YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
⬆️⬆️#የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ በ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጭ ግንባታው በመካሄድ ላይ ያለውን የቡልቡላ ኢንትግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎበኙ።
©ebc
@yenetube @mycase27
#የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ

በኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንትና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን የሚመራ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች ቡድን በቅርቡ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን #ጎብኝቷል፡፡

እነዚህ አመራሮች በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማና ሳስጋ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ነው የጎበኙት፡፡

የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት እስከ አሁን ላደረጉት አስተዋጽኦ ወ/ሮ ጠይባ አመስግነው፣ እነዚህ ዜጎች ወደነበሩበት አከባቢ እስኪመለሱ ድረስ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናከሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
@yenetube @mycase27
#በሰሜን ሸዋ ዞን የሸኖ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ #ተሾመ ሙሉጌታን ጨምሮ 26 ተከሳሾች እስከ 8 ዓመት የሚደርስ እስራትና በገንዘብ #ተቀጡ

ተከሳሾቹ ያለአግባብ 60 ሺህ 556 ካሬ ሜትር መሬት በመሸንሸን ከ12 በላይ ለሚሆኑ ባለሀብቶች በመስጠት እና በመቀበል ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም በሙስና ወንጀል ነው የተከሰሱት።

የቅጣት ውሳኔውን #የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው የበየነው።

አንደኛ ተከሳሽ የሸኖ ከተማዋ ከንቲባ የነበሩት #ተሾመ ሙሉጌታን ሲሆኑ ከአንደኛ እስከ 11 ያሉት ተከሳሾች ደግሞ በከተማው መሬት አስተዳደር ውስጥ በተለያዩ ሙያ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ ናቻ፡፡

ከ11ኛ እስከ 26 ያሉ ተከሳሾች በኢንቨስትመንት መሬት የወሰዱ ተከሳሾች #ናቸው
ምንጭ ፦ OBN
@yenetube @mycase27