YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተከሰተ የእንስሳት በሽታ የሞቱ ከብቶች ብዛት 1,400 ደረሰ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ አራት ዞኖች ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በተከሰተ የእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ፤ ከ1,400 በላይ ከብቶች መሞታቸውን የአካባቢው የስራ ኃላፊዎች ተናገሩ። በክልሉ የሚገኙ 6,500 የሚሆኑ ከብቶች የበሽታው ምልክት እንደታየባቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ገልጿል።

ከጋሞ ዞን ወደ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና አሌ ዞኖች የተዛመተው የእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ፤ በዋናነት የሚያጠቃው በሬዎችን እና ላሞችን ነው። በወረርሽኙ የተጠቁ ከብቶች፤ ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት፣ የመተንፈሻ አካላት ጭንቀት እና ሳል፣ ከአፍንጫቸው ውሃ የሚመስል ፈሳሽ መውጣት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ምልክቶች ይታዩባቸዋል።

ምንነቱ እስካሁን በምርመራ ያልታወቀው ይህ የእንስሳት በሽታ፤ በከብቶች ጭንቅላት እና ትከሻቸው አካባቢ እብጥት ያስከትላል። “የከብቶችን አቅም በማዳከም በፍጥነት እንደሚገድል” የሚነገርለት ይህ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ በታየበት በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ብቻ 693 ከብቶች ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ መሞታቸውን የወረዳው ግብርና መምሪያ  ገልጿል።  

የጋርዳ ማርታ ወረዳ የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲሱ ሀሼ፤ በሽታው “በፍጥነት የሚዛመት” እንደሆነ አስረድተዋል።

የአካባቢው አርብቶ አደሮች ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ምክንያት፤ በሽታው ወደ ጎፋ ዞን ተዛምቶ 216 ከብቶች መሞታቸውን የዞኑ የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደግፌ ተናግረዋል።

#Ethiopiainsider
@Yenetube @Fikerassefa
😭34👍19
የምክር ቤት አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነሷቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

👉 የባህር በር ለማግኘት እየተሄዱ ያሉ የዲፕሎማሲያ አካሄዶች ያስገኙት ውጤት ምንድን ነው? የባህር በር ጥያቄ ሕጋዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እልባት እንዲያገኝ የተከናወኑ ሥራዎችን፣ የተገኙ ውጤቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?

👉 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሰላም እፎያታ ቢያስገኝም፤ በስምምነቱ መሰረት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦቹ በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? የሰላም ስምምነት አፈጻጸሙስ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

👉 በትግራይ ክልል እየታየ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ወደግጭት እንዳያመራና ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ምን እየተሰራ ይገኛል?

👉 በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለው መገዳደል፣ መጠፋፋት እና የፖለቲካ ተቃርኖ ዛሬም ዋጋ እያስከፈለን በመሆኑ፤ መንግሥትና መሪው ፓርቲ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመፍታት ላይ በተሰሩ ሥራዎች የተገኘ ውጤት ምን ይመስላል?

👉 በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ታጥቀው ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?

👉 ታጣቂዎችን የመልሶ ማደረጃት ሥራ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

👉 በሰላም እጦት ምክያት በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን እንግልት ከመሰረቱ ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?

👉 የፍትሕ ተደራሽነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሰረቱ ለመፍታት መንግሥት በቀጣይ ምን ለመስራት አስቧል?

👉 ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከአሥር ዓመቱ ስትራቴጅክ እቅዱ አንፃር ያላቸው አፈፃጸም ምን ይመስላል?

👉 በስድስት ወር ውስጥ የመንግሥት ወጪና ገቢ ምን እንደሚመስል ማብራሪያ ይሰጥበት?

👉 በተለያዩ ዘርፎች የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂት ለመፍታት በቀጣይ የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?

👉 በአምራች ዘርፉ ያለውን የጥሬ ዕቃ እና የሌሎች የአቅርቦት ችግሮ ለመፍታት መንግሥት ምን እየሠራ ይገኛል?

👉 የ10 ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ማሳካት መቻላችንን የሚያመላክቱ መስፈሪያዎች ምንድን ናቸው? ፤ ሴክተሮችስ ከዚህ ዕቅድ ጋር ምን ያህል ተናበው እየሰሩ ነው?

👉 መንግሥት በድጎማ የሚያቀርበው ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይሸጥ ምን አይነት ጠንካራ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?

👉 በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት ሠራተኛን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በኑሮ ውድነት እየተቸገሩ ባሉበት ሁኔታ እንዴት የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ሊባል ይችላል? የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍38😁32
🚀 ቡስትግራም:ለቲክቶክ 📹 ፣ ኢንስታግራም 📷፣ ፌስቡክ 👍፣ ዩቲዩብ ✈️ እና ቴሌግራም ✈️ በቀላሉ ላይኮች፣ ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።


📹 የቲክቶክ እድገት: ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷 የኢንስታግራም ማሻሻያ: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

👍 የፌስቡክ አገልግሎት: የፔጅዎ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ፖስቶች ላይ ኢንጌጅመንቶች ይጨምሩ።

📹 የዩቲዩብ አገልግሎት: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

OPEN BOOSTGRAM - 🔗 https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍535🔥3👎2
YeneTube
Photo
በሕዝብ የተመረጠን እና ኃይል የመጠቀም ስልጣን ያለውን መንግሥት በጦር ኃይል ለማውረድ መሞከረ ተጠቀባይነት የለውም" ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ

👉 "በአንድ እግራቸው በርሃ በአንድ እግራቸው ፓርላማ ያሉ አካላት አራት ኪሎ የመግባት አባዜያቸው የሚለቃቸው አይደለም" ብለዋል


የሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የመንግሥትን የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል፡፡

የምክርቤቱ አባላት የመንግሥትን የግማሽ ዓመት ሪፖርት መነሻ በማድረግ፤ ለጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከልም የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ያነሱት ይገኝበታል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ "ባለፉት 7 ዓመታት በተለይም በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በሌሎችም ክልሎች የሚፈፀሙ የጦር ወንጀሎችን ለፍርድ ማቅርብ ለምን አልተቻለም? የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመሰሉ ጉዳዮች ውጤታማ እንዲሆኑ ከተፈለገ በተለይም በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የተኩስ አቁም መደረግ አለበት" ብለዋል፡፡

አክለውም "ታጣቂዎቹ ወደ ሰላም የሚመጡበት መንገድ በሙሉ አሟጠው እንዲሰሩ" ሲሉም በወከላቸው "የባህርዳር ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ሥም እጠይቃለው" ብለዋል፡፡

ከእርሳቸው በተጨማሪ በርካታ ምክር ቤቱ አባላትም "በኢትዮጵያ የተሟላ ሰላም ለማምጣት ምን እየተሰራ ይገኛል? በተለይም ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ለመወያየት የመንግሥት ቁርጠኝነት ምን ይመስላል? የቀድሞ ታጣቂዎችንም መልሶ ከሟቋቋም አንፃር የሚሰሩ ሥራዎች ምን ይመስላሉ? እንዲሁም በሰላም እንዲሁም በሰላም እጦት ምክንያት በሕዝብ የሚደርሱ እንግልትን ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፡

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያና ምላሽ "መንግሥት መሬትን ሲወስድብህ ተወው፣ ይወሰደው፤ ወይም በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት ማውረድ እፈልጋለሁ ሲል መንግሥት ዝም ብሎ መመለከት የለበትም" ብለዋል፡፡

"መንግሥት ሰላም ያስቀደመ መሆን ይገባዋል፡፡ ሰላም ያደፈረሰ ነገር ሲኖርም ወደ ገፊያ ከመግባት በፊት መመልከት የሚኖርበት ነገር ያሳፈልጋል" ሲሉም ተናረዋል፡፡

"ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ችግር አለ" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ዋናው የመጀመሪያው የመጠፋፋት ባህል ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ የወታደራዊ መንግሥት እሳቤ ነው" ሲሉ ገልጸውታል፡፡

"በድርድር እና በውይይት የሚባል ልምምድ ባለመኖሩ ምክንያት አብዛኛው ፖለቲከኛ በመገዳደል የማመን አባዜ ዛሬም ችግር ሆኖብናል" ብለዋል፡፡

"የፍረጃ ችግር ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት አለ" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ካዛንቺስ የመሰለ የሱ መንደር እንደዚህ አምሮበት ሲታይ የሚያደንቅ አንድ ፓርቲ የለም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

"በአንድ እግራቸው በርሃ በአንድ እግራቸው ፓርላማ ያሉ አካላት አራት ኪሎ የመግባት አባዜያቸው የሚለቃቸው አይደሰለም" ሲሉም ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍38👎17😁72
"ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር መፍታት የሚቻለው በሀሳብ ልዕልና ብቻ ነው" ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

የኢፊደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የ2017 የግማሽ ዓመት አፈጻጸምን አስመልክተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከምክር ቤት አባላትም ጥያቄዎች ተነስቷል፡፡

"ችግሮችን በጠመንጃ ለመፍታት መሞከር ሀገሪቱን ወደ ማትወጣው ቀውስ ውስጥ ሊስገባት ይችላል" ሲሉ የተናገሩት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የምክር ቤቱ አባሉ ደ/ር ደሳለኝ ጫኔ ናቸው፡፡

"አሁን ያሉትን ችግሮች መፍታት የሚቻለው በሀሳብ ልዕልና ብቻ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በተለያዩ ቦታዎች ባሉት ግጭቶች ዜጎች ሕወታቸውን ማጣታቸውን እና በርካቶች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እንዲም ቤንሻንጉል ክልል ያሉት የጸጥታ ችገሮች ኢኮኖሚው የሚፈለገውን ያህል እንዳያድግ እንቅፋት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩትም እንዲፈቱ ሲሉም የምክር ቤት አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጠይቀዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍426👎3
የአፈር ማዳበሪያን በተመለከተ

“እንደ ህዳሴ ግድብ ሁሉ የኢትዮጵያ ቀጣዩ ታላቅ ስራ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ነው።ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመር አለብን ብለን ስራ ጀምረናል። ይህን ስራም በተለይ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተሳሰር ለመስራት እየተጋን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው ተናግረዋል።

የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት ተጠናቋል።ከቀጣይ ዓመት ቀዳሚ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቻችን (Flagship Project) መካከል የኢትዮጵያን ኀልውና የሚያረጋግጥ ቀዳሚ የማዳበሪያ ፋብሪካ መገንባት ነው።ፕሮጀክቱ በሦስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል።የፋብሪካውን ግንባታ በግል ባለሃብቶች፣ በመንግስትና በግል ባለሃብቶች ቅንጅት ወይም ሌሎችን አማራጮች በመጠቀም እውን ለማድረግ ይሰራል ተብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍27👎8😁43
🇪🇹🇪🇷 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን አትወጋም አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰሞኑ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ግጭት ይቀሰቀሳል የሚሉ ስጋቶች ተጨባጭ አይደሉም ብለዋል።

"ወረራ ይፈፀምብናል ብለን አንሰጋም። ለዛ በቂ ዝግጅት አለን። በሠላም የባህር በር ጥያቄያችን እንዲመለስ እንፈልጋለን። ከጎረቤቶቻችን ጋር በጋራ መበልፀግ እንፈልጋለን" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል።


@yenetube @Fikerassefa
👍28😁187👀2
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ለአንድ ዓመት እንደሚራዘምና አመራሮቹም እንደሚቀያየሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከምክር ቤት አባላት በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈፃጸም ላይ ለተነሳው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፤ "ስምነቱ ከፍተኛ ድል የተገኘበት ታሪካዊ ስምምነት ነው" ብለዋል፡፡

"ስምምነቱን የተፈራረምነው ያሸፍነውን ጦርነት አቋርጠን ነው፡፡ ይህም ለሰላም ያለንን ከፍተኛ ፍላጎት አሳቷል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"መቀለ ከተማን ለመቆጣጠር አንድ ሁለት ቀን ሲቀረን የሰላም ስምምነት መፈራረማችን ለሰላም ያለንን ፍላጎት ያሳያል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ስምምነቱ በርካታ መሻሻሎች ስለማምጣቱ፣ ጊዜያዊ አስተዳዳር መቋቋሙ፣ የተለያዩ አገልግሎትን የማስጀመር ሁኔታ መኖሩ ከመሻሻሎቹ መካከል እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከስምምነቱ ጋር በተያያዘ ክፍተቶች መካከል የታጣቂዎች ጉዳይ መሆኑንም በምላሻቸው አካተዋል፡፡

የተሃድሶ ሥራውን በተመለከተም "የተሃድሶ ሥራው በተሟላ መንገድ አለመፈጸሙ በዋናነት የሚጎዳው የትግራይን ሕዝብ ነው" ያሉ ሲሆን፤ "ለትግራይ የሚላከው በጀት ለታጣቂዎች ከዋለ ልማት አይመጣም ማለት ነው" ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮች በራያ እና በፀለምት ጥሩ ሥራ ተሰርቷል፡፡ በወልቃይት አከባቢ የተጀመሩ ሥራዎች ግን በሚገባው መንገድ አልሄዱም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

"የፌደራል መንግሥት ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ፍላጎት ቢኖረውም፤ በተፈናቃዮች ላይ የሚሰራ አፍራሽ ፖለቲካ አስቸጋሪ ሆኖብናል" ሲሉም ገልጸዋል፡፡

"ባለፉት 2 ዓመታት በፕሬዝዳንት ጌታቸው፣ በጄነራል ታደሠ ወረደ እና ጄነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ የተመራው ግዚያዊ አስተዳዳር ጦርነት እንዳይኖር አድርጓል" ብለዋል፡፡

"ምንም እንኳን ቀድሞ በነበረ ጦርነት ላይ ብንወቅሳቸውም ባለፉት ሁለት ዓመት በነበረው ቆይታ ግን ማድነቅ ያስፈልጋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ግዚያዊ አስተዳዳሩ ጊዜው በመጠናቀቁ እሱን በተመለከተ ሥራዎች እየተሰሩ ነው" ብለዋል፡፡

በዚህም እስከ ቀጣዩ ምርጫ ያለውን የቆይታ ጊዜ ግዚያዊ አስተዳደሩ የሚመራበትን ሕግ የማሻሻል ሥራዎች እንደሚሰሩና አመራሮች የመቀያየር ሥራ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

"የትግራይ ሕዝብ ጦርነት በአይፈልግም፡፡ በውይይታችንም የተረዳነው ይህንን ነው፡፡ ጦርነት የሚፈልጉ ኃይሎች ጦርነት በእንደማያዋጣ መንገንዘብ አለባቸው፡፡ መከላከያ በሌሎች ክልልች ሥራ ላይ ነው በሚል ከሕግ አግባብ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ከድርጊታቸው መቆጠብ አለባቸው" ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍71😁1671👎1
Forwarded from In Africa Together
🚨 ታላቅ ዜና ! 🚨

🎓 ከኢን አፍሪካ ቱጌዘር – የዓለምአቀፋ ዩኒቨርሲቲዎች ሴሚናር! 🌍

📢 የፊታችን እሁድ በአዲሱ ዋና መስሪያቤታችን ከአሜሪካ 🇺🇸, ካናዳ 🇨🇦, ጀርመን 🇩🇪, ኔዘርላንድ 🇳🇱, ስዊድን 🇸🇪, ፊልላንድ🇫🇮 እና ከሌሎች ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚደረግ ሴሚናር አዘጋጅተናል

📅 ቀን: እሁድ፣ መጋቢት 14፣ 2016
📍 ቦታ: CMC፣ ሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት
ሰአት : 03:00 - 09:00
🎟 መግቢያ: በነፃ!

ሴሚናሩ ላይ በመሳተፎ የሚያገኙት ጥቅም ?

ከተለያዮ የዮኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር የመገናኘት እድል – በኦንላይን 🌍
የተለያዮ ስኮላር ቪፕ መረጃዎች
ምዝገባዎን እዛው የሚያጠናቅቁበት – ወደውጭ ሀገር ሄደው የመማር ህልሞን ያሳኩ ✍️
የቪዛ ስልጠና እና እገዛ
በያንዳንዱ እርምጃዎት ላይ የባለሙያ እገዛ የሚያገኙበት ።

🎓 በዲግሪ ፣ በማስተርስ ፣ በፒ.ኤች.ዲ

📌 ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ አሁኑኑ ይመዝገቡ : [https://forms.gle/qhDWVQLPD6KwHUnp7]

🔄 ወደውጭ ሀገር ሄደው መማር ለሚፈልጉ ጓደኞቾ ያጋሩ 🎉
👍4👎1
Luxembourg work visa
ሉዘምበርግ የሥራ ቪዛ


መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት
ፎቶ በሶፍት ኮፒ
እድሜ ከ19—65
የትምህርት ደረጃ: ሃይስኩል እና ከዛ በላይ

የስራዎቹ አይነት
የፋብሪካ ሥራዎች
የግብርና ሥራዎች
የጽዳት ሥራዎች
የኮንስትራክሽን ሥራዎች
የሆቴል ሥራዎች
የመጋዘን ሥራዎች
የዴሊቨሪ ሥራዎች
የላውንደሪ ስራ
መምህር
ነርስ
መካኒካል/ሲቪል ኢንጅነሪንግ
ካሸር
መካኒክ
የፎርክ ሊፍት ኦፕሬተር

ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም
በሰአት ከ15 - 30 ዶላር  
አኮሞዴሽን ያለው
የጤና ኢንሹራንስ ያለው

ፕሮሰስ ግዜ
ከ 2 ወር - 2 ወር ከ15 ቀን ይፈጃል
የመሳካት እድሉ ከ 98% በላይ

ቅድሚያ ክፍያ 25% ቀሪ ክፍያ ቪዛ ሲያልቅ
አጠቃላይ ክፍያ 900,000 ብር ትኬት አይጨምርም



ዋሥትና
የድርጅት ውልና የባንክ ቼክ እንሰጣለን
   
   ለበለጠ መረጃ

የቴሌግራም
inbox ላይ : @Sabinavisa2

☎️👇

🤳ስልክ  ቁጥር :
+251927555551 / 2 / 3 / 4 / 8

Website

https://sabina.et/

ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 አድራሻ:- ሃያ ሁለት ጎላጎል ህንፃ ፊት ለፊት ታውን እስኩዌር ሞል 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 602

👉እንዲሁም በሃዋሳ ቱሩፋት ወርቁ ቡቼ ታወር ፊት ለፊት አዲስ የገበያ ማዕከል 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor
👎5👍4
🎺🎺🎺 ቅናሻችን አምልጧችሁ የነበረ  ደንበኞቻችን በዲያስፖራ ቁጥር 2 ሳይታችን ልንክሳችሁ መጥተናል


65,000 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር

📣60% የባንክ ብድር የተመቻቸለት

⚡️Aluminium form work Technology 24 ሰዓት እየተሰራ ያለ

👉ቅድመ ክፍያ ከ 8% ጀምሮ

💥2 ከርሰ ምድር ውሀ
💥standby generator
💥ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ
💥4 የ ሰው ሊፍት እና 1 የ እቃ መጓጓዣ
💥በቂ የመኪና ማቆሚያ ከ 3 እስከ 6 ቤዝመንት
💥5 መዋኛ ገንዳ የ ልጆች እና የ አዋቂ
💥የባስኬትቦል መጫወቻ
💥ቤተ መፃህፍት (library)
💥ጂም እና ስፓ
💥የልጆች መጫወቻ ስፍራ
💥አረንጓዴ ስፍራ
💥ለ ማህበራዊ ጉዳይ የሚውል ሰፊ አዳራሽ
💥ዘመናዊ ለ እርድ የሚሆን ቦታ

ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉   ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ከነ መታጠቢያው ,ላውንደሪና  ስቶር ጋር

የተለያየ የካሬ አማራጭ:-

📌 ስቱዲዮ(studio)
        56.60 ካሬ
📌 ባለ አንድ መኝታ
         77.70ካሬ , 69 ካሬ ,85ካሬ, 98ካሬ
📌  ባለ ሁለት መኝታ
        99ካሬ,123ካሬ,128ካሬ እና 148.20 ካሬ
📌 ባለ ሶስት መኝታ
      118ካሬ,104ካሬ,123ካሬ, 139ካሬ, 146ካሬ,151ካሬ, 157ካሬ
📌 ባለ አራት መኝታ
       170ካሬ እና 186ካሬ



👉 እንዲሁም የንግድ ሱቆች 

✉️ ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ ደንበኞቻችን በDHL የቤት ባለቤት መሆን ትችላላችሁ

ለበለጠ መረጃ እንዲሁም ለሳይት ጉብኝት በ ☎️ +251929928392 ይደውሉልን
Telegram  @BetelZewelde
👍21😭1
የንግድ ሱቆችን በፒያሳ
✍️  ከሚኒሊክ አደባባይ ፊት ለፊት ባለ 5 ወለል ዘመናዊ የንግድ ሱቅ ማዕከል ከቴምር ፕሮፐርቲስ

✍️ ከ900 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

✍️ በተለያዩ የካሬ አማራጮች እንደምርጫዎ የቀረበ

✍️ ግንባታው በ1 አመት ከ 6 ወራት ተጠናቀው የሚረከቡት

✍️ ከ$ እና የግንባታ እቃዎች ዋጋ ጭማሪ ስጋት ነፃ ሆነዉ የግንባታ ሂደቱን መሠረት አድርገዉ ከፍለው የሚያጠናቅቁት

📍 መገኛ ቦታዉ

✍️ ከመርካቶ በቅርብ ርቀት፣ የአዉቶብስ እና ባቡር ጣቢያ መሀል፣ ከአራዳ ጊዩርጊስ ፊት ለፊት፣ የታክሲ መዉጫ እና መዉረጃ እንደመሆኑ ጥሩ የንግድ እንቅስቃሴ አለበት።

✍️ ነግደው የሚያተርፉበት፣ አከራይተዉ ጠቀም ያለ ገቢ የሚያገኙበት፣ መልሰዉ ቢሸጡት የሚጠቀሙበት ልዩ እድል

✍️ የቀሩን ውስን ሱቆች ስለሆኑ በ +251912685310 ይደውሉልን
👍2
በአካዳሚክ ምክንያት ከአንድ ተቋም የተባረረ ተማሪ ወደ ሌላ ተቋም ሲመዘገብ ቀድሞ በተባረረበት ተቋም ያገኘው ውጤት እንደማይያዝለት ተናገሩ

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካዳሚክ  ምክንያት ለተባረረ (dismissed) ተማሪ የኮርስ ኤግዘምሽን በተመለከተ አዲስ መመሪያ በላከው ደብዳቤ አስታውቃል።

ባለስልጣኑ በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ስልጣን ተሰጥቶታል።

በተሰጠው ስልጣንም በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት ማንኛውም ተቋም ስልጣን ባለው አካል የወጣ የቅበላ መስፈርት ያለሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደማይቻል ደንግጓል፡፡ አንድ ተማሪ በአካዳሚክ ምክንያት ከአንድ ተቋም በሚባረርበት ጊዜ ተማሪው ብቁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው።

በዚህም ተማሪው በአዲስ መልክ ሌላ ተቋም ውስጥ በትምህርት ዘመኑ በተቀመጠው የመቁረጫ ነጥብ ውጤት የሚያስገባው ከሆነ ተመዝግቦ ቢማር ቀድሞ በተባረረበት ተቋም በአንዳንድ ኮርስ ያገኘው ውጤት ኤግዘምት የማይደረግ በመሆኑ ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማሳስቢያ ተሰጥቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍13😭4👎1
75% የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት አላገኘም!

75 በመቶ የሚሆኑ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በሙያ ብቃት በሌላቸው ሰዎች የሚዘጋጅ በመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት፣ በጥቅምት ወር በተካሄደው ቅድመ ኦዲት 25 በመቶ ያህሉ ነጋዴዎች ብቻ የሂሳብ መዝገባቸው ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጧል።

የተቋሙ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ እንደገለጹት፣ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ በባንክ ሂሳባቸው ከሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ጋር የማይጣጣም ነው። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በባንክ አካውንታቸው ላይ ቢታይም፣ በሂሳብ መዝገባቸው ላይ ምንም ትርፍ እንዳላገኙ ያሳያሉ።

አንዳንዶቹ ደግሞ ገንዘቡን በህጋዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ወጪ አድርገው ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም የተባለ ሲሆን የሚመጣው የሂሳብ መዝገብ ፕሮፌሽናል ባልሆኑ ሰዎች እየተዘጋጀ ነጋዴው ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑም ተገልጿል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👎14👍113
12 የኢትዮጵያና ኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ወታደራዊ አዛዦች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በትግራይ "የጦር ወንጀል" ፈጽመዋል በሚል በጀርመን ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ

👉🏼ክሱን እንዲመሰረት የጠየቁት የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊ እና የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ግለሰቦች ናቸዉ


አንድ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊንና አንድ የቀድሞ የረድኤት ሠራተኛን ጨምሮ ስምንት የትግራይ ተወላጆች ፤ 12 የኢትዮጵያና ኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ወታደራዊ አዛዦች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በትግራይ "የጦር ወንጀል" እና "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች" ፈጽመዋል በማለት ለጀርመን ዓቃቤ ሕግ አቤቱታ አቅርበዋል።

የወንጀሎቹ ሰለባና ወንጀሎቹ ሲፈጸም እማኝ የነበሩት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፣ የጀርመን ፌደራል ዓቃቤ ሕግ በወንጀሎቹ ላይ የምርመራ መዝገብ እንዲከፍትና በአገሪቱ ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሠርት ጠይቀዋል።

ግለሰቦቹ አቤቱታውን ያቀረቡት፣ ሌጋል አክሽን ወርልድዋይድ በተሰኘ የሕግ ተቋምና ሌሎች ድርጅቶችና የሕግ ባለሙያዎች ድጋፍ ነው።

የጀርመን ዓቃቤ ሕግ በውጭ አገራት በተፈጸሙ ዓለማቀፍ አስከፊ ወንጀሎች ዙሪያ ምርመራ የማድረግ ሥልጣን አለው።

ዋዜማ

@Yenetube @Fikerassefa
👍403😁2
በአፍሪካ እየጨመረ የመጣው የስፑትኒክ ተፅዕኖ እንዳሳሰበው የአውሮፓ የውጭ አገልግሎት ገለጸ

የአውሮፓ ሕብረት የዲፕሎማሲ አገልግሎት ሪፖርት የስፑትኒክ አፍሪካ የፈረንሳይኛ ይዘት ዓለም አቀፍ ተደራሽነት እና ተፅዕኖ አየጨመረ መጥቷል ብሏል።

ሪፖርቱ "የአውሮፓ ሕብረት እ.አ.አ 2022 አርቲ እና ስፑትኒክ ላይ እገዳ ከጣለ በኋላ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ" ጠቁሟል።

🗣"ይህ ዝንባሌ ሩሲያ በግልጽ የሚዲያ ተፅዕኖ አቅጣጫ የመቀየር እና በአንድ ክልል ውስጥ ያሉ ገደቦችን ለማካካስ ሌላ ቦታ ተጽዕኖዋን ማጠናከር እንደምትችል ያሳያል" ሲል ሪፖርቱ ገልጿል።

የሩሲያ መንግሥት በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ በሩሲያ ሚዲያ ላይ የተጣለው እገዳ ፖለቲካዊ ሳንሱር እንደሆነና የአውሮፓ ባለስልጣናት "የተቃውሞ ድምጽ የማፈን ፖሊሲያቸውን" እያጠናከሩ መምጣታቸውን ደጋግሞ ይገልጻል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍163🔥2👀1
የሱዳን ጦር ከሁለት ዓመት ጦርነት በኋላ የፕሬዝዳንቱን ቤተ መንግስት መልሶ ያዘ

የሱዳን ጦር በካርቱም የሚገኘውን ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት ከተቀናቃኙ ፓራሚሊተሪ የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች በመንጠቅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ወታደራዊ መሪዎች ገልፀዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለጠፉት ቪዲዮ እና ፎቶግራፎች የተደሰቱ ወታደሮች የጦር መሳሪያቸውን ከፍ በማድረግ ሲጮሁ እና ተንበርክከው ሲፀልዩ ያሳያሉ። ሰራዊቱ አርኤስኤፍ ተብሎ የሚጠራውን የትጥቅ ተቀናቃኞቹ ከተባረረ ከሁለት አመት በኋላ ዋና ከተማይቱን መልሶ ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ይመስላል።

የመከላከያ ቡድኑ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።የጦሩ ቃል አቀባይ ነቢል አብደላህ በመንግስት ቲቪ እንደተናገሩት ወታደሮቹ በማዕከላዊ ካርቱም የሚገኘውን ቤተ መንግስት እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ተቆጣጥረዋል ብለዋል። አብደላህ አክለውም ሰራዊታችን የጠላት ተዋጊዎችን እና መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ አውድመዋል ሲሉ ተደምጠዋል። ድሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ትግላችንን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን ብለዋል። ካርቱም የሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ከሁለት አመት በፊት የጀመረባት እና አንዳንድ ታላላቅ ጦርነቶች የተካሄዱባት ከተማ ናት።

ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቴ አርኤስኤፍ አብዛኛውን ዋና ከተማዋን እና የሱዳንን ምዕራባዊ ክፍል ይዞ ቆይቷል።ካርቱምን ማስመለስ ለሱዳን ጦር ኃይሎች ትልቅ ድል እና በግጭቱ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ሰራዊቱ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በማዕከላዊ ሱዳን አንዳንድ ክፍሎችም ድል አስመዝግቧል። ሐሙስ እለት፣ በሪፐብሊካን ቤተ መንግስት አቅራቢያ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እና የአየር ድብደባ ከባድ ፍንዳታ እንደነበረም እማኞች ተናግረዋል።ቅዳሜ እለት በቀረፀ የቪዲዮ መልዕክት፣ የአር ኤስ ኤፍ ኮማንደር መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ፣ ሄሜቲ በመባል የሚታወቁት፣ በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት እና በአካባቢው በቁጥጥራችን ስር ያሉትን አካባቢዎች ለመከላከል ቃል ገብተው ነበር።
@Yenetube @FikerAssefa
👍16👎1
🚀 ቡስትግራም:ለቲክቶክ 📹 ፣ ኢንስታግራም 📷፣ ፌስቡክ 👍፣ ዩቲዩብ 📹 እና ቴሌግራም ✈️ በቀላሉ ላይኮች፣ ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።


OPEN BOOSTGRAM - 🔗 https://tttttt.me/boostgramPromoBot/boostgram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1