This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
To participate in the giveaway: 1. Follow @back2school_eth account on Instagram. 2. Put #backtoschoolafricaexpo and “to register call on +251 97 408 2036
+251 97 408 2037
in your TikTok video caption.
+251 97 408 2037
in your TikTok video caption.
ተቃዋሚው የአፋር ሕዝብ ነጻነት ፓርቲ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ባስቸኳይ ከአፋር ክልል እንዲወጡ እና መከላከያ ሠራዊት በክልሉ እንዲሰማራ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ፓርቲው ፌደራል መንግሥቱ ከሃላፊነት በመሸሽ ከትግራይ ኃይሎች ጋር ግንኙነት ሰላም ለመፍጠር የአፋር ሕዝብ እንቅፋት እንደሆነበት አድርጎ አቅርቧል በማለት ከሷል። ፌደራል መንግሥቱ እና ሕወሃት ተኩስ ለማቆም የደረሱበትን ውሳኔ በበጎ እንደሚያየው የገለጠው ፓርቲው፣ ሆኖም ውሳኔው የአፋር በርካታ አካባቢዎች በሕወሃት ቁጥጥር ስር ያሉ መሆናቸውን፣ የአፋርን ሰብዓዊ ቀውስ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ የሕዝቡን ጥቅሞች እና ስጋቶች ከግምት ያላስገባ በመሆኑ ውሳኔውን በጥርጣሬ እንደሚያየው ጠቁሟል። የአፋር ሕዝብ መገለል ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግጭት ውስጥ እንዳያስገባው ስጋት እንዳለውም ፓርቲው አስጠንቅቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር እርቅ እንዲያወርድ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ-መንበር ጥሪ አቀረቡ።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ይኸን ጥሪ ያቀረቡት ዛሬ የኦፌኮ ሁለተኛ አጠቃላይ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሔድ ሲጀምር ነው።ፕሮፌሰር መረራ በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ አመት በላይ በትግራይ ከተዋጋው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጋር ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስታውሰው በኦሮሚያም ባለሥልጣናቱ "ሸኔ" ከሚሉት ታጣቂ ጋር እርቅ ሊያወርድ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ኦፌኮ ከጅማሮው መቃወሙን ያስታወሱት መረራ አሁንም መንግስት በትግራይ ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያን ጨምሮ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ልዩነቶችን በእርቅ በመቋጨት ለህዝብ ሰላም እንዲሰጥ ጠይቀዋል "ማንም ያሸንፍ ፤ ጫካ ያሉት የኦሮሞ ልጆችም ያሸንፉ ፣ ሌሎችም ያሸንፉ ነገርግን የኦሮሞን ሕዝብ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል" ያሉት የኦፌኮ ሊቀ-መንበር "በኦሮሞ አምላክ ይሁንባችሁ። የቻላችሁ ሰዎች አስቡበት ብላችሁ ንገሯቸው።የኦሮሞን ህዝብ አጥፍታችሁ አትጥፉ፤ ይህ ጨወታ አያዋጣንም።በመላ የኦሮሚያ ዱር ላሉት ያቺኑ ለህወሃቶች የሰጣችኋትን ዕድል ለእነርሱም ስጡ" የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር መረራ በንግግራቸው ከኦፌኮ 206 ጽህፈት ቤቶች 203ቱን በመዝጋት እና አመራርና አባላትን በማሰር መንግስት ከምርጫ ተሳትፎ ፓርቲያቸውን እንደገፋ ጠቅሰው ተችተዋል።ዛሬ እና ነገ በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤው ኦፌኮ የአመራር ሹም ሽር ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዶይቼ ቬለ ዘግቧል።በፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤው ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ የእስር ቆይታ በኋላ ባለፈው ታህሳስ መጨረሻ የተፈቱት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ የፓርቲው አመራሮች ታድመዋል።
[DW]

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ገለጸ፡፡
ፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡ፓርቲው በዚሁ ጉባዔው ከፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በተጨማሪ፥ አቶ በቀለ ገርባን የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡እንዲሁም አቶ ጀዋር መሀመድን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ተገልጿል፡፡በተጨማሪም ፓርቲው እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤው አቶ ጀዋር መሀመድን ጨምሮ 17 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።ትናንት መካሄድ የጀመረው የኦፌኮ ጉባኤ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን፥ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡
[FBC]

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ፕሪምየር ሊጉ አድጓል!
ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ጨዋታ እየቀረዉ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
Via Hatrick Sport
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ጨዋታ እየቀረዉ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
Via Hatrick Sport
@YeneTube @FikerAssefa
የጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።ለፕሬዝዳንቱ ክብር 7 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።
ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለቱን አገራት ትብብር ወደላቀ ደረጃ የሚያደርስ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ኢትዮጵያና ጂቡቲ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው።

https://tttttt.me/sabinaadvisor
የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa
👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው
#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa
👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው
#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
Forwarded from Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡
ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡
ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።
ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።
እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun

ተዋናይ ዊል ስሚዝ ኦስካርስ በተሰኘው የፊልም ጥበብ የሽልማት መድረክ የሚስቱን ስም አንስቶ ያብጠለጠለውን ታዋቂውን ኮሜዲያን ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ።
ክሪስ ሮክ፤ የዊል ስሚዝ ሚስት ጄዳ ፒንኬት ስሚዝን የፀጉር ቁርጥ በቀልድ ወረፍ ካደረገ በኋላ ነው ይህ የተከሰተው።ዊል ስሚዝ ከመቀመጫው በመነሳት ወደ መድረኩ አቅንቶ ክሪስ ሮክን በጥፊ አጋጭቶ ሲመለስ ብዙዎች ጉዳዩ ቀልድ ነው ብለው አስበው ነበር።ነገር ግን ወደ ወንበሩ ከተመለሰ በኋላ "የሚስቴን ስም በ. . . አፍህ አታንሳ" ብሎ ሲጮህ ነው ብዙዎች ተዋናዩ ማምረሩን የተረዱት።
ስሚዝ ከዚህ ብዙዎችን ካስበረገገ ድርጊት በኋላ የኦስካር ሽልማቱን ሲያነሳ ለድርጊቴ ይቅርታ በሉኝ ብሏል።"አካዳሚውን [ኦስካር ሸላሚው ኮሚቴ] እንዲሁም ለሽልማት የታጩ የተውኔት አጋሮቼን ይቅርታ መጠየቅ እሻለሁ" ሲል ተማፅኗል።
ዊል ስሚዝ፤ ኪንግ ሪቻርድ በተሰኘው ፊልም ላይ የቴኒስ ከዋክብቱን ቬነስና ሰሪና ዊሊያምስ አባት ሆኖ በመተወኑ ነው በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስም የከበደውን የኦስካር ሽልማት ያገኘው።"ጥበብ የሕይወት ቅጂ ናት።ልክ እንደ ተወንኩት ሪቻርል ዊሊያምስ የእብደት ሥራ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ፍቅር የእብድ ሥራ እንድትሠሩ ያደርጋችኋል።"
ባለቤቱ ፒንኬት ስሚዝ ከዚህ በፊት የፀጉር መነቀል የሚያስከትል አለፔሲያ የተሰኘ በሽታ እንዳለባት ተናግራ ነበር።የዊል ስሚዝ ጥፊ ሰላባ የሆነው ክሪስ ሮክ በሁኔታው እጅግ ተደናግጦ "በቴሌቪዥን ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ክስተት ታድመናል" ሲል ተደምጧል።
Via BBC

በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ መቋቋም እንደተቻለ የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡
በሶማሌ ክልል ላለፉት ወራት በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ በተለይ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ የክልሉ መንግስት ድርቁን ለመቋቋምና ህዝብና እንስሳትን ለመታደግ በሰራው ስራ ድርቁን መቋቋም እንደቻለ ገልጿል፡፡
አሁን ላይ የድርቅ አደጋ ጊዜ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝና በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች የበልግ ዝናብ መጣል መጀመሩን የገለጸው የክልሉ መንግስት፤ ድርቁን ለመቋቋም እንደተሰራው ሁሉ፣ በድህረ ድርቁ ወቅትም ጠንካራ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ትላንት አመሻሹን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡
በክልሉ አካባቢዎች መዝነብ ከጀመረው የበልግ ዝናም በድርቁ የተጎዱ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግና በወንዞችና ተፋሰስ አከባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች፣ ወረርሽኝና ተዛማጅ ጉዳዮች ለመከላከል ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውንም አክሏል፡፡
የክልሉ አደጋ ስጋት አመራርና የጤና ቢሮ አመራሮች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወደ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በመውረድ አስፈላጊው ትብብርና ድጋፍ እንዲሰጡ የክልሉ መንግሥት ኮሚቴዎችን አዋቅሮ ማሰማራቱም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡
የድርቅ አደጋውን ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥትና ህዝብ ጎን በመሆን የክልል መንግስታትና ህዝቦች፤ ባለሀብቶች፣ ግብረሰናይ ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራል መንግሥት ላደረጉት ድጋፍና ትብብር የክልሉ መንግሥት ምስጋና ማቅረቡን ከክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአማራ ክልል በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው አራት ዞኖች የሚገኙ ከ60 ሺህ በላይ ህጻናትን መንከባከብ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ!
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋና ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞኖች የሚገኙና በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ60 ሺህ በላይ ህጻናትን መንከባከብ የሚያስችል ፕሮጀክት በደሴ ከተማ ይፋ ተደርጓል።ፕሮጀክቱ የአንድ ዓመት መርሃ ግብር ሲሆን፤ በአራቱ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ላይ ይተገበራል ተብሏል።
ፓዝ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ባደረገው የዳሰሳ ጥናት በአማራ ክልል ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ህጻናት በጦርነቱ ሳቢያ ክፉኛ መጎዳታቸውን ማረጋገጡን የፓዝ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ትርሲት ግርሻው ተናግረዋል። በአካባቢዎቹ የተደረገው ጦርነት በበርካታ ህጻናትና እናቶች ላይ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረሱን የጠቆሙት ዳይሬክተሯ፤ መርሃ ግብሩ ከሰሜን ወሎ ዞን ግዳንና ራያ ቆቦ ወረዳዎች፣ ከደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ፣ ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዞን ሰቆጣ ዙሪያና ዳህና ወረዳዎች እንዲሁም ከሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ የሚተገበር መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህም 60 ሺህ የሚደርሱ ህጻናትና ከ15 ሺህ በላይ የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶች በቀጥታ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል። ከ446 ሺህ በላይ ህዝብ ደግሞ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።ይህ የቅድመ ልጅነት ዘመን እንክብካቤ መርሃ ግብር 500 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፤ የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው ቢግ ዊን ፊላንትሮፊ የተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ነው።
በመሆኑም በአማራ ክልል የከፋ ጉዳት የደረሰባቸው በአራት ዞኖችና ስድስት ወረዳዎች የሚገኙ ህፃናትና እናቶች በዚሁ የክብካቤ በመርሐ ግብር መካተታቸውን ተናግረዋል።የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ያደታ፤ በኢትዮጵያ 59 በመቶ የሚሆኑ ህፃናት በዕድሜያቸው ልክ መድረስ ከሚገባቸው አካላዊና አዕምሯዊ ዕድገት ያልደረሱ ስለመሆናቸው ገልጸዋል።
ፓዝ ኢትዮጵያ የጀመረው የቅድመ ልጅነት ዘመን፣ የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶች ክብካቤ መርሃ ግብር ውጤታማ እንዲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ መጠቆማቸውን ከደቡብ ወሎ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።በፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን ም/ አስተዳዳሪ ተስፋ ዳኛው በበኩላቸው፤ ፓዝ ኢትዮጵያ የቅድመ ልጅነት ዘመን እንክብካቤው ህፃናት በአካላቸው የጠነከሩ በአዕምሯቸው የጎለበቱ ሆነው እንዲያድጉ የሚያስችል በመሆኑ፤ በሚመለከታቸው የመንግስት መዋቅሮች ተገቢው ድጋፍና ክትትል ይደረጋለታል ብለዋል።

በሱማሌ ክልል በቦምባስ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ሰዎች መሞታቸው ኢዜማ አስታወቀ!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መጋቢት 12/2014 በሱማሌ ክልል በቦምባስ ከተማ በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና በዜጎች ላይም የአካል ጉዳት ማጋጠሙን ታማኝ ከሆኑ ምንጮች መረጃ ደርሶኛል ሲል አስታውቋል፡፡
ፓርቲው በቦምባስ ከተማ ሊካሄድ በነበረው የአኪሾ የጎሳ መሪ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት፤ የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል በመጠቀማቸው የሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡
በክልሉ በተለያዩ ጊዜ ማኅበረሰቡን ያሳተፈ የጎሳ ምርጫ የሚደረግ ሲኾን፤ በቅርቡ ሊደረግ የነበረው የአኪሾ ጎሳ መሪ ምርጫ ድብቅ የፖለቲካ አላማ ያላቸው አካላት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ባደረጉት ጥረት በጸጥታ አካላትና በሕዝቡ መሀከል ግጭት እንዲነሳ በዛም ደግሞ ንጹሃንን ተጎጂ ያደረገ ጉዳት ደርሷል፡፡
በሱማሌ ክልል በተለያየ ጊዜ የሰውና የመንግሥትን ንብረት ያወደመ፣ የሰውን ሕይወት የቀጠፈ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ የግጭቱ መነሻ ምን እንደሆነ ሳይጣራ፣ አጥፊዎች ተለይተው ለህግ ሳይቀርቡ፣ የፍትህ ሥርዓቱ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ሳያስተላልፍ፤ በመንግሥት ኃላፊዎች እገዛ ጭምር ግልፅ ያልሆነ የእርቅ ሂደት መከናወኑ ግጭቶች እንዲደጋገሙ መንገድ ከመክፈቱ በተጨማሪ የክልሉን ሰላም ከቀን ወደ ቀን አስተማማኝ እንዳይሆን እያደረገው ይገኛል ሲልም ኢዜማ ገልጿል፡፡
የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከዚህ ድርጊት በስተጀርባ እጃቸው ያለበትና የሚመለከታቸውን አካላት ማንነት በማጣራት አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ ያሳሰበው ፓርቲው፤ ግጭቱን ተከትሎ የቆሰሉ አካላት ተገቢ ሕክምና እንዲያገኙ፣ የሟች ቤተሰቦችም ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡
[Addis Maleda]

ከፍተኛ ስርቆት በመዲናችን አዲስ አበባ ተፈጽሟል ተባለ!
- ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ተብሏል!
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጎሮ ሰፈራ ልዩ ቦታው ፖስታ ቤት መቲ ጋራዥ አካባቢ በቀን 11፣ 2014 ዓ.ም የቻይና ነጋዴዎች ተከራይተው ይሰሩበት የነበረው መጋዘን ላይ ከፍተኛ ስርቆት የተፈጸመው፡፡በዚህ ስርቆት 418 ያህል ቴሌቪዥኖች የተሰረቁ ሲሆን ቁጥራቸው የማይታወቅ ላፕቶፕ ኮምፒተሮች የመኪና ባትሪዎች እንደዚሁም 63ሺህ ጥሬ ገንዘብ አብሮ መሰረቁን ነው ኢትዮ ኤፍ ኤም አገኘሁት ያለው መረጃ የሚጠቁመው፡፡
እነዚህ ነጋዴዎች መጋዘኑን የተከራዩት ከአንድ ወር በፊት የነበረ ሲሆን ከቻይና በርካታ እቃዎችን እያስመጡ ለነጋዴዎች ያከፋፍሉበታል የነበረ መጋዘን ነው፡፡አቶ መኮንን ድርጊቱን ያቀነባበሩት የጥበቃ ሰራተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ያላቸውን ግምት ያስቀመጡ ሲሆን አሁን ላይ እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ብለዋል፡፡
ቃላቸውን ለፖሊስ የሰጡት የጥበቃ ሰራተኞች በበኩላቸው ስርቆቱ የተፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በለበሱ ሰዎች ነው ያሉት አቶ መኮነን ፣ከድርጊቱ መፈጸም በላይ የጸጥታ አካላት የሰጡት ምላሽ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡
የቤት አከራዩ አቶ መኮንን ስርቆቱ በተፈጸመበት እለት መብራት ጠፍቶ እንደነበረ እና የአይሱዚ መኪና መጋዘን ውስጥ ገብቶ መጫኑን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ጥቆማቸውን እንዳደረሱዋቸው ተናግረዋል፡፡
[Ethio FM]

“መንግስት ከታጠቁ ሃይሎች ጋር ድርድር መጀመር አለበት ”የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ)
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ) 2 መደበኛ ጉባዔ ከመጋቢት 17-18 ማካሄዱን ተከትሎ በሀገሪቱና በህዝቡ ያጋጠሙ ፈተናዎች ላይ በመወያየት የፓርቲውን ቀጣይ የትግል መዕራፍ እና እስትራቲጂ አቅጣጫውን አስቀምጧል።
ከ 4 ዓመታተ በፊት የመጣው ለውጥ ሀገራችን ወደአዲስ የሰላም እና ዲሞክራሲ ያሸጋገራል የሚል ተስፋ ቢኖርም የለውጡ ሂደት ተቀልብሶ ወደ ዲሞክራሲ የነበርው ሽግግር እድል ባክኖ የእርስ በርስ ጦርነትና የሀገር መፍረስ አደጋ ተጋርጦብናል ሲል የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ) የመደበኛው ግባዔ መጠናቀቁን ተከትሎ ባውጣው መግለጫ አስታውቋል ።
በቅርቡም የፌደራሉ እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ጦርነትን ለማቆም ያሳለፉት ውሳኔ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲለውጥ ጥሪውን አስተላልፏል ኦፌኮ።
መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋርም የገባበትን ጦርነት በሰላማዊ መንግድ ለመፍታት ቁርጠኝነቱን ሊያሳይ እንደሚገባም ፓርቲው አሳስቧል።
በሁሉም የአገሪት አካባቢዎች ግጭት እንዲቆም ፤ መንግስት ከታጠቁ ሃይሎች ጋር ድርድር እንዲጀምር እና ብሔራዊ ምክክሩ ላይ እንዲሳትፉ ፤ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች በተለይም የኦፌኮ እና ኦነግ አባለት ከእስር እንዲፈቱ የሚሉት ጉዳዮዎች ኦፌኮ በአቋም መግልጫው አጽኖት የሰጠባቸው ጉዳዮች ናቸው።

አዲስ አበባ በአፍሪካ ለኑሮ ውዷ ከተማ ተባለች!
ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ የተባለ ድህረገጽ ይዞ በወጣው መረጃ መዲናችን አዲስ አበባ በአፍሪካ ለኑሮ ውዷ ከተማ ተብላለች። ድህረገጹ ባወጣው አሃዛዊ ኢንዴክስ(index) አዲስአበባ በ58.92 በአንደኛ ደረጃ ተቀምጣለች። በሁለተኛ እና በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት የኮትዲቯሯ አቢጃን እና የዚምባቡዌዋ ሃራሬ ሲሆኑ 55.73 እና 52.33 በቅድመ ተከተል የተሰጣቸው ኢንዴክስ ነዉ።
https://africa.businessinsider.com/local/lifestyle/15-african-cities-with-the-highest-cost-of-living-index-scores/11ghkpw

#ወርቃማ_ሕጎች
የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
#አእምሮህ_ማግኔት_ነው!
ሁልጊዜም አእምሮህ ማግኔት መሆኑን አስታውስ፡፡ አንተን የተቆጣጠሩህን ሃሳቦች እና በውስጥ የሰረፁትን እምነቶች የሚያምኑ እና የሚያስቡ ሌሎች ሰዎች ወዳንተ እንደሚያቀርብም ልብ በል፡፡
በትክክለኛ መንገድ የስበት ህግ (law of attraction) ብለን የምንጠራው አንድ ህግ አለ፡፡ ውሃ ከፍታውን የሚፈልግበት፣ በህዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የየራሳቸውን አምሳያ የሚፈልጉበት ህግ፡፡ ፕላኔቶችን በትክክለኛ ቦታቸው ጠብቆ እንደሚያቆየው የስበት ህግ፡፡
ይህ ህግ የሚለዋወጥ ቢሆን ኖሮ የማንጎ ፍሬ ከአበባው ውስጥ በርራ በፓፓያ አበባ ውስጥ በመግባት በከፊል ማንጎ፣ በከፊል ደግሞ ፓፓያ የሆነ ዛፍ ይፈጥሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ግን ሰምተን አናውቅም፡፡ ይሄንን የስበት ህግ ትንሽ በመከተል በሴቶች እና በወንዶች መካከል እንዴት እንደሚሰራ ማየት እንችላለን፡፡
ውጤታማና ሃብታም ወንዶች የሚፈልጓት ሴት የእነሱኑ አይነት ሴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለ ወንድም እንደዚያው፡፡ ይህ የሚሆነው በተፈጥሮ ነው - ልክ ውሃ ወደ ታች እንደሚፈሰው፡፡
“ሁሉም አምሳያውን ይስባል” የሚለው አባባል የማይገሰስ ሀቅ ነው፡፡ አንድ ወንድ የሚፈልጋት ሴት በብዙ መልኩ እሱን የምትመስለውን ሴት መሆኑ እውነት ከሆነ፣ የምትፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰብ የእነዚህን ሰዎች ሀሳቦች እና እምነቶች በመቆጣጠር እና በማዳበር ማግኔት የመስራትን ጥቅም ማየት አትችልም?
#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና አዟሪዎች እጅ ይገኛል።
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ከነገ በስቲያ ጀምሮ ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ!
በሳዑዲ አረቢያ በእስር ቤት እና በማዕከላት ውሰጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።16 የመንግስት ተቋማትን በአባልነት የያዘው ኮሚቴው ዜጎችን መመለስ ለመጀመር የተደረጉ የመጨረሻ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ዛሬ የገመገመ ሲሆን ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ ዜጎችን መመለሱ እንደሚጀምር ይፋ ሆኗል።
በውይይቱ እንደተገለፀው የበረራ፣ የማቆያ ማዕከላት ዝግጅት፣ የመገልገያ ቁሳቁስ፣ የምግብ እና መጠጥ አቅርቦት፣ የአልባሳት፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የህክምና አገልግሎትን ለተመላሾች በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ በመቻል ረገድ የተደረጉ ዝግጅቶች በግብረ ሃይሉ አባላት ውይይት ተደርጎባቸዋል።የኮሚቴው ሰብሳቢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዳሉት የመመለሱ ተግባር ተመላሽ ዜጎችን ካሉበት አምጥቶ እስከ መኖሪያ ቀያቸው የማድረስ ስራን የሚሸፍን ነው።
ይህንኑ ከመነሻው እስከ መድረሻው በተሳለጠ ቅብብሎሽ ለመፈፀም ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አምባሳደር ብርቱካን አሳስበዋል።ተመላሾች አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ክልሎች ከየማዕከላቱ ቶሎ በማንሳት ወደ መኖሪያቸው መውሰድ ያለባቸው በመሆኑ ያደረጉት ዝግጅትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ክልሎቹ ያልተጠናቀቁ የዝግጅት ስራዎችን በቀሪ ቀናት እንዲያጠናቅቁ አሳስበዋል።በየጊዜው የቅበላ አቅምን በማሳደግ ዜጎችን ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለማውጣት መንግሥት የተቻለውን ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥልም አምባሳደሯ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለሥልጣን ሁለተኛውን የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ጨረታ በመጭው መስከረም እንደገና እንደሚጀምር ካፒታል ጋዜጣ ከባለሥልጣኑ መስማቱን ጠቅሶ ዘግቧል። ባለሥልጣኑ ጨረታውን ለማውጣት የሚያስችለውን ቅድመ ጥናት እንዳጠናቀቀ ዘገባው ገልጧል። ባለሥልጣኑ ለሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ በተያዘው ዓመት መግቢያ ላይ ጀምሮት የነበረውን የጨረታ ሂደት ባለፈው ታኅሳስ ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጫለሁ ማለቱ ይታወሳል።የሁለተኛው ቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ጨረታ ሂደት የተቋረጠው፣ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ኩባንያዎች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት እንደሆነ በወቅቱ ተገልጧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa