YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢንዶኔዢያ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት የተጎዱትን በመፈለግ ላይ የነበሩ የነፍስ አድን ሠራተኞች ሁለተኛ ዙር በተከሰተ የመሬት ናዳ ተጭኗቸው መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

መጀመሪያው በዌስት ጃቫ ቺያንጁዋንግ መንደር በጣለ ከባድ ዝናብ ሳቢያ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከስቶ ነበር።ሌላኛው አደጋ ደግሞ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው እየወጡ ባለበት ሰዓት የተከሰተ ነው።በአደጋውም ቢያንስ 12 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም።በኢንዶኔዢያ በዝናብ ወቅት የመሬት መንሸራተት አደጋ የተለመደ ሲሆን፤ የደን መጨፍጨፍ ለዚህ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል።በቅርብ የተከሰተው አደጋ ከዋና ከተማዋ ጃካርታ 150 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰሜዳንግ የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል።የአደጋ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ራዲይታ ጃቲ በመግለጫቸው እንደተናገሩት አደጋዎቹ ያጋጠሙት በ3፡30 ሰዓት ልዩነት ነው።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ኦፓል የተሰኘው ውድ ዋጋ የሚያወጣው የጌጣጌጥ ማዕድን (የከበረ ድንጋይ) በአዲስ አበባ ባልተለመ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በህገ ወጥ መንገድ እየተቸበቸበ መሆኑን ዋዜማ ሬድዮ ከምንጮቼ ሰምቻለው ብላለች። በከተማው እየታየ ያለው ህገ ወጥ የኦፓል ንግድ በህገ ወጥ መንገድ ሀብትን ከሀገር የማሸሽ አንዱ ስልት መሆኑን ከተለያዩ ምንጮች መረዳት ተችሏል ይላል ዘገባው። ዝርዝሩን ያንብቡት

http://bit.ly/2LjaE6I

@YeneTube @FikerAssefa
በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ዙርያ ድርድሩን ለመቀጠል ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ሱዳን አስታወቀች!

የሱዳን መንግስታዊ የዜና ወኪል ሱና እንደዘገበው የሶስቱ ሀገራት የኢትዮጵያ፣ግብፅና ሱዳን ተደራዳሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት ከግድቡ ውሃ ሙሌትና መያዝ ጋር በተያያዘ ለተጨማሪ ውይይት ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።

ሆኖም ግን የሶስቱ ሀገራት የውጪና የውሃ ሚኒስትሮች በቨርቿል ባካሄዱት ውይይት ድርድሩን ለመቀጠል ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ሱና ዘግቧልን።

ኢትዮጲያ ለአፍሪካ ህብረት በላከችው ደብዳቤ በወርሃ ሀምሌ 13.5 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በሁለተኛ ዙር ለመሙላት የቀረበውን ሱዳን ተቃውማለች።

የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ ውይይቶችን ላልተወሰነ ጊዜ አንቀጥልም ሲሉ ተናግረዋል።ሆኖም ግን ኢትዮጵያና የግብፅ በተናጠል በሰጡት መግለጫ የሱዳንን ተቃውሞ ከማዕቀፉ ውጪ ነው ሲሉ መተቸታቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።

ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
አስታራቂ ብሔራዊ ትርክት ለመገንባት የትምህርት አሰጣጡ በጥንቃቄ እንዲፈተሽ ማሳሰቢያ ተሰጠ!

ክልሎች በየፊናቸው በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርትን በፈለጉበት መንገድ ቀርፀው እየሄዱበት ያለው አካሄድ፣ መስተካከል እንዳለበት የታሪክ ምሁራን ጠየቁ። አስታራቂ ብሔራዊ ትርክት ለመገንባት የትምህርት አሰጣጡ በጥንቃቄ መፈተሽ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/3sdrLYg

