YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለባህርዳር ዩንቨርስቲ ነባር መደበኛ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ

የ2012 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 12 እና 13 በዩንቨርስቲው ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር በመቅረብ እንድትመዘገቡ ተብላቿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የ10ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤት ከደቂቃዎች በኋላ ይፋ ይሆናል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ዛሬ መስከረም 2/2012 ከ10 ሠዓት ጀምሮ እንደሚለቀቅ ተገለፀ፡፡የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የዐስረኛ ክፍል ውጤት ዛሬ መስከረም 02/2012 ዓ.ም ከ10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚለቀቅ ገልጾ ተማሪዎች በኤጀንሲው ድህረ ገጽ
www.neaea.gov.et/app . neaea.gov.et ወይም በአጭር የጽሁፍ መልእክት 8181 ላይ ID- በማለት አድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የፈተና ውጤትን ይፋ አደረገ።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረ እግዚአብሄር በ2011 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ፈተና ዙሪያ ከፋና ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ከተፈታኞቹ መካከልም #ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች #አራት_ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

75 ነጥብ 5 በመቶ ያህል ተፈታኞች 2.0 እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያመጡ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።2.0 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። ከተፈታኞቹ መካከል ወንዶች 682 ሺህ 572 ሲሆኑ 572 ሺህ 997 ሴቶች ናቸው፡፡ከእነዚህ መካከል 894 ሺህ 318 በመደበኛ፣ 354 ሺህ 782 በግል እና 6 ሺህ 469 ደግሞ በማታው ክፈለ ጊዜ ተፈታኞች እንደነበሩ ነው የተገለጸው።

በዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን የኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል።ባለፈው አመት ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡት ተፈታኞች 71 በመቶ መሆናቸው የሚታወስ ነው።ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገጽ http://
app.neaea.gov.et ወይም www.neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብለው የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል!

ውጤታቹን በኤጀንሲው ድረ ገጽ

http://app.neaea.gov.et ወይም www.neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብላችሁ የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ችላላችሁ ተብላቿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል!

ውጤታቹን በኤጀንሲው ድረ ገጽ

http://app.neaea.gov.et ወይም www.neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብላችሁ የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ችላላችሁ ተብላቿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰልፉ ተራዝሟል!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዳክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው በሚል መስከረም 4 ቀን ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙ ተገልጿል።

የሰልፉ አስተባባሪዎች ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው። ሰልፉም ወደ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም መዘዋወሩን አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል።

ምንጭ: ኢትዮ ኤፍ ኤም
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እሁድ ወደ ካፋ ዞን ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። መንግሥት ጉዞ መኖሩን ከመግለፅ በቀር ያለው ነገር ባይኖርም ቦንጋ «እንኳን ወደ ቤተሰብዎ በደህና መጡ» ለማለት መዘጋጀቷን የሚጠቁሙ ምስሎች በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ተሰራጭተዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
"እነማን እንደተያዙ አናውቅም"--- አቶ ዳውድ ኢብሳ

ከትናንት ምሽቱ የቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ የኦነግ- ሸኔ አባላትና ሌሎች ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው ናቸው የተባሉ 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰማሁና ዛሬ ማምሻውን አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ደወልኩ። መልሳቸው የነበረው:

"እነማን እንደተያዙ አናውቅም። መረጃውን እንደሁሉም ሰው ከሚድያ ነው የሰማሁት። እርግጥ ነው በየግዜው ተያዙ እየተባለ ይወራል፣ እኛም ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖብናል። ስለዚህ ስለተባለው ነገር አላውቅም።"

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ውጤት እንዴት እንደሚሰላ እየጠየቃችሁ ላላችሁ :

A=4
B=3
C=2
D=1
F=0

ነጥብ የሚይዝ ሲሆን የሂሳብ እንግሊዝኛና ሲቪክ ውጤታችሁ ላይ ካመጣችሁት የተሻለውን 4 የትምህርት አይነት ውጤት በመውሰድ ከላይ በተቀመጠው መሠረት የሰባቱን ውጤት ደምራችሁ ለ7 በማካፈል ውጤታቹን ማወቅ ትችላላችሁ።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በደቡብ ክልል የደምባ ጎፋ ወረዳ አስተዳደር አምቡላንስ ወደ ሰራተኛ ማጓጓዣ ቀይሯል፤ አስተዳደሩ «በወረዳው ካሉ አምቡላንሶች አንዷ በውስጧ የሚገኙ የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪ ቁሳቁሶችና የአደጋ ጊዜ መብራት ተነስቶ ...ወደ ሰርቪስ እንድትቀየር» ወስኗል። Via Eshete Bekele @YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የደምባ ወረዳ አምቡላንስ ለማጓጓዣ እንድትውል የተላለፈውን ውሳኔ ማጣራት መጀመሩን አስታወቀ። አንድ ኮሚቴ ወደ ወረዳው መላኩን ያስታወቀው ቢሮው «መስከረም 3 ቀን 2012 ጉዳዩን አጣርቶ የማረሚያ ዕርምጃ» ይወሰዳል ብሏል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ለመስከረም 4/2012 ዓ.ም የተጠራው ሰልፍ ለሌላ ጊዜ ተራዘመ።

የፊታችን እሁድ እንዲካሄድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የተጠራው ሰልፍ ለሌላ ጊዜ ተራዘመ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው በሚል መስከረም 4/ 2012 ዓ.ም ሰልፍ ተጠርቶ ነበር።በቤተ ክርስቲያኗ የተጠራውን ሰልፍ የሚያስተባብሩ 10 አስተባባሪ ማኅበራት ሰብሳቢ ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ የእሁዱ ሰልፍ ቀነ ገደብ በማስቀመጥ መራዘሙን ተናግረዋል። ሰልፉ ቤተ ክርስቲያኗ እና ምዕመኑ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸውን ተከትሎ መጠራቱንም አስታውሰዋል።

አሁን ላይም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ መንግስት ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግና "ችግሮችን ተነጋግረን እንፈታለን" በማለቱ ሰልፉ ለጥቅምት 30/2012 ዓ.ም ተራዝሟል ብለዋል።
ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ጋር በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ሰብሳቢው በሚደረጉ ውይይቶች የሚደረስባቸው ስምምነቶች በየሁለት ሳምንቱ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ገልጸዋል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በጋምቤላ ክልል ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች የገደሉ ታጣቂዎችን መንግሥት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቀ።

አክሽን አጌይንስት ኸንገር የተባለው ዓለም አቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ጥቃት የተፈጸመባቸው በጋምቤላ ክልል ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ከሚኖሩበት ኙንዬል ከተባለ የመጠለያ ጣቢያ (Nguenyyiel Refugee Camp) ሥራቸውን አጠናቀው በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል። በጥቃቱ የመስክ ሰራተኛ እና አሽከርካሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የግብረ-ሰናይ ሰራተኞች መሆኑን የሚጠቁም ምልክት በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ከ45 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት:

«ሕዝብ ወኪሎቹን መርጦ ሕገ-መንግሥቱ እስኪታወጅ እና መንግሥት እስኪቋቋም ድረስ ወታደራዊው ደርግ ሥልጣን ይዞ አገሪቱን ይመራል»

ደርግ በኢትዮጵያ ራዲዮ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም.

@YeneTube @FikerAssefa
ከ25 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን:

ዕውቁ አሜሪካዊ ራፐር ቱፓክ ሻኩር(2Puc) ላስ ቬጋስ ኔቫዳ ሳለ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል 6 ቀን ቆይቶ ህይወቱ ያለፈው።

ራፐሩ በወቅቱ ከነበሩት ተፅዕኖ ፈጣሪ ጥቁር ሰዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ
ፖሊስ ያወጣውን Postmortem በመጠራጠር የሞቱ ዜና በርከት ላሉ የሴራ ፅንሰ ሃሳቦች ተጋልጦ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
በሚቀጥሉት አስር ቀናት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ዝናብ ይጥላል፡፡

በሚቀጥሉት አስር ቀናት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ እንደሚጠበቅ የብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።የክረምት ዝናብ ሰጪ የሜቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በአገሪቱ ሰሜንና ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች እየተዳከመ እንደሚመጣ የሚጠበቅ ቢሆንም በመጪዎቹ አስር ቀናት ግን በርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች ዝናብ ይኖራቸዋል ሲል ኤጀንሲው አመልክቷል።

በዚህ መሰረት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጅማ፣ ኢሊባቡር፣ ሁሉም የሸዋ ዞኖች፣ አዲስ አበባ፣ አማራ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ የባህርዳር ዙሪያ፣ አዊ ዞንና የሰሜን ሸዋ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ከዚህም ሌላ አብዛኛው የትግራይ ክልል ዞኖች፣ የጋምቤላና የቤንሻንጉል ዞኖች፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የከፋ፣ የቤንቺ ማጂ፣ የጉራጌ፣ የሐዲያ፣ የወላይታ፣ የዳውሮ፣ የጋሞ ጎፋ፣ የሲዳማ ዞኖችም በተመሳሳይ ዝናብ ይኖራቸዋል። የሚጠበቀው ዝናብ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ለቅጽበታዊ ጎርፍ መከሰት መንስኤ ሊሆን ይችላል ሲልም ኤጀንሲው አመልክቷል።

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa