YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለትምርት አልገባው ላለ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ
እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን
👉እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
👉እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል
👍ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
https://tttttt.me/meritibe
👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ላጤውባለትዳር
የፊልም እና የቴአትር ባለሞያዎች የተጣመሩበትን ይሄንን ቴአትር ማክሰኞ ምሽት በ 11:30 በብሔራዊ ቴአትር መጥተው ይመልከቱ🔥🔥
#ተዋንያን
ቸርነት ፍቃዱ 🔥
ናርዶስ አዳነ🔥
የምስራች ግርማ🔥
ምትኩ በቀለ🔥
ዳንኤል ተገኝ🔥
ሀና ጌትነት🔥
#ደራሲ ዳንኤል ሙሉነህ
#አዘጋጅ ሔኖክ ብርሀኑ
#HK Entertainment ተዘጋጅቶ የቀረበ😍
ለበለጠ መረጃ :_09 21 59 34 71
@H2n8k
ዛሬ ረፋዱን የዲላ ከተማ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ

👉በዲላ ከተማ የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አካላት ገብተዋል

በቅርቡ የጌዴኦ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ በዞኑ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሁከት ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የዞኑን ሰላም ለማስጠበቅ ሲባል የተለያዩ ዉሳኔዎችን እያሳለፉ እንደሆነ ታዉቋል። በዚህም በዞኑ የባለሁለት ተሽከርካሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ አብርሀም መኩሪያ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በጌዴኦ ዞን ሊፈጠር ይችላል ተብሎ የታሰበዉን የጸጥታ ስጋትም ለማስቀረት የፌዴራል እና የክልል የጸጥታ አካላት እንደገቡም ሰምተናል። የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት ረፋዱን ከነበረዉ የከተማዋ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ ዉጪ ሰላም እንደሆነ ገልጸዋል።

በዛሬዉ እለትም ረፋዱን ስጋት ያደረበቸዉ የንግድ ሱቆች ተዘግተዉ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተጨማሪም ከዲላ ከተማ የሚነሱ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እጥረት እንደነበርም ገልጸዋል።

የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀው ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላት እንዳሉ አስታዉቆ ነበር። ይህን ለመከላከልም የፌዴራል እና የክልል የጸጥታ ሀይሎች በዞኑ እንደሚገኙ ተሰምቷል።


Via:- ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
ኢራን ኒውክለር ቦንብ ለመስራት የሚያስፈልጋት ነገር ቢኖር የፖለቲከኞቿ ውሳኔ ብቻ ነው ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡

በቴክኒክ እና በሌሎች የዘርፉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቿን አጠናቀዋል ያሉት እነኚህ ባለሙያዎች፣ የኒውክለር ቦንቡን ለማምረት የፖለቲከኞች ውሳኔ ብቻ እየተጠበቀ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡

ከማል ካራዚ የተባሉት የሃገሪቱ ከፍተኛ የደህንነት አማካሪ ሃገሪቱ በጥቂት ቀናት ዩራኒየም የማበልፀግ አቅሟ ወደ 60 ከመቶ መድረስ መቻሉን አስታዉሰዋል፡፡
በቀጣይም 90 ከመቶ ለማድረስ ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

የባይደንን ጉብኝት ተከትሎ ይህንን አስተያየት የሰጡት ከማል ካራዚ፣ ኢራን ሃገራቸው የፖለቲከኞቿ ውሳኔን ማጣቷ እንጂ ኒውክለርን ለመታጠቅ እሩቅ ሆና አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከሰሞኑ አሜሪካ እና እስራኤል በሃይልም ቢሆን የኢራንን የማብላያ አቅም ለመስበር እያቀዱ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
አትሌት ጎይቲቶም ገብረሥላሴ በ18ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች ማራቶን አሸነፈች

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጎይተቶም ገብረሥላሴ በ18ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች ማራቶን 1ኛ በመውጣት ለሀገሯ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

@Yenetube @Fikerassefa
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሰመራና አጋቲና ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ ወደ 9 ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ወደሚፈልጉት አካባቢ እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ።

መሠረቱን በትግራይ  ላይ ያደረገው የራእይ ፖርቲ ሊቀ መንበር አቶ ሊላይ ኃይለማርያም የሕወሓት ኃይሎች የአፋር ክልሏን አባላ ከተማን በከባድ መሣሪያ ሲደበድቡ ሕዝቡ በአራቱም አቅጣጫ ተደናግጦ በመሸሹ እና በኋላ የክልሉ መንግሥት ከየበረሃው እነዚህን ሰዎች ከያሉበት አሰባስቦ ወደ ካምፕ ያስገባቸው መሆናቸውን ጠቅሰው የችግሩ መነሻ ሥረ መሠረት እና ከሕዝብ አገኘነው ያሉትን መረጃ ለ DW ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ ) ከግንቦት 15 እስከ 20 ቀን 2014 ዓ. ም ፣ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል አዋሳኝ የሆኑ ሦስት የአፋር ክልል ወረዳዎች ፣ ማለትም ከአባላ ፣ከኮነባ፣ ከበራሕለ ታኅሣሥ 2014 ዓ. ም የተያዙ 9 ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች በተለያዩ አካላት ድጋፍ እየተደረገላቸው መቆየታቸውን ተናግሮ ነበር። ኢሰመኮ እነዚህ ሰዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲለቀቁም በወቅቱ ጠይቋል። ድርጊቱ "በብሔር ማንነት ላይ የተመሠረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እሥር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል፣ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸውም እስኪመለሱ ድረስ በካምፑ ውስጥ ለመቆየት የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖሩ በሙሉ ፈቃደኝነት ያለ እንቅስቃሴ ገደብ ሊሆን ይገባል" በማለት ሰዎቹ ከመኖሪያቸው አካባቢ እንዲወጡና በካምፖቹ ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉት ከፈቃዳቸው ውጪ መሆኑን ገልጾ ነበር።

ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታ እየተደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ በኮሚሽኑ የክትትል እና ምርመራ የሪጅን ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ ሰላማዊት ግርማይ ሥራው በሂደት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።"የሚመለሱበት ኮሚቴ ተዋቅሯል። የየከተሞቹ ከንቲባዎች ሰዎቹ አነጋግረዋቸዋል። መመለስ የሚፈልጉበትን ሁኔታ ዝርዝሩን ለይተዋል" ብለዋል።

"ክልሉ በወቅቱ የወሰደው እርምጃ ትክክል ነው" ያሉት አቶ ሊላይ "ሕዝቡ ተመልሶ ወደ ከተማው [አባላ] እንዳይሄድ አካባቢው በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ነበር ፣ በቅርብ ቀን ሄጄ እንዳየሁት አባላ ወደ ምድረ በዳ ተቀይሯል። በሙሉ ከተማው ወድሟል ፣ ሕዝቡም ቢመለስ የት ይገባል ፣ ምን ይበላል የሚለውም ለክልሉ ምንግሥት ትልቅ ጥያዌ ነበር" ብለዋል።ማሕበራዊ መሠረቱን ትግራይ ያደረገው የራእይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሊላይ ኃይለማርያም በካምፕ ውስጥ ያሉት ሰዎች አሁን የሚገኙበትን ሁኔታ ሲገልጹ "መታወቂያ እያወጡ እየሰጧቸው ነው። አሁን ለ አምስት ሺህ ሰው መዝግበው መታወቂያ እየሰጡ ነው። ከዚያም ባሻገር የአፋር ሽማግሌዎች እና ትግርኛ ተናጋሪ የአገር ሽማግሌዎች ሰሞኑን ውይይት ያካሂዳሉ" በማለት የተለቀቁ ሰዎች መኖራቸውንም ጭምር ተናግረዋል።

"እነዚህ ሰዎች ወደዚያ ተመልሰው ሰላማዊ ኑሯቸውን የሚኖሩበትን ፣ የሚቋቋሙበትን፣ እርዳታ ብናደርግላቸው" ሲሉም የተማጽኖ ጥሪ አቅርበዋል።
ስለ ጉዳዩ  ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተጨማሪ ማብራሪያና ምላሽ ለማግኘት ደጋግሜ ጥረት ባደርግም ለጊዜው አልተሳካም።አቶ ሊላይ እንዳሉት ከሆነ ግን እንዚህን ሰዎች የመደገፉ ጫና የክልሉ መንግሥት ጫንቃ ላይ ያረፈ ነው። ብዙ ነገሮችም እየተስተካከሉ መሆኑን አብራርተዋል።በወቅቱ ኢሰመኮ አነጋግሯቸው የነበሩት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባለሥልጣናት ካምፕ ውስጥ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ለደህንነታቸው ጥበቃ እና ከፀጥታ ሥጋት ጋር በተያያዘ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን ለመለየት በሚል የእንቅስቃሴ ገደብ መጣላቸውን ገልፀው ነበር።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሪገን 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች የ1500ሜትር ፍፃሜ ጉዳፍ ፀጋዬ የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጲያ አስገኝታለች።ኬንያዊቷ አትሌት ስታሸንፍ ፍሬወይኒ ሀይሉ 4ኛ ሂሩት መሸሻ 12ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

እንኳን ደስ አለን!🇪🇹

@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ!

በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች በመጨረሻዎቹ ሴኬንዶች ለተሰንበት ግደይ ሄለን ኦብሪን በክርን መታታለች በሚል ኬንያ ለዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያስገባው ቅሬታ ውድቅ ሆኗል።

ለተሰንበት ሄለንን አስቀድማ የቀደመቻት በመሆኑንና የመቅደሟን ዕድል መጠቀም በሚል ክሱ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል ተብሏል።

Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
ሱዳን፤ በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር መካከል የትኛውም ታጠቂ ሃይል እንዳይንቀሳቀስ መወሰኑን አስታወቀች!

በጄነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን የጸጥታ እና መከላከያ ምክር ቤት ሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በመተማ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛትን መንገድ እንዲከፈት ተወስኗል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ጥብቅ ቅንጅት በማድረግ የዓለም አቀፍ የድንበር ቁጥጥር እንዲጠናከር እና የትኛውም የታጠቁ ሃይሎች በሁለቱ ሀገራት መካከል እንዳይንቀሳቀሱ ምክር ቤቱ ወስኗል።

ውሳኔው የሁለቱ ሀገራት አመራሮች በድንበር አካባቢ ለተቀሰቀሰው ውጥረት “አፋጣኝ እና ዘላቂ” መፍትሔ ለማበጀት የጀመሩትን ውይይት መነሻ በማድረግ እንዲሁም “የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሱዳን ግዛት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከኢትዮጵያ በኩል ለታየው መልካም ፈቃድ” የተላለፈ ምላሽ መሆኑን ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ ፈፃሚ ጎንደር ገቡ!

በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ለጉብኝት ጎንደር ከተማ ገቡ፡፡ አምባሳደሯ አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። አምባሳደሯ በቆይታቸው በወቅታዊና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሃት ከፌዴራል መንግሥት ጋር ለሚደረገው ድርድር ተደራዳሪዎችን መሰየሙን አስታወቀ!

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተውን የእርስ በርስ ጦርነት በሰላም ለመፍታት ለሚደረገው ድርድር የሰላም ቡድን መቋቋሙን የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

የፌዴራል መንግሥት ለዚሁ ይደረጋል ለባለው ድርድር ተደራዳሪ ኮሚቴ በማቋቋም ሥራ መጀመሩን መግለፁ ይታወሳል።

ይህንም ተከትሎ የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ”ለድርድር የሚሆን ልዑክ ወደ ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ እንሆናለን” ሲሉ መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ቃላ አቀባዩ ተደራዳሪ ቡድኑ ውስጥ እነማን እንደተካተቱና ቁጥራቸውን በተመለከተ ያሉት ነገር ባይኖርም፤ በከፍተኛ ሥልጣን ደረጃ የሚገኙ አባላት ያሉት ኮሚቴም መቀቋቋሙን ግን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሃት ጋር የሚደረገው ምንም አይነት ድርድር ሊመራ የሚችለው በአፍሪካ ህብረት ብቻ መሆኑን አቋሙን ያስታወቀ አስታውቋል። ይህንንም ተከትሎ የህወሃት አመራሮች በህብረቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በማንሳት ድርድሩ በህብረቱ ጥላ ሥር ብቻ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።

“ኹሉንም የድርድር ሂደቶች ለአፍሪካ ኅብረት መስጠቱ ለእኛ በጣም ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ያሉት ጌታቸው፣ ማንኛውም ድርድር በሰላም ጥረት ውስጥ ንቁ ሚና የተጫወቱትን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ማካተት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ቃል አቀባዩ በተጨማሪም በአማራ ክልል ዘንድ የይገባኛል ጥያቄ ያለበትና፤ በአሁኑ ወቅት በአማራ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ያለው ምዕራብ ትግራይ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም በማለት መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘገባው አስነብቧል።

ከህወሃት ከምዕራብ ትግራይ በተጨማሪ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለድርድር አይቀርብም በሚል በተደጋጋሚ መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን እስካሁን የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ የለም።

የፌዴራል መንግሥት ከህወሃት አመራሮች ጋር የሚያደርገው ውይይት መቼ እንደሚጀመርም ሆነ፣ የት እንደሚደረግ ከኹለቱም ተደራዳሪ ወገኖች በኩል እስካሁን የተገለጸ መረጃ ባይኖርም፤ በህወሃት በኩል የኬንያ መዲና ናይሮቢ ትሁን የሚል ሃሳብ ቀርቧል።

Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በ2014 በጀት ዓመት ከ336 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ!

የገቢዎች ሚኒስቴር ባሳለፍነው በ2014 በጀት ዓመት ከ336 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።
ሚኒስቴሩ በዚህ በጀት ዓመት ሊሰበስብ ካቀደው 360 ቢሊዮን ብር ውስጥ 336 ቢሊዮን 710 ሚሊዮን 021 ሺህ 930 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 93.53 በመቶ ማሳካቱ ነው የተገለፀው።

አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር የብር 57 ቢሊዮን 494 ሚሊዮን 923 ሺህ 697 ብር ወይም የ20.59 በመቶ እድገት እንዳለው ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ተናግረዋል።

የተሰበሰበው ገቢ ምንጭም ከአገር ውስጥ ታክስ 196 ቢሊዮን 211 ሚሊዮን 638 ሺህ 548 ብር ሲሆን፤ ከውጭ ንግድ፣ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 140 ቢሊዮን 498 ሚሊዮን 338 ሺህ 382 ብር መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ በ2022 ሀገራዊ የታክስ አስተዳደር ተገንብቶ ሀገራዊ ወጪን በራሷ ገቢ ለመሸፈን የምታደርውን ጥረት ለማሳካት ተልእኮ የተሰጠው የገቢዎች ሚኒስቴር በስኬት ገቢን የመሰብሰብ አቅሙ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

ገቢው በሀገሪቱ በተፈጠረው ጦርነት ብዙ ተቋማት ከስራ ውጭ በሆኑበት፣ በጦርነቱ ምክንያት የንግዱ እንቅስቃሴ በተቀዛቀዘበት፣ በተለያዩ አካባቢዋች በሚፈጠሩ ግጭቶች ተቋሞች በአግባቡ ስራቸውን እንዳይሰሩ በተቸገሩበት እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ ስራውን ተረጋግቶ ባላከናወነበት ሁኔታ ውስጥ መሰብሰቡ አፈፃፀሙን የተሻለ ሊያስብለው እንደሚችል ተጠቁሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሚቀጥለው በጀት ዓመት የተልዕኮየን 60 በመቶ እፈጽማለሁ አለ!

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በ2015 በጀት ዓመት 60 በመቶ ተልዕኮውን እንደሚፈጽም አስታወቀ፡፡ኮሚሽኑ ከሦስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ ላይ የ2015 በጀት ገቢራዊ እቅዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተባባሪና አማካሪ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው ፥ በትግበራ ምዕራፍ 20 ሺህ መድረኮች በማዘጋጀት ሁለት ሚሊየን ሰዎች እናወያያለን ብለዋል፡፡በበጀት ዓመቱ ከ3 ነጥብ 2 ቢለየን በላይ ብር ከመንግስት የሚጠይቅ ሲሆን ፥ 208 ሚሊየን ብሩ ከአጋር ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡አጀንዳ ና ተሳታፊ ልየታ፣ መዋቅር ዝርጋታና መሰል ተግባራት የቀጣይ ተግባራት አቅጣጫዎች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ $60 ሚሊየን ድጋፍ አገኘ!

የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ 60 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ።የገንዘብ ድጋፉ በተለይም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ለአስቸኳይ የሰብዐዊ ርዳታ የሚውል መሆኑን ገልጿል፡፡የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በፋሚን ሪሊፍ ፈንድ በኩል ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ያደረገው ድጋፍ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባው 1.6 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የሰብዐዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የሚያስችለው ነው ተብሏል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ካንትሪ ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ተወካይ ክላውድ ጂቢዳር ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የተገኘው አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ለኢትዮጵያውያን በትክክለኛው የችግር ጊዜ የደረሰ ነው በማለት በግጭት እና በሀገሪቱ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ድጋፉ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ድጋፉ የሚሊዮኖችን ህይወት የሚታደግ በመሆኑ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ባደረጉት ድጋፍ እና አጋርነት ዳይሬክተሩ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ባለፉት አስር ሳምንታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከ3,800 በላይ በሚሆኑ የጭነት መኪኖች ከ130,000 ቶን በላይ ምግብ እና ሌሎች ህይወት አድን ሰብአዊ አቅርቦቶችን ወደ ትግራይ ክልል ማቅረቡን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተባቸው አፋር፣አማራ እና ትግራይ ክልሎች ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሰብዓዊ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያመላክታል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬዉ እለት የዲላ ከተማ እንቅስቃሴ ወደ ቀደመ ሁኔታዉ መመለሱን ነዋሪዎች ተናገሩ!

የጌዴኦ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ፤ በዞኑ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሁከት ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ በማሳሰብ የተለያዩ ቅድመ መከላከያ ዉሳኔዎችን እያሰሰለፈ መሆኑ ይታወቃል። በትናንትናው እለትም የዞኑን ሰላም ለማስጠበቅ ሲባል የባለሁለት ተሽከርካሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ የዞኑ መንግስት ኮሚኒሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ አብርሀም መኩሪያ ለብስራት ራዲዮ መናገራቸዉን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

ሆኖም በትናንትናው እለት በተለይም የዲላ ከተማ ስጋት ባደረባቸዉ ነዋሪዎች እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ ፣ የንግድ ሱቆችም ረፋዱን ተዘግተዉ እንዲሁም የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችም እጥረት እንደነበር ከነዋሪዎች ሰምተን ነበር።

በዛሬዉ እለት የዲላ ከተማ በአመዛኙ ወደ ቀደመ እንቅስቃሴዋ መመለሷን ነዋሪዎቹ ለብስራት ራዲዮ ገልጸዋል። ነዋሪዎች ምንም አይነት የጸጥታ ስጋት የለም ያሉ ሲሆን ከትናንተ ረፋድ በተሻለ በእለቱ የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደነበር አንስተዋል። ሆቴሎች እና ሌሎች የንግድ ተቋማትም ከትናንት በተሻለ በዛሬዉ እለት አገልግሎት እየሰጡ ናቸዉ ብለዋል።

ዞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀው ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላት እንዳሉ አስታዉቆ ነበር። ይህን ለመከላከል የፌዴራል እና የክልል የጸጥታ ሀይሎች በዞኑ እንደሚገኙ ብስራት ራዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@Yenetube @Fikerassefa
#የስኬት_አቦጊዳ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

አ-ቦ-ጊ-ዳ- ብሎ ስኬትን ከስር መሰረቱ አስጀምሮ የሚያስጠና፣ አስጠንቶም የስኬት ዲግሪን የሚያስጭን ምርጥ መጽሐፍ፡፡

አስተሳሰብ ላይ፣ ጽናት ላይ፣ ውጤታማነት ላይ እንዲሁም ስኬትና ገንዘብ ላይ ልክ እንደ የኔታ መሰረት አስይዞ ለውጤታማነት የሚያበቃ!

ከ2 መቶ ሚሊየን በላይ ጎብኚዎች ባሏቸው የስኬት አስተማሪዎች የተዘጋጀ፣ ከፍተኛ ሽያጭ የተቀዳጀ መጽሐፍ ነው፡፡

🤔አስተሳሰብ🧠

ብዙውን ጊዜ የአስተሳሰብህ እስረኛ በመሆንህ አስተሳሰብህን ካልቀየርክ በስተቀር በሕይወትህ ውስጥ ያለን ምንም ነገር መቀየር አትችልም፡፡ አስተሳሰብህ አልቀየር ብሎ አስቸግሮሀል? እነሆ የስኬት አቦጊዳ… አስተሳሰብ ምእራፍ ይረዳሀል- አስተሳሰብህን ስትቀይር ሕይወትህን ትቀይራለህ!

💰💰ገንዘብና ስኬት🏆🎖🏅

የሚሊየን ብር ሀሳቦች የሚገኙት በአንተ ውስጥ ነው፡፡ አንተ ብዙ ሀሳቦችን በፈጠርክ ቁጥር የሚሊዮን ብር ሀሳብ የመፍጠር እድልህ ይጨምራል፡፡ የሚያስፈልግህ ትንሽ ለወጥ ያለ ሀሳብ ማሰብ ወይም በተፈጠረው ሀሳብ ላይ ትንሽ ነገር መጨመር ነው፡፡ ይህ የስኬት አቦጊዳ መጽሐፍ አንዱ ተግባር ደግሞ ውስጥህ የተደበቁ የሚሊዮን ብር ሀሳቦችን እንድታወጣ መርዳት ነው- ገንዘብና ስኬት!

ስኬታማ የሚያደርጉ መርሆችን ልክ እንደ አቦጊዳ ጥጥት የሚያደርጉበት መጽሐፍ!

#የስኬት_አቦጊዳ

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል፡፡

📗📒📕
(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጻችንን ይቀላቀሉ።)

👇
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun

Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/
መፍትሔ ስራይ ወአይነ ጥላ
መርጌታ ጥበቡ
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን ባገኘነው ትምህርትና ጥበቡ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት በምናመጣቸው መድሀኒቶች ፍቱን ህክምናወችን እንሰጣለን።
👉ለኪንታሮት በሽታ ታማሚው ከቤቱ ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል
👉በሌሊት ለሚሸና
👉ለነገረበትን
👉ሆዱን ለሚአመው
👉ለስኳር ህመም መቀነሻ
👉ለትምርት አልገባው ላለ
👉ሁሉም ቦታ ላይ ላሉ ቁርጥማት
👉ለዲስክ መንሸራተት ዘላቂ ፈውስ
👉ለአቃቤ እርእስ ለጥላት መጠበቂያ
👉ለማንኛውም አይነት ቁስል
👉ለፊት ማድያት
👉ለሳል በሽታ
👉ለግርማሞገስ በሄደበት ሁሉ ሰው እንዲወደው
👉ለአይነ ጥላ
👉ለማህጸን እንፌክሽን
👉ለአእምሮ ጭንቀት
👉የሚአስቡት ሁሉ አልሳካ ላለ
👉ለወገብ ህመም
👉ለነርብ
👉ለእራስ ህመም
👉ጋኔን አጋንንት የሰውጅ ለያዘው
👉ፍቅረኛ ላጣ
👉የሌባ ገትር ሌባ እማያስነካ
👉ለሚጥል በሽታ
👉ገንዘብ ለሚበተንበት
👉ስራ አልሳካለት ላለ
👉ለቡዳ
👉ለመስተፋቅር
👉ገበያ ለሚገረግረው ለገብያ
👉ለመፍትሄ ስራይ
👉ለስንፈተ ወሲብ ሲገናኝ ለሚቸኩልበት
👉ለአስም (ሳይነስ)
👉ለትዳር ለማይስማሙ ለመስተዋድድ
እንዲሁም የተለያዩ
መድኀኒቶችን እንቀምማለን
👉እኛ ጋር ለሚአገኙት ማንኛውም አይነት አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈጽማሉ ።
👉እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል
👍ይደውሉ
👉☎️0917040506
0912718883
https://tttttt.me/meritibe
👉ቻናሉን በመቀላቀል ጥንታዊ የአባቶች ጥበብ እንደወረደ ያገኙታል በየስሀቱ የምንለቃቸውን ተደብቀው የቆዪ የብራና መጽሀፍ በሚፈልጉት አይነት ይለቀቃሉ የሚፈልጉትን ለማግኔት ይቀላቀሉ ሼር ሼር ሼር ያድርጉ
#ላጤውባለትዳር
የፊልም እና የቴአትር ባለሞያዎች የተጣመሩበትን ይሄንን ቴአትር ማክሰኞ ምሽት በ 11:30 በብሔራዊ ቴአትር መጥተው ይመልከቱ🔥🔥
#ተዋንያን
ቸርነት ፍቃዱ 🔥
ናርዶስ አዳነ🔥
የምስራች ግርማ🔥
ምትኩ በቀለ🔥
ዳንኤል ተገኝ🔥
ሀና ጌትነት🔥
#ደራሲ ዳንኤል ሙሉነህ
#አዘጋጅ ሔኖክ ብርሀኑ
#HK Entertainment ተዘጋጅቶ የቀረበ😍
ለበለጠ መረጃ :_09 21 59 34 71
@H2n8k
ሳማንታ ፓወር በተያዘው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ሶማሊያ እንደሚያቀኑ ገለጹ!

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤአይዲ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በተያዘው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ሶማሊያ እንደሚያቀኑ ገልጸዋል፡፡ኃላፊዋ በአገራቱ በሚኖራት ጉብኝት ድርቅን ተከትሎ እየተከሰተ ባለው ሰብአዊ ቀውስ ምክንያታ የተጎዱ ዜጎችን እንደሚጎበኙ አስታወቀዋል፡፡

ሳማንታ ይህንን ያሉት የሚያስተዳድሩት ተራድኦ ድርጅት ለአፍሪካ ቀንድ አገራት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ገደማ ድጋድ ማድረጉን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡ድጋፉ በኢትዮጵያ በኬኒያ እና በሶማሊያ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኮይ እርዳታ የሚውል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድጋፉ ለአደጋ ጊዜ የሚሆኑ ምግቦች፣ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ፣ ክትባት ፣ ለተላላፊ በሽታዎች ህክምና እና ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች እና ህጻናት ለሚውሉ አገልግሎቶች እንደሚውል አስረድተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa