YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በመላው አፍሪካ ጨዋታ 10,000 በሴቶች ወርቅ፣ ብር፣ ነሀስ

🥇 ፀሀይ ገመቹ
🥈 ዘይነባ ይመር
🥉 ደራ ዲዳ

#አረንጓዴው_ጎርፍ
@YeneTube @FikerAssefa
ሲፋን ሐሰን አሸንፋለች!

በዙሪክ የዳይመንድ ሊግ በሴቶች 1500 ሜትር ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሐሰን አሸንፋለች ሲፋን ውድድሩን በ3.57.08 ጨርሳለች #ገንዘቤ_ዲባባ 4ኛ፣ #ጉዳፍ_ጸጋዬ 9ኛ እንዲሁም #አክሱማዊት_አምባዬ 13ኛ ሆነው ጨርሰዋል።

Via:- እሸት በቀለ
@YeneTube @FikerAssefa
ዩጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ የዳይመንድ ሊግ 5000 ሜትር ውድድርን በአሸናፊነት ጨርሷል። ውድድሩን ያጠናቀቀበት 12.57.41 የግሉ ምርጥ ሰዓት ነው።

#ሐጎስ_ገብረሕይወት 2ኛ፣ #ጥላሁን_ኃይሌ 4ኛ፣ #ሰለሞን_ባረጋ 5ኛ #ዮሚፍ_ቀጀልቻ 6ኛ ሆነው ጨርሰዋል
@YeneTube @FikerAssefa
"በአዋጅ እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተሰጠ መብት እና ስልጣንን በፌስቡክ ለመሻርና ህዝብን ለማወናበድ በሚሞክሩ ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል።" ABH Partners

ድርጅቱ ስሜ ያለ አግባብ ጠፍቷል ሲል ከላይ የምታዩትን መግለጫ አውጥቷል። 176.3 ሚልዮን ብር ካሳም ጠይቋል ።

@YeneTube @FikerAssefa
”ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ሥርዓት ካልተበጀላቸው ለአገር ከፍተኛ አደጋ ይሆናሉ‘ - ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር

የአገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ በየአካባቢው ያሉ በግለሰብ የሚመሩ የወጣት ኢመደበኛ አደረጃጀቶች ተቋማዊ እንዲሆኑ ስርዓት ካልተበጀላቸው ለአገር ከፍተኛ አደጋ እንደሚሆኑ ተጠቆመ።

የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነህ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ መንግስት በቅንነት ሽማግሌዎችን እና የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትን እያቀረበ ነው። አንዳንድ የምሁራን ማህበር እየተባሉ ኢመደበኛ በሆነ መልኩ የሚሳተፉ አሉ። በተለያዩ አካባቢዎች ሌሎችም መደበኛ ያልሆኑ የወጣት አደረጃጀቶች አሉ። ወደፊትም ሌሎች ሊፈጠሩ ይችላሉ።

ነገር ግን ከማናቸውም አደረጃጀቶች ጀርባ የግለሰቦች ፍላጎቶች መኖራቸው መዘንጋት የለበትም። ያንን መዘወር የሚፈልጉ የፖለቲካ ሃይሎች ይኖራሉ። እነዚህ አደረጃጀቶች ከጠነከሩ ማዕከላዊ መንግስቱ ያዳክማሉ።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
#update

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልኡካቸው የኢንቨስትመንት እድሎችንና ጅማሮዎችን ማበረታታትን በተመለከተ ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡

የመጀመሪያው ውይይት ከጃፓን የውጪ ንግድ ድርጅት (ጄትሮ) ሊቀመንበር ጋር ሲያካሂዱ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት ጄትሮ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያደረገች ላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ይችላል፡፡ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸውን ለማስፋፋትና ቀጣናዊ ውህደትን በሚያበረታታው የመደመር እሳቤ መሰረት የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮችን ለመርዳት እንዲነሱ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በጎአድራጊና በሳሳካዋ አፍሪካ ስር የኢትጵያን የግብርና ዘርፍ ድጋፍን የሚመራውን የኒፖን ፋውንዴሽን ሊቀመንበር የሆኑትን ዮሄ ሳሳካዋን አነጋገሩ፡፡ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በተለይም ጃፓን ካላት የተፋሰስ ወንዞችን ማጽዳት ስኬት በመነሳት የአዲስ አበባ ወንዞችን የማጽዳትና የከተማ ግብርና ልማት ዙሪያ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እንዲሁም የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ፕሬዝዳንት ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ሰላምን ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት በነበራቸው ውይይት ወቅት አድንቀዋል፡፡ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በኢኮኖሚ ማሻሻያው ቅድሚያ የሚሳጣቸውን በማጉላት ጃይካ እነዚህኑ የትኩረት አቅጣጫዎች በማሳካት፣ በሰው ኃብትና ኢንዱስትሪ ልማት ዙሪያ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በፀደቀው የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የስነ ምግባር ደንብ አዋጅ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየመከሩ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ባፀደቀው የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የስነ ምግባር ደንብ አዋጅ ላይ እየመከረ ነው።

ምክር ቤቱ አዋጁን በተመለከቱ አተያዮች ፣ አረዳድና አመለካከቶች ላይ እመክራለሁ ያለ ሲሆን ከህግና ስርዓት ያፈነገጡ ግንኙነቶችን በማድረግ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ በሚሞክሩ ፖርቲዎች ዙሪያ ለመምከር የሚያስችል አጀንዳ ስለመያዙም አስታውቋል።

Via:- ኢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ-ጃፓን ቢዝነስና ኢንቬስትመንት ፎረም ተካሄደ።

በዮኮሃማ ጃፓን እየተካሄደ ካለው 7ኛው የቲካድ ስብሰባ ጎን ለጎን ሁለተኛው የኢትዮ-ጃፓን የቢዝነስ ፎረምና ኤግዝቢሽን ተካሂዳል።

በዚሁ ፎረም 180 የጃፓን ባለሃብቶች እንዲሁም 43 የኢትዮጵያ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

በፎረሙ መክፈቻ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን እንዲሁም የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት (ጄትሮ) ፕሬዚዳንት ንግግር አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ የጃፓን ባለሃብቶችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን አንስተው ፤ ባለሃብቶቹ ይህንን ምቹ ሁኔታ እንዲጠቀሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን በበኩላቸው፣ ቶኪዮ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ የጃፓን ባለሃብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከተለያዩ ጃፓን ኩባንያዎችና ተቋማት ለሚደረግላቸው ድጋፍ በማመስገን ኤምባሲው ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ያለውን አመቺ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲጠቀሙ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደርም ለተሳታፊዎች የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አመቺነት አስመልክቶ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት (ጄትሮ) ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የተሻሻለ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዳሉ እንደሚያውቁና ይህንንም በየጊዜው ለአባላቶቻቸው እንደሚያስተዋውቁ ገልፀል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ኢንቨሽትመንት ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአፍሪካ ልማት ዙሪያ ምክክር የሚያደርገው የቶኪዮ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ (Tokyo International Conference on Africa Development) TICAD እ.ኤ.አ ከ1993 ጀምሮ አፍሪካ ከድህነትና ኃላቀርነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ በጃፓን ጠንሳሽነትና አመራር ለአፍሪካ ልማት የሚካሄድ ኮንፈረንስ ሲሆን በጥምር አዘጋጅነት የአለም ባንክ፣ የተ.መ.ድ ልማት ድርጅት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ:- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኢቦላ የሞቱት ሰዎች ቁር 2 ሺህ መድረሱ ተገለጸ፡፡

ቁጥሩ ቫይረሱ እንደገና በተቀሰቀሰ በአንድ አመት ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሀገሪቱ መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡

ሕይወታቸው ካለፈው ዜጎች በተጨማሪ ከ3 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸውም ይነገራል፡፡
ቫይረሱ ባለፈው አመት ነሃሴ ወር በድጋሚ ከተቀሰቀሰ በኋላ የበርካታ ሰወችን ሕይወት መቅጠፉ ተነግሯል፡፡

ከአውሮፓውያኑ 2013 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት ውስጥም ከ11 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ ሕይወታቸው ማለፉን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ባሳለፍነው ረቡዕ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወደ ኡጋንዳ የገባች የ9 ዓመት ልጅ ኡጋንዳ ወሰን ላይ በተደረገላት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘበት ተገልጿል፡፡
ከእናቷ ጋር ወደ ኡጋንዳ የገባቸው ይህች ህፃን አሁን ላይ ከቤተሰብ ተነጥላ ሆስፒታል እንደምትገኝም ነው ዘገባው የሚያስረዳው፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ለመጨመር ማቀዱን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ከዚህ ባለፈም ወደ ጃፓኗ ቶኪዮ የቀጥታ በረራ ለመጀመር ማቀዱንም ዋና አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተናግረዋል።ወደ ቻይና የተለያዩ ከተሞች የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ በ50 በመቶ በማሳደግ ከ35 በላይ እንደሚያደርግም ነው ዋና ስራ አስፈፃሚው የተናገሩት፡፡ወደ ቻይና የተለያዩ ከተሞች የሚደረጉ በረራዎችን ለማሳደግ የተፈለገው የቻይና ባለሃብቶች፣ የንግድ ሰዎች እና ጎብኝዎች ወደ አፍሪካ የመሄድ ፍላጎታቸው ከፍ በማለቱ ነው ተብሏል፡፡እንዲሁም አየር መንገዱ ወደ ጃፓን ቶኪዮ በሳምንት አምስት ቀን የሚያደርገውን በረራ በፈረንጆቹ 2021 ወደ ሰባት ከፍ ለማድረግ አቅዷል፡፡ወደ ጃፓን ቶኪዮ የሚደረገው ይህ በረራ የቀጥታ በረራ እደሚሆንም ታውቋል።

ምንጭ፦ asia.nikkei.com
@YeneTube @FikerAssefa
የስኳር ኮርፖሬሽን ምንም ያወጣሁት የአክሲዮን ሽያጭ የለም አለ።

የኢፌዲሪ ስኳር ኮርፖሬሽን በመንግሥትም ሆነ በኮርፖሬሽኑ በኩል ምንም አይነት ለሽያጭ የወጣ የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የአክስዮን ሽያጭ አለመኖሩን አስታወቀ። ኮርፖሬሽኑ እንዳስታወቀው ‹‹ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር›› የተባለ ኩባንያ በመገናኛ ብዙኃን ከሚያስነግረው ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ በኅብረተሰቡ ዘንድ ኮርፖሬሽኑ አክስዮን እንደሸጠ ተደርጎ ብዥታ በመፈጠሩ እና ይህንም ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች ወደ ኮርፖሬሽኑ በመምጣት አላስፈላጊ ጫና እየተፈጠረበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይህን መግለጫ ለመስጠት እንደተገደደ አስታውቋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
Sport!!
Loza Abera has officially joined Maltese Top flight side Birkirkara.
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Sport!! Loza Abera has officially joined Maltese Top flight side Birkirkara. @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊዋ ሎዛ አበራ የማልታ ሊግ ሻምፒዮን የሆነውን ቢርኪርካራ በአንድ ዓመት ውል ፈርማለች።

ከስዊድን ያልተሳካ ሙከራ በኃላ በግማሽ ዓመት ለአዳማ ከተማ የፈረመችው ሎዛ ከአዳማ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ማንሳት ችላለች።
በሃዋሳ ከተማ የጀመረው የሎዛ የእግር ኳስ ህይወት ደደቢት፣አዳማ አቋርጦ ቢርኪርካራ ላይ ማረፍያውን አድርጓል።

የማልታን ሊግ ለ8 ጊዜ ማንሳት የቻለው ቢርኪርካራ የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑ ተከትሎ በቀጣይ ዓመት በቻምፒዮንስ ሊግ አውሮፖ ሚሳተፍ ይሆናል።

Via :- Hatrick
@YeneTube @FikerAssefa
#ሰበር _ዜና_ሲአን

“በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚወጣ ሌላ የህግ ማዕቀፍ ተቀባይነት አይኖረውም” አለ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ደስታ ሌደሞ፡፡

የዞኑ አስተዳደሪ ይህንን ያሉት⬆️

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው፡፡ በመግለጫቸውም በትላንትናው ዕለት ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝብ ህዝበ ውሳኔ የሚካሄድበት ቀን በማሳወቁ መላውን የሲዳማ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡

ሀዋሳ ከተማና የሲዳማ ህዝብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ነው ያሉት አቶ ደስታ ሌደሞ በትላንትው ዕለት ምርጫ ቦርድ እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን ውስጥ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሌላ የህግ ማዕቀፍ ይዘጋጃል ለተባለው ከህግ-መንግስቱ ውጪ የሆነ ሌላ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል፡፡

አቶ ደስታ አክለውም ከሲዳማ ህዝብ ክልል ጥያቄ ጋር ተያይዞ ሌላ የውይይት መድረክ ይኖራል ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ እኛ አሁን እንደ ዞን አስተዳደር ከህዝበ ውሳኔ /ሪፍረንደም/ ዙሪያ ውጪ ሌላ ከክልል ጉዳይ ጋር ተያይዞ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ሀሳብም ዕቅድም የለንም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ቦርዱ ባወጣው ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዕድሚው ለመራጭነት የደረሰ ህብረተሰብ ክፍል ከወዲሁ እራሱን እንዲያዘጋጅም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via:-SMN
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም ተቋሙን ተወዳዳሪ፣ ብቁ እና ተመራጭ ማድረግ የሚያስችለውን የሶስት ዓመታት የስራ ስልት ይፋ አደረገ።

ስትራቴጂው ከሀምሌ 2011 እስከ ሰኔ 2014 የሚያገለግል መሆኑን ዛሬ አስታውቊል።

የተቋሙም መዳረሻ ያመላክታል የተባለው ይህ ስልት ተቋሙን በተያዘው የመንግስት የበጀት አመት ላይ የባለቤትነት ለውጥ የማያመጣ እና በመንግስት ይዞታ ስር የሚቆይ እንደሆነም አስቀምጧል።

ይሁንና በሚቀጥሉት የስትራቴጅው አመት ላይ የተቋሙ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ ሌሎች አካላት እንዲሳተፉበት ይደረጋል ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ አሳውቀዋል።

ኢትዮ ቴሎኮም የአመቱን የቢስነስ እቅድ ሲያስቀምጥም የደንበኞቹን ቁጥር ከ43.6 ሚሊዮን ወደ 50.4 ፣ የገቢ መጠኑንም በ2011 መጨረሻ አሁን ካለበት 36.3 ቢሊዮን ወደ 45.4 ቢሊዮን ለማሳደግ ማቀዱን አመልክቷል።
ተቋሙ እንዳለው የደንበኞች ፍላጎት ከድምጽ አገልግሎት ይልቅ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ እያደገ በመምጣቱ የሚከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች በዚሁ ላይ የሚያተኩር ይሆናል።

የገቢ ምንጬንም አሁን ካሉ አገልግሎቶች በላይ በመሻገር ሌሎች አገልግሎቶችን በማቅረብ ለማሳደግ ወስኗል ኢትዮ ቴሌ ኮም።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
የዶ/ር አርከበ እቁባይ እጅ ያረፈበት አዲስ መፅሀፍ "China- Africa and an Economic Transformation"

Via:- Elias Mesert
@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ ኮርያ እና ጃፓን የነበሩት ጠ/ሚር አብይ ነገ ጠዋት ወደ እስራኤል ያመራሉ!

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጋዜጠኞች በላከው መረጃ የኢትዮጵያው መሪ ከእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤንጃሚን ኔታናያሁ እና ከፕሬዝደንቱ ሬኡቨን ሬቭሊን ጋር ሰኞ ይገናኛሉ።

Via:- Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀምራል፡፡

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ምክር ቤት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀምራል፡፡በቆይታውም የክልሉ መንግስት የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የ2012 የስራ ዘመን ዕቅድና በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።የምክር ቤቱ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
በዋልያ፣ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮዎች ላይ ወቅታዊ ቆጠራ ሊካሄድ ነው።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብርቅየ የዱር እንስሳት በሆኑት ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮዎች ላይ በመጭው መስከረም ወር ወቅታዊ ቆጠራ ሊያካሂድ ነው።የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በመጭው መስከረም ወር ላይ ሁለተኛ ዙር ወቅታዊ ቆጠራ ይካሄዳል።የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አበባው አዛናው ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ቆጠራው የሚካሄደው ብርቅየ የዱር እንስሳቱ ያሉበትን ሁኔታ አውቆ ክትትል ለማድረግ ነው።የቆጠራ ሥራው በፓርኩ ክልልና አዋሳኝ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች የሚካሄድ ሲሆን፥ ይህም በተጨባጭ መረጃ ተመስርቶ ለጎብኝዎች መረጃ ለመስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa