ስፖርት !! ትግራይ ስታዲየም የተደረገው 2020 ቻን ማጣሪያ ጨዋታ ውጤት ዋሊያዎቹ ተሸንፈዋል።
⏰ ተጠናቀቀ
🇪🇹ኢትዮጲያ0⃣➖1⃣ሩዋንዳ 🇷🇼
@YeneTube @Fikerassefa
⏰ ተጠናቀቀ
🇪🇹ኢትዮጲያ0⃣➖1⃣ሩዋንዳ 🇷🇼
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሖሳዕና በነበራቸው ቆይታ የኮሎኔል በዛብሕ ጴጥሮስ ጉዳይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ስምምነት አንድ አካል እንደሆነ መናገራቸውን በውይይቱ የተሳተፉት የሐዲያ ዞን አስተዳደር የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን አባይነሕ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
ዛሬ ማምሻውን በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የ12 ክፍል ተማሪዎች የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የከተማ አስተዳዳሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የሃይመኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የተጋበዙ የሃይመኖት አባቶች ተማሪዎቹ በሚገቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እና አካባቢዎች በመልካም አራያነት የሚጠቀሱ ተግባራትን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል፡፡ራሳቸውን በመልካም ስነ ምግባር በማነጽ የእኩይ አላማ ማስፈፀሚያ መሆን እንደማይገባቸውም አስረድተዋል፡፡መርሃ ግበሩ ተማሪዎቹ በ2012 የከፍተኛ ትምህርት ቆይታቸው ሰላማዊ እና አንድነቱ የተጠበቀ የመማር ማስተማር ለማስፈን የሚያስችል እንደሆም ነው የተገለጸው፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa

ሰንቀሌ ወታደራዊ ካምፕ የታሰሩት ወጣቶች #ተፈቱ !!!
በሰንቀሌ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ በጅምላ ታስረው የነበሩት ወጣቶች ከእስር እየተፈቱ ነው። ከምዕራብ # ወለጋ ፣ ምዕራብ # ጉጂ እና ቄለም ወለጋ ከመጡት በስተቀር ከሌሎች የኦሮሚያ አከባቢዎች የታሰሩት ወጣቶች መፈታታቸው ታውቋል። ከላይ ከተጠቀሱት ሦስት አከባቢዎች የመጡት ወጣቶችንም ለመፍታት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የእስረኛ ቤተሰቦች ወጣቶቹን ለመውሰድ የትራንስፖርት መኪና በማሰባሰብ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
በዚሁ መሠረት ከምዕራብ ወለጋ ለታሰሩት ወጣቶች የሚያስፈልገው የአውቶቢስ መኪና ብዛት 12 ሲሆን ለምዕራብ ጉጂ 14 እና ለቄለም ወለጋ ደግሞ 12 አውቶብስ መኪኖች እንደሚያስፈልጉ የእስረኛ ቤተሰቦች ገልፀዋል። ከሶስቱ አከባቢዎች ለታሰሩ ወጣቶች ብቻ 38 አውቶብስ መኪና ማስፈለጉ የእስረኞቹ ብዛት ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበር መገመት ይቻላል።
በሌላ አነጋገር ከሶስቱ አከባቢዎች ብቻ ወደ 2000 ወጣቶች ታስረው እንደነበር መገመት ይቻላል።
ምንጭ:- ስዩም ተሾመ

YeneTube
በድሬ ዳዋ ከተማ ቀፊራ እና አዲስ ከተማ በሚባሉ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ። አንድ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ "አምቡላንሶች ሰዎችን ወደ ሆሰፒታል ሲያመላልሱ ነበር። ጉዳት ደርሶባቸው ደም የሚፈሳቸው ሰዎችንም ተመልክቻለሁ'' ብለዋል። የግጭቱ መነሻ ደግሞ "አዲስ ከተማ ጋራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አዲስ በተገነባው የተክለኃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ላይ ሰዎች ድንጋይ በመወርወራቸው…
በድሬዳዋው ግጭት ሰዎች መገደላቸውን እንዳረጋገጡ የዐይን እማኞች ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ግጭቱ የብሔር መልክ አለው። ግጭቱን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት ቢኖርም ለጥቃት የመደራጀት ጉትጎታ በመታየቱ ሥጋት አይሏል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Average speed of mobile internet. (Mbps)
1. Iceland: 72.5
2. Norway: 67.8
3. Qatar: 60.3
4. Canada: 59.6
6. Australia: 55.7
28. France: 38.7
33. Turkey: 34.7
41. US: 31.2
49. China: 28.9
52. UK: 28.3
54. Saudi: 27.1
70. Brazil: 20.5
77. Russia: 18.4
111. India: 9.9
(SpeedTest)
@YeneTube @FikerAssefa
1. Iceland: 72.5
2. Norway: 67.8
3. Qatar: 60.3
4. Canada: 59.6
6. Australia: 55.7
28. France: 38.7
33. Turkey: 34.7
41. US: 31.2
49. China: 28.9
52. UK: 28.3
54. Saudi: 27.1
70. Brazil: 20.5
77. Russia: 18.4
111. India: 9.9
(SpeedTest)
@YeneTube @FikerAssefa
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ መከበሩ ኢሬቻን ወደ ቱሪዝም ገበያ የማውጣት ስራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ገለጸ።
ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅም በጸጥታ ሃይሉ በቂ ዝግጅት መደረጉንና፤ ለስኬታማነቱም የአባ ገዳ ፎሌ ወጣቶች ብሎም የህብረተሰቡ ድጋፍ ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ ለኢ.ፕ.ድ እንደገለጹት፤ የኢሬቻ በዓል ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይገድበው ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት የሚያከብረው በዓል ነው። ከሁለት ዓመት ወዲህ ደግሞ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እየተሳተፉበት ያለ በዓል ነው። ይህ እየሰፋ ሲሄድ ደግሞ ኢሬቻ የአገር ብሎም የዓለም እሴትነቱ እየጎላ ይሄዳል።በመሆኑም በዓሉ ከቱሪዝም ሀብትነቱ ባለፈ ለህዝቦች አንድነትና ለአገር ግንባታ ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል። ከዚህ አኳያ በዓሉ በአዲስ አበባ መከበሩ ኢሬቻን የጋራ እሴት ለማድረግ፣ ለአገር ግንባታና ለአብሮነት ማጠናከርያ ለማዋል፤ ብሎም እሴቶቹን ለማስተዋወቅ ወደ ገበያ የማውጣት ስራ ነው።
ምንጭ:ኢፕድ

ኢትዮጵያ ባለፉት ኹለት ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ንግድ 183 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሐምሌና ነሐሴ 2011 ከ52 ሺሕ 300 ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ አገራት የተላከ ሲሆን፣ ከባለፈው 2010 ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ከ6 ሺሕ 585 ቶን በላይ ጭማሬ ማሳየቱንም ለማወቅ ተችሏል። ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጭማሬ አሳይቷል።ቡና ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ቀዳሚ ሲሆን፣ በባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ774 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለአገሪቷ አስገኝቷል።
ምንጭ: አዲስ ማለዳ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በእጅ #በሞባይል የታገዘ የተለያዩ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ነጻነት ለሜሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ድርጅቱ አገልግሎቶቹን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በአነስተኛና በጥቃቅን ሙያዎች ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሞባይል በመታገዝ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ሊሰጥ ነው። እንደ መደበኛው የኢንሹራንስ አገልግሎት ቅርጫፍ እየከፈቱ አረቦን በአካል እየመጡ እንዲከፍሉ ማድረግ አዋጪና ቀልጣፋ ባለመሆኑ አገልግሎቶቹ በሞባይል በመታገዝ የሚሰጡ ይሆናል።
በሞባይል የታገዘ የኢንሹራንስ አገልግሎት ህብረተሰቡ ባለበት ቦታና አካባቢ ሆኖ አገልግሎቱን እንዲያገኝ የሚያስችለው መሆኑን አመልክተው አገልግሎቱን ለመጀመር የድርጅቱን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና ሶፍት ዌር የማሻሻል ስራ እንደሚሰራና ለዚህም 450 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን ተናግረዋል።

ነጃሺ ባንክ 678 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ሸጠ
አዲስ በመመስረት ላይ የሚገኘው ነጃሺ ባንክ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ላይ 678 ሚሊዮን ብር መሸጡን አስታወቀ። ባንኩ ወደ ስራ ለመግባት በሚያስችለው ደረጃ ላይ 378 ሚሊዮን ብር የሸጠ ሲሆን በውጭ አገራት በሚገኙ የዲያስፖራው ማኅበረሰብ ደግሞ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ሽያጭ ማካሔዱን ይፋ አድርጓል።
ባንኩ በአጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ መድረክ ላይ ባካሔደው ሽያጭ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን ግማሽ ቢሊየን ብር አሟልቷል። 678ሚሊየን ብር መስራቾች አክሲዮን በመግዛት የባንኩ ባለቤቶች ሆነዋል።
አንዲሁም አማራ ባንክ አክሲዮን 260 ሚልዮን ብር መሸጡን ከትላንት በስቲያ አስታውቋል።
ምንጭ:- አዲስ ማለዳ

"ጎንደር ርዕሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሚደረገው ፀሎት እስከ መስከረም 21 የሚቀጥል ሲሆን፤ምህላ ለግል ህይወታችን፣ለከተማዋ፣ ለክልላችን፣ለሀገራችን ብሎም ለዓለማችን በረከትን እና ሰላምን ይሰጣልና ኑ አብራችሁን ለሀገራችን እንፀልይ ።"
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
550 ኮንቴነር መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶች ወደ አገር ገብተዋል፡- የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ባለፋት 2 ወራት ከ550 ኮንቴነር በላይ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ማንሣቱን አስታወቀ፡፡
ከ25 ዓይነት በላይ መድኃኒቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማንሳት መቻሉን የኤጀንሲው የመድኃኒት ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ አጋር ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡
መድኃኒቶቹ ለኤች.አይ.ቪ፣ ለሆድ ሕመም፣ ለኢንፌክሽን፣ ለስነተዋልዶ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችና ሪኤጀንቶች እንደሆኑ ወ/ሮ አጋር አብራርተዋል፡፡
መድሀኒቶቹን በቀጥታ በተለያዩ ቅርንጫፎችና በዋናው መ/ቤት የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን እንደገቡ አስረድተዋል፡፡
ወደ ቅርንጫፍ ቀጥታ መሄዱም ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ ለማህበረሠቡ በቶሎ መድኃኒቶችን ተደራሽ ለማድረግ ወሣኝ ሚና አለው ሲሉ ባለሙያዋ አክለዋል፡፡
እክሎች እንዳይከሠቱ በባንኩ፣ በሞጆ ደረቅ ወደብ፣ በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና በኤጀንሲው መካከል ውል ለመፈራረም በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ባለሙያዋ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት
@Yenetube @Fikerassefa

⬆️ሰሞኑን ወደ ደቡብ ኮሪያ ያቀኑት የወላይታ ዞን ተወካዮች ስኬታማ ጉዞ አድረገው ተመልሷል።
የተለያዩ አበይት ተግባራትን ለማከናወን የተንቀሳቀሰው ቡድን ለአንድ ሳምንት ያህል ቆይታ ያደረገ ሲሆን ቆይታቸውም ስኬታማ እንደነበረ ተገልጿል።
በወላይታ ዞን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የተቀጣጠለውን የኢንዱስትሪ አብዮት ይልቅ እንድጎለብት ለማድረግ በዞኑ መንግሥት የተጀመረው አበረታች ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በተለይም የውጭ ባለሀብት በአከባቢው የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ማድረግ ዋናው የትኩረት ማዕቀፍ በመሆኑ በኮሪያ ከሚገኙና በዞኑ በተጠናው የፖተንሺያል ጥናት መሰረት ውጤታማ ሊሆኑ ከምችሉ ባለሃብቶች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከጥር ወር ጀምሮ ወደ አካባቢያችን በመንቀሳቀስ ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጿል ።
በሌላ በኩል የወላይታ ሶዶ ከተማን በደቡብ ኮሪያ ከሚገኘው Hongcheon ከተማ ጋር የእህትማማችነት ግንኙነት እንድኖረው ለማድረግ በተደረገው ጥረት ከከተማው ካንቲባና የካቢኔ አባላት ጋር ውይይት ተደርጎ በቀጣይ ስምምነት ለመፈራረም መስማማታቸውን ገልፀዋል።
በሀገራችን ብሎም በዞናችን ወጣቶች የአስተሳሰብ ለውጥ ውስጥ በመግባት የልማት አቅም እንዲሆኑ ለማድረግ የወጣቶች ስብዕና ማዕከል ግንባታ በወላይታ ሶዶ እንዲገነባ በደቡብ ኮሪያ ከሚገኘው የIYF ተቋም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴ ላይ የመንግስት አካላት ሚና በተመለከት፣ የግብርና ልማት ሥራ ውጤታማነት በተለይም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ላይ የህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጥ በሚያስችል ሂደት የልምድ ልውውጥ ተደርጓል።
በመጨረሻም የጊፋታን በዓል በሀገር ዓቀፍና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የተጀመረውን ጥረት ለማበረታታት ከIYF ሠራተኞች ጋር በዓሉን አክብሯል።
Via:- ወላይታ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን

ኦዳ የተቀናጀ የትራንስፖርት አገልግሎት 50 አውቶብሶችን እና ሁለት የነዳጅ ማደያዎችን በትናንትናው እለት በይፋ ስራ አስጀመረ።
ኦዳ የተቀናጀ የትራንስፖርት አገልግሎት በ400 ሚሊየን ብር በመግዛት ከውጭ ሀገር ያስገባቸውን 50 አውቶብሶች በትናንትናው እለት ነው በይፋ አስመርቆ ስራ ያስጀመረው።በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
Via Fana

በወልቂጤ ከተማ በ5 መቶ 94 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ሆስፒታል ሊገነባ ነው።
እንደ ሀገር ለሚገነቡ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ምሳሌና ማሳያ ሊሆን የሚችል የግንባታ የዲዛይን ስራ የተዘጋጀበት የወልቂጤ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታል የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን ከማገዝ ባሻገር ህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ነው ያሉት የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ የሆስፒታሉን ግንባታ ለማስጀመር የተደረገውን ርብርብና የጋራ ጥረት አድንቀዋል፡፡
የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ግሩም ወልደሰንበት በበኩላቸው የሆስፒታሉ ግንባታ የተሻለ የጤና አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ህዝቡ በየጊዜው የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ መፍታት የተቻለበት መሆኑን አውስተው ሆስፒታሉም በተቀመጠለት የግዜ ገደብ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ከህዝቡ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ:የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ

አዴፓ ከነገ ጀምሮ በፖለቲካና በልማት ጉዳዮች ላይ ይመክራል።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በፖለቲካና በልማት ጉዳዮች የሚመክር ስብሰባ ከነገ ጀምሮ እንደሚያካሂድ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።በጽህፈት ቤቱ የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ እንደገለጹት በስብሰባው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ ከ2 ሺህ 500 በላይ አመራሮች ይሳተፋሉ።
ለ3 ቀናት በሚቆየው ስብሰባ ያለፈውን ዓመት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች የእቅድ አፈፃፀም ይገመገማል።ያገጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎችም ይታያሉ ብለዋል።የክልሉን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ፣ የወጣቶችን የስራ እድል ፈጠራ፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ስራዎች ዋነኞቹ የመወያያ አጀንዳዎች መሆናቸውም ተገልጿል።በ2012 የድርጅትና የልማት ስራዎችን እቅድና የማስፈፀሚያ ስልቶች ቀርበው አመራሩ በሚያደረገው ውይይት ዳብሮ የእቅዱ አካልም ይሆናል ተብሏል።
ምንጭ፡- ኢዜአ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በኅዳር የሚካሔደውን የሲዳማ ሕዝበ-ውሳኔ የሚመራ ፅ/ቤት እንዲቋቋም ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት እንዳለው ሕዝበ-ውሳኔውን የሚያስተባብረው ፅህፈት ቤት ተጠሪነት ለክልሉ ምክር ቤት ይሆናል።
Via:- Eshete Bekele
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- Eshete Bekele
@YeneTube @Fikerassefa