#የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ለአዲሲቷ #ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀ-መንበር የሆኑት #ኦባንግ ሜቶ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን #አስታወቁ።
#ኦባንግ በግል #የፌስቡክ ገፃቸው በጻፏት አጠር ያለች ፅሁፍ ከባልደረቦቻቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ አሳውቀዋል።
በኢትዮጵያ በርካታ #አስደሳች ዜና እንደሚሰማ የገለጹት ኦባንግ በርካታ ፈተናዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
ኦባንግ ሜቶ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ ጥሰቶች አሳሳቢ ደረጃዎች ላይ መድረሳቸውን ገልጸው ለቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ #ኦባማ ደብዳቤ ፅፈው ነበር።
በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች እየተገኙ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚሞግቱ ንግግሮች በማድረግም ይታወቃሉ።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ለረዥም ዓመታት በውጭ አገራት ይኖሩ የነበሩ የለውጥ አቀንቃኞች፣ #የሰብዓዊ መብት #ተሟጋቾች፣ #የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ እና ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ #በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
©DW
@yenetube @mycase27