰን ሆስፒታል ጎን በመቆም ደቡብ አፍሪካ ዜግነት ስለሌላት እና የተረጋገጠ ቋሚ የዜግነት ማስረጃ ማቅረብ አልቻለችም በማለት ህክምናውን እንዳታገኝ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።ታማሚዋ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ህመሙ በደረሰባት ወቀት በደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግሥት ላይ የሚገኘውን ሁሉም ሰው የራሱ ህልውና፣ የእኩልነት እና ህክምና የማግኘት መብት እንዳለው የሚጠቅስ አንቀጽ አንስታ ብትከራከርም ተቀባይነት ሳታገኝ ቀርታለች።

አሁን የታማሚዋ ኩላሊት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን ይህም የሆነው በወቅቱ ተገቢውን ወሳኔ ባለማግኘቷ እንደሆነ ትገልፃለች። ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ጉዳዩን ያዩት ዳኛ በወቅቱ ምን ተከስቶ እንደንደነበር ግልፅ አይደለም ብለዋል።አያይዘውም አመልካቿ የድንገተኛ ጊዜ ህክምናን እንዳልተከለከለች እና የጤናዋ ሁኔታ በተረጋጋበት ወቅት ወደ ሀገሯ ተመልሳ ቋሚ ህክምና ማግኘት እንደምትችል ገልፀዋል።ሔለን ጆንሰን ሆስፒታል ያቀረበው ማስረጃ፣ በወቅቱ ድንገተኛ ለኩላሊት እጥበት የሚያገለገሉ መሣሪያዎች እጥረት በማጋጠሙ አዲስ ታማሚዎችን መቀበል አለመቻሉን በፍርድ መዝገቡ ላይ ተገልጿል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ማበረታቻ ይሆን ዘንድ ከሃምሌ ወር ጀምሮ የአንድ እርከን ደሞዝ ጭማሪ አደረገ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመስሪያ ቤቱ አስተዳደር ደንብ 155 መሰረት ነዉ ትናንት ባደረገዉ ምክክር የደሞዝ እርከን ጭማሪዉን ያደረገዉ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በልዩ የደሞዝ እስኬል የሚተዳደር በመሆኑ ምክንያት መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች በቅርቡ ያደረገዉ የደሞዝ ማስተካከያ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽንን ያካላካተተ ነበር፡፡

የደሞዝ ጭማሪዉ ለመስሪያ ቤቱ ከተያዘዉ በጀት የሚሸፈን ይሆናልም ተብሏል፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤም መላዉ ሰራተኛ በቅንነትና በትጋት ይበልጥ በማገልገል የ2012 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን እቅድን ለማሳካት መስራት አለበት የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2011 የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ በፓርላማ አድናቆት ማትረፉ የሚታወስ ነዉ::

ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በ2011 በአማራ ክልል ትምህርታቸውን አቋጠው የነበሩ 47 ሺሕ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል አለ፤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፡፡

በሳለፍነው የ2011 የትምህርት ዘመን በቅማት የማንነት ጥያቄ ምክንያት በክልሉ በነበረ አለመረጋጋት 47 ሺህ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መቋረጠቸው የሚታወስ ነው፡፡በተያዘው አመት ተማሪዎቹ ወደ ትምርታው እንዲመለሱ መደረጋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ለአሃዱ ተናግረዋል፡፡በቅርቡም በጎንደር ዞኖች በተከሰተው ግጭት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተስተጓጉለወ እንደነበር ያስታወሰው ቢሮው አሁን ላይ መጠነኛ ሰላም በመኖሩ ትምህረት ቤቶች ስራቸውን እጀመሩ ነው ብሏል፡፡

Via Ahadu Radio
@YeneTube @FikerAssefa