YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የዋጋ ግሽበት እንዲባባስ ባደረጉ 609 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስድብ ተባለ!

በከተማዋ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ግሽበት እንዲባባስ ባደረጉ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በከተማዋ የተለያዩ ህገወጥ አሰራሮችን በመጠቀም የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ እንዲጨምር ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ ፍተሻ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም በድርጊቱ ተሳትፈው የተገኙ 609 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ ተናግረዋል።ከዚህ ባለፈም ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ የንግድ ተቋማት ማስጠንቀቂያ የተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡ የአቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣም፣ የግብይት ሰንሰለቱ በህገ ወጥ ደላሎች መያዝ እና የህገ ወጥ ንግድ መበራከት በከተማዋ ለተከሰተው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል።ቢሮው በቀጣይ በከተማዋ የሚስተዋለውን የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠርም ከጸጥታ አካላት እና ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

Via ኤፍ.ቢ.ሲ
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በቦልቪያናዊዉ ናማኒ ቺንቼ ኢቬሊን የፓስፖርት ቁጥር AE57255 ከብራዚል ሳዖ ፖሎ አዲስ አበባ የገባዉ 8 ኪሎ ግራም የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ በቦሌ የጉምሩክ ፈታሾች በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

ዕፁን ይዞት ይጓዝ በነበረዉ ግለሰብ ላይ ከብራዚል ሳኦ ፖሎ ጀምሮ በጉምሩክ ኮሚሽን ኢንተለጀንስ ቡድን ባደረገዉ የተቀናጀና ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊዉል መቻሉ ተገልጿል፡፡
ይህንን አድካሚና የተቀናጀ ስራ በመስራት እፁን መያዝ ለቻሉ የቦሌ አየር ማረፊያ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራር አካላትና ሰራተኞች የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል፡፡

ባለፈዉ ሳምንትም 20 ሚሊየን ብር የሚገመት 10.8 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ መያዙ የሚታወስ ነዉ፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
ገንዘቤ ዲባባ በዶሐ ከሚካሔደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጪ ሆነች። ገንዘቤ በቀኝ እግሯ ላይ በደረሰባት ጉዳት ምክንያት በሚቀጥለው ሳምንት ከሚጀመረው ውድድር ውጪ መሆኗን አትሌቷን የሚወክለው ፔኔዳ ስፖርት አስታውቋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ የነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ!

@YeneTube @FikerAssefa
ብሪታኒያ ዜጎቿ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክሯን አስተላለፈች!!

የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩም ሆነ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የሚያመሩ ዜጎቹ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከደኅንነት ስጋት ጋር በተያያዘ እንዳይዘዋወሩ አስጠንቅቋል። ማስጠንቀቂያውም አምስት ክልሎችን ያካተተ ሲሆን ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሱማሌ እና ጋምቤላ ናቸው።

የውጭ እና ኮመን ዌልዝ (common wealth) ቢሮ ይፋ እንዳደረገው በጋምቤላ ክልል አራት ወረዳዎች እና ከደቡብ ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ዐስር ኪሎሜትር ድረስ መቅረብ እንደሌለባቸው አስጠንቅቋል። በሱማሌ ክልል ጃር ጃር፣ ቆራሔ እና ደሎ የተባሉ አካባቢዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት የሱማሌ ክልል 100 ኪሎ ሜትር መራቅ እንደሚኖርባቸውም አሳስቧል። በትግራይ ክልልም ከኢትዮ- ኤርትራ ድንበር ዐስር ኪሎ ሜትር እንዲሁም ደብረ ዳሞ እና የሓ የጎብኝዎች መዳረሻዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ ሲል አስጠንቅቆ፥ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ፀገዴ፣ ምዕራብ አርማጭሆ እና ታች አርማጭሆ አካባቢዎች ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ዜጎቹን አሰጠንቅቋል።

ቢሮው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞን ከአዲስ አበባ ጋምቤላ ከሚወስደው ዋና መንገድ ውጪ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት እንዳለ ይፋ አድርጓል።

መግለጫው በየዓመቱ ከአገረ እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ እስከ 20ሽሕ የሚደርሱ ጎብኝዎች እንደሚመጡ ገልፆ ኹሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ጉብኝቶች ከችግር እና ከደኅንንት ስጋት የፀዱ እንደነበሩና አሁንም ዜጎች ችግር እንዳይገጥማቸው ቅድመ ጥንቃቄ መውሰድ ጠቃሚ እንደሆነ አስታውቋል።

Via:- addis maleda
@YeneTube @Fikerassefa
ቶታል ኢትዮጵያ በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ የሞተር ዘይት መለወጫ ጣቢያዎች እንደገነባ አስታወቀ።

ላለፉት 69 ዓመታት በኢትዮጵያ የነዳጅ ማከፋፈል ዘርፍ ተሰማርቶ የቆየው ቶታል ኢትዮጵያ፣ በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ 52 የተሽከርካሪዎች የሞተር ዘይትና የቅባት መለዋወጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባና ክልል ከተሞች መገንባቱን አስታወቀ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ 32፣ በክልል ከተሞች 20 የሞተር ዘይትና የቅባት መለወጫ ጣቢያዎችን ከሽያጭ ወኪሎች ጋር በመተባበር በ40 ሚሊዮን ብር ወጪ ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን ኩባንያው አስታውቋል፡፡ እያንዳንዱ ጣቢያ በአማካይ ለአሥር ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
ሜቴክ የኢምፔሪያል ሆቴል ቢሮውን እንዲለቅ ሊደረግ ነው።

ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ከዓመታት በፊት በ108 ሚሊዮን ብር የገዛውን እና ለቢሮ አገልግሎት ሲጠቀምበት የነበረውን የኢምፔሪያል ሆቴልን እንደሚለቅ ፋና ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ከ300 በላይ ድርጅቶች የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎቻቸውን አቀረቡ።

መስከረም 7/2012 ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ከ300 በላይ ድርጅቶች የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎቻቸውን በመላክ የፋይናንስ ድጋፍ ጥያቄ አቀረቡ።ፕሮጀክቶቹን ያቀረቡት ህጋዊ እውቅና ያላችው መንግስታዊ ያልሆኑ እና ሀገር በቀል የልማት ድርጅቶች ናቸው። የህዝብና የሞያ ማህበራት፣ የፌደራል፣ የክልል እና የአካባቢያዊ የመንግስት ተቋሞች እንዲሁም ሰፊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን የሚተገብሩ የግሉ ዘርፍ ድርጅቶች ናቸው።

ድርጅቶቹ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጋር አብረው ለመስራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።ለትረስት ፈንዱ የቀረቡት የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ቁጥር ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ መሆኑንም አመልክቷል።

ምንጭ: በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Start your Journey to Work In Europe Now.
Jawisaro Travel Consultancy has started new registration On Work Visa in Europe
1) Work Visa in Europe And In Canada
⭕️ No requirement
⭕️ Visa within 2 month
⭕️ Monthly salary with over
40,000Birr
2) Student visa In Canada🇨🇦🇨🇦 is also available
With Very very Cheap Agent fee ❗️❗️
Deadline is soon come fast and register. Special Offer for New Graduates
As we always say it is Company with no limitation JUST CONTACT US
+251932516194
+251988058420
Join our Channel @Jah_Travel_Agency
ይህንን መተግበሪያ በስልኮ ላይ በመጫን ውሎዎን ቀለል ያድርጉ!

አዳዲስ ቦታዎችን ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለለጓደኛዎ ያጋሩ፣ በተጨማሪም የተለያዩ ፕሮግራሞችና Events የሚካሄዱበትን ቦታና ሰዐት በቀላሉ ይመልከቱ!!


There’s a lot to explore around you. Download Ahun, get the best out of your city!

Now available on the Play Store and App Store!!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahun.android


https://apps.apple.com/ke/app/ahun/id1474285014


Join us on telegram

—- https://tttttt.me/Ahun_app

Follow us on Instagram

https://instagram.com/ahun.app?igshid=ab6oe4ob8485
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የባህር ዳር - ዘማ ወንዝ - ፈለገብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀዋል፡፡

በሁለት ኮንትራት ተከፍሎ ግንባታው ሲካሄድ የቆየው የባህርዳር - ዘማ ወንዝ -ፈለገ ብርሃን 175 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።ለመንገዱ ግንባታ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን ከ2.4 ቢሊየን ብር በላይ የግንባታ ወጪ ተደርጓል፡፡በምረቃው ስነ~ስርዓት የፌዴራል እና የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

#DPMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግጭት በመሳተፍ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች 156 መድረሱን ሸገር የክልሉን መንገሥታዊ ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ሰኔ 16 ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት፣ 59 ንጹሃን መገደላቸው ይታወሳል፡፡ ክልሉ የግጭቱን ተፈናቃዮች እስካሁንም መልሶ በማቋቋም ላይ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ዋሽንግተን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን የማኅበራዊ ሜዲያ ምንጮች አመልክተዋል፡፡ ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለመቃወም የወጡ ናቸው፡፡ የሰንበት ተማሪዎች በብዛት ተሳታፊ ናቸው፡፡ የሐይማኖቱ አባቶችም ንግግር አድርገዋል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዋሳ⬆️

የኢትዮጵያ ሂሞፊልያ ሶሳይቲ በሀዋሳ የምስረታ ጉባኤው ዛሬ በኬራዊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አደረገ። ሂሞፊልያ (የደም አለመርጋት ችግር) በኢትዮጵያ 10,000 ሕሙማን አሉ ተብሎ ይገመታል። ከነዚህ ውስጥ ግን 333 ብቻ ናቸው ሕክምና በማግኘት ላይ የሚገኙት።

Via:- ናትናኤል - መስራች
@Yenetube @Fikerassefa
ሲዳማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውስኔ ዙሪያ ከደቡብ ክልል የተለያዩ ተቋማት ጋር መወያየቱን አስታወቀ።

ቦርዱ እንዳስታወቀው አስቀድሞ ባወጣው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሀ ግብር መሰረት የተለያየ ሀላፊነት ያላቸው የህግ አስፈጻሚ እና የጸጥታ አካላት እና የቦርዱ የስራ አመራር አባላት የህዝበ ውሳኔውን አፈጻጸም ሰላማዊነት ዙሪያ ተወያይቷል።

በውይይቱም የፌደራል ፓሊስ ተወካዮች ፣ የደቡብ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ተወካዮች፣ በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሀላፊ፣ የአዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ፣ የሲዳማ ዞን ፓሊስ ሀላፊ, የክልሉ የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

https://telegra.ph/Yenetub-09-19
ኢ/ር ታከለ ኡማ በስታዲየም ዙሪያ ላሉ በ46 ማህበራት ለታቀፉ 278 ስራ አጥ ወጣቶች የመስሪያ ሱቆችን አስረከቡ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የንግድ ሱቆችን በልዩ ሁኔታ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በማህበር ለተደራጁ ወጣቶቹ በዛሬው ዕለት በዕጣ አስተላልፏል፡፡የመስሪያ ሱቆቹ ስፋት ዝቅተኛው 82 ካ.ሜ ሲሆን ከፍተኛው 392 ካ.ሜ ሆኖ በወጣው ዕጣ መሠረትም ለባለዕድለኞቹ ተላልፈዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በዕጣ ማውጣት መርሃ ግብሩ ላይ ለስታዲየም ዙሪያ ስራ አጥ ወጣቶች የተፈጠረው የስራ ዕድል የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ወጣት ህይወት ለመቀየር የያዘው ግዙፍ ፕሮጀክት አካል ነው ብለዋል፡፡በተያዘው አመትም ካለፈው አመት በተሻለና የወጣቶችን ህይወት በሚቀይር መልኩ አዳዲስ ዕቅዶችን በመንደፍ ለወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል እንደሚፈጠር ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡የንግድ ሱቆቹን ከመስጠት በተጨማሪም ለወጣቶቹ ጠንካራ ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተገልጿል።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
በስደት ላይ በሳውዲ አረቢያ የነበሩት የቀድሞው የቱኒዝያ ፕሬዘዳንት ቤን አሊ በ83 ዓመታቸው መሞታቸው ተገለጸ።

የቀድሞው ፕሬዘዳንት ከ8 ዓመት በፊት የአረብ አብዮት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር ወደ ሳውዲ የተሰደዱት።

83 ዓመት የሆናቸው እኝህ ስደተኛ በካንሰር ህመም ተጠቅተው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር ሆስፒታል መግባታቸው የተሰማው።

በቤን አሊ የፕሬዘዳንትነት ዘመን ቱኒዝያ በስራ አጥነት፣ሙስና እና ሌሎች አፈናዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የአገሪቱ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥተው ፕሬዘዳንቱን ለስደት ዳርገዋል።

የቀድሞው ፕሬዘዳንት ወደ ቀድሞ ወዳጃቸው ሳውዲ አረቢያ ከተሰደዱ በኋላ በቱኒዚያ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዶ በቅርቡ ሌላ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው።

Via:- EthioFM
@YeneTube @FikerAssefa
በሜክሲኮ ኤል ቡዌን ፓስተር መጠለያ ከሚገኙ 130 ገደማ ስደተኞች መካከል ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል። ስደተኞቹ አሜሪካ ለመግባት ያቀዱ ቢሆኑም የትራምፕ አስተዳደር ቁጥጥር አግዷቸዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተለያዩ ምክንያቶች የተሰናበቱ የደቡብ ክልል ነዋሪዎች ቃል የተገባላቸዉን የማቋቋሚያ ድጎማ #መነፈጋቸዉን አስታወቁ።

«ተመላሽ» በሚል ጥቅል ስም የሚጠሩት የቀድሞ ወታደሮች እንደሚሉት ከየነበሩበት ክፍለ ጦር ሲሰናበቱ የየአካባቢያቸዉ መስተዳድር የመኖሪያ፣የሥራ፣የትምሕርትና የሌሎችንም ድጋፎች እንደሚያደርግላቸዉ ቃል ተገብቶላቸዉ ነበር።ይሁንና ቃሉ እስካሁን ገቢራዊ ባለመሆኑ አንዳዶች ለጎዳና ኑሮ፣ሌሎች ደግሞ ለስነልቡናዊ ቀዉስ ተዳርገዋል።

አንድ የደቡብ ክልል ባለስልጣን የቀድሞ ወታደሮቹን ቅሬታ «ተገቢ» ይሉታል። እስካሁን ግን መስተዳድራቸዉ ከጥናት በስተቀር ተጨባጭ መፍትሔ አልሰጠም።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክክል የአሚበራ ወረዳ ነዋሪዎችና የዓይን ምስክሮች እንዳሉት የዉኃዉ ሙላት በመቶ የሚቆጠሩ  ነዋሪዎችን አፈናቅሏል።ግምቱ በዉል ያልታወቀ ሰብል አጥፍቷልም።

በክረምቱ ዝናብ ምክንያት የአዋሽ ወንዝ መልቶ ከገደፉ በመፍሰሱ በአፋር ክልል #በሰዎች#እንስሳትና ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን የክልሉ ነዋሪዎች አስታወቁ። በአፋር ክክል የአሚበራ ወረዳ ነዋሪዎችና የዓይን ምስክሮች እንዳሉት የዉኃዉ ሙላት በመቶ የሚቆጠሩ  ነዋሪዎችን አፈናቅሏል። ግምቱ በዉል ያልታወቀ ሰብል አጥፍቷልም። ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት እስካሁን ድረስ ከአፋር መስተዳድም ሆነ ከፌደራሉ መንግስት የደረሳቸዉ ርዳታ የለም። የአዋሽ ወንዝ የቆቃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ለማስተፈስ ሲለቀቅና ክረምቱን ሲሞላ በየዓመቱ ሰዉና ንብረት ይጎዳል።

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa