በአስመራ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለዋል ተብለው የነበሩት የኤርትራ የማዕድን ምኒስትር ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም አገግመው ወደ #ቤታቸው_መመለሳቸውን በጃፓን የኤርራ አምባሳደር #እስጢፋኖስ አፈወርቂ #አስታወቁ።
ጄኔራል ስብሃት በአስመራ ከተማ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል የተባለው ባለፈው ታኅሳስ 2011 ዓ.ም. ነበር።
በኤርትራ ላይ የሚያተኩሩ እና በተቃዋሚዎች የሚተዳደሩ ማኅበራዊ ድረ-ገፆች ጄኔራሉ በሽጉጥ ጭንቅላታቸው ላይ ተመተው መቁሰላቸውን ፅፈው ነበር።
የኤርትራ መንግሥት በአገሪቱ የትጥቅ ትግል ከፍ ያለ ሚና እንደነበራቸው በሚነገርላቸው ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም ላይ ተሞከረ ስለተባለው ግድያ በይፋ የሰጠው ማብራሪያ አልነበረም።
አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ «ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም በውጭ ሀገር ከተደረገላቸው ስኬታማ ሕክምና በኋላ አገግመው ከውድ ቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ አስመራ መመለሳቸውን በመስማቴ ደስ ብሎኛል» ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
አምባሳደሩ የማዕድን ምኒስትሩ ሕክምና የተደረገላቸው የት እንደሆነ በይፋ ያሉት ነገር የለም። በአስመራ ከተማ በጄኔራል ስብሃት ላይ ጥቃቱ መፈጸሙ ከተሰማ በኋላ የተሰራጩ መረጃዎች ለሕክምና ያመሩት ወደ ዱባይ እንደነበር ይጠቁማሉ።
Via:-DW
@Yenetube @Fikerassefa