YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ነው አቶ አብዲ መሃመድ ኡመርን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የፈቀደው።

በዚህም መሰረት የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመስማት ለመስከረንም 4 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በበላይ ተስፋዬ
©fbc
@yenetube @mycase27
#የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አባል የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛ #ብርሃኑ ተክለያሬድን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ሁከት #እንዲፈጠር ረድተዋል በሚል የተጠረጠሩ #ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮም ተፈቅዶለታል።

በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ሰብዓዊ መብትን የሚጥስ አያያዝ እየተተገበረባቸው እንደ ሆነ ለፍርድቤቱ ተናግረዋል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ የሆኑት ሄኖክ አክሊሉ ደንበኞቻቸው በጨለማ እና ቀዝቃዛ ክፍል እንዲታሰሩ መደረጋቸውን፣ ከህገ-መንግስቱ በተፃራሪ ፍርድ ቤት የቀረቡት ከ48 ሰዓታት በኋላ መሆኑን እንዲሁም ወጣት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በተለይ «የአዕይምሮ ህመም አለበት» ተብሎ ከሚጠረጠር ሰው ጋር እንዲታሰር መደረጉ ለህይወቱ አስጊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎች በተገቢው መንገድ እንዲያዙ ፖሊስን ማሳሰቡንም አክለው ነግረውናል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎች ሁከትን በማስተባበር እና በመፍጠር ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ያሳያሉ ያላቸውን ሰነዶች እና የባንክ ደብተር እንዳሉት ሆኖም ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ቀን ያስፈልገኛል በማለት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ብርሃኑ ተክለያሬድ ከዚህ ቀደም በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ በነበረው ተሳትፎ ፣ቆየት ብሎ ደግሞ «የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄን ሊቀላቀል ሞክሯል » በሚል ለእስር መዳረጉ አይዘነጋም።

📌ብርሃኑ በቅርቡ ከእስር ከተፈቱ የፖለቲካ እስረኞች መካከል አንዱ ነበር።
ምንጭ ፦ BBC
@yenetube @mycase27
#update ቡራዩ

በቡራዩ ከተማና አካባቢው ከተፈጸመው ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች #ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በቡራዩ ከተማና አካባቢው በተፈጸመ ወንጀል በማስተባበር፣ በማነሳሳት፣ ገንዘብ በማከፋፋል እና በመኪና በመሸኘት የተጠረጠሩ እነ ሳምሶን ጥላሁን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች ላይ ሃሰተኛ መታወቂያ፣ የመንግስት መሃተምና ቲተር እንዲሁም በቤት ውስጥ 74 ገጀራና ቢላ መያዙን #ፖሊስ አስታውቋል።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ በተጠረጠሩት ሳምሶን ጥላሁን፣ አለሙ ዋቅቶላ፣ ቡልቻ ታደሰ፣ ሃሺም አሚር፣ ሽፈራሁ ኢራና እና አሊ ዳንኤል አስተያየት እና መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ስራን #አዳምጧል
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዳዩ
@yenetube @mycase27
#update ፍርድ ቤቱ⤵️⤵️

#​ፍርድ ቤቱ በተስፋዬ ኡርጌ የምርመራ ጉዳይ ላይ መርማሪ ፖሊስ በሚቀጥሉት 7 ቀናት የቴክኒክ ምርመራ ውጤት ይዞ እንዲቀርብ የመጨረሻ #ማስጠንቂያ ሰጠ

በተስፋዬ ኡርጌ የምርመራ ጉዳይ ላይ መርማሪ ፓሊስ በሚቀጥሉት 7 ቀናት የቴክኒክ የምርመራ ውጤት ይዞ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂ ሰጥቷል።

በቀደሞው የመረጃ ደህንነት ሰራተኛ የምርመራ ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ በማስጠንቀቂያ የሰጠው መርማሪ ፓሊስ የተጨማሪ አስር ቀናት ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ 1ኛው ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው ለማርማሪ ፖሊስ ከማስጠንቀቂያ ጋር የተጨማሪ 7 ቀናት የምርመራ ጊዜ #በመስጠት የምርመራው ውጤቱን ለጥቅምት 12፣2011 ይዞ እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
©fbc
@yenetube @mycase27
#update አቶ አብዲ መሐመድ

የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ከእስር ቤት መስኮት ሰብረው #ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ገለጸ።

አቶ አብዲ መሐመድ ከሐምሌ 26 ቀን እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ፥ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

አቶ አብዲ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀጠሮ ችሎት በቀረቡበት ወቅት፥ ለደህንነታቸውና ለጤናቸው ሲባል የፖሊስ ቢሮ ውስጥ ታስረው መቆየታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ይሁንና አቶ #አብዲ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና አንድ የጥበቃ አባልን ጉሮሮ በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ #በማብራሪያው

አቶ አብዲ መሐመድ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን በመጥቀስ፥ ሆን ተብሎ ስሜን ለማጥፋትና እኔን ለመምታት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል።

ድርጊቱን ፈጽመዋል መባሉ ውሸት መሆኑንና በእርሳቸው ላይም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው እንደሆነም ተናግረዋል።

ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታሳሪ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነታቸው ላይ ስጋት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል።

በአንድ አጋጣሚም አንድ እስረኛ የሽንት ቤት በር ገንጥሎ እሳቸው ላይ በመጣል ጉዳት ሊያደርስ መሞከሩንም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

የታሰሩበት እስር ቤትም የማይመችና በጤናቸው ላይ እክል እንደፈጠረባቸውም ነው አቶ አብዲ የተናገሩት።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ አቶ አብዲ መሐመድ ማንኛውም እስረኛ በሚቆይበት እስር ቤት እንደታሰሩ ጠቅሶ፥ በእርሳቸው ላይ ምንም አይነት ጫና አለመደረጉን ገልጿል።

በተጨማሪም ፖሊስ ከእርሳቸው ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ለግጭቱ መቀስቀስ ተጠያቂ መሆናቸውንና በዚህም ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸውንም አስረድቷል።

ፖሊስ በአብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው #ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ምርመራውን እያካሄደ ያለው ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ይዞ እንዲቀርብ በማሳሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@yenetube @mycase27