YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተከሰተ የእንስሳት በሽታ የሞቱ ከብቶች ብዛት 1,400 ደረሰ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ አራት ዞኖች ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በተከሰተ የእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ፤ ከ1,400 በላይ ከብቶች መሞታቸውን የአካባቢው የስራ ኃላፊዎች ተናገሩ። በክልሉ የሚገኙ 6,500 የሚሆኑ ከብቶች የበሽታው ምልክት እንደታየባቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ገልጿል።

ከጋሞ ዞን ወደ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ እና አሌ ዞኖች የተዛመተው የእንስሳት በሽታ ወረርሽኝ፤ በዋናነት የሚያጠቃው በሬዎችን እና ላሞችን ነው። በወረርሽኙ የተጠቁ ከብቶች፤ ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት፣ የመተንፈሻ አካላት ጭንቀት እና ሳል፣ ከአፍንጫቸው ውሃ የሚመስል ፈሳሽ መውጣት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ምልክቶች ይታዩባቸዋል።

ምንነቱ እስካሁን በምርመራ ያልታወቀው ይህ የእንስሳት በሽታ፤ በከብቶች ጭንቅላት እና ትከሻቸው አካባቢ እብጥት ያስከትላል። “የከብቶችን አቅም በማዳከም በፍጥነት እንደሚገድል” የሚነገርለት ይህ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ በታየበት በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ብቻ 693 ከብቶች ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ መሞታቸውን የወረዳው ግብርና መምሪያ  ገልጿል።  

የጋርዳ ማርታ ወረዳ የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲሱ ሀሼ፤ በሽታው “በፍጥነት የሚዛመት” እንደሆነ አስረድተዋል።

የአካባቢው አርብቶ አደሮች ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ምክንያት፤ በሽታው ወደ ጎፋ ዞን ተዛምቶ 216 ከብቶች መሞታቸውን የዞኑ የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደግፌ ተናግረዋል።

#Ethiopiainsider
@Yenetube @Fikerassefa
😭34👍19