@YeneTube @FikerAssefa
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በግማሽ በጀት ዓመቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ከ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ እንደገለጹት÷ በስድስት ወራት በከተማው በቦንድ ግዢ ሽያጭ እና በስጦታ የተሰበሰበው ገንዘብ ባለፉት 8 ዓመታት በድምሩ ከተሰበሰበው የሚበልጥ ነው::ከ2003 ዓ.ም ሐምሌ ወር እስከ 2012 ዓ.ም ሐምሌ ወር ባሉ ዓመታት በከተማዋ የተሰበሰበው 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር እንደነበር ጠቁሟል::ለገቢው ማደግ ምክንያት መንግስት ፕሮጀክቱን በግልፅነት መምራት መቻሉ እንደሆነ አመልክተዋል::

ፕሮጀክቱ ላይ የነበሩ ችግሮች ይፋ ተደርገው የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በሕዝብ እና በመንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር መደረጉንም አስታውቀዋል::የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መከናወንም ማህበረሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ እንዲያደርግ መነቃቃት መፍጠሩንም ጠቁመዋል::በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 789 ሚሊዮን ብር እሰበስባለሁ ያለው ከተማ አስተዳደሩ በግማሽ ዓመት ውስጥ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መቻሉንም አመልክተዋል::

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
በካፒቶል ሂል የተደረገውን አመፅ ተከትሎ ዲሞክራቶች በነገው ዕለት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚያስችል ድምፅ በህዝብ እንደራሴው ምክር ቤት ይሰጣሉ።

በካፒቶል ያጋጠመውን ክስተት ተከትሎ ትራምፕ አመፁን አነሳስተዋል በሚል ዲሞክራቶችን ይከሳሉ፡፡ውሳኔው የባይደን የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ቀናት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልና ትራምፕ በድጋሚ ለወደፊቱ በፌደራል መስሪያ ቤቶች ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ሊያግድ የሚችል ነው፡፡በምክር ቤቱ በነገው እለት አብላጫ ድምፅ ካገኘ ወደ ሴኔቱ ይላካል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልጣን ሊለቁ 10 ቀናት የቀራቸው ቢሆንም 2/3ተኛውን ድምፅ በሴኔቱ እንዲለቁ ከተሰጠ ስልጣናቸውን ይለቃሉ፡፡ሴኔቱ ግን ትራምፕ ከስልጣን ለመልቀቅ ያላቸው በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች በመሆናቸው ይህንን ለማድረግ የቀረው ግዜ የህገ-መንግስት ጥያቄ ውስጥ ሊከት ይችላል፡፡mየፖለቲካ ሳይንስ ሙሁሩ ፕሮፌሰር ቶማስ ኬበ በበኩላቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ህገ-ምንግስቱ በግልፅ ያስቀመጠው ነጥብ የለም ባይ ናቸው፡፡

Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
80 ኪሎሜትር የሚረዝመው የቱሉ ቦሎ -ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ወደ አሰፓልት ንጥፍ ስራ መሸጋገሩን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

እስካሁን ባለው አፈጻጸም 26 ኪሎሜትሩ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የፕሮጀክቱን ክፍሎች አስፓልት ለማልበስ እየተሰራ ነውም ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ሲሚንቶ ከፋብሪካዎች ተረክበው እንዲያቀርቡልኝ ከተመደቡ 37 የልማት ድርጅቶች እና ወኪሎች በትክክል ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉት ሰባቱ ብቻ ናቸው አለ፡፡

በሲሚንቶ ምርት ላይ የታየውን እጥረትና የዋጋ ንረት ተከትሎ መንግሥት ባለፈው ዓመት አዲስ የግብይት ሰንሰለት ተዘርግቷል ማለቱ ይታወሳል፡፡አዲሱ የግብይት ሰንሰለት 6 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት በመረከብ ለቸርቻሪዎች እንዲያከፋፍሉ እና ራሳቸውም እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው፡፡የልማት ድርጅቶቹ ራሳቸው ከሚመርጧቸው ወኪል አከፋፋዮች ጋር ተራ ገብተው ምርቱን ያነሳሉ ተብሏል፡፡ወኪል አከፋፋዮቹን ጨምሮ በአጠቃላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ 93 የሲሚንቶ አቅራቢዎች እንዳሉ ተነግሯል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 37ቱ ለአማራ ክልል ሲሚንቶ እንዲያቀርቡ የተመደቡ እንደሆኑ ከክልሉ ንግድ ገበያና ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አቢታ ገበያው ተናግረዋል፡፡በትክክል ለክልሉ ሲሚንቶ እያቀረቡ የሚገኙት ግን 8ቱ ብቻ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡በወር እየቀረበልን ያለውም 378,745 ኩንታል ብቻ ነው ብለዋል፡፡ድርጅቶቹ ግን 538,082 ኩንታል በወር ለክልሉ እያቀረብን ነው በሚል ለፌዴራል መንግስት ሪፖርት እያረቡ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

በትክክል እየቀረበ ካለው ጋር የ159,337 ኩንታል ልዩነት አለው ብለዋል፡፡ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሳውቀናል ያሉት ዳይሬክተሩ ከሠሞኑም በዚሁ ላይ ከፌዴራል መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ተናግረዋል፡፡በክልሉ ከሲሚንቶ በተጨማሪ በብረት መሸጫ ዋጋ ላይም ከፍተኛ ጭማሪ መታየቱን የተናገሩት አቶ አቢታ ይህን ተከትሎ የግንባታ ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ መቀዛቀዙን ጠቅሰዋል፡፡በክልሉ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ እስከ 600 ብር እንደሚሸጥ አቶ አቢታ ተናግረዋል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢ አሰባሰብ አብይ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

ከዞኑ ኮማንድ ፖስት ጋር በመቀናጀት ማሳ ላይ የሚገኝ የተፈናቃዮች ሰብል የመሰብሰብ ስራ በቅርቡ እንደሚካሄድ ተመልክቷል፡፡የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ባበክር ከሊፋ ዛሬ እንዳስታወቁት ፤ኮሚቴው ባለፈው ሳምንት ባደረገው ጥረት 9 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡ገቢው በአሶሳ እና መተከል ዞኖች ጨምሮ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የተሰበሰበ መሆኑን አመልክተዋል፡፡የመንግስት ሠራተኞች እስከ አንድ ወር ደመወዝ ፤የመንግስት ተቋማት ደግሞ እያንዳንቸው ከ20 ብር ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ኮሚቴው ለተፋናቃዮች በመጀመሪያ ዙር በ15 ቀናት ውስጥ 50 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ የያዘውን እቅድ እንደሚሳካ እንደሚያመላክት ጠቁመዋል፡፡ኮሚቴው ለማሰባሰብ ካቀደው ውጪ እስከ 31 ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብ፣ አልባሳት እና የቤት ቁሳቁሶችን ተፈናቃዮቹ ወደሚገኙበት በማድረስ ድጋፍ ያደረጉ የተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም መኖራቸውንም አወስተዋል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን፣ የስም ለውጥ ሊደረግለት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድ-ካስት ባለስልጣን ተቋማዊ የስም ለውጥ እንደሚደረግለት፣ የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አንዷለም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ሀላፊው ስለጉዳዩ ሲያብራሩ፣የኢትዮጵያ ብሮድ-ካስት ባለስልጣን፣10 ዓመታትን በተሻገረ አዋጅ እየተመራ ያለ እና ተቋማዊ ስያሜውም ዘመኑ ያስገኛቸውን ተጨማሪ የሚዲያ አማራጮችን ለመቆጣጠር የማያስችለው ነው፡፡አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅ ፀድቆ ስራ ላይ ሲውል፣የኢትዮጵያ ብሮድ-ካስት ባለስልጣን ተቋማዊ ስያሜው፣የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ወደ ሚል ይቀየራል፡፡

የባለስልጣኑንም ተጠሪነት አሁን ካለበት የማስታወቂ ሚኒስቴር ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይዞራል፡፡ከዚህ ባሻገርም የኢዲሱ አዋጅ መፅደቅ፣ለመ/ቤቱ ከሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ባለፈ፣የህትመት እና የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ለመቆጣጠር እንደሚያስችለው፣ የኢትዮጵያ ብሮድ-ካስት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አንዷለም ተናግረዋል፡፡አዲስ የተረቀቀው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ፣በሚኒስትሮች ም/ቤት ታይቶ፣ተጨማሪ ግብዓት ተካቶበት እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመርቷል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ወለጋ ዞን በሁለት ወራት ውስጥ 265 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለፀ፡፡

ሰሞኑን በዞኑ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተወሰደ እርምጃ 8 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡ፖሊስ መምሪያው እንዳስታወቀው 6 የኦነግ ሸኔ አባላት እና 87 ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡በሁለት ወራት በዞኑ ውስጥ በተሰራው የህግ የበላይነትን በማስከበር ስራው 265 የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገለፀው በወቅቱ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችም ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 4 መኮንኖች በዋስትና እንዲለቀቁ ፈቀደ!

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን በመመልመል ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ 4 መኮንኖች በ100 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወሰነ።ተጠርጣሪዎቹ ሌ/ኮሎኔል ምሩፅ በርሔ ፣ ኮሎኔል ገብረመድሕን ገብረመስቀል ፣ ኮሎኔል ተስፋይ ሃጎስ እና ኮሎኔል መብራቱ ተድላ ናቸው።

4ቱ መኮንኖች ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በርካታ ቀናት መቆጠሩን እንዲሁም መርማሪ ፖሊስ በተደጋጋሚ ሚሰጠውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መረጃዎችን በአግባቡ እየሰበሰበ ባለመሆኑ እያንዳንዳቸው የ100 ሺ ብር ዋስትና አስይዘው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል የቀድሞውን ርዕሰ መስተዳድር አባይ ወልዱን ጨምሮ እሁድ መያዛቸው የተነገረው የሕወሓት ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዘው አዲስ አበባ ከገቡት ውስጥ የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ የኖሩት እና ኋላም ወደ ትግራይ ሄደው የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ይገኙበታል፡፡እሁድ አባይ ወልዱና አብርሃም ተከስተን ጨምሮ 9 የሕወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው መነገሩ ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን ወደ ሕዳሴው ግድብ ድርድር መመለሷን ገለጸች!

“ግድቡን በተመለከተ ሌሎች አማራጮች ይኖራሉ” ሲሉ የሱዳን ዉጭ ጉ/ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡ ሀገሪቱ ትናንት ውድቅ ያደረገችውን ፣ ከባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ የማድረግ ሀሳብ መቀበሏንም ገልጻለች፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በራያ አላማጣ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ ደመወዝ አላገኘንም ሲሉ አማረሩ።

ከአላማጣ አስተያየታቸውን ለዶቼቬለ የሰጡት የመንግሥት ሠራተኞቹ እንዳሉት መንግሥት በትግራይ ሲያካሂድ የነበረውን የሕግ ማስጠበቅ ዘመቻን ተከትሎ ባለፉት ወራቶች ደመወዝ ባለመቀበላችን ለከፋ ችግር ተጋልጠናል ብለዋል፡፡

የራያ አላማጣ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴና የአላማጣ ከተማ አስተዳደር በበኩላቸው ችግሩ የተፈጠረው በሕግ ማስከበሩ ወቅት የሠራተኞች ሰነድ በመጥፋቱ ያንን የማሰባሰብና የማጥራት ሥራ ሲከናወን በመቆየቱ ነዉ ብለዋል። አሁን ግን ሥራው የተጠናቀቀ በመሆኑ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ሁኔታ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ ምንም እንኳ የባጀት እጥረት ቢኖርም በክልሉ ካቢኔ ተወስኖ ለሠራተኞቹ ደመወዝ ይከፈላል ብሏል፡፡ 

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ስነምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ህግን የማስከበር ሀላፊነት አብሮ አልተሰጠኝም አለ!

የሥነ-ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ፤ በተቋማት ውስጥ የአሰራር ጥናት ማድረግ እና በአፈጻጸም በመመሪያው መሰረት በመንግስት ተቋማት ግዢ እየተፈጸመ መሆኑን በማረጋገጥ ችግሮችን ከመለየት ባለፈ ፣ የሚመጡ ጥቆማዎችን መመርመር እና ማረጋገጥ እንደማይችል ተገልጿል፡፡ይህ በመሆኑም ኮሚሽኑ በሚፈለገው መጠን አቅም እንዳይኖረው አድርጎታል ሲሉ የኢፌድሪ የስነ-ምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጸጋ አራጌ በተለይ ለብስራት ተናግረዋል፡፡እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ ከሆነ ፣ ኮሚሽኑ አቅምና ጉልበት እንዲኖረው ከተፈለገ ህግን የማስከበር ሃላፊነቱ አብሮ ሊሰጠው ይገባል፡፡

ምን ያህል የሙስና ጥቆማ ቀረበ? ምን ያህሉስ ተመረመረ? ብሎ ፖሊስን ለመጠየቅ የሚያስችል ስርአት አለመዘርጋቱን በመጠቆም ፣ ጸረ ሙስናን እንዲከታተል ሃገራዊ ሃላፊነት የተሰጠው ግን ለኮሚሽኑ ነው ብለዋል፡፡ ይህም እንደሃገር መፈታት ያለበት ችግር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ሙስናን በሚመለከት ከህብረተሰቡ የሚመጡ ጥቆማዎች ቢኖሩ እንኩዋን ፣ ኮሚሽኑ የመመርመር እና የማረጋገጥ ብሎም ጉዳዩን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚያስችል አሰራር አብሮ እንዳልተሰጠው ሃላፊው ተናግረዋል፡፡በ2019 በወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከ183 ሀገራት 37በመቶ በማምጣት ሙስናን በመከላከል ረገድ 96ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ በኮንታ ልዩ ወረዳ ተገኝተዉ ሰሞኑን በይፋ የሚጀመረዉ ገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት የሚገነባበት ስፍራ እና የአከባቢዉን እምቅ ተፈጥሮ ሀብት ጎበኙ፡፡

በሀገራችን ከሚገነቡ 3 ትላልቅ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነዉ ኮይሻ ፕሮጀክት የሚገነባበት ሂደት ለማስጀመር የሚያስችሉ የተለያዩ ሀገራዊ፣ ክልላዊና ልዩ ወረዳዊ የሀብት ማሰባሰብና የግንዛቤ መፍጠር ንቅናቄ ሥራዎች ስሰሩ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በግንባታዉ አጀማመር ሂደትና በአከባቢዊ ኢንቨስትሜንት አማራጮች ዙሪያ ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ ከዉጭ ባለሀብቶችና ከፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአባቢዉ ተገኝተዉ ቆይታ ማድረጋቸውን የልዩ ወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

በህይወት ታሪካቸው እንደተገለጸው የማይጸብሪን ግንባር በመምራትና አካባቢውን ከጁንታው ነፃ በማድረግ የሕግ ማስከበር ዘመቻው እንዲሳካ ሀላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡ የጦር መሪ ናቸው።

የውትድርና ህይወትን በ17 ዓመታቸው የጀመሩትና ለ36 ዓመታት በትግል የቆዩት ኮሎኔል አለምነው በ51 ዓመታቸው በሀገረ ሠላም የጁንታውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከጠላት ጋር በተካሄደ ውጊያ ነው ህይወታቸው ያለፈው።
የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በጀግንነት ባህልና በክብር በደቡብ ጎንደር ዞን በንፋስ መውጫ ከተማ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈጽሟል።

የ5 ልጆች አባት የሆኑት ኮሎኔል አለምነህ ደርግን በማስወገድ፣ በኢትዬ ኤርትራና በሠላም አስከባሪነት ዘመቻዎችና በተለያዩ የትግል ቦታዎች ጀግንነታቸውን ያሳዩ ፅኑ የጦር መሪ እንደነበሩ #አብመድ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
በሞተር አሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ገደብ ቅሬታ አስነሳ

“የሰላም ማስከበር ዘመቻውን” ተከትሎ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ሞተር አሽከርካሪዎች ላይ ማምሻውን ከ 12 እስከ ሦስት ሰዓት ድረስ ደርቦ መጫን እንዲሁም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት በሁዋላ ከተማዋ ውስጥ የሞተር እንቅስቃሴዎች ማድረግ ላይ የተደረገው የሰዓት ገደብ አለመነሳቱ ቅሬታ አሰነስቷል።

"ከስራ መውጫ ሰዓቴ ምሽት አራት ሰዓት በመሆኑ ለትራንስፖርት ወጪ ተዳርጊያሁ" በማለት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ እና ሞተር አሽከርካሪ የሆነው አቶ ተስፋሁን ባዩ ቀሬታውን ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል።

አቶ ሽመልስ ፀጋዬ በበኩሉ "እንደሀገር ሰላምን ማስቀደሙ መልካም የሚባል ነው፤ ይሁን እንጂ በአንፃራዊነት አካባቢያዊ እንቅስቃሴው ከሌሎች አንፃር፤ ሰላም በመሆኑ ሊፈቀድ ይገባ ነበር፡፡" በማለት አስተያየቱን ተሰጥተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ታሪኩ ታመነ "በሀገር ደረጃ ያለውን የሰላም ማስከበር ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ተገምግሞ እየተተገበረ ነው፡፡ ደርበው በመጫንም ሆነ ሰዓት እላፊ ሲያሽከረክሩ የተያዙ ሞተረኞችን እየመከርን እየመለስን ነው፤ የሰላሙ ሁኔታ ምን ያህል አስተማማኝ ነው የሚለውንም ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ከገመገምን በሁዋላ ወደቀድሞው እንቅስቃሴ የሚመለስ ይሆናል" ብሏል።

ምንጭ: - አዲስ ዘይቤ
@Yenetube @Fikerassefa
የአጊቱ ጉደታ የቀብር ሥነ-ስርዓት

የአጊቱ ጉደታ የቀብር ሥነስርዓት አዲስ አበባ እንደሚፈፀም ታወቀ። በጣሊያን ውስጥ የፍየል ወተት ዉጤቶችን በማዘጋጀት እጅግ እዉቅናን ያገችዉ ኢትዮጵያዊትዋ አጊቱ ጉደታ አስክሬን ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መድረሱን የሃገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ትናንት ሰኞ በጣልያን የአጊቱ ጉደታ ቤተሰቦች ፤ወዳጆች እና አድናቂዎች እንዲሁም የሃገሪቱ ፖለቲከኞች እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት የፀሎት ስነስርዓት እና የአስክሬን ሽኝት ተካሂድዋል። በጣልያንዋ ትሬንቲኖ ግዛት ዉስጥ ከፍተኛ እዉቅናን ያገኘችዉ የአጊቱ ጉደታ ሱሌማን የተባለ በድርጅትዋ ታሰራዉ በነበረዉ ሱሌማን በተባለ የ 32 ዓመት ሰዉ መገደልዋ የታወቀዉ አጊቱ ተገድላ ቤት ዉስጥ ከተገኘች ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነበር። በኩባንያዋ ታሰራዉ ከነበረዉ ከዚህ ሰዉ ጋር አጊቱ በገንዘብ ክፍያ ቅራኔዉስጥ ገብተዉ እንደነበርም ተዘግቧል።
ከፍየል ወተት በምታመርተዉ አይብ ታዋቂነትን ያገኘችዉ አጊቱ ዶቼ ቬለ የኢንጊሊዘኛዉ የቴሌቭዝን ክፍል ስራዋና መኖርያዋ ቦታዋ ድረስ ሄዶ ዘገባ ሰርቶ ነበር። ኢጊቱ ጉደታ በምትኖርበት በጣልያን አፍሪቃዉያን ስደተኞችን በማገዝ ጣልያዉያንንም ጭምር በመርዳትዋ ተወዳጅነትዋ እጅግ የላቀ ነበር። የስደተኞች ተስፋ ሕይወት ስኬት ተምሳሌት እና ታታሪ ተብላም ትታወቃለች። «የፍየሎቹ ንግሥት» በሚል መጠርያም ትታወቃለች። የዛሬ 10 ዓመት ግድም ከትዉልድ ሃገርዋ ከኢትዮጵያ ወደ ጣልያን የመጣችዉ አጊቱ ጉደታ ከፍተኛ ትምህርትዋንም እዝያዉ በጣልያን እንዳጠናቀቀች ተዘግቦአል።
አጊቱ በያዝነዉ የጎርጎረሳዉያን ዓመት መጀመርያ ወር የመጀመርያ ቀን 43 ዓመት ይሞላት ነበር ። የቀብር ሥነስርዓትዋ በአዲስ አበባ ይፈፀማል። ነፍስ ይማር!

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa