የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ መፅሀፍ በኦሮሚኛ እና በአማርኛ በቅርቡ በገበያ ላይ ይውላል። መደመር የሚለው መፅሀፍ 3መቶ ብር የሚሸጥ ሲሆን ገቢው በገጠር ላሉ ትምህርት ቤቶች ይውላል።
Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልኡካቸው በሆሳዕና ከተማ ህዝባዊ ውይይት ለማድረግ ሲደርሱ በአካባቢው ነዋሪ በሆሳዕና አቢዮ ስቴድየም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል::
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
#lRRECHA_PEACE_RACE_2019
የኢሬቻ ለሰላም ሩጫን በወንዶች የአለም ወጣቶች ሻምፒዮና በ10 ሺህ የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት በሪሁ ዓረጋዊ ከሱር ኮንስትራክሽን አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ሀይለማርያም ኪሮስ ከኢ/ት ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ደጀኔ ደበላ ከኦሮሚያ ውሀ ስራዎች ሶስተኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነዋል።
Via Ariyat Raya

የቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የ80 ቀን መታሰቢያና ሃውልት ምረቃ በመቐለ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስተያን ተፈፅሟል!
Via Petros Ashenafi Kebede
@YeneTube @Fikerassefa
Via Petros Ashenafi Kebede
@YeneTube @Fikerassefa
የመንግስት ሚድያዎች ሆይ!
ህዝብ ቅሬታ እያነሳባችሁ ስለሆነ በደንብ ስሙ፣ ሰምታችሁም ማስተካከያ አድርጉ።
ምስል: ከሶሻል ሚድያ - ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @Fikerassefa
ህዝብ ቅሬታ እያነሳባችሁ ስለሆነ በደንብ ስሙ፣ ሰምታችሁም ማስተካከያ አድርጉ።
ምስል: ከሶሻል ሚድያ - ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @Fikerassefa
የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ፡፡
የ2012 ዓ.ም የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡
የዘንድሮ የጊፋታ በዓል ከመስከረም 15 እስከ 18 ባሉት አራት ቀናት ከወረዳ ጀምሮ በዞኑ መቀመጫ ሶዶ ከተማ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፈውበት በደማቅ ሥነ-ሥርአት እንደሚከበር ነው የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፀጋው ስሞኦን የተናገሩት፡፡
የጊፋታ በዓልን ዓላማ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ለማስተዋወቅ ልኡካን በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ሁሉ በበዓሉ ላይ ለመታደም በጎ ምላሽ መስጠታቸውንም የመምያው ኃላፊ አንስተዋል፡፡በዓሉ የህዝብ ለህዝብ ትስስርና አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው ያሉት አቶ ፀጋው በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብም ክፍተኛ ጥረት እተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ዋናው በዓል መሰከረም 18/2012 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
Via SRTA

ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በየወሩ አሥራ ስምንት ሺ ብር የቤት ኪራይ አበል እንዲከፈላቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ።
በሌሎች ጥቅማጥቅሞች ላይ ማሻሻያ ያደረገ ሲሆን የማሻሻያ መመሪያው ከነሀሴ አንድ ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል። የከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ለመወሰን ህዳር አንድ ቀን 1997 ዓ.ም የወጣውን መመሪያ ለማሻሻል የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት መመሪያ መሰረት የቤት ኪራይ አበል የሚከፈላቸው ከፍተኛ ኃላፊዎች መንግሥት የመኖሪያ ቤት ማቅረብ ካልቻለ ኃላፊው ቤት እስኪሰጠው ድረስ በየወሩ 18 ሺ ብር የሚከፈለው ይሆናል።መንግሥት መኖሪያ ቤት ያልሰጣቸው ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች የቤት ኪራይ የሚከፈላቸው በየመስሪያ ቤቱ በጀት ተይዞለት መሆኑን የሚያብራራው መመሪያው ባልና ሚስት ሁለቱም ባለስልጣናት ከሆኑ ግን ጥቅሙ የሚሰጠው ለአንደኛው አካል ብቻ መሆኑን አመልክቷል።
ምንጭ:አዲስ ዘመን

የኢሬቻ ታላቁ እሩጫ ላይ ለሩጫው ተሳታፊዎች የተሰጠው የሽልማት ሜዳልያ ይህን ይመስላል።
ኢትዮ 360ዎቹ ሀብታሙ አያሌው እና ኤርሚያስ ለገሰ ያሰራጩት መረጃ Fake News መሆኑን ታውቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮ 360ዎቹ ሀብታሙ አያሌው እና ኤርሚያስ ለገሰ ያሰራጩት መረጃ Fake News መሆኑን ታውቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ዛሬ10:00 ላይ በትግራይ ስቴዲዮም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ቋሚ ተሰላፊዎችን አሳውቋል።
ግብ ጠባቂ:
Mentsenot Alo
ተከላካዮች:
Desta Demu
Aschalew Tamene
Yared Baye
Ahemed Reshid
አማካዮች:
Amanuel Yohannes
Hayeder Sherefa
Kenean Markneh
አጥቂዎች:
Amanuel G/Mikael
Fekadu Alemu
Mesfen Tafesse
አስልጣኝ
ኢንስራክተር አብርሃም መብራት
@YeneTube @FikerAssefa
ግብ ጠባቂ:
Mentsenot Alo
ተከላካዮች:
Desta Demu
Aschalew Tamene
Yared Baye
Ahemed Reshid
አማካዮች:
Amanuel Yohannes
Hayeder Sherefa
Kenean Markneh
አጥቂዎች:
Amanuel G/Mikael
Fekadu Alemu
Mesfen Tafesse
አስልጣኝ
ኢንስራክተር አብርሃም መብራት
@YeneTube @FikerAssefa
ትኩረት ለድሬዳዋ!
የእሬቻ የሩጫ ፕሮግራም እና የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። ድሬዳዋ ግን ረብሻ ተከስቶ ሰዎች ጭንቅ ላይ እንዳሉ መልእክት እየደረሰኝ ነው። እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ትኩረት ስጡልን።
በተለይ በኮኔል፣ በመጋላ፣ በደቻቱ እንዲሁም በአዲስ ከተማ ተደጋጋሚ ተኩስ እየተሰማ ነው። የጸጥታ ሃይሉ አስለቃሽ ጥይት እየተኮሰ እንደሆነና በዚህ መሐል ህጻናት እና አረጋውያን እየተሰቃዩ እንደሆነ መረጃ ደርሶኛል።
ሰላም ለሀገራችን!
Via:- Elias Meseret

ሁከት አስነስተዋል በተባሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ተገለጸ።
በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሁከት ሲያስነሱ ነበር የተባሉ ተማሪዎችና መምህራን ላይ ዕርምጃ መወሰዱን፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሁከት የተሳተፉ ተማሪዎች እስከ ሁለት ዓመት ዩኒቨርሲቲ እንዳይገቡ ዕገዳ የተጣለባቸው፣ እስከ ወዲያኛው ዩኒቨርሲቲ ገብተው እንዳይማሩ የታገዱ፣ እንዲሁም በጥፋታቸው በወንጀል የተጠየቁ መኖራቸውን ሚኒስትሯ ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) ገልጸዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት ተቀስቅሰው በነበሩ ሁከቶችና ግጭቶች ተማሪዎች መሞታቸው፣ ንብረት መውደሙና ተማሪዎች ከትምህርታቸው መስተጓጎላቸው የሚታወስ ነው፡፡ምን ያህል ንብረት እንደወደመ እስካሁን በገንዘብ አልተተመነም የሚሉት፣ በሚኒስቴሩ ከፍተኛ አማካሪ ዓለማየሁ ከበደ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
ዕርምጃ የተወሰደባቸው መምህራንና ተማሪዎች ቁጥር በግልጽ ባይታወቅም፣ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ሁከት አስነስተዋል የተባሉ 20 ተማሪዎች እስከ ወዲያኛው ከትምህርት መታገዳቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ሁከት በማስነሳት ረገድ እጃቸው አለበት የተባሉ መምህራንም የዲሲፒሊን ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው አስረድተዋል፡፡
ምንጭ: ሪፖርተር

YeneTube
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልኡካቸው በሆሳዕና ከተማ ህዝባዊ ውይይት ለማድረግ ሲደርሱ በአካባቢው ነዋሪ በሆሳዕና አቢዮ ስቴድየም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: #PMOEthiopia @YeneTube @FikerAssefa
በውይይቱ ወቅት የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን ስለጉብኝታቸው አመስግነው ዋና ዋና የልማት ጥያቄዎች አንስተዋል::
ለሥራ ፈጠራ በመሰረተ ልማት: በጤናና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ዙሪያ ጥያቄዎችን የነሱት ነዋሪዎቹ የሀድያ ህዝቦችን የቆየ ልምድ በማጠናከር ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ አንስተዋል::
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ቅሬታዎችን በሚዛናዊና የጋራ እሴትና መርሆችን በማያጠፋ መልኩ መቅረብ አለባቸው ብለዋል:: እንዲሁም የሆሳዕና ነዋሪዎች እውቀትና በክልሉ በአንድነት ለመቆየት ያነሱትን ሀሳብ አድንቀዋል:: በተጨማሪም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሆሳዕና ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ነዋይ በማሰባሰብ በአካባቢው ልማት አንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል::ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ሲመልሱም የጉብኝቱ አካል ለሆኑት ለጤናና ለግብርና ሚንስትሮችና ለመንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎች ጥናት እንዲያካሂዱና ለየዘርፎቹ ቁልፍ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::

