YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
ጎንደር ላይ በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የተጠራው ሰልፍ እንደሚካሄድ ሰምተናል!

በቤተክርስቲያኗ እና በእምነቱ ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ ታቅዶ በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው ሰልፍ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ለጥቅምት 30 መራዘሙ ይታወሳል። ከዚህ ጋር ተያይዞግን ጎንደር ላይ መስከረም 4/2012 ዓ.ም ለማካሄድ የታቀደው ሰልፍ ላይ የተደረገ የፕሮግራም ለውጥ እንደሌለ ለፖሊስ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንደተሰጣቸው የሰልፉ አስተባባሪዎች ነግረውናል።


""ከአዲስ አበባውን ሰልፍ መራዘም ጋር ተያይዞ ጎንደር ላይ የሚካሄደው ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በማያያዝ ብዥታ መፈጠር አይኖርበትም::ሰልፎቹ የአላማ ተመሳሳይነት እንጂ በአንድ አመራር ስር አይደሉም::በመሆኑም ሰልፉ አስፈላጊዉን ዝግጅት በማጠናቀቅ በታሰበለት የጊዜ ሰሌዳ እና እቅድ ይካሄዳል:: ተጨማሪ ስለዝርዝር ሁኔታዉ ዛሬ ህብረቱ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል::" የሰልፉ አስተባባሪዎች የነገሩን ነው።

መግለጫውን ተከታትለን አዲስ ነገር የሚኖር ከሆነ እናሳውቃቿለን።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ለትምህርት ቤቶች እድሳት 833 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ለማደስ 833 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን እና ኮንትራክተሮቹም በዕጣ እና በቁርጥ ሒሳብ ውሳኔ መመረጣቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሕንፃ ገብረስላሴ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የከተማ አስተዳደሩ 356 የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ሲያድስ የቀድሞ ተማሪዎች ኅብረተሰቡ እና ባለሀብቶች ደግሞ 8 ትምህርት ቤቶችን አሳድሰዋል።

ቢሮው በበኩሉ ትምህርት ቤቶቹን ለማሳደስ ከ655 ኮንትራክተሮች ጋር በመዋዋል አሰርቷል። ለእድሳቱ የነበረው ጊዜ ሁለት ወራት ብቻ በመሆኑ ለተደራጁ ወጣቶች ብቻ የቁርጥ ሒሳብ መመሪያ በመከተል እና የዕጣ መረጣ በማካሄድ ሥራው እንዲከናወን ተደርጓል።እንደ አቶ ሕንፃ ገለጻ፤ የኮንትራክተሮች መረጣው ለደረጃ 7 እና 8 ኮንትራክተሮች ብቻ የተሰጠ ዕድል ነው። በሕዝብ ፊት የተለያዩ ኃላፊዎች በተገኙበት የዕጣ አወጣጥ ሥነሥርዓት ተካሂዶ የተደራጁ ወጣቶች ሥራውን እንዲያከናውኑ ተደርጓል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from KIDUS.M
Start your Journey to Work In Europe Now.
Jawisaro Travel Consultancy has started new registration On Work Visa in Europe
1) Work Visa in Europe And In Canada
⭕️ No requirement
⭕️ Visa within 2 month
⭕️ Monthly salary with over
40,000Birr
2) Student visa In Canada🇨🇦🇨🇦 is also available
With Very very Cheap Agent fee ❗️❗️
Deadline is soon come fast and register. Special Offer for New Graduates
As we always say it is Company with no limitation JUST CONTACT US
+251932516194
+251988058420
Join our Channel @Jah_Travel_Agency
There’s a lot to explore around you. Download Ahun, get the best out of your city!

Now available on the Play Store and App Store!!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahun.android


https://apps.apple.com/ke/app/ahun/id1474285014


Join us on telegram

—- https://tttttt.me/Ahun_appc

Follow us on Instagram

https://instagram.com/ahun.app?igshid=ab6oe4ob8485
⬆️⬆️
ለተማሪዎች የተዘጋጁት ዩኒፎርሞች እና የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የትምህርት ቤቶች እድሳትም ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።በርክክብ ሥነሥርዓቱ የአገራችን ታላላቅ ከያንያን አና የተማሪዎች ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት አስቸኳይ ሁሉን አቀፍ የውይይት መድረክ እንዲያመቻች ተጠየቀ!

የአገሪቱን ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል አስቸኳይ ሁሉን አቀፍ አገራዊ የውይይት መድረክ መንግስት እንዲያመቻች የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) ጥሪ አቀረበ፡፡ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎችበማንነታቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደል፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀል፣ ንብረትን መነጠቅና የጅምላ እስር በሰፊው እያጋጠማቸው መሆኑን የጠቆመው ኢሃን፤ በሌላ በኩል ታይቶ በማይታወቅ የኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ ነው ብሏል፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች መደራረባቸውን ተከትሎም ሕዝብ በመንግስት ላይ ያለው እምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ በመሄድ ላይ ነው ብሏል ንቅናቄው በመግለጫው፡፡ በአገሪቱ ባሉ የፖለቲካ ቡድኖች መካከልም ያለው አለመተማመንና ጥርጣሬ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የጠቆመው ኢሃን፤ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከልም የተፈጠረው መከፋፈልና ተቃርኖ መንግስትን በጋራ ለመምራት ከማያስቻላቸው ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡በእነዚህ ሁኔታዎች የተነሳም የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ በቀጣይ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ለመተንበይ አዳጋች የሆነበት ደረጃ ላይ መድረሱን፣ እነዚህ ችግሮችም የቅርብ ጊዜ አመራሩ የፈጠራቸው ሳይሆን ለረጅም ጊዜ የተከማቹና ስር የሰደዱ የአገሪቱ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ምስቅልቅሎች መገለጫ መሆኑን ንቅናቄው አመልክቷል፡፡

እነዚህን የአገሪቱን ህልውና በእጅግ እየተፈታተኑ ያሉ ችግሮችን ኢሕአዴግ ብቻውን የመፍታት አቅም እንደሌለው የገለፀው ንቅናቄው፤ የአገሪቱን ተደራራቢ ችግሮች ስትራቴጂያዊ በሆነ መልኩ በየደረጃው ለመፍታት የሚቻልበትን መንገድ በጋራ ለመቀየስ መንግስት አስቸኳይ ሁሉን አቀፍ አገራዊ የውይይት መድረክ እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡ አገሪቱን ካንዣበበው የህልውና አደጋ ታድጎ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገርም ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ቀዳሚ መፍትሄ ነው ብሎ እንደሚያምንም ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ በቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አባላት የተቋቋመና በኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሚመራ የፖለቲካ ድርጅት ነው፡፡

Via Addis Admas
@YeneTube @FikerAssefa
የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በቀድሞ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የስንብት ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ዚምባቡዌ ዋና ከማ ሀረሬ እየገቡ ነው።

ዚምባቡዌን ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስተዳደሩት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ይፈጸማል።

ከቀብር ስነ ስርዓታቸው በፊት በሚደረገው የስንብት መርሃ ግብር ላይም የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳን ጨምሮ ከ12 ባላይ የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via:- FBC
@Yenetube @FikerAssefa
ኤርትራ እና ሱዳን የጸጥታ እና ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።

ሁለቱ አገሮች ወዳጅነታቸውን ለማጠናከር የተስማሙት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን በሚያደርጉት ጉብኝት ላይ ነው። ለሁለት ቀናት ጉብኝት የሚያደርጉት ኢሳያስ ኻርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሉቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርሐን ተቀብለዋቸዋል።

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ኦስማን ሳሌሕ እና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ ወደ ኻርቱም ካቀናው ልዑካን ቡድን መካከል እንደሚገኙበት የኤርትራ ማስታወቂያ ምኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። ማስታወቂያ ምኒስትሩ እንዳሉት ሁለቱ መሪዎች የምጣኔ-ሐብት፣ የንግድ፣ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ የጸጥታ እና ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ከስምምነት ደርሰዋል። ኤርትራ እና ሱዳን ባለፈው ሰኔ መጨረሻ የተዘጉ ድንበሮቻቸውን ለመክፈት መስማማታቸው አይዘነጋም።

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
በሳኡዲአረቢያ ሁለት የነዳጅ ማጣሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው በአነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ሲሆን÷ አብቃይቅ እና ክሁራይስ በተባሉ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ አሳት መነሳቱ ተነግሯል፡፡

የነዳጅ ማጣሪዎቹ በእሳት ሲጋዩ የሚያሳዩ የምስልና ድምጽ ምስሎች በመገናኛ በዙሃን መለቃቃቸውንም ነው የተገለጸው፡፡

እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

በየመን በኢራን የሚደገፈው የሃውቲ አማጽያን ጦር ቃል አቀባይ ለጥቃቱ 10 አነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማሳመራቱን ይፋ አድርጓል፡፡

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
የኢዜማ ፖርቲ ሴቶች ኮሚቴ በተፎካካሪ ፖርቲ አመራሮች (ፕ/ር መራራ ጉዲና) ቤት በመሄድ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል:: ይህ አንዱ የአብሮነት መገለጫ ባህላችን ነው::

ኢዜማ በፕ/ሮ መራራ ጉዲና ቤት

መረጃውን ያደረሰን አክቲቪስት ናትናኤል መኮንን ነው።
@YeneTube @Fikerassefa
#Ethiopia የኢዜማ ፖርቲ ሴቶች ኮሚቴ በተፎካካሪ ፖርቲ አመራሮች ቤት በመሄድ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል:: ይህ አንዱ የአብሮነት መገለጫ ባህላችን ነው::

ኢዜማ በፕ/ሮ በየነ ፔጥሮስ ቤት

መረጃውን ያደረሰን አክቲቪስት ናትናኤል መኮንን ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
በሀዋሳ ከተማና አካባቢዋ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 70 የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው ተይዘው የህክምና ዕርዳታ ማግኘታቸው ተገለጸ፡፡

#hawassa
@YeneTube @Fikerassefa
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በየአጥቢያዎቹ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ጸሎተ ምህላ አወጀ፡፡

ሀገረ ስብከቱ ለመስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ከፊታችን ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ጸሎተ ምህላ አውጇል፤ ለመስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመላከተው የፀሎተ ምህላው ዓላማ በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚደርሰውን መከራ፣ ግፍ እና መሰደድ አስመልክታ ለፈጣሪዋ መልዕክት ለማቅረብ ነው፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫውን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም ኦርቶዶክስ ለሀገር ባለውለታ መሆኗ ተረስቶ እና ተዘንግቶ ቤተ ክርስቲያኗ ለጥቃት፤ ምዕመኖቿ ለእንግልት እየተጋለጡ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የአበበ ቢቂላ ስታዲዮም በቅርቡ ስራ ይጀምራል

በእድሳት ምክንያት ላለፉት ሁለት ዓመታት አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየው የአበበ ቢቂላ ስታዲዮም አሁን ላይ ዕድሳቱ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ።

በተያዘው አዲስ ዓመት የውድድር ዘመን እስከሚጀመርበት ጊዜ ድረስ ስታዲዮሙ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል።

የአበበ ቢቂላ ስታዲዮም በ1995 ዓ .ም ስራ ጀመረ ይሁን እንጂ ደረጃውን የጠበቀ አልነበረም።

አሁን ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከፍተኛ በጀት በመመደብ ለስታዲዮሙ ሙሉ እድሳት አድርጓል።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
ጎንደር ላይ በነገው ዕለት የሚካሄደውን ሰልፍ አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫው የሰልፉ አላማ የተብራራ ሲሆን ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት እንደተደረገ ለማወቅ ችለናል።የሰላማዊ ሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በስልክ እንደገለፁልን ከከተማው ከንቲባና የፀጥታ አካላት ጋር ጭምር ውይይት እንደተደረገ ምንም እንኳን ሰልፉ እንዲራዘም ፍላጎት ቢኖራቸውም በቂ ዝግጅት እንደተደረገ በመረዳታቸው እንደፈቀዱ የፀጥታ አስከባሪዎችንም እንደሚመድቡ ገልፀውልናል ብለውናል።

ሰላማዊ ሰልፉ ከጠዋቱ 1:30 - 5:00 የሚዘልቅ ሲሆን መነሻው መስቀል አደባባይ ነው፣ ከዛም በአርበኞች አደባባይ አድርጎ እስከ ከንቲባ ጽ/ቤት ተደርሶ እንደገና በመመለስ መስቀል አደባባይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ለዚህም የእምነቱ ተከታዮች በክርስቲያናዊ አለባበስ በስፍራው ተገኝተው ለቤተ ክርስትያኒቱ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ አክለው ገልፀውልናል።

ፎቶ:የሰልፉ መርሃ ግብር
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2