YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳለው ከሆነ ሐሙስ ዕለት እስራኤል በጋዛ ላይ በከፈተችው ጥቃት ቢያንስ 85 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 133 ደግሞ ቆስለዋል

የሕክምና ባለሙያዎች እንደገለጹት የእስራኤል የአየር ድብደባ በጋዛ ሰሜናዊ እና ደቡባዊ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ ቤቶችን ኢላማ አድርጓል።

እስራኤል በጉዳዩ ላይ ምንም አስተያየት አልሰጠችም።
😭24👍5
ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የኢንቨስትመንት ባንኮች እና የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ አገኘች!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለአምስት አዳዲስ ድርጅቶች የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንቨስትመንት ባንኮችና የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ ፈቃድ የተሰጠበት እንዲሁም አጠቃላይ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ቁጥር ከአራት ወደ ዘጠኝ ከፍ ያደረገበት ነው።

ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ሲቢኢ ካፒታል አ.ማ - ኢንቨስትመንት ባንክ ፣ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ - ኢንቨስትመንት ባንክ ፣ ኢትዮ-ፊደሊቲ ሴኩሪቲስ አ.ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ (Securities Dealer) ፣ ኤች ኤስ ቲ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ. ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ፣ ኢኩዥን የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ኃ.የተ.የግ. ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ይህ ታሪካዊ ክስተት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ገበያ ለማሳደግና ለኢንቨስትመንት እድሎች መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍29🔥3😁1
ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውኃ ትራንስፖርት የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች እየገቡ ነው

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጭነው ወደ ሀገር ቤት በማምራት ላይ ናቸው።

ጣና ነሽ ፪ የተሰኘችው ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት ጀልባ 38ሜ እርዝመት እንዳላት እና በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላት መዘገቡ ይታወሳል።

ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣና የመዝናኛ ጀልባ እንደሆነች የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መረጃ ያመለክታል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍313😁3
በመዲናዋ የደንብ ልብስ መለያን አስመስለው በመልበስ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣንን መለያ አስመስለው በመልበስ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ተጠርጣሪዎቹ የደንብ ልብሱን አስመስለው በመልበስ የባለስልጣኑ ሰራተኞች አላስፈላጊ ተግባራትን እንደፈጸሙ በማስመሰል የሱቅ ማስታወቂያ ሰርተዋል፡፡

ግለሰቦቹ በዚህ ሕገ ወጥ ተግባራቸውም በርካታ ሰዎችን ማሳሳታቸውን ነው የገለጹት፡፡

ተጠርጣሪዎቹ አሁን ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍24😁123
#በሱዳን የፕሬዝዳንቱ ቤተ-መንግሥት ላይ በሰነዘረ የድሮን ጥቃት 3 ጋዜጠኖች ተገደሉ

መጋቢት 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አር ኤስ ኤፍ) በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በሚገኘው የሪፐብሊካን ቤተ-መንግሥት ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ሦስት ጋዜጠኖች መገደላቸው ተገልጿል፡፡

በጀነራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ሠራዊት (ኤስ ኤ ኤፍ) ፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥቱን ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ ከሚመሩት በፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አር ኤስ ኤፍ) እጅ በማስለቀቅ በዛሬው ዕለት በቁጥጥሩ ሥራ ማስገባቱን አሐዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ይህንንም ተከትሎ፤ ከሰዓታት በኋላ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በከፈተውና በቤተ-መንግሥቱ ውስጥ በሚገኝ ወታደራዊ እና የሚዲያ ስብስብ አዳራሽ ላይ ባነጣጠረ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት 3 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገልጿል፡፡

ጋዜጠኞች በቤተ-መንግሥቱ ተገኝተው ለሱዳን መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲዘግቡ በነበሩበት ወቅት በጥቃቱ ሰለባ እንደሆኑም የሱዳን ጦር ምንጮች ለኤፍ ፒ ገልጸዋል፡፡

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቤተ-መንግሥቱን ጨምሮ የሱዳን በርካታ አካባቢዎችን ለበርካታ ጊዜያት ተቆጣጥሮ የቆየ ሲሆን፤ የሱዳን ጦር ከሁለት ዓመት ጦርነት በኋላ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥቱን መልሶ በመቆጣጠሩ ወሳኝ የተባለን ድል መቀዳጀቱ ተነግሯል።

ነገር ግን አሁን ላይ ፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ በቤተ-መንግሥቱ ጥቃት ከማድረሱ በተጨማሪ፤ አሁንም የካርቱም ደቡባዊ ክፍልን እና የካርቱም ተጎራባች በሆነችውን ኦምዱርማን ከተማ መካከል ያሉ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ይገኛል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍324👀2😭1
ፖሊስ ቲክቶከሮቹ በቁቁጥር ስለዋሉበት ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ይፋ አደረገ

ሸጋው ጫኔ አንለይ፣  መሀመድ ሀምዛ ያሲን፣ አቤኔዘር ተስፋዬ በየነ እና ጌትነት ደምለው ዳምጤ የተባሉ ግለሰቦች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 10 ልዩ ቦታው  ደብረወርቅ ህንፃ አካባቢ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቀድሞ የደምብ ልብስ የሚመስል  በማሰፋት በጎዳና ንግድ ላይ የሚተዳደሩትን ግለሰቦች ንብረት በመበተንና በመደብደብ የቢሮውን ገፅታ በሚያንቋሽሽ መልኩ  የሀሰት ቪዲዮ አዘጋጀተው በቲክቶክ ማሰራጨታቸውን ተከትሎ በቀረበባቸው አቤቱታ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ግለሰቦቹ በተቋሙ እና በሰራተኞቹ ላይ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ አሉታዊ ስሜት እንዲፈጠር አስበው የተቋሙን የቀድሞ የደምብ ልብስ የሚመስል አዘጋጅተው ድርጊቱን መፈፀማቸውን ፖሊስ አስታውቋል፤ የፈፀሙት ድርጊት በህግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት በህግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ መሰል ድርጊት የሚፈጽሙ ግለሰቦችም ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስቧል፡፡ 

ምንጭ:- አአ ፖሊስ
@Yenetube @Fikerassefa
😁29👍186👀2
የገንዘብ ቅጣቱ የመጀመሪያ ደረጃ ጥፋት ፣ሁለተኛ ደረጃ ጥፋት እያለ እስከ አምስተኛ ደረጃ የሚያስቀምጣቸው የቅጣት እርከኖች አሉት።

🗣የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደምብ 185/2017 የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ምሽት 4 ሰዓት ድረስ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ ተቋማት ደግሞ ምሽት 3:30 ድረስ እንዲቆዩ የሚያስገድድ ደምብ ከመጋቢት 10 ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል።

ደንቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ያጸደቀው የካቲት 29/2017 ዓ/ም የነበረ ሲሆን ይህ ደንብ መመሪያዎች ተዘጋጅተውለት ከመጋቢት 10/2017 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል

@Yenetube @Fikerassefa
👍17👎42😁1
1👍1
YeneTube
Photo
የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በ2 ክልሎች የ'ይገባኛል' ጥያቄ ምክንያት የህልውና አደጋ እንደተጋረጠበት ተገለጸ

በደቡብ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ላይ የሚገኘው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በክልሎች የ'ይገባኛል' ጥያቄ ምክንያት የህልውና አደጋ እንደተጋረጠበት ተገልጿል፡፡

ፓርኩ ከአጎራባች አካባቢዎች የመጡ ከአንድ ሺሕ በላይ አባወራዎች ወደ ፓርኩ ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ ገብተው በመስፈራቸው ምክንያት፤ 50 በመቶ የፓርኩ ይዞታ ከታቀደለት ዓላማ ውጭ እየሆነ ይገኛል ተብሏል፡፡

ሰፋሪዎቹ በተከለለው በፓርኩ ክፍል መኖሪያ ቤትና ትምህርት ቤቶችን ገንብተዋል፤ በሚያሰማሯቸው የግጦሽ እንስሳት አማካኝነትም ጥብቁን ደን እያወደሙ፣ እንስሳትን እያደኑ፣ እና ሌሎች የፓርኩን ሕልውና የሚፈታተኑ ተግባራት እየፈጸሙ በፓርኩ የተጠለሉ ብርቅዬ እንስሳት ላይ የመጥፋት አደጋ አንዲጋረጥ ማድረጋቸውን የጋሞ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ታከለ ሀሚሶ ፓርኩ በ1966 ዓ.ም. እንደተቋቋመ አስታውሰው፤ እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ይተዳደር እንደነበር ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"በፓርኩ ውድመት ቅሬታ የተነሳባቸው ሰፋሪዎች፤ ከ1983 ዓ.ም በኋላ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የፈለሱ ናቸው" ብለዋል፡፡

አክለውም በፓርኩ ውስጥ ያሉ እንደ ዜብራ ያሉ እንስሳትን ለማየት በፓርኩ ውስጥ በትንሹ 30 ደቂቃ መጓዝ እንደሚጠበቅ ጠቁመው፤ "ይህ የሆነውም እንስሳት መኖሪያ ቤታቸውን ተቀምተው በመሸሻቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የመምሪያ ኃላፊው አቶ ታከለ የፓርኩን ነባር ወሰን ለማስጠበቅ፤ ሕገ-ወጥ ሰፋሪዎችን በማስወጣት ሌላ አካባቢ ለማስፈርና እና ፓርኩን በአግባቡ ለማልማት ከኦሮሚያ ክልል ባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ቢፈረምም፤ ወደ ትግበራ አለመግባቱ ለሕገ-ወጥ ሰፋሪዎቹ መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

አሐዱ የጋሞ ዞንን አቤቱታ በመያዝ በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያን ስለ ጉዳዩ አነጋግሯል።

የመምሪያው ኃላፊ ዳዊት ዘለቀ በሰጡት ምላሽም፤ ወደ ፓርኩ የገቡ ሰፋሪዎች መኖራቸውን እንደማያውቁና ፓርኩ በክልሉ ከሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ከአጎራባች ክልሎች በሕገ-ወጥ መንገድ ገብተዋል የሚለው መረጃ ፈፅሞ የተሳሳተ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው፤ "ነዋሪዎቹ የሚገኙትም በነባር ይዞታቸው እና በክልላቸው ነው" ብለዋል፡፡

ነዋሪዎቹን ወደ ሌሎ አካባቢዎች ለማስፈር የተካሄደ ስምምነት ስለመኖሩ እንደማያውቁም ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አሐዱ በሁለቱ ክልሎች የ'ይገባኛል' ጥያቄ ምክንያት አደጋ ላይ የወደቀውን የፓርኩን ህልውና ጉዳይ ለማጣራት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣንን ጠይቋል።

ፓርኩ በሁለቱ ክልሎች የሚገኝ መሆኑንና፣ ሕገ-ወጥ የደን ጭፍጨፋና፣ አደን እየተካሄደበት እንደሚገኝ አምነው "የሚነሳበት የባለቤትነት ጥያቄ በጥናት ያልተረጋገጠ ነው" ሲሉ፤ የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ሰለሞን መኮንን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከምዕራብ ጉጂ ዞን ሕገ-ወጥ ሰፋሪዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ሰለሞን፤ 'ቦታው የሰፋሪዎቱ ነባር ይዞታ ነው' የሚለው ግን የተሳሳተ መረጃ እንዳልሆነ አብራርተዋል።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አያይዘውም ከዚህ በፊት በሁለቱም ወገን የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት የጋራ የምክክር መደረክ መዘጋጀቱን አስታውሰው፤ "ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመሰጠት እየተሰራ ይገኛል" ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍33👎95
አል ዐይን አማርኛ  ሥራ ሊያቆም መሆኑን ተገለፀ

ባለቤትነቱ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት የሆነው አል ዐይን አማርኛ የበይነ መረብ የዜና ማሠራጫ፤ ሥራ ሊያቆም መሆኑን ዋዜማ ዘግቧል፡፡

የዜና ማሠራጫው በአማርኛ ቋንቋ ዜናዎችንና ዘገባዎችን የሚያዘጋጁ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎቹን የቅጥር ውል ማቋረጡን ዘገባው አረጋግጧል፡፡

ዘጋቢዎቹ ሥራቸውን እየሠሩ ባሉበት ወቅት ምንም ዓይነት ቅድመ ማስጠንቂያ ሳይደርሳቸው፣ በድንገት የሥራ ውላቸው መቋረጡን የሚያመላክት መልዕክት በኢሜይል እንደደረሳቸው ተዘግቧል፡፡

ተቋሙ የሠራተኞቹን ውል ያቋረጠው፤ የአማርኛ ዜና አገልግሎቱን አቁሞ የኢትዮጵያ ቢሮውን ዘግቶ ለመውጣት በማሰቡ መሆኑን የዜና ምንጩ ተረድቻለው በሏል፡፡

Via ዋዜማ
👍28😭20👎64👀3😁1
ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ከ1 ሰዓት በኋላ የምታደርገውን ጨዋታ ለማየት ይህን አፕ ዳውን ሎድ አድርጉ። Cricfy TV በነፃ ነው። ለሌላ ጊዜም ይጠቅማችኋል።

Application ለማውርድ በዚህ ገፅ ላይ ካደረግን Copyright ሊዘጋብን ሰለሚችል አዲስ ቻናል ከፍተናል ለቀናል አፕልኬሽኑን

https://tttttt.me/+LMTodBBw8oI4MjY0
👍11😁9🔥71
45' | ኢትዮጵያ 🇪🇹 0-2 🇪🇬 ግብፅ

31' ሞ ሳላህ

40' ዚዞ



ጎሉን ለማየት

https://tttttt.me/+LMTodBBw8oI4MjY0


#2026_የዓለም_ዋንጫ_ማጣርያ
😁15👍9🔥9👎5👀32
የሙሉ ሰአት ውጤት

ኢትዮጵያ 🇪🇹 0-2 🇪🇬 ግብፅ

31' ሞ ሳላህ

40' ዚዞ

#2026_የዓለም_ዋንጫ_ማጣርያ
😁45👍25👎61👀1
Forwarded from In Africa Together
🚨 Big Announcement! 🚨 

🎓 In Africa Together – Global University Seminars! 🌍 

📢 Join us this Sunday at our new headquarters for exclusive seminars with top universities from the USA 🇺🇸, Canada 🇨🇦, Germany 🇩🇪, Netherlands 🇳🇱, Sweden 🇸🇪, Finland 🇫🇮, and more!

📅 Date: Sunday, March 23, 2025 
📍 Location: CMC, in front of Civil Service 
Time: 09:00 AM - 03:00 PM
🎟 Entry: FREE!

What’s in it for you? 
Meet University Representatives – Live sessions from top universities 🌍 
Scholarship & Financial Aid Info – Learn how to fund your studies 💰 
On-the-Spot Registration & Contracts – Secure your future today! ✍️ 
Visa & Admission Guidance – Step-by-step expert advice 🛂 

🎓Bachelor’s, Masters & PhD

📌 Seats are limited! Register now: [https://forms.gle/qhDWVQLPD6KwHUnp7

🔄 Share with friends who dream of studying abroad! See you there! 🎉
👍5
Luxembourg work visa
ሉዘምበርግ የሥራ ቪዛ


መሥፈርቶች
የታደሰ ፖስፖርት
ፎቶ በሶፍት ኮፒ
እድሜ ከ19—65
የትምህርት ደረጃ: ሃይስኩል እና ከዛ በላይ

የስራዎቹ አይነት
የፋብሪካ ሥራዎች
የግብርና ሥራዎች
የጽዳት ሥራዎች
የኮንስትራክሽን ሥራዎች
የሆቴል ሥራዎች
የመጋዘን ሥራዎች
የዴሊቨሪ ሥራዎች
የላውንደሪ ስራ
መምህር
ነርስ
መካኒካል/ሲቪል ኢንጅነሪንግ
ካሸር
መካኒክ
የፎርክ ሊፍት ኦፕሬተር

ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም
በሰአት ከ15 - 30 ዶላር  
አኮሞዴሽን ያለው
የጤና ኢንሹራንስ ያለው

ፕሮሰስ ግዜ
ከ 2 ወር - 2 ወር ከ15 ቀን ይፈጃል
የመሳካት እድሉ ከ 98% በላይ

ቅድሚያ ክፍያ 25% ቀሪ ክፍያ ቪዛ ሲያልቅ
አጠቃላይ ክፍያ 900,000 ብር ትኬት አይጨምርም



ዋሥትና
የድርጅት ውልና የባንክ ቼክ እንሰጣለን
   
   ለበለጠ መረጃ

የቴሌግራም
inbox ላይ : @Sabinavisa2

☎️👇

🤳ስልክ  ቁጥር :
+251927555551 / 2 / 3 / 4 / 8

Website

https://sabina.et/

ወደ ቢሮአችን ይምጡ !
👉 አድራሻ:- ሃያ ሁለት ጎላጎል ህንፃ ፊት ለፊት ታውን እስኩዌር ሞል 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 602

👉እንዲሁም በሃዋሳ ቱሩፋት ወርቁ ቡቼ ታወር ፊት ለፊት አዲስ የገበያ ማዕከል 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201

ከታላቅ አክብሮት ጋር   !!!

https://tttttt.me/sabinaadvisor
👍6
የንግድ ሱቆችን በፒያሳ
✍️  ከሚኒሊክ አደባባይ ፊት ለፊት ባለ 5 ወለል ዘመናዊ የንግድ ሱቅ ማዕከል ከቴምር ፕሮፐርቲስ

✍️ ከ900 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

✍️ በተለያዩ የካሬ አማራጮች እንደምርጫዎ የቀረበ

✍️ ግንባታው በ1 አመት ከ 6 ወራት ተጠናቀው የሚረከቡት

✍️ ከ$ እና የግንባታ እቃዎች ዋጋ ጭማሪ ስጋት ነፃ ሆነዉ የግንባታ ሂደቱን መሠረት አድርገዉ ከፍለው የሚያጠናቅቁት

📍 መገኛ ቦታዉ

✍️ ከመርካቶ በቅርብ ርቀት፣ የአዉቶብስ እና ባቡር ጣቢያ መሀል፣ ከአራዳ ጊዩርጊስ ፊት ለፊት፣ የታክሲ መዉጫ እና መዉረጃ እንደመሆኑ ጥሩ የንግድ እንቅስቃሴ አለበት።

✍️ ነግደው የሚያተርፉበት፣ አከራይተዉ ጠቀም ያለ ገቢ የሚያገኙበት፣ መልሰዉ ቢሸጡት የሚጠቀሙበት ልዩ እድል

✍️ የቀሩን ውስን ሱቆች ስለሆኑ በ +251912685310 ይደውሉልን
👍4
በሐዋሳ ከተማ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ በጊዜያዊነት ተከለከለ

የሲዳማ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨንበላላ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በሐዋሳ ከተማ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ መከልከሉን የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ መዋቅር ኮሚቴ ተቋቁሞ አቅጣጫ መሰጠቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር እና ወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ካሳ ጨቦ ተናግረዋል።

ለበዓሉ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የክልሉ አድማ በታኝ ቅድመ ዝግጅታቸውን እንደጨረሱ ነግረውናል።

ማህበረሰቡ ለፀጥታ መዋቅሩ አጋዥ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡት ምክትል ኮሚሽነሩ፥ በሐዋሳ ከተማ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በመንገድ ላይ እንቅስቃሴዎች መቆጣጠሪያ የደህንነት ካሜራ (CCTV) ክትትል እንደሚደረግ ለጣቢያችን አስረድተዋል።

በተጨማሪም በዓሉ በሚከበርባቸው ቦታዎች ዐቃቤ ሕግ፣ ዳኛና መርማሪ ፖሊሶችን የያዘ ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት መቋቋሙን ጨምረው ገልፀዋል።

የፊቼ ጨንበላላ በዓል ከመጋቢት 18 እስከ መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን በዓሉ ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስም የተወሰኑ መንገዶች የሚዘጉ ይሆናል ነው የተባለው።
@Yenetube @Fikerassefa
👍14👎53
የዓለም ንግድ ድርጅት፣ አባል አገራት በኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ዙሪያ አስተያየታቸውን እስከ ሚያዝያ 8 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።

ድርጅቱ፣ ኢትዮጵያና አባል አገራት በገበያ ተደራሽነት ዙሪያ የሚያደርጓቸውን የሁለትዮሽ ድርድሮች በቶሎ እንዲያጠናቅቁና ይህን ድርድር ማድረግ የሚፈልጉ አባል አገራት እስከ ሚያዝያ ሦስተኛ ሳምንት ፍላጎታቸውን በጽሁፍ እንዲያሳውቁ አሳስቧል። ድርጅቱ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ላይ በርካታ አገራት ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመኾን የወሰደቻቸውን ርምጃዎች ቢያደንቁም፣ አንዳንድ አባል አገራት ግን የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ በተጨባጭ ውጤት እየተለካ መታየት አለበት እንጅ በጊዜ ገደብ መታሠር የለበትም የሚል አቋም ማንጸባረቃቸውን ድርጅቱ ጠቅሷል። ኢትዮጵያ በቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት ድርጅቱ ካሜሩን ላይ በሚያደርገው ጉባኤ የድርጅቱ ሙሉ አባል ለመኾን ጥረት በማድረግ ላይ ናት።

@YeneTube @FikerAssefa
👍7👎21
2👍1