YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ የ2011 የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት #መቀበያ ነጥብ ይፋ አድርጓል። @yenetube @mycase27
ኤጀንሲው የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ ነጥብ #ይፋ አደረገ

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ በ2011 ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብን ይፋ #አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው ዛሬ እንዳስታወቀው በየዓመቱ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት #መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል የሥራ ገበያውን መሰረት በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መስፈርት ተመርኩዞ የመቁረጫ ነጥቡን ይፋ እንዳደረገ አመልክቷል፡፡

በዚህም መሰረት በ2010 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል 725 ሺህ 652 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመደበኛው ዘርፍ እንደሚገቡ ኤጀንሲው አመልክቷል፡፡

ከዚህም ውስጥ 230 ሺህ 828 ሴቶች ናቸው፡፡ በመምህራን ኮሌጅ እንዲሁም በፖሊስና መከላከያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡት ቁጥር በዚህ መግለጫ አለመካተቱም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፡የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ
@yenetube @mycase27
ምክር ቤቶቹ ነገ የፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሙላቱን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ የሪፐብሊኩን #ፕሬዚዳንት ይሾማሉ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመውም፥ ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር #ሙላቱ ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል አዲስ ፕሬዚዳንት #ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቶቹ ነገ የፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱን #መልቀቂያ በመቀበል አዲስ የሪፐብሊኩን ፕሬዚዳንት ይሾማሉ
©FBC
@yenetube @mycase27