**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች
መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**
የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-
- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።
አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።
መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ
ለጤናወ መፍትሄ👇
https://tttttt.me/meritibe

ምርጫ ቦርድ አብን “አግባብነት ያለው ምርጫ” እንዲያካሂድ ወሰነ
ምርጫ ቦርድ፣ አብን በ2 ወራት ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ ሰኔ 18፣2014ዓ.ም ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ መወሰኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በ2 ወራት ጊዜ ውስጥ ወይም እስከ ሰኔ 18፣2014ዓ.ም ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂድ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
ቦርዱ አብን ቀደም ሲል ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ መግባባት አልተደረሰበትም ያለውን “የአመራር ሪፎርም ወይም ለውጥ ማድረግ” በቀጣዩ ጉባኤ በአጀንዳነት እንዲያዝና እና ተገቢነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ ወስኗል፡፡
ኢትዮጵያን ከተደቀነባት የህልውና አደጋ ለመታደግ የብሔራዊ ደህንነት እርምጃ እንዲወሰድ አብን ጥሪ አቀረበ
“ፓርቲው በደንቡ መሰረት የሚቀርጻቸውን ሌሎች አጀንዳዎች ጨምሮ በጉባኤ የመነጋገር መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ቀደም እልባት ያላገኘውን አጀንዳ ማለትም የአመራር ሪፎርም ወይም ለውጥ ማድረግ ለጉባኤው በአጀንዳነት ቀርቦ ተገቢ ውሳኔ እንዲሰጥበትና አግባብነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ“ ሲል ምርጫ ቦርድ ወስኗል፡፡
ምርጫ ቦርድ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፣ ቦርዱ የአብንን ጉባኤ እንዲሳተፉ የመደባቸው ባለሙያዎች ሪፖርት እና ቅሬታ አለን ያሉ የ308 ሰዎች ስምና ፊርማ ያለበት ቅሬታ መቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡
በጉባኤው የተሳተፉ የቦርዱ ባለሙያዎች በምርጫ ቦርድ መመሪያ መሰረት፣ በፓርቲው የተደረጉ ማሻሻዎች እና የ2 አመት የፓርቲው የስራ እንቅስቃሴ ለጉባኤው ቀርቦ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን መታዘባቸውን ጠቅሷል ምርጫ ቦርድ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ምርጫ ቦርድ የአመራር ለውጥ እንዲደረግ በርካታ ጥያቄ የቀረበ ቢሆን በእለቱ ከመድረክ በኩል ጉባኤው የተጠራው ቦርዱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የመተዳደሪያ ደንብ ለማሻሻል እና ለማጽደቅ መሆኑን እና የአመራር ለውጥ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እንዲካሄደ ማብራሪያ መሰጠቱን ታዝቢያለሁ ብሏል፡፡
ታዛቢዎቹ የፓርቲው አመራሮች የጉባኤውን መጠናቀቅ ተናግረው ከአዳራሽ መውጣታቸውን እና አብላጫ ቁጥር ያላቸው የጉባኤው አባላት የአመራሮቹን ከአዳራሽ መውጣት፣የአመራር ለውጥ አለመካሄዱን እና የመድረኩን መዘጋት መቃወመቸውን ቦርዱ መታዘቡን አስታውቋል፡፡
ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ማሻሻያ የተደረገባቸው የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጾች የተካተቱበት ረቂቅ ደንብ ጉባኤው ከመካሄዱ ከ5 ቀናት በፊት ለምርጫ ቦርድ እንዲያቀርብም ወስኗል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች
🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031
🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee

አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!
ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!
በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል
የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy
አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
0118345171
ለበለጠ መረጃ @marakiapplication

መንግሥት በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ የድሮን ጥቃት ማደረጉ ተገለጸ
👉የአየር ጥቃቱ በሲቪል ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱም ተነግሯል
ዕረቡ ሚያዚያ 19 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራሉ መንግሥት በስፋት በኦሮሚያ ክልል በሚንቀሳቀሰው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የታገዘ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ የአካባቢው ባለሥልጣን እና የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ተናገሩ።
እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው እና የፌደራሉ መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀውን 'ሸኔ' ቡድን ለማጥፋት ለአንድ ወር የሚዘልቅ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን መንግስት ከጥቂት ሳምንታት ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ ባለፉት ሳምንታት በተለይ በምዕራብ ሸዋ ዞን በኹለቱ አካላት መካከል ጥንካራ ውጊያ ሲካሄድ መቆየቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን አቡና ግንደበረት ወረዳ ነዋሪ በአካባቢው በታጣቂ ቡድኑ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ መቆየቱን ገልፀዋል።
ነዋሪዎች፣ ባለፈው አርብ ሚያዚያ 14 ቀን 2014 ብአቡና ግንደበረት ወረዳ ብደጎማ ኮቢ ቀበሌ መንግሥት በፈጸመው የአየር ጥቃት በሲቪል ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
"ባለፈው ዓርብ ደጎማ ኮቢ ቀበሌን ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአየር ከደበደቡ በኋላ 25 ሰዎች ተገድለዋል። በዛ አካባቢ ወደ 400 ሰዎች ይኖራሉ አሁን ጥቃቱን በመሸሽ አንድም ሰው መንደር ውስጥ የሉም። ሸሽተው ጫካ ገብተዋል።" ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የምዕራብ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ተስፋዬ ሚሬሳ በበኩላቸው፤ በአካባቢው መንግሥት በድሮን የታዘገ ጥቃት መሰንዘሩን ገልጸው በአየር ጥቃቱ ንጹሃን ሰዎች ስለመጎዳታቸው መረጃው የለኝም ብለዋል።
"መንግሥት ሙሉ አቅም ተጠቅሞ እርምጃ እየወሰደ ነው። ሲቪል ሳይጎዳ ድሮን ጥቅም ላይ ውሏል። በዚህ አካባቢ ያለን መረጃ ጉዳት እየደረሰበት ያለው ኦነግ ሸኔ እንደሆነ ነው እንጂ ሲቪል ሰዎች ላይ አይደለም። ከአባቢው የወጡ ሲቪሎች እንዳሉ ግን መረጃው አለን" ብለዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ጦር ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ በተመሳሳይ መንግሥት በሠራዊታቸው ላይ የድሮን ጥቃት መሰንዘሩን ገልጸው፤ "በአየር ድብደባው ወታደራዊ ስኬት አላገኙም። ይልቁንም ሲቪሎች ናቸው እየተጎዱ ያሉት። ደጎማ የሚባል ቦታ ሦስት ቤቶች አቃጥሏል። እኛ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። የሚያሳስበን በሲቪሉ ሕዝብ ላይ የሚደርሰው ጉዳት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ከቀናት በፊት "ሸኔን የማጽዳት" ዘመቻው ተጠናክሮ መቀጠሉን እና ይህ ወታደራዊ ዘመቻ የተፈለገለትን ዒላማ እያሳካ እንደሆነ በመግለጫ አውጥቶ ነበር።
ይሁን እንጂ የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፤ "ወታደሮቻችን እየተዋጉ ነው። ድል እንጂ ሽንፈት አልገጠመንም። ከ400 በላይ ወታደር ማርከናል። የተለያዩ ጦር መሣሪያዎችን ማርከናል" ብለዋል።
ነዋሪዎች በምዕራብ ሸዋ ዞን አቡነ ግንደበረት ወረዳ የመንግሥት ጥቃትን ተከትሎ የታጣቂ ቡድኑ አባላት አካባቢውን ጥለው ወጥተዋል ቢሉም ኦዳ ተርቢ ግን፤ "ለወታደራዊ ስትራቴጂ ቦታ ይቀያይራሉ እንጂ አልወጡም" ይላሉ።
"ድል እያደረግን ነው። መንግሥት ወታደር ልኮ የያዘው ቦታ የለም" በማለት ቃል አቀባዩ ይናገራሉ።
የምዕራብ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ተስፋዬ ሚሬሳ ባለፉት ቀናት በዞኑ በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች 'ኦነግ ሸኔን' የሚያወግዙ ሰልፎች ሕዝቡ አከናውኗል ይላሉ።
"ሸኔ በሕዝቡ ላይ የሚያደርሰው ስቃይ እጅግ እየተባባሰ በመምጣቱ በዞኑ ባሉ በርካታ ወረዳዎች የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። ታጣቂዎቹን የሚቃወመው ሰልፍ እየተካሄደ ያለው ታጣቂዎቹ በሚንቀሳቀሱባቸው ወረዳዎች ውስጥ ነው" ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዚያ 12 ቀን 2014 ባወጣው መግለጫ "አሸባሪውን ሸኔ የማጽዳት ዘመቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ያለ ሲሆን፤ "በቡድኑ ላይ እየተመዘገቡ ያሉ ድሎች የኦሮሞ ሕዝብ በቅርቡ ከቡድኑ እረፍት እንደሚያገኝ ማሳያዎች ናቸው" ማለቱም የሚታወስ ነው።
Via:- Addis Maleda

#እናወግዛለን!!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በጎንደር ከተማ በትላንትናው እለት፤ ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በተፈጠረው ግጭት እና በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፣ ድርጊቱንም እናወግዛለን!
ሀገር የሁላችን ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ከልካይ ምክንያት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች መብታቸው ተከብሮ ሊኖሩ ይገባል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁንም ክቡሩ የሰው ህይወት እንደዘበት የሚቀጠፍባት ሀገር እንደሆነች ቀጥላለች፡፡
በተቀናጀ ሁኔታ የሀገርን እና ህዝቧን ደህንነት ለማስጠበቅ መስራት አስቸኳይ እና አንገብጋቢ አጀንዳው እንዲሆን አሁንም መንግስትን እናሳስባለን፡፡
መንግስት ጉዳዩን በፍጥነት አጣርቶ አጥፊዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ እንዲሁም ችግሩ እንዳይስፋፋ እና የበለጠ ጥፋት እንዳያመጣ እንዲቆጣጠር እንጠይቃለን!
የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ የመኖር እሴቱን ከሚሸረሽሩ ተግባራት እራሱን እንዲጠብቅ እየጠየቅን የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ህዝብን የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን!
#ኢዜማ

#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ለተመረቁ ተማሪዎች #መደበኛ_ዲግሪ ለመስጠት እንደሚቸገር አሳውቋል፡፡
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከአራት ሺህ በላይ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ማግኘት ባለመቻላቸው ሥራ ለመቀጠር መቸገራቸውን ይገልጻሉ።
በተማሪዎቹ ቅሬታ ዙሪያ በሪፖርተር ጋዜጣ የተጠየቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) " የተማሪዎቹ ሙሉ መረጃ ሳይገኝ መደበኛ ዲግሪ ለመስጠት እንደሚቸገሩ " ገልጸዋል።
" ሰላምና መረጋጋት በሰሜን ኢትዮጵያ በአስተማማኝ ሁኔታ ሲሰፍን ከመጡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቆሙበት መረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ ዲግሪው ይሰጣቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡
እስከዚያው ግን በተሰጣቸው ጊዚያዊ ሰርተፊኬት ሥራ መፈለግ እንደሚችሉ ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተፈናቅለው በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ተማሪዎች ግን " ትምህርት ሚኒስቴር በአንድ ሴሚስተር የውጤት መግለጫ ወረቀት/Grade Report አሰናብቶናል " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ይህ ወረቀት በሥራ ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠር እንደማያስችላቸው በመጥቀስ ሚኒስቴሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል፡፡

”በከተማችን የተፈጠረው ችግር በምንም ሁኔታ የሙስሊሙንና የክርስትና ዕምነት ተከታይ ማህበረሰቡን የማይወክል ነው።” ፦ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት
ዕረቡ ሚያዚያ 19 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በትናትናው ዕለት በጎንደር ከተማ የተፈጠረው ችግር በምንም ሁኔታ የሙስሊሙንና የክርስትና ዕምነት ተከታይ ማህበረሰቡን የማይወክል መሆኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት አስታወቀ።
በከተማ አስተዳደሩ በአራዳ ክፍለ ከተማ ላይ የተፈጠረው ግጭት በምንም ሁኔታ የኹለቱን ዕምነት ተከታይ ማህበረሰብን የማይወክል ጥፋት ተፈጽሟል! ያለው የከተማው የፀጥታ ምክር ቤት፤ ጥፋቱ የተፈፀመው በጥቂት ጽንፈኛና አክራሪ ግለሰቦች የተከበሩትን የኹለቱን ዕምነት ተከታዮች ወደ ለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ ለግጭት የማያበቃ ምክንያትን በመምዘዝ ጥፋት እንዲፈጠር የተቀነባበረና የተመራ ሴራ ነው ብሏል።
የጎንደር ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ጉዳዮን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዚህ እኩይ ተግባር ከኹለቱም የዕምነት ተከታዮች የህይዎትና አካል መጉደል እንዲሁም የንብረት መቃጠልና ዘረፋ ማጋጠሙን ገልፆ፤ በተፈጠረው ግጭት በንጹሃን ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን በመግለፅ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝቷል።
”ይህ ቡድን የፈለገው ጎንደርን ማቃጠል፣ መዝረፍና ማዋረድ ሲሆን፤ ይህ ክፉ ተልዕኳቸው በፀጥታ መዋቅሩ፣ በኹለቱም የዕምነት አባቶችና ወጣቶች እንዲሁም በአገር ሺማግሌዎች ጥረት የፈለጉት ጥፋት ሳይደርስ መቆጣጠር ተችሏል” ሲልም ገልጿል።
በተፈጠረው ችግር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የተገኙ ሙስሊሞች እንደ ነበሩና የእምነቱ አባቶችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ለፀጥታ አካላት ያስረከቡ መሆኑን፣ በተመሳሳይም በመስጊድ ውስጥ የተጠለሉ የክርስትና አማኞች እንደነበሩና ከጥቃት የዳኑ መሆኑ መረጋገጡን ፀጥታ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
ይህ ልምድ ደግሞ የዛሬ ሳይሆን ትናንትም የእምነት ተቋማትና አባቶች የችግር ጊዜ ታማኝ መሸሸጊያ /መጠለያ/ ዋስትና መተማመኛ መሆኑ ታውቆ ያደረ በመሆኑ አንደኛው በሌላኛው በእጅጉ የሚያምን አንድና ያው የሚባል የህብረተሰብ ክፍል በመሆናቸው ነው ሲልም ገልጿል።
የጎንደር ህዝብ ታሪክ መረዳዳት መከባበር መቻቻል መፋቀር በፋሲካ ሙስሊሞች የሚያስተባብሩበት በኢድም ክርስቲያን ወንድሞች የሚያግዙበት እንጂ፤ ዛሬ በጥቂት የጥፋት ቡድኖች የተመራው ጥፋት በፍፁም የጎንደርን ልክ የሚመጥንና የሚወክል ባለመሆኑ መላው ህዝብ በአገኘው አጋጣሚ እያወገዘው ይገኛል! በቀጣይም ሊያወግዘው ይገባል ያለ ሲሆን፤ የተፈጠረውን ቃጠሎም ህዝቡ በነቂስ በመውጣት በከፍተኛ ርብርብ መቆጣጠር መቻሉንም በመግለጫው አስታውቋል።
አሁን አካባቢው ሙሉ በሙሉ ከፀጥታ መዋቅርና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ትብብር በማድረግ የተረጋጋ ሰላም ለመፍጠር በሁሉም አካባቢ ስምሪትና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ያለው የከተማው ፀጥታ ምክር ቤት፤ ኹሉም የጎንደር ህዝብ ለከተማችን መረጋጋት ከፀጥታ አካሉ ጎን በመሰለፍ ቀንደኛና የጥፋት ሃይል የሆኑ በህይዎትና በአካል ጉዳት እንዲሁም በዘረፋ የተሰማሩት እየተለቀሙና እየተያዙ በመሆኑ ለዚህም ህዝቡ የተለመደውን ንቁ ተሳትፎ በማድረጉ ምስጋናውን አቅርቧል።
የከተማዋ ነዋሪም፤ በቀጣይም ቀሪ የጥፋት ሃይሎችንም አጋልጦ ለፀጥታ መዋቅሩ በማስረከብ የተለመደውን ትብብር እንዲቀጥል፣ በብሎክ አደረጃጀትም አካባውንና ሰፈሩን፣ የንግድ ተቋማትን እንዲሁም የዕምነት ተቋሞችን በመጠበቅ ከተማዋን ከጥፋት እንዲያድን የጎንደር ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ጥሪ አቅርቧል።
ከዚህ እኩይ ተግባራቸው የማይታረሙ አጥፊዎችን ህግ ለማስከበር በጭራሽ የማይታገስ መሆኑን የገለፀው ምክር ቤቱ፤ በኹከቱ የደረሰውን ጥፋት የምርመራ ቡድኑ እያጣራ ስለሆነ መረጃው እንደተጠናቀቀ ለህዝቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑን አስታውቋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ተሠማርተው ወደ ሀገራቸው ያልተመለሱ ጥቂት የሠራዊት አባላትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ!
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ተሠማርተው ወደ ሀገራቸው ያልተመለሱ ጥቂት የሠራዊት አባላት ወደ ምድብ ስራቸዉ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ፡፡
በሕግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው ወቅት በቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ እና ከሠላም ማስከበር የተመለሡ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሠራተኞች ዛሬም የተቋሙ አባላት ስለሆኑ መብታቸውና ጥቅማጥቅማቸው ይከበራል ያለዉ ማብራሪዉ ፡፡ አሁን ያለው ግጭት በማናቸውም አግባብ ከተፈታ ወደ ሥራቸው ተመልሰው ሃገራቸውን ያገለግላሉ በሚል አቋም እየተሰራ መሆኑን አብራርቷል፡፡
˝በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላላችሁ፤ ከሠራዊት ጋር ግዳጅ እየተወጣችሁ ላላችሁና ለጊዜው ከስራ ውጭ ሁናችሁ ነገር ግን ደመወዝና ጥቅማጥቅማችሁ ተጠብቆ ያላችሁ ወታደሮች በወያኔ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ሳትንበረከኩ አገራችሁን እንድታገለግሉ፤ ቤተሰባችሁን እንዳትበትኑ፤ ጥቅማችሁ እንዳይቋረጥ፤ በክህደት ታሪክ እንዳትመዘገቡ˝ ሲል አሳስቧል፡
የማብራሪያዉ ሙሉቃል እንደሚከተለዉ ቀርቧል
አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የሀገር ሉአላዊነት ምሽግ የሆነውን መከላከያ ሠራዊት በመምታት ለውጡን ቀልብሶ ወደ ስልጣን በመመለስ ኢትዮጵያን መግዛት፤ መግዛት ካልቻለ የራስን ዕድል በራስ መወሰን በሚል ክልሎችን በመገነጣጠል ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ ይዞ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሠሜን ዕዝ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት ከፈተ፡፡ አሸባሪው ቡድን በሠሜን ዕዝ ሰራዊታችን ላይ ጥቃት ከመፈፀሙ አስቀድሞ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪዎችን "ኢንፍልትሬት" በማድረግ ለእኩይ አላማቸው በማዘጋጀት የሠሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊታችን ላይ ጥቃት በመክፈት ሠራዊታችንን ከውስጥና ከውጭ እንዳጠቃ ይታወቃል፡፡
የሕግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው ሲጀመር ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩ ከወታደር እስከ ከፍተኛ አመራር ያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች ለዘመቻው ስኬትና እርስ በእርስ እንዳንማታ ሲባል ደመወዝና ቀለባቸው ሳይቋረጥ በቤታቸው እንዲቆዩ መደረጉ ይታወቃል፡፡
ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በፊት ወደ ውጭ ሀገር ሰላም ለማስከበር የተላኩ ትግርኛ ተናጋሪዎች ግን በሰራዊታችንና በተልዕኮው ላይ ችግር አይፈጥሩም በሚል በስራቸው እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡ ሆኖም ግን ሕወሓት የትግርኛ ተናጋሪዎች ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ በውጭ በሚገኙ የወያኔ ቅጥረኞች የሃሰት ፕሮፖጋንዳ በመነዛቱ በአባላቱ ላይ ውዥንብር ፈጥሯል።
ሀገር ቤት ከተመለሳችሁ ትታሰራላችሁ የሚል የማስፈራሪያ ውሸት በመንዛትና በዘረኝነት በመቀስቀስ አገራቸውንና ተቋማቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የሠራዊት አባላትን የማስኮብለል ስራ ተሰርቷል፡፡ የሠራዊት አባላቱ ተቋማቸውንና ሀገራቸውን ጠልተው ሳይሆን ወያኔ በሰራው አፍራሽ ስራ ስጋት ገብቷቸው የተወሰኑ ወታደሮች ሰላም ማስከበር በሄዱበት አገር ቀርተዋል፡፡ ወያኔ ጥቂት አፍራሾችን በውስጣቸው በመፍጠር የእኩይ ዓላው አስፈፀሚ አድርጓቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡
ከዚህ ቀደምም በዳርፉር፣ ተልእኮ ላይ ተሰማርተው የነበሩት ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ሲደረግ በተመሳሳይ ውዥንብር ጥቂት ወታደሮች ቀርተዋል፡፡ ሱዳን ከሚገኘው ሳምሪ ተቀላቅለው ሲዋጉ የሞቱም ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉንም ጫና ተቋቁመው ሃገርና ተቋማቸው የሰጣቸውን ግዳጅ ፈፅመው ለተመለሱ የትግርኛ ተናጋሪ የሰራዊታችን አባላት ተቋማችን ከፍተኛ ምስጋና ያቀርብላቸዋል።
በህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው ወቅት በቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ እና ከሠላም ማስከበር የተመለሡ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሠራዊት አባላት እና ሲቪል ሠራተኞች ዛሬም የተቋሙ አባላት ስለሆኑ መብታቸውና ጥቅማጥቅማቸው ይከበራል፡፡ አሁን ያለው ግጭት በማናቸውም አግባብ ከተፈታ ወደ ሥራቸው ተመልሰው ሃገራቸውን ያገለግላሉ በሚል አቋም እየተሰራ ይገኛል፡፡
አሁንም በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላላችሁ፤ ከሠራዊት ጋር ግዳጅ እየተወጣችሁ ላላችሁና ለጊዜው ከስራ ውጭ ሁናችሁ ነገር ግን ደመወዝና ጥቅማጥቅማችሁ ተጠብቆ ያላችሁ ወታደሮች በወያኔ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ሳትንበረከኩ አገራችሁን እንድታገለግሉ፤ ቤተሰባችሁን እንዳትበትኑ፤ ጥቅማችሁ እንዳይቋረጥ፤ በክህደት ታሪክ እንዳትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa

በፈረንሣይ መንግስት እገዛ የሚመራው የላሊበላ ፕሮጀክት ከአለት የተሠሩትን የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት አሁን ያለውን የብረት መጠለያን በማንሳት በምትኩ ከቀርከሀ የተሠራ መጠለያ እንዲደረግ ሀሳብ አቀረበ።
አ.አ.አ በ1978 በአለም ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት፣ ትምህርታዊ፣ ሳይንሳዊ እና የባህል ድርጅት /ዬኔስኮ/ የተመዘገበው ታሪካዊው የላሊበላ አብያተ ክርስቲያን ከጊዜ ወደ ጊዜ በቅርሱ ላይ እያጋጠመው የሚገኘውን ጉዳት ለመቀነስ እ.ኤ.አ በ2008 ዩኔስኮ በአውሮፓ ህብረት እርዳታ አራት ኢንዱስትሪያል ወይም የብረት መጠለያዎች የሠራ ቢሆንም ባለበት የዲዛይን እና የግንባታ ችግር ውዝግብ ሲያስነሳ ቆይቷል።
ዘለቄታው መፍትሄ ለመስጠት የተለያዩ ጥናቶች እንደተደረጉ የሚገልፁት ፌቨን ተወልደ የላሊበላ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ውጤቶች የብረት መጠለያውን ማስወግድ አስፈላጊ መሆኑን አሳይተዋል ለዚህም በምትኩ ከቀርከሀ የተሠራ አና ለእይታ የሚማርክ ሽፋን ከላዩ ተጨማሪ ሸራ መሰል ሽፋን ያለው መከለያ ለመስራት በሀሳብ ደረጃ ለዩኔስኮ መቅረቡን ተናግረው በሀሳብ ደረጃ ተቀባይነት እንዳገኘ እና የዲዛይን እንዲሁም ተጨማሪ የሚቀሩ ጥናቶች ተጠናቀው እንዲቀርብለት መጠየቁን ገልፀዋል።
የሚቀሩ ጥናቶችን አጠናቆ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ስራአስኪያጅዋ ለካፒታል ተናግረው በ2023 ሰኔ መጨረሻ ለሚደረገው የዩኔስኮ አመታዊ ስብሰባ ላይ እንደሚቀርብ አክለዋል።ሀሳቡ ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት ካገኘ የሚደረገው እድሳት ከ2024 በፊት ሊጀመር ይችላል።እ.ኤ.አ በ2019 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፈረንሳይ ባለስልጣናት ላሊበላን ለመታደግ ድጋፍ እንዲያደርጉ በጠየቁት መሠረት የፈረንሳይ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል እንደገቡላቸው ሚታወስ ነው።
Via Capital

ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በተመለከተ ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን እንዲያቀርብ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ!
ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በተመለከተ ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠይቋል።ቦርዱ ሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ያቀረባቸውን የጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች እና ጠቅላላ ጉባኤውን በታዘቡት የቦርዱ ተወካዮች የቀረበውን ሪፖርት መመርመሩን አስታውቋል።ይሁንና የጠቅላላ ጉባኤውን ሂደት፣ በጉባኤው የተላለፉ ውሳኔዎች እና የተደረጉ ምርጫዎችን በተመለከተ ከሕጉ አንጻር ለወሰን ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን ማየት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሟል።
በሆኑም ፓርቲው ምርጫ ቦርድ በዝርዝር ያስቀመጣቸውን ጉዳዮች ከሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በፊት ለቦርዱ እንዲያቀርብ አሳውቋል።ቃለ ጉባኤን በተመለከተ፣ በጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤው ላይ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባው ምልአተ ጉባኤ ተሟልቷል ቢባልም በግልፅ የጠቅላላ ባኤው ተሳታፊ አባላት ብዛት ስላልተቀመጠ ተገልፆ እንዲቀርብ፤ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የተጠቆሙበት ሂደት፣ እነማን እንደተጠቆሙ፣ ከተጠቆሙት ውስጥ የተመረጡት አባላት እያንዳንዳቸው በስንት ድምፅ እንደተመረጡ በጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ውስጥ ያልተገለፀ በመሆኑ ይሄው ተካትቶ እና ተረጋግጦ እንዲቀርብ፤ በፓርቲው የቀረበው ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተፈርሞ እንዲቀርብ፤ የማዕከላዊ ኮሚቴው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን የመረጠበትን ሂደትየሚያሳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ቃለ ጉባኤ ስላልቀረበ እንዲቀርብ ጠይቋል።
የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብን በተመለከተ ደግሞ በመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 18/3 መሠረት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ብዛት እና ስብጥርን በተለከተ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ ካለ የመመሪያውን ኮፒ ማዕከላዊ ኮሚቴው መመሪያውን ካፀደቀበት ቃለ ጉባኤ ጭምር እንዲቀርብ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ቢትኮይንን ህጋዊ ምንዛሪ አድርጋ ለመጠቀም መወሰኗን የሀገሪቱን የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጠቅሶ ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
"የተፈጠረው የፀጥታ ችግር አሳዛኝና የከተማዋን ሕዝብ አብሮነት ታሪክ የማይገልፅ ነው" የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር)
በጎንደር ከተማ ትናንት የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) ውይይቱ ችግሩን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ያለመ ነው ብለዋል።
ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ "ትናንት የተፈጠረው የፀጥታ ችግር አሳዛኝና የከተማዋን ሕዝብ አብሮነት ታሪክ የማይገልፅ ነው" ብለዋል።የፀጥታ ችግር የፈጠሩ አካላትን በመለየት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የክልሉ መንግሥት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በጋራ እንደሚሠራም ገልጸዋል። ነዋሪዎች ለከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልክት አስተላልፈዋል።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው የተፈጠረው ችግር ለጠላት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመኾኑ ችግሩን በውይይት ለመፍታት ሕዝቡ ባለቤት መኾን አለበት ብለዋል። በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅርም ያሉትን ክፍተቶች ለማስተካከል ጠንካራ ሥራ ይሠራል ብለዋል።የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎችም ከመንግሥት ጋር በመኾን እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ችግሩን ለመፍታት በስክነት መወያዬት ይገባል ብለዋል።የውይይቱ ተሳታፊዎችም የቆየውን አብሮነት ለመሸርሸር የሚሠሩ አካላትን ተከታትሎ በቁጥጥር ሥር በማዋል ሕግ የማስከበር ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
[AMC]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሁለት ም/ዋና ዳይሬክተሮችን ሾመዋል።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ሁለት ም/ዋና ዳይሬክተሮችን ሾመዋል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ዳንኤል ጉታ እና አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ከሚያዚያ 17/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በመሆን ተሹመዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ሁለት ም/ዋና ዳይሬክተሮችን ሾመዋል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ዳንኤል ጉታ እና አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ከሚያዚያ 17/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በመሆን ተሹመዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች
መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**
የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-
- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።
አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።
መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ
ለጤናወ መፍትሄ👇
https://tttttt.me/meritibe
መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**
የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-
- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።
አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።
መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ
ለጤናወ መፍትሄ👇
https://tttttt.me/meritibe
ህወሓት ከተቆጣጠራቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች “ሙሉ በሙሉ ወጥቻለሁ” ማለቱ ውሸት ነው ሲል የአፋር ክልል ገለጸ!
የህወሓት ሃይሎች ከጎረቤት አፋር ክልል ሙሉ በሙሉ መውጣታቸውን ሮይተርስ የህወሓትን ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳን ጠቅሶ ከሁለት ቀናት በፊት መዘገቡ ይታወሳል፡፡አቶ ጌታቸው ከአፋር ክልል መውጣት ማለት በጣም አስፈላጊ የሆኑ የምግብ እርዳታ በርሃብ ውስጥ ላለችው ትግራይ ይደርሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
ነገርግን የአፋር ክልል መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የህወሓት ኃይሎች ከያዟቸው የአፋር ክልል ቦታዎች አለመውጣታቸውን አስታውቋል፡፡“አሸባሪው ህወሀት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ከወረራቸው በአፋር ክልል የኪልበቲ ረሱ ዞን ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ወጥቻለሁ በማለት ከሰሞኑ ከእውነት የራቀ የሀሰት የማደናገሪያ ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ላይ ይገኛል።” ብሏል የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ፡፡
[Alain]

በሐረሬ ክልል ሐረር ከተማ ዕሁድ'ለት ከፈነዳው ቦምብ ጋር በተያያዘ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሆቴል ውስጥ በፈነዳው ቦምብ ሌሎች 8 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል። ለቦምብ ጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ተቋም ግን ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች የሽብር ጥቃት ሲያሴሩ የነበሩ 34 የአልሸባብ አባላትን በቁጥጥር ስር አውያለሁ ብሎ ነበር።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የተጣሉ ፈንጂዎች በሚገርም ሁኔታ ህጻናትን አካል ጉዳተኛ እያደረጉ ወይም እየገደሉ እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ለሮይተርስ ተናገሩ።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ በሳምንት 25 ያህል የተጎዱ ህፃናት ወደ ሆስፒታል ይመጣሉ። አንዳንድ ህፃናቱ ታካሚዎች ከመሬት ላይ የእጅ ቦምቦቹን እንዳነሱ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ የተቀበሩ ፈንጂዎችን መርገጣቸውን ተናግረዋል። ካሳጊታ የሚባለው አካባቢ ነዋሪዎች ለዜና ምንጩ እንደገለፁትም ባለው ሁኔታ ምክንያት ከምንጭ ውኃ ለማምጣት ወይም ወደ እርሻ ቦታዎች መሄድ አስግቶዋቸዋል።
በአጭር ጊዜ በአፋር ክልል እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ጉዳቶች የደረሰበት ምክንያት አልተገለፀም። ይሁንና በትግራይ ክልል በጀመረው እና ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተስፋፋው የሀገሪቱ ጦርነት በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። ሚሊዮኖችን ከቀያቸው አፈናቅሏል። በፈንጁ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ጎልማሶች እንዳሉ ነገርግን አብዛኞቹ ተጠቂዎች ምን እንደሆነ የማያውቁ ህፃናት እንደሆኑ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ በጠቅላላ ምን ያህል ሰዎች በፈንጅ ጥቃት በሆስፒታል እንደታከሙ ቁጥር ባይጠሩም በታህሳስ እና የካቲት መካከል በአፋር ትልቁ፣ የዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል፣ በሳምንት 25 የሚጠጉ ተጎጂዎች ይገጥሙት እንደነበር ታመር ኢብራሂም የተባሉ የቀዶ ህክምና ክፍል ዋና ነርስ ለሮይተርስ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሊያ ታደሰ ለሮይተርስ እንደተናገሩት፤በአፋርም ሆነ በሌሎች ክልሎች በፈንጂ ምክንያት ተጎጂ እየሆኑ ስላሉ ሕፃናት የሚያውቁት ክስተት የለም። ሮይተርስ ዜና ምንጭ ምን አይነት ፈንጂዎች ጉዳቱን እንዳደረሱ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ዘግቧል። የህውኃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሃይሎች ምንም አይነት የተቀበሩ ፈንጂዎችን አልተውም ብለዋል።ተጠያቂ ነው ብለው የጠቀሱትም አካል የለም።ሮይተርስ ከፌዴራል መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ቢሮ እና ከጦሩ ቃል አቀባይ ለጥያቄዎቹ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሰካቱንም አክሎ ዘግቧል።
[DW]