YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በእጅ #በሞባይል የታገዘ የተለያዩ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ነጻነት ለሜሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ድርጅቱ አገልግሎቶቹን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በአነስተኛና በጥቃቅን ሙያዎች ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሞባይል በመታገዝ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ሊሰጥ ነው። እንደ መደበኛው የኢንሹራንስ አገልግሎት ቅርጫፍ እየከፈቱ አረቦን በአካል እየመጡ እንዲከፍሉ ማድረግ አዋጪና ቀልጣፋ ባለመሆኑ አገልግሎቶቹ በሞባይል በመታገዝ የሚሰጡ ይሆናል።

በሞባይል የታገዘ የኢንሹራንስ አገልግሎት ህብረተሰቡ ባለበት ቦታና አካባቢ ሆኖ አገልግሎቱን እንዲያገኝ የሚያስችለው መሆኑን አመልክተው አገልግሎቱን ለመጀመር የድርጅቱን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና ሶፍት ዌር የማሻሻል ስራ እንደሚሰራና ለዚህም 450 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን ተናግረዋል።
@YeneTube @Fikerassefa