Any one who is interested in buying bitcoin
1. 1200 dollar total
2. 1 dollar = 60 birr
3. non negotiable
contact me at @awscoolboy
1. 1200 dollar total
2. 1 dollar = 60 birr
3. non negotiable
contact me at @awscoolboy
በግብጽ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ አመጽ እና ግጭት መቀስቀሱ ተነግሯል፡፡
በወደብ ከተማዋ ሲዊዝ 200 ያህል ተቃዋሚዎች ጎዳና ላይ ወጥተው ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡
በተቃዋሚዎች እና የጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት መከሰቱን እና ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ መጠቀሙ ነው የተነገረው፡፡
በርካታ ተቃዋሚዎች በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
የአልሲሲ አስተዳደር ግን በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል ነው የተባለው፡፡
አርብም በተመሳሳይ መልኩ ግብፃውያን በካይሮ ታህሪር አደባባይ ወጥተው በአልሲስ አስተዳዳር የሙስና ተግባር ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል ተብሏል፡፡
FBC

“ሁሉንም ልጆቿን በእኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እጅ ለእጅ ተያይዘን በብልሃት መስራት አለብን” ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
**
“ሁሉንም ልጆቿን በእኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እጅ ለእጅ ተያይዘን በብልሃት መስራት አለብን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን የተናገሩት ከሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው፡፡
የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ስለጉብኝታቸው አመስግነው ዋና ዋና የልማት ጥያቄዎች አንስተውላቸዋል::
በሥራ ፈጠራ፣ በመሰረተ ልማት፣ በጤናና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ዙሪያ ጥያቄዎችን ያነሱት ነዋሪዎቹ የሀድያ ህዝቦችን የቆየ ልምድ በማጠናከር ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል::
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቅሬታዎችን በሚዛናዊና የጋራ እሴትና መርሆችን በማያጠፋ መልኩ መቅረብ አለባቸው ብለዋል::
የሆሳዕና ነዋሪዎች እውቀትና በክልሉ በአንድነት ለመቆየት ያነሱትን ሀሳብም አድንቀዋል::
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሆሳዕና ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ነዋይ በማሰባሰብ በአካባቢው ልማት አንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉም ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥሪ አቅርበዋል::
ለመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ሲመልሱም የጉብኝቱ አካል ለሆኑት ለጤናና ለግብርና ሚንስትሮችና ለመንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎች ጥናት እንዲያካሂዱና ለየዘርፎቹ ቁልፍ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::
Via:- EBC

የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን በያዝነው አዲሱ 2012 ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ተቋማት ፍቃድ እንደሚሰጥ አስታወቀ።
ይህን ያሉት በቅርቡ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተደርገው የተሾሙት አቶ ባልቻ ሬባ ናቸው።
@YeneTube @Fikerassefa
ይህን ያሉት በቅርቡ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተደርገው የተሾሙት አቶ ባልቻ ሬባ ናቸው።
@YeneTube @Fikerassefa
በድሬ ዳዋ ከተማ ቀፊራ እና አዲስ ከተማ በሚባሉ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።
አንድ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ "አምቡላንሶች ሰዎችን ወደ ሆሰፒታል ሲያመላልሱ ነበር። ጉዳት ደርሶባቸው ደም የሚፈሳቸው ሰዎችንም ተመልክቻለሁ'' ብለዋል።
የግጭቱ መነሻ ደግሞ "አዲስ ከተማ ጋራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አዲስ በተገነባው የተክለኃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ላይ ሰዎች ድንጋይ በመወርወራቸው ነው'' ብለውናል።
"የአዲስ ከተማ ሰፈር ልጆች ድንጋይ ወረወሩ የተባሉትን ልጆች ደበደቡ ሲባል ነው የሰማነው" ብለዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://telegra.ph/ddiredawa-09-22