YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እስማማለሁ አለ!

ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ላለፉት 16 ወራት ግጭት ውስጥ የቆየው ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እንደሚስማማ ገለጸ።ህወሓት ይህን ያለው ትናንት ሐሙስ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርስ ለማስቻል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ካስታወቀ በኋላ ነው።

የፌደራሉ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የተከሰተውን ሰብአዊ ቀውስ "በእጅጉ ሊያሻሽል" ስለሚችል እና "በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል" ተስፋ በማድረግ መሆኑን ገልጿል።መንግሥት ይህ ውሳኔ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ "በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ" ጠይቋል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ ላይ በበቂ መጠን እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ጥሪውን እንደሚቀበል ገልጿል።በትግራይ ካለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታው የሚደርስ ከሆነ "የትግራይ መንግሥት ግጭት ለማቆም ቁርጠኛ ነው" ብሏል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን እና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖርያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱን አስታውሷል።ደንቡ ላለፉት ሶስት ወራት እንዲራዘምም ተደርጎ እንደነበር ገልጿል።

አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር መወሰኑን አሳውቋል።ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጉጂ አባ ገዳ መኖሪያ ቤታቸው ላይ 'ኦነግ ሸኔ' ጥቃት መፈጸሙን ተናገሩ!

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ እና የጉጂ አባ ገዳ የሆኑት ጂሎ ማንዶ ታጣቂዎች በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።አባ ገዳ ጂሎ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ዕለት መጋቢት 14/2014 ዓ.ም. ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቤታቸው ላይ ለተፈጸመው ጥቃት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራውን እና መንግሥት ሸኔ የሚለውን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ግን ታጣቂዎቻቸው 'የተባለውን ጥቃት አልፈጸሙም' ሲሉ አስተባብለዋል።አባ ገዳው ጥቃት በተፈጸመበት ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ባለመኖራቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውንና በንብረት ላይ ከደረሰው ውጪ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል።

"በቁጥር ስንት ሆነው እንደመጡ ባላውቅም በአራት ሞተር ሳይክሎች መጥተው ቤቱ ላይ ተኩስ ከፈቱ። በርካታ ጥይት ተኩሰው ቤት ሰባብረው፣ ቤት ውስጥ የነበረ አንድ ኩንታል ቡና በትነው ሄዱ እንጂ ሰው እና ከብት ምንም አልሆነም" በማለት የነበረውን ሁኔታ አባ ገዳ ጂሎ ያስረዳሉ።አባ ገዳው ታጣዊዎች ትጥቅ ፈትተው የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ ማስተላለፋቸው የጥቃቱ ዒላማ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ያምናሉ።"እነርሱ መጀመሪያም ቂም ይዘውብኝ ነበር። እየደወሉ፤ 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር በሰላም ግቡ እያልክ የምትቀሰቅሰው አንተ ነህ' ሲሉኝ ቆይተዋል" በማለት አባ ገዳው ይናገራሉ።

"እየደወሉ '600 የሚሆን ሠራዊት አስገብተህ (ትጥቅ አስፈትተህ) መሳሪያቸውን ወርሰሃል፤ ያን መሳሪያ እስክታመጣ በሕይወትህ ፍረድ' ይሉኛል" ሲሉ ጂሎ ማንዶ ከታጣቂዎቹ ይደርስባቸው ስለነበረው ዛቻ ያስረዳሉ።እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ቃል አቀባይ የሆነው ኦዳ ተርቢ፤ የኦሮሞ ነጻነት ጦር አባ ገዳዎችን እና የገዳ ሥርዓትን እንደሚያከብር ገልጸው፤ "በከረዩ አባ ገዳዎች ላይ የተፈጸመውን እና የመንግሥት (የዐቢይ) ጦር ለሥርዓቱ ያለውን ንቀት ከግምት በማስገባት ይህ የተፈጸመው በእነርሱ (በመንግሥት ጦር) ሊሆን ይችላል" ብለዋል።ከዚህ ቀደም የጉጂ እና የቦረና አባ ገዳዎች 'ኦነግ ሸኔ' የኦሮሞ ጠላት ነው በማለት ማወጃቸው ይታወሳል።ታጣቂዎች ትጥቅ እንዲፈቱም ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ብሪታኒያ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ላልተወሰነ ጊዜ በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጥል ተኩስ አቁም ማድረጉን እና ያልተገደበ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለትግራይ እንዲገባ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን በአድናቆት እንደምትመለከተው ገልጻለች።

ብሪታኒያ አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል ባወጣችው መግለጫ፣ ሕወሃት ተመሳሳይ ርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አድርጋለች። ሕወሃት ዘግየት ብሎ ለተኩስ አቁም ዝግጁ መሆኑን ገልጧል።

@Yenetube @Fikerassefa
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የአውሮፓ ህብረት አገራቸውን በአባልነት እንዲቀበላት ጠየቁ፡፡

ዜሌንስኪ ጥያቄውን ያቀረቡት ትናንት ሌሊት በቪዲዮ ሊንክ (ምስለ ጉባኤ) መላ ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ባስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ ሜይል ኦን ላየን ፅፏል፡፡ጦርነቱ እንደቀጠለ ሲሆን ሩሲያ ድኔፕሮ ወደ ተባለው የዩክሬይን 4ኛው ትልቅ ከተማ ሁለት ከፍተኛ ሚሳየሎን መተኮሷ ተሰምቷል፡፡የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ልዩ የመሪዎች ጉባኤ መጠናቀቅ ተከትሎ ሩሲያ በዩክሬን ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ የምትጠቀም ከሆነ ለምላሹ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ይሁንና ባይደን ምላሻቸውን በምን ዓይነት ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚያደርጉት የታወቀ ነገር የለም፡፡የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጦርነቱ መጀመሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ጣልቃ የሚገባ ካለ ውርድ ከራሴ ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በባሌ ዞን በሚገኙ አካባቢዎች የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል የመጠገን ሥራ እየተከናወነ ነው!

በባሌ ዞን በሚገኙት የሮቤ፣ ጎባ፣ ጋሠራ፣ አጋርፋ፣ ሲናና፣ ዲንሾ እና አካባቢያቸው ከትናንት በስቲያ አንስቶ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል የመጠገን ሥራ እየተከናወነ ነው።

በዞኑ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ያጋጠመው ከመልካ ዋከና የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ሮቤ የሚሄደው መስመር በዲንሾ አካባቢ ተቆርጦ በመውደቁና የማከፋፈያ ጣቢያውን የከረንት ትራንስፎርመር በማቃጠሉ ነው።በኃይል ማከፋፈያው ላይ ያጋጠመውን ብልሽት በመጠገን አገልግሎቱን እስከምሽት ድረስ ለማስቀጠል ርብርብ እየተደረገ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይፋዊ ስራ የማስጀመሪያ ፕግራም አካሄደ::

የዋዜማ ሪፖርተር እንደዘገበው በፕሮገራሙ ከተለያዩ የሃይማቶት ተቋማት የተውጣጡ የሃይማት አባቶችና የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን ይወክላሉ የተባሉ የአገር ሽማግዎች የጸሎትና ምርቃት ስነ ስርዓት አከናውነዋል፡፡
ኮሚሽኑ በፓርላማ ከተቋቋመ ጀምሮ ቢሮውን በማድረጀት ላይ መሆኑን፣ በቀጣይ ሶስት አመታት የሚፈጽማቸውንና በአዋጅ የተሰጡትን 12 ዋና ዋና ሃለፊነቶች የሚያስፈጽምበት ደንብና መመሪያ እያዘጋጀ ስለመሆኑ እንዲሁም ከሚዲያ ጋር ሊኖር ስለሚችል ግንኙነት የሚረዳ የሚዲያ ስተራቴጅ ዝግጅት ላይና ሌሎች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንና ዋና ኮሚሽነር ዶ.ር መስፍን አርአያ ተናግረዋል፡፡ኮሚሸነሩ በተያዘው በጀት አመት ቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ የተጀመሩ ጥቂት ስራዎችን በማጠናቀቅ ለቅድመ ውይይት ስራ እንደሚዘጋጅ ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ የተለያዩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በውይይቶቹም በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦችንና ግብአቶችን ማሰባሰብ መቻሉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ሆኖም አሁንም ህብረተሰቡን ለማዳመጥ ተጨማሪ አማራጮችን መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ካለበት ሆኖ ጥቆማዎችን መስጠት የሚችልበት የስልክ ቁጥሮችን አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ህብረተሰቡ ማንኛውንም ቅሬታና ጥቆማዎችን በነፃነት የሚሰጥባቸው የጥቆማ መስጫ የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት!
አጭር ቁጥር ፡- 👉 9977
የሞባይል ስልኮች
👉 09-00640830
👉 09-00640789

አስፈላጊ የሰነድ መረጃዎችን በቴሌግራም ለማያያዝ እና ለአጭር መልእክቶች( text messages) የሞባይል ቁጥሮችን መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ በሰጡት መግለጫ ፥ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ሲካሄድ የቆየው የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡

16 ተቋማትን ያካተተ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አንስተው ፥ በዚህም ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ ይጀመራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ከ102 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ግብ ተቀምጦ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
https://tttttt.me/sabinaadvisor

የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week

👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል እንደ ባንክ፣ ኤሌክትሪክ እና ቴሌኮምንኬሽን ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን ባስቸኳይ እንደገና እንዲጀምር በቃል አቀባያቸው ስቲፋኒ ዱጃሪክ በኩል ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። ጉተሬዝ ሁሉም ወገኖች ሰብዓዊ ዕርዳታ ሳይስተጓጎል ወደ ትግራይ እንዲገባ እንዲያመቻቹም አሳስበዋል። ሁሉም ወገኖች አሁን የወሰኑትን በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረት ግጭት የማቆም ውሳኔ ወደ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ማሸጋገር እንዳለባቸው ጉተሬዝ ጨምረው አሳስበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኦፌኮ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው!

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ) 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል።ጉባኤው ለ2 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የተውጣጡ የፓርቲው አባላትና ኃላፊዎች ተገኝተውበታል።በጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በብላቴ ማእከል በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለሚገነባ አውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

በብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማእከል ለሚገነባው አውሮፕላን ማረፊያ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡት የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የኢፌድሪ ጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ቩም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የደቡብ ክልል ርእስ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ናቸው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ የ75 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድን ያካተተ ነው።ከመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ ሥርዐቱ ጎን ለጎን የልዩ ዘመቻዎች ኀይልና የሪፐብሊካን ጥበቃ ኀይል በዓል ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።በበዓሉ ለኮማንዶ፣ አየር ወለድ ልዩ ኀይል፣ ጸረ ሽብርና ባሕር ጠለቅ ክፍሎች የሜዳይ ሽልማት እንደሚሰጥ የወጣው መርኃግብር አመላክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ስድስት ወራት በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ በሰዎችና በዝሆኖች መካከል በተፈጠረ ግጭት 11 ዝሆኖችና 4 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።

የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልል የሚያዋስነው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ ከተጋረጠበት አደጋ ማዳን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተካሄደ ነው።ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ባዘጋጀወው በዚህ መድረክ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።በመድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት በመጠለያ ጣቢያው በዝሆኖችና በሰዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 11 ዝሆኖችና 4 ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።

ህገወጥ ሰፈራ፣ ደን ጭፍጨፋና፣ የጎሳዎች ግጭትና የእርሻ መስፋፋት ለዝሆኖችና ለሰዎች ግጭት መንስኤ መሆኑም ነው የተጠቆመው።ከዚህ በተጨማሪ መጤ አረሞች እና ያልተጠኑ የኢንቨስትመንት ፍቃዶች በተጨማሪነት ለዝሆኑ ቁጥር መመናመን እንደምክንያት እንደቀረበ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ለማ ተናግረዋል።የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ በ1963 ዓ.ም ሲቋቋም 600 ይደርስ የነበረው የዝሆኖች ቁጥር አሁን ላይ 300 መድረሱ በመድረኩ ተጠቁሟል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ባለመወሰኑ ተቀጣሪዎች በሚስተዋለው የኑሮ ውድነት በእጅጉ እየተፈተኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አስታወቀ::

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአገሪቱ ላይ እየተስተዋለ ያለው የኑሮ ውድነት ተቀጣሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል:: በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ መሠረት የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ባለመወሰኑ በተለይ ዝቅተኛ ደመወዝ የሚያገኙ ሠራተኞች አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል::

ከሁለት ዓመት በፊት በወጣው የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት የደመወዝ ቦርድ ይቋቋማል እንደሚል አስታውሰው፤ ይህ የደመወዝ ቦርድ በየዓመቱ ኑሮ ውድነቱን እያየ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን የመወሰን ሥልጣን እንዳለው አስረድተዋል::

መነሻ የደመወዝ ወለል ባለመኖሩ አሰሪዎች በፈለጉት ዋጋ ሠራተኞችን ይቀጥራሉ ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በዚህም የተነሳ ከሰባት መቶ ብር ጀምሮ ተቀጥሮ የሚሠራ ሠራተኛ አለ:: ደመወዛቸው አምስት ሊትር ዘይት እንኳ መግዛት የማይችል በመሆኑ ምሳ ይዘው ወደ ሥራ መሄድ እንኳን የማይችሉ ሠራተኞች መኖራቸውን አስገንዝበዋል::

ፌዴሬሽኑ በአገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛው የደመወዝ ወለል ስንት ይሁን የሚል ጥናት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀው፤ የምንጠብቀው የቦርዱን መቋቋም ስለሆነ መንግሥት የሠራተኞችን ችግር በውል ተገንዝቦ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ዝቅተኛው የደመወዝ መነሻ የሚስተካከልበት መንገድ መፍጠር አለበት ብለዋል::

በተጨማሪም አንዳንድ ድርጅቶች በዶላር እጥረትና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት ሥራ በአግባቡ መሥራት አልቻልንም በሚል ሠራተኛ የመቀነስ ሁኔታ እየተስተዋለ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ካሣሁን፤ በኑሮ ውድነት ከመፈተን ባለፈ ሥራቸውን የማጣት ስጋት የተደቀነባቸው ሠራተኞችም በርካታ ናቸው:: በመሆኑም መንግሥት ሠራተኞቻቸውን ይዘው ላሉ ድርጅቶች ብድር በማመቻቸትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ሠራተኛ እንዳይቀንሱ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል::

በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተደረገው ጦርነት ምክንያት ድርጅታቸው ወድሞ ሥራቸውን መቀጠል ያልቻሉ ሠራተኞች መኖራቸውን አስታውሰዋል:: መንግሥት ለእነዚህ ድርጅቶች አስፈላጊውን እገዛ አድርጎ ወደ ሥራ የሚመለሱበትን ሁኔታ መፍጠር ቢቻል የብዙዎችን ሸክም ሊያቃልል እንደሚችልም ጠቁመዋል::

የሠራተኛ ማኅበራት ሠራተኞች ከሸማቾችና አምራቾች በቀጥታ የሚገዙበትን እድል ለመፍጠር እየሠሩ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲቀመጥ ከመንግሥት ጋር ውይይት የማድረግ ሃሳብ መኖሩን ተናግረዋል::

መንግሥት በሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድና ዘይት ከውጭ በማስገባት የዋጋ ንረቱን በጊዜያዊነት ለማረጋጋት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል:: ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ግን ቦርዱን አቋቁሞ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ማስቀመጥ ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ ጠቁመዋል::

[Addis Zemen/EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
የብረታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠን ከ20 ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ብርታ ብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠን ከ20 ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማለቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የምርት መጠኑ ከ20 ወደ 10 በመቶና ከዛ በታች ዝቅ ማለቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፊጤ በቀለ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ምርቱን 20 በመቶ ማምረት ከፍተኛ ነበር ያሉ ሲሆን፣ አሁን ግን እየተመረተ ያለው ከ10 በመቶ በታች መሆኑን አስረድተዋል።

ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በዓመት ከ11 ሚሊዮን ቶን በላይ የሚሆኑ ምርቶችን የማምረት አቅም ስላለው 385 ቢሊዮን ብር ማግኘት ይቻል ነበር ያሉት ፊጤ፣ አሁን ግን በግማሽ ዓመት እንኳ እየተመረተ ያለው 20 ቢሊዮን ብር የሚያስገኝ ምርት ብቻ ነው ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም ትኩረቱን በመካከለኛና ትላልቅ የማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ቴክኖሎጂን መጠቀም፣ መቅዳትና ማላመድን መሠረት ያደረገ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በማውጣት የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

በፖሊሲው አፈጻጸም ሂደት የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም መሰረታዊ ለውጥ ከማምጣት አንፃር ስኬታማ እንዳልነበር ከተደረጉ ጥናቶች መረዳት ተችሏል፡፡

በመሆኑም ለአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ልማት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ፤ የኢንተርፕራይዞችን የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ ከምርታማነታቸው ጋር ያላቸው ትስስር የሚያጠናክር፤ ለፈጠራ ስራ /Innovation/ ትኩረት የሚሰጥ ፖሊሲ በማስፈለጉ፣ ከግብርና እና ከማኑፋክቸሪንግ በተጨማሪ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይሲቲ ለአገራዊ ብልጽግና መሰረት ተደርገው በመወሰዳቸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲታገዙ ማድረግ የሚገባ በመሆኑ፣ በአጠቃላይ ለአዳዲስ ለውጦች እና ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት የሚችል እና የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማትን የሚያፋጥን ሁሉአቀፍ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ግብዓቶች በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

2. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው የ11 የአስፈጻሚ ተቋማትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ሲሆን በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት፡-

• የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን፣

• የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣

• የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣

• የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣

• የኢትዮጵያ ደን ልማትን ሥልጣን፣

• የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት፣

• የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣

• የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣

• የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣

• የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና

• የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት

አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ያጸደቀ ሲሆን ደንቦቹ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውሉ ምክር ቤቱ መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa