YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ለአዲሲቷ #ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር የሆኑት #ኦባንግ ሜቶ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን #አስታወቁ

#ኦባንግ በግል #የፌስቡክ ገፃቸው በጻፏት አጠር ያለች ፅሁፍ ከባልደረቦቻቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ አሳውቀዋል።

በኢትዮጵያ በርካታ #አስደሳች ዜና እንደሚሰማ የገለጹት ኦባንግ በርካታ ፈተናዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።

ኦባንግ ሜቶ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ ጥሰቶች አሳሳቢ ደረጃዎች ላይ መድረሳቸውን ገልጸው ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ #ኦባማ ደብዳቤ ፅፈው ነበር።

በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች እየተገኙ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚሞግቱ ንግግሮች በማድረግም ይታወቃሉ።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ለረዥም ዓመታት በውጭ አገራት ይኖሩ የነበሩ የለውጥ አቀንቃኞች፣ #የሰብዓዊ መብት #ተሟጋቾች#የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ እና ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ #በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
©DW
@yenetube @mycase27
ሶማሌ ክልል ‼️

የሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር ከክልሉ ተፈናቅለዉ የነበሩ #ከ250ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን ወደየቀያቸዉ መልሶ #ማቋቋሙን የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር #አስታወቁ

ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የኢትዮጵያ የንግድ ባንክ የሰጠዉን ርዳታ ትናንት ሲቀበሉ እንዳሉት መስተዳድራቸዉ ተጨማሪ ተፈናቃዮችን ወደየቀያቸዉ እየመለሰ ነዉ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች መርጃ የለገሰዉን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የባንኩ ፕሬዝደንት ባጫ ጊና ለአቶ ሙስጠፋ አስረክበዋል። የሶማሌ ክልልን ባለፈዉ አንድ ዓመት ባወከዉ ግጭት #ከ6_መቶ 65 ሺሕ በላይ ሕዝብ #ተፈናቅሏል

አሁን ወደየቀያቸዉ የተመለሱትና ያልተመለሱት ተፈናቃዮች የነበሩበትም ሆነ ያሉበት ሥፍራ በግልፅ አልተነገረም። ንግድ ባንክ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መርጃ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር መለገሱን ፕሬዝደንቱ አስታዉቀዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በአስመራ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለዋል ተብለው የነበሩት የኤርትራ የማዕድን ምኒስትር ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም አገግመው ወደ #ቤታቸው_መመለሳቸውን በጃፓን የኤርራ አምባሳደር #እስጢፋኖስ አፈወርቂ #አስታወቁ

ጄኔራል ስብሃት በአስመራ ከተማ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል የተባለው ባለፈው ታኅሳስ 2011 ዓ.ም. ነበር።

በኤርትራ ላይ የሚያተኩሩ እና በተቃዋሚዎች የሚተዳደሩ ማኅበራዊ ድረ-ገፆች ጄኔራሉ በሽጉጥ ጭንቅላታቸው ላይ ተመተው መቁሰላቸውን ፅፈው ነበር።

የኤርትራ መንግሥት በአገሪቱ የትጥቅ ትግል ከፍ ያለ ሚና እንደነበራቸው በሚነገርላቸው ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም ላይ ተሞከረ ስለተባለው ግድያ በይፋ የሰጠው ማብራሪያ አልነበረም።

አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ «ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም በውጭ ሀገር ከተደረገላቸው ስኬታማ ሕክምና በኋላ አገግመው ከውድ ቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ አስመራ መመለሳቸውን በመስማቴ ደስ ብሎኛል» ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

አምባሳደሩ የማዕድን ምኒስትሩ ሕክምና የተደረገላቸው የት እንደሆነ በይፋ ያሉት ነገር የለም። በአስመራ ከተማ በጄኔራል ስብሃት ላይ ጥቃቱ መፈጸሙ ከተሰማ በኋላ የተሰራጩ መረጃዎች ለሕክምና ያመሩት ወደ ዱባይ እንደነበር ይጠቁማሉ።

Via:-DW
@Yenetube @Fikerassefa