YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ችግራችን ሊፋታ ነው!!ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አውቶማቲክ መክፈያ (ኤቲኤም ) ማሽኖችን እያደሰ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞቹ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት በጀመራቸው ስራዎች ካለፈው እሁድ ጀምሮ የተሻሻሉ የኤቲኤም ሶፍትዌሮችን መግጠም ጀምሯል።

ባንኩ የደንበኞችን መረጃ ፍልሰት ለመቆጣጠር እና ማሽኖቹ ፈጣን እና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ነው አዲስ ቴክኖሎጂ ያስገባው።

ሆኖም በቅርቡ የተጀመረው አዲስ አሠራር የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ዕድሳት ለማከናወን ከሚጠበቀው በላይ ጊዜ ወስዷል ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቢዝነስ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ በልሁ ታከለ ናቸው።

ባንኩ በመላው ሀገሪቱ 1ሺህ 7መቶ ኤቲኤም ማሽኖች አሉት፡፡ከእነዚህ ውስጥ 8መቶውን ለማዘመን እየሰራ ነው።

የቢዝነስ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ በልሁ ባንኩ የቴክኒክ ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመቅረፍ አስቦ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ይሁን እንጂ ከአቀደው በላይ ጊዜ በመውሰዱ የደንበኞች መጉላላት ገጥሞታል፡፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት 4 ሚሊዮን ካርድ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡

#አብመድ
@Yenetube @Fikerassefa
በኮሮና ቫይረስ መያዙ ሳይታወቅ ሕይወቱ ያለፈ ሰው የቀብር ሥነ ሥርዓት የፈጸሙና ንክኪ ያላቸው 45 ግሰዎች ወደለይቶ ማቆያ መግባታቸውን የእንሳሮ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ የሆነ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ ወደ ማቆያ ሳይገባ ናሙና ሰጥቶ ነበር፡፡ ናሙና እንደሰጠ በድንገት ውጤቱ ሳይታወቅ ሕይወቱ አልፏል፡፡ የግለሰቡ ሕይወት እንዳለፈም አስከሬኑ ወደ ትውልድ ቀየዉ ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ተልኳል፡፡ይህ የሆነው ባለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም ነበር፡፡ እስከዚው ቀን ድረስ ውጤቱ ስላልታወቀ ዘመድ አዝማድ ተሰብስቦ አስከሬኑን በመያዝ ወደ እንሳሮ ወረዳ አቅንቶ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እሑድ ግንቦት 30/2012 ዓ.ም ተከውኗል፡፡ በዚሁ ዕለት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሠረት ግለሰቡ የኮሮና ቫይረስ እንደነበረበት አረጋግጧል፡፡የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ መረጃው እንደደረሰዉ ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ሰዎች ጋር በመሆን የቀብር ሥርዓቱ በተፈጸመበት እንሳሮ ወረዳ አቅንቶ ከግለሰቡ ጋር ቀጥታ ንክኪ የነበራቸውን ግለሰቦች እየለየ መሆኑን የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ጸዳሉ ሰሙ ንጉሥ ተናግረዋል፡፡

የእንሳሮ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሲስተር በቀለች ሞገስ ደግሞ የቀጥታ ንክኪ ይኖራቸዋል በሚል ጥርጣሬ 45 ሰዎች በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ በወረዳው ሦስት ቀበሌዎች ላይ ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱና ባሉበት ሆነው ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነም ታውቋል፡፡ከሟች ጋር የቀጥታ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብው ከተጠረጠሩ ግለሰቦች ውጭም እነዚህ ግለሰቦች የነበራቸው የንክኪና ግንኙነት ታሪክም እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ድረስ በሰሜን ሸዋ ዞን ደረጃ 182 ግለሰቦች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡በእንሳሮ ወረዳ በለይቶ ማቆ እንዲቀመጡ የተደረጉት ግለሰቦች ናሙና ከዛሬ ጀምሮ መመርመር እንደሚጀምርም ታውቋል፡፡

#አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

በህይወት ታሪካቸው እንደተገለጸው የማይጸብሪን ግንባር በመምራትና አካባቢውን ከጁንታው ነፃ በማድረግ የሕግ ማስከበር ዘመቻው እንዲሳካ ሀላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡ የጦር መሪ ናቸው።

የውትድርና ህይወትን በ17 ዓመታቸው የጀመሩትና ለ36 ዓመታት በትግል የቆዩት ኮሎኔል አለምነው በ51 ዓመታቸው በሀገረ ሠላም የጁንታውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከጠላት ጋር በተካሄደ ውጊያ ነው ህይወታቸው ያለፈው።
የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በጀግንነት ባህልና በክብር በደቡብ ጎንደር ዞን በንፋስ መውጫ ከተማ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈጽሟል።

የ5 ልጆች አባት የሆኑት ኮሎኔል አለምነህ ደርግን በማስወገድ፣ በኢትዬ ኤርትራና በሠላም አስከባሪነት ዘመቻዎችና በተለያዩ የትግል ቦታዎች ጀግንነታቸውን ያሳዩ ፅኑ የጦር መሪ እንደነበሩ #አብመድ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa