YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ላጤውባለትዳር
የፊልም እና የቴአትር ባለሞያዎች የተጣመሩበትን ይሄንን ቴአትር ማክሰኞ ምሽት በ 11:30 በብሔራዊ ቴአትር መጥተው ይመልከቱ🔥🔥
#ተዋንያን
ቸርነት ፍቃዱ 🔥
ናርዶስ አዳነ🔥
የምስራች ግርማ🔥
ምትኩ በቀለ🔥
ዳንኤል ተገኝ🔥
ሀና ጌትነት🔥
#ደራሲ ዳንኤል ሙሉነህ
#አዘጋጅ ሔኖክ ብርሀኑ
#HK Entertainment ተዘጋጅቶ የቀረበ😍
ለበለጠ መረጃ :_09 21 59 34 71
@H2n8k
ጆ-ባይደን የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አሜሪካ እንዲጎኙ ግብዣ አቀረቡ

ጆ ባይደን እና ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በሳዑዲ አረቢያ ተገናኝተው ተወያይተዋል
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዓመቱ መጨረሻ በፊት የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን አሜሪካ እንዲጎበኙ ግብዣ አቀረቡ።

ጀ-ባይደን ይህን ያሉት ሁለቱ መሪዎች በሳዑዲ አረቢያ እየተካሄደ ባለው የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማት እና ደህንነት ጉባዔ ላይ ባደረጉት የጎንዮሽ ወይይት ነው።

ጆ-ባይደን ለኢሚሬትስ አቻቸው "ዛሬ የሚያጋጥሙህ ፈተናዎች አብረን የምናሳልፈውን ጊዜ በጣም አስፈላጊ ያደርገዋል፤ ወደ አሜሪካ በይፋ ልጋብዝህ እፈልጋለሁ" የሚል ጥያቄ እንዳቀረቡላቸውም ነው ዋሽንግተን ፖስት የዘገበው።

የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ሳዑዲ አረቢያ ናቸው
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የቅርቡ የወንድማቸው ህልፈትን ተከትሎ በግንቦት ወር የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የአቡ ዳቢ ገዥ የሆኑት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ፤ በአፍሪካ ቀንድ፣ በሰሜን አፍሪካ እና ከዚያም በላይ ባሉት ፖሊሲዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር የቻሉ አንደሆኑ ይገራል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ባስመዘገበቸው ፈጣን እድገት “ትንሿ ስፓርታ” እስከ በመባል ለሰደረሰችው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የበስተጀርባ ኃይል ናቸው ተብለው በበረካቶች የሚሞካሹ መሪ ናቸው።

ከሁለት አስርት ዓመታት በኃላ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና እስራኤል መካከል ተጋርዶ የነበረው የዲፕሎማሲ ግርዶሽ ሰብረው በመግባት አረብ ኢሚሬትስን ከአስራኤል ጋር ወዳጅነት የፈጠረች የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር በማድረግ በኩል ጉልህ የዲፕሎማሲ ሚና የተጫወቱ መሪም ናቸው ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ፡፡

በውሳኔው ደስተኛ ያልሆነችው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፤ የባይደን አስተዳደር ውሳኔውን ደግሞ እንዲያጤንና እንዲቀለብስ ስትወተውት መቆየቷም አይዘነጋም። የአረብ ሊግም በተመሳሳይ የሃውቲ አማጽያን በሽብርተኝነት እንድትፈርጅ አሜሪካን ጠይቋል።

ይህን ተከትሎም አሜሪካ የሃውቲ አማጽያንን በድጋሚ በአሸባሪነት ልትፈርጅ መሆኗ እስከ ቅርብ ጊዜ ስትገልጽ ነበር።

እናም የአሁኑ መሪዎቹ ውይይት በእነዚህ ሁሉም ጉዳዮች ላይ በመምከርና መፍትሄ በማበጀት አቡዳቢ-ዋሽንግተን ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ያሻግራል ተብሎ ይጠበቃል።

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አረብ ኤሚሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና መረጋጋት ላይ ዋነኛ አጋር ሆና ተቀጥላች አሉ

የኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ለ1443 የሂጅራ ስኬት ለሳውዲ ንጉስ የደስታ መልእት አስተላልፈዋል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ሀገራቸው በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና መረጋጋት ላይ ዋነኛ አጋር ሆና እንደምተጥል አረጋገጡ።

የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማትና ደህንነት ጉባዔ በዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ ጄዳህ ተካሂዷል።

በጉባዔው ላይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን እና የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድን ጨምሮ ሌሎችም የገልፍ ሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ለሩሲያ፣ ለቻይናና ለኢራን ክፍተት አንሰጥም- ፕሬዝዳንት ባይደን 

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት፤ ሀገራቸው በቀጠናው ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ እንዲሁም አለም አቀፋዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እና የጋራ ችግሮችን ለመጋፈጥ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል።

አረብ ኢሚሬትስ በአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ የምትከተለው ፖሊሲ በሚዛናዊነት ላይ የተመሰረተ እና ከአለም ሀገራት ጋር የጋራ የጥቅም መሰረትን በማስፋት ለሀገራዊ ልማትና ሰላምና መረጋጋት ግቦችን ማስፈን መሆኑን አስረድተዋል።

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ እንዳሉት "በቀጠናችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ትልቅነት ለማንም የተሰወረ አይደለም” ያሉ ሲሆን፤ “እንዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እና የህዝቦቻችንን ምኞት ለማሳካት የጋራ ጥረቶችን ማጠናከር ይጠይቃል” ብለዋል።

“ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ያገናዘበ ሚዛናዊ አካሄድ መከተልን ይጠይቃል” ያሉት መሃመድ ቢን ሰልማን፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ለመቋቋም የካርበን ልቀተን መቀነስ ልቀትን መሰረት ያደረገ አሰራር መከተላቸውን አስታውቀዋል።

ጆ-ባይደን የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አሜሪካ እንዲጎኙ ግብዣ አቀረቡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ጆ ባይደንም በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ለመሰረተ ልማት እና ለንጹህ የኃይል ልማት በቢሊየን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ኢንቨስት እናደርጋለን ብለዋል።

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በበኩላቸው፤ ቀጠናው እና ሀገሮቻችን አሁን ዓለማችንን እያጋጠመ ላለው ችግር መፍትሄ ማፈላግ ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

Via Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተመራቂ ስለ እናቱ ↙️

ለዚህ የደረስነው ኢትዮጵያ ኖራ ስላስተማረችን ነው ሃገራችን ኖራ ስላስተማረችን ነው እየተሸከሙ ያስተማሩ እናቶች ነው ያሉን እየታገሉ ያስተማሩ እናቶች ነው ያሉን ዛሬ እንዲህ አምሮብን ዛሬ አጊጠን ዛሬ ለብሰን ስንታይ ብርቱዎች ሆነን ሳይሆን ብርቱ የሆኑ እናቶች ስላሉን ነው።

#ሼር
@Yenetube @Fikerassefa
እንኳን ደስ አለን

18ተኛ የአለም አትሌቲክስ ሻፒዮና
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች ለተሰንበት ግደይ በ10ሺ ሜትር ፍፃሜ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን አስገኝታለች።

እንኳን ደስ አለን
እንኳን ደስ አለን

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። ለተሰንበት ግደይ በ10ሺ ሜትር ፍፃሜ የወርቅ ተሸላሚ ሆናለች።

እንኳን ደስ አለን
በ400 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የትራንስፎርመር ፋብሪካ ተመረቀ!

በሰሜን ሽዋ ዞን አንጎላላና ጠራ ወረዳ በ400 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባ የትራንስፎርመር ማምረቻና መጠገኛ ፋብሪካ ተመርቋል።ዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ የንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ቴዎድሮስ ወልደገብርኤል ፋብሪካው በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የትራንስፎርመር እጥረት በመፍታት ለማገዝ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው ብለዋል።

የትራንስፎርመር ማምረቻና መጠገኛ ፋብሪካ በዓመት ከ700 እስከ 1 ሺሕ ትራንስፎርመሮችን ማምረት የሚችል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።እንዲሁም የተበላሹትን በመጠገን ደግሞ ከ1 ሺሕ 500 እስከ 2 ሺሕ የመጠገን አቅም እንዳለው ገልፀዋል።

ፋብሪካው በእንጅነሪንግ ዘርፍ ለተመረቁ 80 ለሚሆኑ ቋሚና 100 ለሚሆኑ ጊዜያዊ የሥራ እድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።ከዚህ ባለፈም በከፍተኛ ወጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን ትራንስፎርመር በማስቀረት በዓመት ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለማስቀርትም ያግዛል ተብሏል።ፋብሪካው በውስጡ አራት የማምረቻ፣ የመገጣጠሚያና የመጠገኛ ወርክ ሾፖች እንዳሉት ተጠቁሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
ታምራት ቶላ በማራቶን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ!

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ እና ይበር ሜዳሊያዎችን በወንዶች ማራቶን አግኝታለች።

ኢትዮጵያን የወከለው ታምራት ቶላ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያውን አጥልቋል።

ሌላው በውድድሩ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ ሙስነት ገረመው የብር ሜዳሊያ አግኝቷል።

በዚህም የወንዶችን ማራቶን ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያውን ጠቅልላ ወስዳለች።


እንኳን ደስ አለን!

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ብራቮ፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተሰራ የግል ፋይናንስ አስተዳዳሪ መተግበሪያ

በጀቶን በብቃት ለማውጣት ፣ የገንዘብ ልውውጦን በቀላሉ ለመከታተል ፣ የፋይናንስ እውቀቶንም ለመጨመር አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው ይጠቀሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችንም ቻናላችን በመቀላቀል በቀለላሉ ያገኙ
https://tttttt.me/birravo
Forwarded from YeneTube
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለትምርት አልገባው ላለ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ
እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን
👉እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
👉እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል
👍ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
https://tttttt.me/meritibe
👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
Forwarded from YeneTube
Room.et

ከ 200 ብር ጀምሮ ጥራት ያላችውን የሆቴል ክፍሎችን ባሉበት ቦታ ሆነው ይያዙ።

Room.et ተጠቅመው ሲይዙ፣ የሆቴል እና የገስት ሃውስ ክፍሎች በጥራት ፤ በዋጋ፤ ርቀት እና አገልግሎት አይነት አነጻጽረው በካሽ፤ በቴሌብር እና አሞሌ ክፍያ መፈጸም ይችላሉ።

በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና የክልል ከተሞች እንገኛለን። 9883 ይደውሉ ወይንም

Room.et መተግበሪያ ያውርዱ
👉🏻 https://bit.ly/3bMJou0

ትክክለኛውን የሩም ማዕበራዊ ገፆች ይከታተሉ።
TelegramTiktokInstagram
#ማራ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#ሙሉ_በሙሉ_እውነተኛ_ታሪክ

የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት እንስት ይቅርታ ጠይቂና የሞት ፍርዱ ይነሳልሽ ብትባል እንቢ አሻፈረኝ ትላለች፡፡

ምሕረትን እንዳትቀበል ያደረጋት፣ ሕይወቷን ያስመረረውና የሞት ጽዋውን ያሰኛት ምክንያት ምን ይሆን?

የሴተኛ አዳሪዎች ንግስት፣ የልኡላን ቅምጥ የሆነችው እንስት በሴቶች የሚደረጉ አስገራሚ አብዮቶች ምልክት ተብላ ተሞግሳለች፡፡ ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ የሆነው #ማራ መጽሐፍ እነሆ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

📗📒📕
“ከእስር ቤት የምትወጪበት አንድ ተስፋ ተገኝቷል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ የይቅርታ መልዕክት ፅፈሽ ይቅርታ እንዲደረግልሽና ሁለተኛ ወንጀል ላለመስራት ቃል የምትገቢ ከሆነ ከእስር ቤት እንደምትወጪ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”

“አልፈልግም። በምሕረት ብወጣም መግደሌን አላቆምም!”

“አንቺ ወንጀለኛ ነሽ!”

“አይደለሁም! እናንተ ሁላችሁም ናችሁ ወንጀለኞች፡፡ አባቶች፣ አጎቶች፣ ባሎች፣ የሴተኛ አዳሪ ደንበኞች፣ ዶክተሮች፣ ጋዜጠኞች፣ በሁሉም ሙያ ላይ ያላችሁ ሁላችሁም ወንዶች! አባቴ፣ አጎቴ፣ ባሌ… ሁላችሁም ሴተኛ አዳሪ ሆኜ እንዳድግ አስተምራችሁኝ አልፋችኋልና ወንጀለኞች ናችሁ!!!”
📚#ከመጽሐፉ_የተወሰደ

#ማራ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና መጽሐፍ ሽልማቶችን ለማግኘት ቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ።)

*
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ላጤውባለትዳር
የፊልም እና የቴአትር ባለሞያዎች የተጣመሩበትን ይሄንን ቴአትር ማክሰኞ ምሽት በ 11:30 በብሔራዊ ቴአትር መጥተው ይመልከቱ🔥🔥
#ተዋንያን
ቸርነት ፍቃዱ 🔥
ናርዶስ አዳነ🔥
የምስራች ግርማ🔥
ምትኩ በቀለ🔥
ዳንኤል ተገኝ🔥
ሀና ጌትነት🔥
#ደራሲ ዳንኤል ሙሉነህ
#አዘጋጅ ሔኖክ ብርሀኑ
#HK Entertainment ተዘጋጅቶ የቀረበ😍
ለበለጠ መረጃ :_09 21 59 34 71
@H2n8k
ብሔራዊ ባንክ አርብቶና አርሶአደሮችን የሚጠቅሙ አሰራሮችን ገቢራዊ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አርብቶና አርሶ አደሮች የቀንድ ከብቶችን ጨምሮ ደን፣ የመሬት መጠቀሚያ ደብተር፣ ግመልንና የመሳሰሉትን ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን በማስያዝ ብድር ማግኘት የሚችልበትን ሁኔታ እያመቻቸ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) እንዳስታወቁት በቅርብ ጊዜም የዚህ ተግባር ማሳያ የሆነና በርካቶችን የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ የተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ዋስትና በማድረግ መበደር የሚቻልባቸው መንገዶችን የሚደነግግ አዋጅ ወጥቷል፡፡እንደዶ/ር ይናገር ገለፃ፣ ይኼ ማለት አርብቶና አርሶ አደሩ ፎቅና ሌሎች ንብረቶችን ማስያዝ ሳይጠበቅበት በተንቀሳቃሽ ንብረቶቹ ብድር ማግኘት ይችላል፡፡

ዶ/ር ይናገር ቅዳሜ፣ ሐምሌ 9፣2014 ዓ.ም የአሐዱ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በይፋ ሥራ መጀመሩን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ ውስጥ የብድር አገልግሎት የሚያገኘው ሕዝብ ቁጥር አነስተኛ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የሁሉም ንግድ ባንኮች ቁጥር ተደምሮ ከባንክ ብድር የሚወስደው ደንበኛ ቁጥር ከ320 እስከ 330 ሺ እንደማይበልጥ ያሳወቁት ይናገር ደሴ፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.6 ሚሊዮን ተበዳሪዎች እንዲሁም የሊዝ ኩባንያዎች ወደ 300 ሺኅ ተበዳሪዎች አሏቸው ብለዋል፡፡በድምሩ በአገሪቱ ካሉ ባንኮች፣ ማይክሮ ፋይናንስና ሊዝ ኩባንያዎች አጠቃላይ የብድር ተጠቃሚ የሆነው ደንበኛ ቁጥር ከ6 ሚሊዮን ብዙም የማይበልጥ እንደሆነ ዶ/ር ይናገር ተናግረዋል፡፡

ይኸው አሃዝ፣ 110 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት አገር ውስጥ የብድር ተጠቃሚው ቁጥር አነስተኛ እንደሆነና በዚህ ሁኔታም መቀጠልና የአገሪቱን እድገት ማረጋገጥ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
ብድር ወደ ገጠርና ከተማ፣ ወደ አርሶና አርብቶአደሮች ገብቶ፣ በተለይም በርካታ የሥራ እድል መፍጠር የሚችሉትን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መደገፍ እንደሚገባም አበክረው ተናግረዋል፡፡በአገሪቱ ያሉ ተበዳሪዎችም ከፍተኛና መካከለኛ ባለሃብቶች እንደሆኑ አንስተዋል፡፡

በተለይም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የባንክ ደብተር የሌለውና አገልግሎቶቹን የማያገኝ ሰው ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ የተናገሩት ዶ/ር ይናገር፣ ከባንክ አገልግሎት ውጪ ያሉትን ተደራሽ በማድረግ አሐዱ ባንክ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ፋሲል ፋርማስ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ በሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ላይ በሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ሲሆን በአደጋው በሰው ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ 300 ሺህ ብር የተገመተ ንብረት መውደሙን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ አደጋዉ ከዚህ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህ ሂደት ከአምስት ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን ተችሏል።

ህይወቱ ያለፈዉ የ40 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን የእሳት አደጋዉ በተከሰተበት ወቅት በቆጥ ላይ አልጋ ላይ ተኝቶ ነበረ። በሌላ በኩል ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ሶስት ሰዎች በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አምቡላንስ የመጀመሪያ ህክምና ተደርጎላቸዋል።


Via:- #ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
በታንዛኒያ እስር ላይ የነበሩ 126 ኢትዮጵያዊያን ከእስር ተፈተው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ፡፡

ታንዛኒያን አቋርጦ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረግ ህገ-ወጥ ጉዞ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር እየዋሉ ለእስር እንደሚዳረጉ ይታወቃል።

ከነዚህም መካከል በሁለተኛው ዙር 126 ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአገሪቱ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመቀናጀት ወደ ኢትዮጵያ መሸኘታቸው ተጠቁሟል።

የተቀሩትም በቀጣይ በተቀመጠላቸው የጉዞ ፕሮግራም መሠረት ወደ አገር ቤት መመለስ እንዲችሉ እየተሰራ ይገኛል::

በርካታ ኢትዮጵያዊያን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመታለል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከፍለው እጅግ አደገኛ የሆነ ህገ ወጥ ጉዞ የሚያደርጉ ሲሆን በመንገዳቸው ላይ ለርሃብ፣ እስር፣ ስቃይ ብሎም ለሞት እንደሚዳረጉ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ከዚህ ቀደም በመጀመሪያ ዙር ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም 20 ዕድሜያቸው ከ11 እስከ 17 የሚሆኑ በታንዛኒያ በቁጥጥር ሥር ውለው በእስር የቆዩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በካማሺ ዞን በጸጥታ ችግር ምክንያት ማዕድን የማውጣት ሥራ መቋረጡ ተገለጸ!

በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል በሚገኘው ካማሺ ዞን በርካታ ማዕድናት ቢኖሩም፣ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት አሁን ላይ ማዕድን የማውጣት ተግባር ተቋርጦ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።

በዚህም ከአዲስ አበባ፣ ከአማራ እና ከኦሮሚያ ክልል መጥተው ሲሠሩ የነበሩ በርከት ያሉ ባለሀብቶች ሥፍራውን ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በማኅበር ተደራጅተን ከባለሀብቶች ጋር በመሥራት ነበር የምንጠቀመው ሲሉ ገልጸው፣ አሁን ላይ ግን በማኅበር ተደራጅተው እየጠበቁ ቢሆንም ሊሠራ የሚችል ባለሀብት ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3Pn2x52

@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን በጎሳ ግጭት የተነሳ የሟቾች ቁጥር 65 ደረሰ

በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ለቀናት በዘለቀው የጎሳ ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 65 መድረሱን የግዛቱ የጤና ኃላፊ አስታዉቀዋል። በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በሃውሳ እና በቢርታ ብሄረሰቦች መካከል በነበረው ግጭት ከተግደሉት ሰዎች በተጨማሪ 150 የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን ገማል ናስር አል ሰይድ በትላንትናዉ እለት ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ በጥይት የተመቱ እና በስለት የተወጉ ወጣቶች እንዳሉበት ተነግሯል፡፡በብሉ ናይል የሚገኙ ሆስፒታሎች የተራቀቁ መሳሪያዎች እና የህይወት አድን መድኃኒት እጥረት ስላለባቸዉ በዋና ከተማዋ ካርቱም የሚገኙ ባለስልጣናት 15 ክፉኛ የተጎዱ ሰዎችን በአየር መጓጓዣ በማንሳት እንዲረዷቸው አል ሰይድ አሳስበዋል።

ቅዳሜ ዕለት ባለሥልጣናቱ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 31 መሆኑን ተናግረዋል ።በአካባቢው መረጋጋት ለማምጣት ባለስልጣናት ወታደራዊ ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎችን አሰማርተዋል። እንዲሁም ግጭቱ በተከሰተባቸው የግዛቱ ዋና ከተማ ሮዝሬስ እና አል-ዳማዚን ከተሞች ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡

የብሉ ናይል ገዥ አህመድ አል ኦምዳ ለአንድ ወር ማንኛውንም ስብሰባ ወይም ሰልፍ የሚከለክል ትእዛዝ አስተላልፈዋል።


Via:- #ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
ሱዳን በመተማ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን መንገድ ከፈተች

ውሳኔው በሀገራቱ መካከል ለተቀሰቀሰው ውጥረት“አፋጣኝ እና ዘላቂ”መፍትሔ ለማበጀት ያለመ ነው ተብሏል
በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ ሁለቱም ሀገራት የሚያዋስነውና በገላባት እና መተማ መካከል የሚገኘው የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ኬላ ለአንድ ወር ያክል ዝግ ሆኖ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ድንበሩ ከትናንት እሁድ እለት ጀምሮ ክፍት ማድረጓንም ነው ሱዳን ያስታወቀቸው፡፡
ሱዳን ድንበሩን ክፍት ያደረገቸው በጄነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን የጸጥታ እና መከላከያ ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ተከትሎ ነው፡፡

ውሳኔው የሁለቱ ሀገራት አመራሮች በድንበር አካባቢ ለተቀሰቀሰው ውጥረት “አፋጣኝ እና ዘላቂ” መፍትሔ ለማበጀት የጀመሩትን ውይይት መነሻ በማድረግ እንዲሁም “የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሱዳን ግዛት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከኢትዮጵያ በኩል ለታየው መልካም ፈቃድ” የተላለፈ ምላሽ መሆኑን ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
መግለጫው “እውቅና ባለው ህጋዊ አሰራር መሰረት የገላባት ድንበር ማቋረጫ በሁለቱ ሀገራት መካከል እንቅስቃሴ እንዲኖር በሚል ከዛሬ ሰኔ 17 ጀምሮ እንዲከፈት ተወስኗል” ብሏል።

"በሁለቱ ሀገራት መካከል ጥብቅ ቅንጅት በማድረግ የዓለም አቀፍ የድንበር ቁጥጥር እንዲጠናከር እና የትኛውም የታጠቁ ሃይሎች በሁለቱ ሀገራት መካከል እንዳይንቀሳቀሱ ተወስኗል" ሲልም አክሏል መግለጫው፡፡


በድንበር አካባቢ 6 የሱዳን ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት በመንገሱ ምክንያት ገላባት ኬላ ከሰኔ 27 ቀን 2022 ጀምሮ ዝግ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ወታደሮች ድንበር ጥሰው መግባታቸውን እና ትንኮሳ መፈጸማቸውን መግለጹ ይታወሳል፡፡
በቅረቡ በናይሮቢው የኢጋድ አባል ሀገራት የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሱዳኑ መሪ አል ቡርሃን ለዘመናት የዘለቀውን ጉርብትናንና ወዳጅነትን በማስቀደም የተፈጠረው ውጥረት በውይይት ለመፍታት በሚቻልባቸው መፍትሄዎች ዙሪያ መምከራቸውም የሚታወስ ነው፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
#የስኬት_አቦጊዳ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

አ-ቦ-ጊ-ዳ- ብሎ ስኬትን ከስር መሰረቱ አስጀምሮ የሚያስጠና፣ አስጠንቶም የስኬት ዲግሪን የሚያስጭን ምርጥ መጽሐፍ፡፡

አስተሳሰብ ላይ፣ ጽናት ላይ፣ ውጤታማነት ላይ እንዲሁም ስኬትና ገንዘብ ላይ ልክ እንደ የኔታ መሰረት አስይዞ ለውጤታማነት የሚያበቃ!

ከ2 መቶ ሚሊየን በላይ ጎብኚዎች ባሏቸው የስኬት አስተማሪዎች የተዘጋጀ፣ ከፍተኛ ሽያጭ የተቀዳጀ መጽሐፍ ነው፡፡

🤔አስተሳሰብ🧠

ብዙውን ጊዜ የአስተሳሰብህ እስረኛ በመሆንህ አስተሳሰብህን ካልቀየርክ በስተቀር በሕይወትህ ውስጥ ያለን ምንም ነገር መቀየር አትችልም፡፡ አስተሳሰብህ አልቀየር ብሎ አስቸግሮሀል? እነሆ የስኬት አቦጊዳ… አስተሳሰብ ምእራፍ ይረዳሀል- አስተሳሰብህን ስትቀይር ሕይወትህን ትቀይራለህ!

💰💰ገንዘብና ስኬት🏆🎖🏅

የሚሊየን ብር ሀሳቦች የሚገኙት በአንተ ውስጥ ነው፡፡ አንተ ብዙ ሀሳቦችን በፈጠርክ ቁጥር የሚሊዮን ብር ሀሳብ የመፍጠር እድልህ ይጨምራል፡፡ የሚያስፈልግህ ትንሽ ለወጥ ያለ ሀሳብ ማሰብ ወይም በተፈጠረው ሀሳብ ላይ ትንሽ ነገር መጨመር ነው፡፡ ይህ የስኬት አቦጊዳ መጽሐፍ አንዱ ተግባር ደግሞ ውስጥህ የተደበቁ የሚሊዮን ብር ሀሳቦችን እንድታወጣ መርዳት ነው- ገንዘብና ስኬት!

ስኬታማ የሚያደርጉ መርሆችን ልክ እንደ አቦጊዳ ጥጥት የሚያደርጉበት መጽሐፍ!

#የስኬት_አቦጊዳ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

📗📒📕
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጻችንን ይቀላቀሉ።)

👇
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun

Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/