YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሁከት አስነስተዋል በተባሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ላይ ዕርምጃ መወሰዱ ተገለጸ።

በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሁከት ሲያስነሱ ነበር የተባሉ ተማሪዎችና መምህራን ላይ ዕርምጃ መወሰዱን፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሁከት የተሳተፉ ተማሪዎች እስከ ሁለት ዓመት ዩኒቨርሲቲ እንዳይገቡ ዕገዳ የተጣለባቸው፣ እስከ ወዲያኛው ዩኒቨርሲቲ ገብተው እንዳይማሩ የታገዱ፣ እንዲሁም በጥፋታቸው በወንጀል የተጠየቁ መኖራቸውን ሚኒስትሯ ሒሩት ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ጊዜያት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት ተቀስቅሰው በነበሩ ሁከቶችና ግጭቶች ተማሪዎች መሞታቸው፣ ንብረት መውደሙና ተማሪዎች ከትምህርታቸው መስተጓጎላቸው የሚታወስ ነው፡፡ምን ያህል ንብረት እንደወደመ እስካሁን በገንዘብ አልተተመነም የሚሉት፣ በሚኒስቴሩ ከፍተኛ አማካሪ ዓለማየሁ ከበደ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ዕርምጃ የተወሰደባቸው መምህራንና ተማሪዎች ቁጥር በግልጽ ባይታወቅም፣ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ሁከት አስነስተዋል የተባሉ 20 ተማሪዎች እስከ ወዲያኛው ከትምህርት መታገዳቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ሁከት በማስነሳት ረገድ እጃቸው አለበት የተባሉ መምህራንም የዲሲፒሊን ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው አስረድተዋል፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልኡካቸው በሆሳዕና ከተማ ህዝባዊ ውይይት ለማድረግ ሲደርሱ በአካባቢው ነዋሪ በሆሳዕና አቢዮ ስቴድየም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: #PMOEthiopia @YeneTube @FikerAssefa
በውይይቱ ወቅት የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን ስለጉብኝታቸው አመስግነው ዋና ዋና የልማት ጥያቄዎች አንስተዋል::

ለሥራ ፈጠራ በመሰረተ ልማት: በጤናና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ዙሪያ ጥያቄዎችን የነሱት ነዋሪዎቹ የሀድያ ህዝቦችን የቆየ ልምድ በማጠናከር ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ አንስተዋል::
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ቅሬታዎችን በሚዛናዊና የጋራ እሴትና መርሆችን በማያጠፋ መልኩ መቅረብ አለባቸው ብለዋል:: እንዲሁም የሆሳዕና ነዋሪዎች እውቀትና በክልሉ በአንድነት ለመቆየት ያነሱትን ሀሳብ አድንቀዋል:: በተጨማሪም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሆሳዕና ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ነዋይ በማሰባሰብ በአካባቢው ልማት አንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል::ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ሲመልሱም የጉብኝቱ አካል ለሆኑት ለጤናና ለግብርና ሚንስትሮችና ለመንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎች ጥናት እንዲያካሂዱና ለየዘርፎቹ ቁልፍ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
Any one who is interested in buying bitcoin
1. 1200 dollar total
2. 1 dollar = 60 birr
3. non negotiable

contact me at @awscoolboy
በግብጽ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ አመጽ እና ግጭት መቀስቀሱ ተነግሯል፡፡

በወደብ ከተማዋ ሲዊዝ 200 ያህል ተቃዋሚዎች ጎዳና ላይ ወጥተው ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

በተቃዋሚዎች እና የጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት መከሰቱን እና ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ መጠቀሙ ነው የተነገረው፡፡

በርካታ ተቃዋሚዎች በጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
የአልሲሲ አስተዳደር ግን በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል ነው የተባለው፡፡

አርብም በተመሳሳይ መልኩ ግብፃውያን በካይሮ ታህሪር አደባባይ ወጥተው በአልሲስ አስተዳዳር የሙስና ተግባር ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል ተብሏል፡፡

FBC
@YeneTube @Fikerassefa
“ሁሉንም ልጆቿን በእኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እጅ ለእጅ ተያይዘን በብልሃት መስራት አለብን” ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
**
“ሁሉንም ልጆቿን በእኩልነት የምታስተናግድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እጅ ለእጅ ተያይዘን በብልሃት መስራት አለብን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን የተናገሩት ከሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው፡፡
የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ስለጉብኝታቸው አመስግነው ዋና ዋና የልማት ጥያቄዎች አንስተውላቸዋል::
በሥራ ፈጠራ፣ በመሰረተ ልማት፣ በጤናና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ዙሪያ ጥያቄዎችን ያነሱት ነዋሪዎቹ የሀድያ ህዝቦችን የቆየ ልምድ በማጠናከር ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል::
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቅሬታዎችን በሚዛናዊና የጋራ እሴትና መርሆችን በማያጠፋ መልኩ መቅረብ አለባቸው ብለዋል::
የሆሳዕና ነዋሪዎች እውቀትና በክልሉ በአንድነት ለመቆየት ያነሱትን ሀሳብም አድንቀዋል::
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሆሳዕና ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ነዋይ በማሰባሰብ በአካባቢው ልማት አንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉም ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥሪ አቅርበዋል::
ለመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ሲመልሱም የጉብኝቱ አካል ለሆኑት ለጤናና ለግብርና ሚንስትሮችና ለመንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎች ጥናት እንዲያካሂዱና ለየዘርፎቹ ቁልፍ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::

Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን በያዝነው አዲሱ 2012 ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ተቋማት ፍቃድ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ይህን ያሉት በቅርቡ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተደርገው የተሾሙት አቶ ባልቻ ሬባ ናቸው።
@YeneTube @Fikerassefa
በድሬ ዳዋ ከተማ ቀፊራ እና አዲስ ከተማ በሚባሉ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።

አንድ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ "አምቡላንሶች ሰዎችን ወደ ሆሰፒታል ሲያመላልሱ ነበር። ጉዳት ደርሶባቸው ደም የሚፈሳቸው ሰዎችንም ተመልክቻለሁ'' ብለዋል።

የግጭቱ መነሻ ደግሞ "አዲስ ከተማ ጋራ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አዲስ በተገነባው የተክለኃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ላይ ሰዎች ድንጋይ በመወርወራቸው ነው'' ብለውናል።

"የአዲስ ከተማ ሰፈር ልጆች ድንጋይ ወረወሩ የተባሉትን ልጆች ደበደቡ ሲባል ነው የሰማነው" ብለዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ
https://telegra.ph/ddiredawa-09-22
ስፖርት !! ትግራይ ስታዲየም የተደረገው 2020 ቻን ማጣሪያ ጨዋታ ውጤት ዋሊያዎቹ ተሸንፈዋል።

ተጠናቀቀ

🇪🇹ኢትዮጲያ0⃣1⃣ሩዋንዳ 🇷🇼

@YeneTube @Fikerassefa
CECAFA U20 UGANDA 2019

FT | 🇪🇹 Ethiopia 0-4 🇹🇿Tanzania Bara
⚽️Kelvin John
⚽️Andrew
⚽️Andrew
⚽️Andrew
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሖሳዕና በነበራቸው ቆይታ የኮሎኔል በዛብሕ ጴጥሮስ ጉዳይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ስምምነት አንድ አካል እንደሆነ መናገራቸውን በውይይቱ የተሳተፉት የሐዲያ ዞን አስተዳደር የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን አባይነሕ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

ዛሬ ማምሻውን በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የ12 ክፍል ተማሪዎች የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የከተማ አስተዳዳሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የሃይመኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የተጋበዙ የሃይመኖት አባቶች ተማሪዎቹ በሚገቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እና አካባቢዎች በመልካም አራያነት የሚጠቀሱ ተግባራትን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል፡፡ራሳቸውን በመልካም ስነ ምግባር በማነጽ የእኩይ አላማ ማስፈፀሚያ መሆን እንደማይገባቸውም አስረድተዋል፡፡መርሃ ግበሩ ተማሪዎቹ በ2012 የከፍተኛ ትምህርት ቆይታቸው ሰላማዊ እና አንድነቱ የተጠበቀ የመማር ማስተማር ለማስፈን የሚያስችል እንደሆም ነው የተገለጸው፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሰንቀሌ ወታደራዊ ካምፕ የታሰሩት ወጣቶች #ተፈቱ !!!

በሰንቀሌ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ በጅምላ ታስረው የነበሩት ወጣቶች ከእስር እየተፈቱ ነው። ከምዕራብ # ወለጋ ፣ ምዕራብ # ጉጂ እና ቄለም ወለጋ ከመጡት በስተቀር ከሌሎች የኦሮሚያ አከባቢዎች የታሰሩት ወጣቶች መፈታታቸው ታውቋል። ከላይ ከተጠቀሱት ሦስት አከባቢዎች የመጡት ወጣቶችንም ለመፍታት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የእስረኛ ቤተሰቦች ወጣቶቹን ለመውሰድ የትራንስፖርት መኪና በማሰባሰብ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በዚሁ መሠረት ከምዕራብ ወለጋ ለታሰሩት ወጣቶች የሚያስፈልገው የአውቶቢስ መኪና ብዛት 12 ሲሆን ለምዕራብ ጉጂ 14 እና ለቄለም ወለጋ ደግሞ 12 አውቶብስ መኪኖች እንደሚያስፈልጉ የእስረኛ ቤተሰቦች ገልፀዋል። ከሶስቱ አከባቢዎች ለታሰሩ ወጣቶች ብቻ 38 አውቶብስ መኪና ማስፈለጉ የእስረኞቹ ብዛት ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበር መገመት ይቻላል።

በሌላ አነጋገር ከሶስቱ አከባቢዎች ብቻ ወደ 2000 ወጣቶች ታስረው እንደነበር መገመት ይቻላል።

ምንጭ:- ስዩም ተሾመ
@YeneTube @Fikerassefa
Average speed of mobile internet. (Mbps)

1. Iceland: 72.5
2. Norway: 67.8
3. Qatar: 60.3
4. Canada: 59.6
6. Australia: 55.7
28. France: 38.7
33. Turkey: 34.7
41. US: 31.2
49. China: 28.9
52. UK: 28.3
54. Saudi: 27.1
70. Brazil: 20.5
77. Russia: 18.4
111. India: 9.9

(SpeedTest)

@YeneTube @FikerAssefa
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ መከበሩ ኢሬቻን ወደ ቱሪዝም ገበያ የማውጣት ስራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ገለጸ።

ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅም በጸጥታ ሃይሉ በቂ ዝግጅት መደረጉንና፤ ለስኬታማነቱም የአባ ገዳ ፎሌ ወጣቶች ብሎም የህብረተሰቡ ድጋፍ ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ ለኢ.ፕ.ድ እንደገለጹት፤ የኢሬቻ በዓል ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይገድበው ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት የሚያከብረው በዓል ነው። ከሁለት ዓመት ወዲህ ደግሞ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እየተሳተፉበት ያለ በዓል ነው። ይህ እየሰፋ ሲሄድ ደግሞ ኢሬቻ የአገር ብሎም የዓለም እሴትነቱ እየጎላ ይሄዳል።በመሆኑም በዓሉ ከቱሪዝም ሀብትነቱ ባለፈ ለህዝቦች አንድነትና ለአገር ግንባታ ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል። ከዚህ አኳያ በዓሉ በአዲስ አበባ መከበሩ ኢሬቻን የጋራ እሴት ለማድረግ፣ ለአገር ግንባታና ለአብሮነት ማጠናከርያ ለማዋል፤ ብሎም እሴቶቹን ለማስተዋወቅ ወደ ገበያ የማውጣት ስራ ነው።

ምንጭ:ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ባለፉት ኹለት ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ንግድ 183 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሐምሌና ነሐሴ 2011 ከ52 ሺሕ 300 ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ አገራት የተላከ ሲሆን፣ ከባለፈው 2010 ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ከ6 ሺሕ 585 ቶን በላይ ጭማሬ ማሳየቱንም ለማወቅ ተችሏል። ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ጭማሬ አሳይቷል።ቡና ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ቀዳሚ ሲሆን፣ በባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ774 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለአገሪቷ አስገኝቷል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በእጅ #በሞባይል የታገዘ የተለያዩ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ነጻነት ለሜሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ድርጅቱ አገልግሎቶቹን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በአነስተኛና በጥቃቅን ሙያዎች ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሞባይል በመታገዝ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ሊሰጥ ነው። እንደ መደበኛው የኢንሹራንስ አገልግሎት ቅርጫፍ እየከፈቱ አረቦን በአካል እየመጡ እንዲከፍሉ ማድረግ አዋጪና ቀልጣፋ ባለመሆኑ አገልግሎቶቹ በሞባይል በመታገዝ የሚሰጡ ይሆናል።

በሞባይል የታገዘ የኢንሹራንስ አገልግሎት ህብረተሰቡ ባለበት ቦታና አካባቢ ሆኖ አገልግሎቱን እንዲያገኝ የሚያስችለው መሆኑን አመልክተው አገልግሎቱን ለመጀመር የድርጅቱን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና ሶፍት ዌር የማሻሻል ስራ እንደሚሰራና ለዚህም 450 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን ተናግረዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ነጃሺ ባንክ 678 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ሸጠ

አዲስ በመመስረት ላይ የሚገኘው ነጃሺ ባንክ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ላይ 678 ሚሊዮን ብር መሸጡን አስታወቀ። ባንኩ ወደ ስራ ለመግባት በሚያስችለው ደረጃ ላይ 378 ሚሊዮን ብር የሸጠ ሲሆን በውጭ አገራት በሚገኙ የዲያስፖራው ማኅበረሰብ ደግሞ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ሽያጭ ማካሔዱን ይፋ አድርጓል።

ባንኩ በአጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ መድረክ ላይ ባካሔደው ሽያጭ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን ግማሽ ቢሊየን ብር አሟልቷል። 678ሚሊየን ብር መስራቾች አክሲዮን በመግዛት የባንኩ ባለቤቶች ሆነዋል።

አንዲሁም አማራ ባንክ አክሲዮን 260 ሚልዮን ብር መሸጡን ከትላንት በስቲያ አስታውቋል።

ምንጭ:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
"ጎንደር ርዕሰ አድባራት አደባባይ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሚደረገው ፀሎት እስከ መስከረም 21 የሚቀጥል ሲሆን፤ምህላ ለግል ህይወታችን፣ለከተማዋ፣ ለክልላችን፣ለሀገራችን ብሎም ለዓለማችን በረከትን እና ሰላምን ይሰጣልና ኑ አብራችሁን ለሀገራችን እንፀልይ ።"
@YeneTube @Fikerassefa
550 ኮንቴነር መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶች ወደ አገር ገብተዋል፡- የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ባለፋት 2 ወራት ከ550 ኮንቴነር በላይ መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ማንሣቱን አስታወቀ፡፡

ከ25 ዓይነት በላይ መድኃኒቶችን ከሞጆ ደረቅ ወደብ ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለማንሳት መቻሉን የኤጀንሲው የመድኃኒት ኮንትራት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ አጋር ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡
መድኃኒቶቹ ለኤች.አይ.ቪ፣ ለሆድ ሕመም፣ ለኢንፌክሽን፣ ለስነተዋልዶ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችና ሪኤጀንቶች እንደሆኑ ወ/ሮ አጋር አብራርተዋል፡፡

መድሀኒቶቹን በቀጥታ በተለያዩ ቅርንጫፎችና በዋናው መ/ቤት የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን እንደገቡ አስረድተዋል፡፡

ወደ ቅርንጫፍ ቀጥታ መሄዱም ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ ለማህበረሠቡ በቶሎ መድኃኒቶችን ተደራሽ ለማድረግ ወሣኝ ሚና አለው ሲሉ ባለሙያዋ አክለዋል፡፡

እክሎች እንዳይከሠቱ በባንኩ፣ በሞጆ ደረቅ ወደብ፣ በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እና በኤጀንሲው መካከል ውል ለመፈራረም በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ባለሙያዋ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት
@Yenetube @Fikerassefa