የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፖሊስ የኢቦላ ወረርሽኝ ለመከላከል የተመደበን ገንዘብ መዝብረዋል ብሎ የጠረጠራቸውን የቀድሞ የጤና ጥበቃ ምኒስትር ኦሊ ኢሉንጋ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። ሰውየው በጥርጣሬ ከወር በፊት በቁጥጥር ሥር ውለው ቢለቀቁም አሁን ከአገር ሊሸሹ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ በድጋሚ ዘብጥያ ወርደዋል። ኢሉንጋ ከሥልጣናቸው በፈቃዳቸው የለቀቁት ባለፈው ሐምሌ ነበር። 1,974 የአገሪቱ ዜጎች በኢቦላ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ኮንጎ ያቋቋመችው ኮሚቴ አስታውቋል።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ አሞላል ላይ ከነገ እሁድ መስከረም 4 2012 አ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የግብጽ ; የሱዳንና የኢትዮጵያ ውሀ ሚኒስትሮች በካይሮ ይወያያሉ። የኢትዮጵያ የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለም ለዚሁ ጉዳይ ወደ ካይሮ የሚያቀኑ ይሆናል።ሱዳንም አዲስ ባገኘችው የውሀ ሚኒስትር ያሲር አባስ መሀመድ ተወክላ የኢትዮጵያን ጨምሮ ከግብጹ የውሀ እና መስኖ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ ጋር ነው ውይይቱ የሚደረገው።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ከስምንት አመታት በፊት በአገራቸው የጸደይ አብዮት ባይነሳ ኖሮ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ባልሰራች ነበር ሲሉ ተናገሩ።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ፕራምፕ የአልቃይዳ የቀድሞ መሪ #ኦሳማ_ቢን_ላደን ልጅ ሃምዛ ቢን ላደን መገደሉን አረጋገጡ። መቼ እንደተገደለ ግን አልገለፁም።
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ፕራምፕ የአልቃይዳ የቀድሞ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ሃምዛ ቢን ላደን መገደሉን አረጋገጡ። ሀምዛ የተገደለው በአሜሪካ የፀረ-ሽብር ተልኮ አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን አካባቢ ነው ይላል ዛሬ ከኋይት ሀውስ ይፋ የሆነው መግለጫ።
መግለጫው ግን ልጅየው መቼ እንደተገደለ አይገልፅም። ይሁንና የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን የስለላ ድርጅትን ዋቢ በማድረግ ባለፈው ሐምሌ ወር መጨረሻ ሀምዛ ቢን ላደን ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ መገደሉን ዘግበው ነበር። ከኋይትሀውስ የወጣው የዛሬው መግለጫ የቢን ላድን ልጅ መገደል ለአልቃይዳ ቡድን ሽንፈትን ብቻ ሳይሆን ቡድኑ ያሉትን ወሳኝ እንቅስቃሴዎች ይቀንሳል ይላል።
ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው የካቲት ወር የቢን ላደን ልጅ ያለበትን ቦታ ለሚጠቁም አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ይፋ አድርጋ ነበር። ሀምዛ ቢን ላደን አባቱ ከተገደለ በኋላ የአሸባሪው አልቃይዳ ቡድን አንዱ ተተኪ መሪ ነበር ተብሎ ይታመናል።
Via:- DW

27ሚሊዮን ብር የሚገመት አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ!
የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል እየሰሩት ባለው ስራ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በመያዝ ላይ መሆናቸውን ገለጹ።
በዚሁ መሰረት 2 7ሚሊዮን ብር የሚገመት 10.8ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር አውለዋል።
Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa

እኛ የራሳችንን ተወተናል እናንተስ?
ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ “በቤስት ራኒንግ ኢቨንትስ” የውድድር መስፈርት በ1ኛ ደረጃ እየመራ ነው ኢትዮጵያዊያንም ከዚህ በታች ባለው ድረ ገጽ ውድድሩ ከመጠናቀቁ በፈት ድምጻችንን እንስጣቸው!!⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ አህመድ ቦንጋ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ዛሬ ማለዳ ወደ ደቡብ ክልል ቦንጋ ያመሩ ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የመከላከያ ሚኒሰትሩ አቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች አመራሮችም አብረው ተጉዘዋል።
ይሁንና ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ለምን ወደ ስፍራው እንደተጓዙ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ዛሬ ማለዳ ወደ ደቡብ ክልል ቦንጋ ያመሩ ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የመከላከያ ሚኒሰትሩ አቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች አመራሮችም አብረው ተጉዘዋል።
ይሁንና ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ለምን ወደ ስፍራው እንደተጓዙ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።
@YeneTube @Fikerassefa
የቀድሞው የቱኒዝያ ፕሬዘዳንት ቤን አሊ በጠና መታመማቸው ተገለጸ።
ከ8 ዓመት በፊት የአረብ አብዮት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር የቀድሞው የቱኒዝያ ፕሬዘዳንት ወደ ሳውዲ የተሰደዱት።
83 ዓመት የሆናቸው እኝህ ስደተኛ በካንሰር ህመም ተጠቅተው ሆስፒታል መግባታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
በቤን አሊ የፕሬዘዳንትነት ዘመን ቱኒዝያ በስራ አጥነት፣ሙስና እና ሌሎች አፈናዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው የአገሪቱ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥተው ፕሬዘዳንቱን ለስደት ዳርገዋል።
የቀድሞው ፕሬዘዳንት ወደ ቀድሞ ወዳጃቸው ሳውዲ አረቢያ ከተሰደዱ በኋላ በቱኒዚያ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዶ በቅርቡ ሌላ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው።
Via:- EthioFm

ጎንደር!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት የተጥራው ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል!
Photo: Getachew Shiferaw
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት የተጥራው ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል!
Photo: Getachew Shiferaw
@YeneTube @FikerAssefa
ከአዲስ አበባ -ደሴ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ሌሊቱን የጣለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ተዘግቷል።
ዛሬ ሌሊት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከአዲስ አበባ- ደሴ ከደሴ እዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ሆራ ድልድይ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቁም ድንጋይ በተባለው ቦታ ዋናው መንገድ በደለል በመሞላቱ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ተዘግቷል። የአካባቢው አስተዳድር የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
ምንጭ:Ethio FM

ጅማ ከተማ በመግባት ብጥብጥና ሁከት ሊያስነሱ ነበር የተባሉ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን፣ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ወጣቶቹ የተያዙት በአይሱዙ ቅጥቅጥ አውቶብስ ተጭነው ወደ ከተማው ሊገቡ ሲሉ ማክሰኞ ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ኬላ ላይ በፀጥታ ኃይል መሆኑን ለሪፖርተር የገለጹት፣ የከተማው የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ሽብሩ ናቸው፡፡ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት ወጥነው ሲንቀሳቀሱ የከተማው መግቢያ ላይ የተያዙትን ወጣቶች በተመለከተ አስቀድሞ ለፀጥታ ኃይል የደረሰ መረጃ በመኖሩ፣ በቀላሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አቶ ተፈራ አስረድተዋል፡፡
‹‹ከተማዋን የጦርነት አውድማ›› ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ለወጣቶቹ ገንዘብ ከፍለው እንዳሰማሯቸው ገልጸዋል፡፡ በቅጥቅጥ አውቶብስ ተጭነው ወደ ከተማዋ ሊገቡ ሲሉ የተያዙት እነዚህ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ በእጃቸው የያዙት ዱላም ሆነ ሌላ መሣሪያ እንዳልነበረ፣ ከእነሱ አንደበት በተወሰደ መረጃ መሠረት ግን ከተማው ውስጥ ከገቡ በኋላ አስፈላጊውን መሣሪያ በተሰጣቸው ገንዘብ ለመግዛት ተስማምተው ጉዞ መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡
Via Reporter

ደሴና ደብረታቦር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምዕመናን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በቤተክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ፣ ግፍ እና መሰደድ በተመለከተ በሰልፉ ድምጽ እያሰሙ ነው፡፡
ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
ከሰዓታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ከባልደረቦቹ ጋር እንዳቀኑ የዘገብን ሲሆን ከዛ በኋላ ግን ከ #ETV ያገኘነውንና ጠ/ሚው ወደ ወላይታ ሶዶ እንዳቀኑ የሚገልፀውን ዜና ካደረስንላችሁ በኋላ #ETV ከፌስቡክ ገፁ ፅሁፉን አስወግዶታል። መረጃው የተሳሳተ ሆኖ ኖሯል ማለት ነው!
የተሳሳተ መረጃ ስላደረስናችሁ ይቅርታ እንጠይቃለን!
@YeneTube @FikerAssefa
የተሳሳተ መረጃ ስላደረስናችሁ ይቅርታ እንጠይቃለን!
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️ለስራ ጉብኝት ካፋ ዞን የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት ላይ ናቸው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ እና የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው አብረዋቸው ይገኛሉ።
Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከከፋ ህዝብ ተወካዮች ጋር በቦንጋ ከተማ ባደረጉት ውይይት ተወካዮቹ ከክልል አወቃቀር: የመንገድ: ውኅ: ጤናና ቤተ መጽሀፍት የመሳሰሉ የመሰረተ ልማት: የሀብት አጠቃቀም: የሥራ አጥነት: የኢንቨስትመንትና ሌሎችም ጥያቄዎች አንስተዋል::
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የተነሱ ጥያቄዎችን በምክክር አቅም በፈቀደ መጠን ለመመለስ ቃል ገብተዋል:: አቅም ያላቸው አልሚ ባለሀብቶች እንዲመጡ መሥራትና በመተባበርና በስልጣኔ የመንቀሳቀስን አስፈላጊነት በማንሳት ተፈጥሮንና ከባቢን ለመንከባከብ ያሳዩትን ቆራጥነት አድንቀዋል::
የክልል አደረጃጀት ለውጥ የሁሉም ጥያቄ መልስ አይሆንም ያሉት ጠ/ሚሩ ተያያዥነት ያላቸው አማራጭ አሰራሮች ማየት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል:: ሲያጠቃልሉም በትብብርና በመደመር በመሥራት ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል::
#PMOEthiopia

የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የጀመረችው አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም ነበር አሉ።
ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የተካሄደውን የግብጽ አቢዮት ተጠቅማበታለች ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በትላንትናው እለት በካይሮ በተደረገ ብሔራዊ የወጣቶች መድረክ ላይ ነው።ግብጻዊያን ከ8 ዓመት በፊት የሆስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመገርሰስ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ይሄነን አጋጣሚ በመጠቀም የህዳሴውን ግድብ መጀመሯን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የጀመረችው አሁን ቢሆን ኖሮ እንከለክላት ነበር ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን የአገሪቱ የህትመት ሚዲያ አህራም ኦን ላየን የተሰኘው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አስነብቧል።ግብጽ በአብዮቱ ጊዜ የሰራችው ስህተት ዋጋ እያስከፈላት ነው ያሉት ፕሬዘዳንት አልሲሲ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት የሚፈልጉ ግብጻያን ወጣቶች እንዳሉም ተናግረዋል።ይሁንን የፕሬዘዳንቱ ንግግር እየደረሰባቸው ያለውን ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ነው የሚል ትችት እየደረሰባቸው ይገኛል።
ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ ለአገር ውስጥ ፖለቲካ የመጠቀም ፍላጎት ስላላቸው ነውም እየተባሉ ይገኛሉ።ፕሬዘዳንት አልሲሲ ስልጣናቸውን እስከ 2034 ድረስ የሚያራዝምላቸውን ህገ መንግስት በአገሪቱ ፓርላማ ማጸደቃቸውና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ትችቶችን በማስተናገድ ላይ ናቸው።ግብጽ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ጊዜ ወደ ሰባት ዓመት ከፍ ይበልልኝ፣የግድቡን ሁኔታ የሚከታተል በካይሮ እና በአዲስ አበባ ቢሮ ይከፈትና ሌሎች ጥያቄዎችን ማንሳቷ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የግብጽን አዲስ አቋም ፈጽሞ እንደማትቀበልና ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የከፋ ጉዳት እንደማያደርስ በተደጋጋሚ አስታውቃለች።የኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን ብሔራዊ የቴክኒክ አማካሪ በያዝነው ሳምንት በካይሮ ወይም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በኢትዮጵያና ሱዳን በተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል።
ባሳለፍነው ሳምንት የሱዳይ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ከአዲሷ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጋር ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በካርቱም ተወያይተዋል።ከዚህ በፊት ሱዳንና ኢትዮጵያ በህዳሴው ገድብ ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ያልተመቻት ግብጽ ውይይቱን በራሷ ፍላጎት ለማስኬድ የተለያዩ አማራጮችን በመከተል ላይ ትገኛለች።
Via Ethio FM

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ባለፈው ሳምንት ከዚህ አለም በሞት በተለዩት በቀድሞው የዝምባቢዌ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ የስንብት ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ፡፡
በሀራሬ በሚገኘው ብሄራዊ የስፖርት ስታዲየም በተካሄደው ስነ ስርዐትላይ የሀገራትና የመንግስታ መሪዎች እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝደንቶችና በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገኝተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሽዎች የሚቆጠሩ የነጻነት ታገዮችን በማሰልጠን ዝምባቢዌ ከቅኝ ግዛት እንድትላቀቅ የራሷን ሚና መጫወቷ ይታወቃል፡፡ ይህ ሁኔታም በተለይም ሮበርት ሙጋቤ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ቁርኝት ጥብቅ እንዲሆን አድርጓል፡፡
Via President Office