YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አቦይ ስብሐት ነጋ ማን ናቸው?
ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን በመራው ኢህአዴግ ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ የነበረው የህወሓት ቀደምት ታጋይና መሪ እንዲሁም ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ በፌደራል መንግሥቱ ሲፈለጉ ከቆዩት ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ።
በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ መንግሥት ለግጭቱና ለቀውሱ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ሰዎች መካከል አቦይ ስብሐት ይገኙበት ነበር።

ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️

https://telegra.ph/Sebhat-01-12
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ ጎሹ እንዳላማው የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ
2. አቶ ደሳለኝ አስራደ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ
3. አቶ መስፍን አበጀ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ
4. ወይዘሮ ከድጃ ሁሴን በምክትል ቢሮ ኀላፊ ማዕረግ የአደረጃጀት ምክትል ዘርፍ አማካሪ ሁነው ተሹመዋል፡፡

(ምንጭ፡-አብመድ)
@YeneTube @FikerAssefa
ተሰናባቹን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን የሚደግፉ ነውጦች በመላው አሜሪካ ግዛቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ የአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይ አስጠንቅቋል።

መጪው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም ሹመታቸውን ከሚረከቡበት ቀንም ቀድመው ሊከሰቱ እንደሚችሉ ቢሮው መረጃ ደርሶኛል ብሏል።
በጦር መሳሪያ የታገዙ ነውጦች ዋሽንግተን ዲሲን ጨምሮ በአምሳ ግዛቶች መታቀዳቸውን ሪፖርቶች ቢሮው አግኝቷል።ጆ ባይደን ከስምንት ቀናት በኋላ በዓለ ሲመታቸው የሚካሄድ ሲሆን የዝግጅቱንም የፀጥታ ሁኔታ ለማስጠበቅ ከፍተኛ የደህንነት ስራዎች እየተሰራ ቢሆንም ፍራቻዎች ነግሰዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/american-election-01-12
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ዛሬም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወደውስጥ የመግፋቱን እና በድንበር አካበቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማጎሳቆሉ ሕገ ወጥ ድርጊት እንደቀጠለ ነው አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

ቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በትግራይ የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሱዳን በኩል ድንበር ጥሶ መግባቱን አስታውሰዋል።ይህ ድርጊት አሁንም ስለመቀጠሉ አንስተው ኢትዮጵያ ግጭቱን ቀጣናዊ ላለማድረግ ስትል መታገሷን ግን ደግሞ ትዕግሥትም ልክ እንዳለው አክለዋል።ዓለም ዐቀፍ ሕጎችን የጣሰው የሱዳን ድርጊት ለአገሪቱ ሕዝብም ሆነ ለመንግሥት እንደማይጠቅምና የሚገፋውም በሌሎች ሦስተኛ ወገን ኃይሎች እንደሆነ እናምናለን ብለዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ዛሬም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወደውስጥ የመግፋቱን እና በድንበር አካበቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማጎሳቆሉ ሕገ ወጥ ድርጊት እንደቀጠለ ነው አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር። ቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በትግራይ የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሱዳን በኩል ድንበር ጥሶ መግባቱን አስታውሰዋል።ይህ ድርጊት…
“አፍንጫህን የመታህን ወዲያውኑ አፍንጫውን ላትመታው ትችላለህ…” -አምባሳደር ዲና

ከሱዳን ጋር ባለው የድንበር ውዝግብ ኢትዮጵያ ለጦርነት እንደማትቸኩል አምባሳደር ዲና ተናገሩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፣ ሱዳን የሁለትዮሽ የድንበር ስምምነትን በመጣስ ወደ ኢትዮጵያ በተጠናከረ ሁኔታ ገፍታ የመግባት እንቅስቃሴ ላይ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ “ኢትዮጵያ ጦርነት ትጀምራለች ወይ?” ተብለው የተጠየቁት ቃል አቀባዩ “ጦርነት አያስቸኩልም፣ አፍንጫህን የመታህን ወዲያውኑ አፍንጫውን ላትመታው ትችላለህ ፤ ሌላ ጊዜ ግን አንገቱንም ልትቆርጠው ትችላለህ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ዘገባው የአል-አይን ነው፣ ለተጨማሪ👇

https://am.al-ain.com/article/sudanese-forces-are-still-pushing-into-ethiopia-said-dina-mufti

@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አራት የመከላከያ አባላትና ሰባት ንጹሐን ተገደሉ!

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ጭላንቆ ቀበሌ ባሳለፍነው ታኅሳስ 26/2013 አራት የመከላከያ አባላትና ሰባት የማኅበረሰብ ክፍሎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለጸ።

በመተከል ዞን ለወራት በዘለቀው የንጹሐን ዜጎች በታጠቁ ኃይሎች መገደል አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የአዲስ ማለዳ ዘግቧል።አዲስ ማለዳ ምንጮች እንደዘገበው ታኅሳስ 26/2013 በቡለን ወረዳ ጭላንቆ ቀበሌ ላይ ሕይወታቸውን ያጡ የመከላከያ አባላትና የማኅበረሰብ ክፍሎች ባልተጠበቀ ሁኔታ ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ ነው ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ስራ ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ቦሌ ፣ ስታዲየምና አካባቢው የውሃ እጥረት አጋጥሟል!

በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ስራ በጥንቃቄ ጉድለት ባጋጠመ ችግር ፣ 700 ሚሊ ሜትር ስፋት ያለው የውሃ መስመር ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ስራውን እየከወነ የሚገኘውና ጉዳቱን ያደረሰው CCCC የተባለ ተቋራጭ ስለመሆኑም ብስራት ራዲዮ ሰምቷል፡፡በግንባታ ስራው ሂደት ለውሃ መስመሩ ጥንቃቄ ባለመደረጉ ፣ ውሃ በሚያስተላልፈው ከባድ መስመር ላይ ጉዳቱ ሊደርስ ችሏል፡፡

በዚህም ምክንያት በጋንዲ ሆስፒታል ፣ አምባሳደር አካባቢ፣ ቦሌ ሮድ እስከ ደንበል በአጠቃላይ በስታዲየም ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት መቋረጡ ተገልጿል፡፡መስመሩን ጠግኖ ወደ መደበኛ ስርጭት ለማስገባት የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸዉ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

Via Bisrat Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት አራት ተከታታይ የችሎት ቀጠሮ ላይ ሳይቀርቡ የቀሩት እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ!

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ሁከት በማነሳሳት ወንጀት ተጠርጥረው የተከሰሱት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)አመራሮች እና በፖለቲከኛ ጃዋር መሃመድ ስም በተከፈተው መዝገብ ስር የተጠቀሱት ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

ባለፉት አራት ተከታታይ የችሎት ቀጠሮ ላይ ሳይቀርቡ የቀሩት አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም በሁለትና ሶስት ችሎቶች ላይ ያልቀረቡት አቶ ሃምዛ አዳኔ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሁሉም ተከሳሾች ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡ 

ከዚህ ቀደም ታህሳስ 08 ቀን 2013 በዋለው ችሎት የተከሳሾቹ "ልዩ ችሎት" በማረሚያ ቤት አቅራቢያ ይቋቋምልን ጥያቄን ውድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ በእለቱ በተከሳሾች ጠበቆች አማካኝነት ባደረሳቸው ትዕዛዝ ለዛሬው ችሎት "በኃይልም" ቢሆን እንዲቀርቡ የሚል ነበር፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ👇👇

https://telegra.ph/Jawars-trial-01-12
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ፣ ወምበራ፣ ድባጢና ቡሌን ወረዳዎች ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ እስከ ዛሬው ማክሰኞ በደረሰ ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።

በዞኑ ጉባ ወረዳ ትናንት ሰኞ በደረሰው ጥቃት ከ11 ሰዎች ህይወት አልፏል። በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ስፋራ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በዚሁ ጥቃት ሕይወታቸዉን አጥተዋል፤በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች የአካባቢዉ አመልክቷል፡፡አካባቢዉ ላይ ይኖሩ የነበሩና ጥቃቱ ሲከሰት የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች መኖራቸዉን ተጠቁመዋል፡፡ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት ይህንን ጉዳይ ለማጣራት የተደረገው ጥረት የስልክ ጥሪ ባለመቀበላቸዉ አልተሳካም፡፡

በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ በተባለ ስፋራ ትናንት ከሰዓት ታጠቂዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶችንም ማቃጠላቸው የተነገረ ሲሆን የተለያዩ የቁም እንስሳትን መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃት አድራሾቹ ዛሬ በማንዱራ ወረዳ ጉዳት ማድረሳቸው ታዉቋል።ከመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ከተማ በ40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘዋ በጎንዲ በተበለ ስፋራ ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ የታጡቁ ሸማቂዎች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ጉዳት ደረሰባቸው የአካቢው ነዋሪዎች በስልክ ለዶቼቬሌ ገልጸዋል። በዕለቱ ታጠቂዎቹ አድፍጠው በመጠበቅ በጸጥታ ኃይሎች ላይም ጥቃት መፈጸማቸውን ጠቁመዋል።

በወምበራ ወረዳ ሰንኮራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ለሚ ሰንበታ በበጎንዲ የግብርና ስራ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆን በስፋራ የደረሰውን ጥቃት ሸሽተው አሁን ከወረዳው ከተማ እነደሚገኙ አመልክቷል። "ታጠቂዎቹ በጎንዲ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኃላ ሁለት መኪኖችን አቃጥለዋል። የሞቱት ሰዎች 3ቱ የመነስቡ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ ሌሎቹ የሰንኮራ፣ ደብረዘይት፣ ጎጆር የተባለ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ናቸው። ሁለቱ ደግሞ የአንድ በተሰብ አባላት ሲሆኑ የጸጥታ ሀይሎችም ይገኙበታል።ወደ አስራ ስድስት ሰዎች ህወታቸው አልፈዋልም" ብለዋል።

ከክልሉ ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ፣ከዞኑ አስቸካይ ጊዜ አስተዳደደር( ኮማንድ ፖስት) ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ለማግኘት በስልክ ያረኩት ጥረት ስልክ ባለማሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ በቅርቡ በዞኑ የተቋቋመው ግብረ ኃይልም በዞኑ ሰላምን ለማስፈን ያስችላሉ የተባሉ ምክክሮችን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ማድረጉን ከኢዜአ የተገኘ መረጃ ያመልክታል፡፡

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
ኦፌኮ ከሀገራዊ ምርጫው ተገድዶ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል መኖሩን ተናገረ::

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ፖርቲ በሀገራዊ ምርጫው ስለመሳተፉ እስካሁን እንዳልወሰነ ተናግሯል።የፖርቲው ተቀዳሚ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለኤትዮ ኤፍኤም እንዳሳወቁት በመላ ኦሮሚያ በሺዎች የሚቆጠሩ አባሎቻችን ታስረዋል፤ በመቶዎች የሚቁጠሩ ቢሮዎቻችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተዘግተዋል ፤በሰላም የመንቀሳቀሱ ጉዳይም ችግር በመኖሩ ከምርጫው ገፍተን ልንወጣ እንችላለን ብለዋል፡፡

ህዝቡ አትግቡ ካለ መግባት ይቸግራል የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ በተለያየ አጋጣሚ ደጋፊዎቻችን ሰውን እያሳሰራችሁ የት ልትገቡ ነው የሚል ምላሽ እየሰጡን በመሆኑ የበለጠ ችግር እንዳይከሰትም በምርጫው ላለመሳተፍ እያጤንን ነው ይላሉ፡፡እኛ አሁን እያሳሰበን ያለው ነገር በምርጫ መሳተፍና አለመሳተፍ ሳይሆን ቀጣዩ የሀገሪቱ አንድነት ነው፡፡

ሁሉም ዜጋ በጋራ የሚኖሩባት የሚግባቡባት እንድትሆን ከአዳራሽ ያለፈ ብሔራዊ መግባባት የሚያመጡ መድረኮች ያሰፈልጋሉ ፤ ቅድሚያ እዚያ ላይ መደረስ አለበት ነው የሚል አቋም ፖርቲያችን አለው ነው የሚሉት፡፡ባለፉት ሀምሳ አመታት የሚጋጩ ህልሞችን ይዘን ተጉዘናል የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ አንድ ቦታ በቃን ብለን የሁላችንም ህልም የሚስተናገድበትን ወይም የሚቀራረብበትን ሙሉ ለሙሉ እንኳን ማስታረቅ ባንችል በሰለጠነ ፖለቲካ የምንይዝበትን መንገድ ካልፈጠርን በስተቀር ከሳሽና ተከሳሸነቱ አብሮን ይኖራል ባይ ናቸው፡፡ለዚህ ደግሞ ሁሉም ጣቱን ሌላው ላይ ከመቀሰሩ በፊት ራሱን ማየት ይኖርበታል ነው የሚሉት፡፡ህዝቡ አሁን የሚፈልገው ሰላም ነው ለዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችም ይሆኑ ሊሂቃኑ ራሳቸውን ከእኔ ይበልጣል ትርክት ማላቀቅ አለባቸው ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከጥቂት ቀናት ወዲህ በአገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች የሚስተዋለው እርጥበታማና ዳመናማ የአየር ፀባይ ቀጣይነት እንደሌለው ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

በአገሪቱ ወቅታዊ የአየር ፀባይ ለውጥ ዙሪያ የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገለፃ አድርገዋል፡፡ከጥቂት ቀናት ወዲህ በአገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች የሚስተዋለው እርጥበታማና ዳመናማ የአየር ፀባይ ቀጣይነት የሌለው በመሆኑ ስጋት የሚፈጥር እንዳልሆነ የኤጀንሲውና የአለም አቀፍ ትንበያ ማዕከላት መረጃ እንደሚጠቁም ተናግረዋል፡፡

ሆኖም በቀጣይ ጥቂት ቀናት መጠነኛ እርጥበታማና ዳመናማ የአየር ሁኔታ ቢጠበቅም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ስጋት የለም ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ አዲሱ የአየር ፀባይ ለውጥ የተከሰተውም ከህንድ እና ከፓስፊክ ውቂያኖሶች ተነስተው ወደ አገሪቱ በገቡ እርጥበትና ሞቃታማ የአየር ሳቢያ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በህገ-ወጥ መንገድ በተገነቡ እና በተወረሩ መሬቶች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የየካ ክፍለ ከተማ አስታወቀ፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በህገ-ወጥ መንገድ የተወረሩ መሬቶች እና ግንባታ የተካሄደባቸው ላይ ከህብረተሰቡ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል፡፡በክፍለ ከተማው ከ570 በላይ በህገ-ወጥ መንገድ የተወረሩ እና ግንባታ የተካሄደባቸውን መሬቶች አንድ ወር ጊዜ ውስጥ እርምጃ ለመውሰድ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎች በተደረገ የእርምጃ ስራ 127 የሚሆኑ የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ ግንባታዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ክፍለ ከተማው መግለፁን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ከፀጥታ አካላት እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ የተወረሩ እና ግንባታ የተካሄደባቸውን ቤቶች ላይ በሚወሰደው እርምጃ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ክፍለ ከተማው መልዕክቱን አስተላልፏል::

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር በድምቀት ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ለአስመራ ህዝብ ጥሪ መተላለፉን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መመሪያ አስታወቀ ።

የጥምቀት በዓል በጎንደር ከተማ በልዩ ድምቀት ይከበራል። ለዚህም ምክንያቱ ጎንደር የ44ቱ ታቦታት መገኛ፣ የነገሥታት መናገሻ፣ ታሪካዊ እና የአፄ ፋሲለደስ የባህር ጥምቀት ገንዳም መገኛ በመሆኗ ነው።

በመሆኑም ጎንደር ከአስመራ ህዝብ ጋር የነበራትን ጥንታዊ የጠበቀ ግንኙነት ለማስቀጠልና አብሮነትን ለማጠናከር አስመራ በዚህ በዓል እንድትታደም መጋበዟን ከከተማ አስተዳደሩ ባህል ቱሪዝም ስፖርት መመሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ባህረ ጥምቀቱን ምክንያት በማድረግ ወደ ጎንደር የሚሄዱ እንግዶችም በቦታው ሲገኙ ከሃይማኖታዊ ክዋኔ በተጨማሪ የጎንደርን ጥንታዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን እንዲጎበኙ ዝግጅት ተደርጓል። ለዚህም እንግዳ አክባሪው፣ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት እሳቤ እና አመለካከት ያለው የጎንደር ህዝብ እንግዶችን ለመቀበል ቅድም ዝግጀት ማጠናቀቁን ነው መምሪያው ያስታወቀው።

ባህረ ጥምቀቱን ለማክበር ሲደረግ የነበረው ሰፊ ዝግጅት መጠናቀቁን የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መመሪያ አስታወቋል።
በመመሪያው የባህል ዕሴቶች እና ኢንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪ ልዕልና ገብረ መስቀል እንዳሉት ለጥምቀት በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን ቆይቷል።

አቶ ልዕልና እንደሚሉት ከጥቅምት በዓል አከባበር አንዱና ዋነኛው ፋይዳ ማኀበራዊ ትስስርን ማጠናከር ነው። የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በአዋሳኝ አካባቢ የሚገኙ እና የአስመራ ህዝቦችን በማሰባሰብ የቀደመ ጠንካራ የታሪክና የበዓል ግንኙነታቸውን ለመመለስ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ቀድሞ የነበረው ጠንካራ ግንኝነት በሴረኛው ትህነግ ከተቋረጠ በኃላ የአስመራ ህዝብ ለጥምቀት በጎንደር እንዲገኝ የተላለፈ የመጀመሪያው ጥሪ መሆኑን የተናገሩት ቡድን መሪው ጥሪውም የነበረውን የቀደመ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
የጋራ ባህል ያላቸው ሁለቱ ህዝቦች የጥምቀት በዓልን በጋራ ማክበራቸው በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ የአንድነት ስሜት እንዲጠናከር እና በትውልዱ ዘንድ የማይበጠስ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።

የጥምቀት በዓል ለጎንደር እና አካባቢው ማኀበረሰብ ልዩ ድምቀት አለው ያሉት አቶ ልዕልና የበዓሉን ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊት ለመዘከር የአካባቢውን ባህልና ወግ የሚያስተዋወቁ ወጣቶች ፣ ጥበባዊ ሥራዎችን የሚያቀርቡ ባለሙያዎች፣ ኢግዚቢሽንና ልዩ ልዩ ሁነቶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በበዓሉ ጥሪ ለተደረገለት የአስመራ ህዝብም ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግ ታወቋል።

Via:- AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
የአፋር ክልል ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ጉባዔውን ያካሂዳል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው በጉባዔው የተለያዩ ወቅታዊ፣ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ወሳኔዎች ይተላለፋሉ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
Audio
ትምህርት ቤቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ምክንያት ተዘግተው ከርመው እንደገና ማስተማር ከጀመሩ ቀናት ተቆጠሩ፡፡

ኮሮናን እየተከላከሉ የመማር ማስተማሩ ሂደት ምን ይመስላል? ሲል ሸገር በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ምልከታ አድርጓል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን መከሰስ የፓርቲያቸው አባላት ጭምር እየደገፉ ነው

ዲሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥቂት ቀናት ከቀረው ሥልጣናቸው ለማባረር የሚያደርጉት ጥረት ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተነገረ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሥልጣን እንዲባረሩ የሚጠይቀው ክስ እንዲመሰረትባቸው ድጋፋቸውን ከገለጹት መካከል በተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛዋ የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴ ሊዝ ቼኒ፤ ባለፈው ሳምንት ዋሺንግተን ውስጥ ከነበረው ግርግር ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንቱ እንዲከሰሱ ድምጽ እንደሚሰጡ በይፋ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሳምንት ያህል ድምጻቸውን አጥፍተው ከቆዩ በኋላ ማከስኞ ምሽት በሰጡት ቃል ደጋፊዎቻቸው በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ለፈጸሙት ጥቃት ኃላፊነቱን እንደማይወስዱ ገልፀዋል።

የዛሬ ሳምንት በአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት የሚተኩት ዶናልድ ትራምፕን ከቀሯቸው የሥልጣን ቀናት በውርደት እንዲባረሩ ዲሞክራቶች ግፊት እያደረጉ ነው።

የአገሪቱ ምክር ቤት በፕሬዝዳንቱ ላይ አመጽ በማነሳሳት በሚቀርብባቸው ክስ ላይ በዛሬው ዕለት ድምጽ የሚሰጥ ሲሆን፣ በዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በስልጣን ዘመናቸው ሁለት ጊዜ የተከሰሱ መሪ ይሆናሉ።
የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ሴት ልጅ የሆኑት ሊዝ ቼኒ ባወጡት መግለጫ ላይ ትራምፕ "በሕገ መንግሥቱና በገቡት ቃል ላይ ክህደት ፈጽመዋል" ብለዋል።

የዋዮሚንግ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሊዝ ጨምረውም ፕሬዝዳንቱን "አመጸኞቹን ጠርተው በማሰባሰብ የጥቃቱን እሳት ለኩሰዋል" ሲሉ ከሰዋቸዋል።

ሁለት ተጨማሪ የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባላትም በትራምፕ ላይ የሚከፈተውን ክስ በመደገፍ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑትና የትራምፕ ወዳጅ ኬቭን ማካርቲ ክሱን እንደሚቃወሙት የገለጹ ሲሆን፣ የፓርቲያቸው አባላት በሙሉ በምክር ቤቱ ውስጥ የተቃውሞ ድምጽ እንዲሰጡ ጥሪ እንደማያደርጉ ገልጸዋል።

ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ለቅርብ ሰዎቻቸው ተናገሩት ብሎ እንደዘገበው፣ ፕሬዝዳንቱን በዲሞክራቶች መከሰሳቸው ትራምፕን ከፓርቲው ለማስወገድ ይረዳል ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል።

ማኮኔል ለተባባሪዎቻቸው ጨምረው እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሊያስከስስ የሚችል ጥፋት ፈጽመዋል ብለው እንደሚያምኑ ዋሽንግተን ፖስት ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
Audio
በቀጣዮቹ 20 ዓመታት 107 የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገነቡባቸው ከተሞች ከመላ ኢትዮጵያ ተለይተዋል ተባለ፡፡ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያሏት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ብዛት 13 ነው፡፡

ዘገባው የሸገር ነው፣ የድምፅ ዘገባው ከላይ ተያይዟል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች በግጭቶች ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች እየተደረገ ያለውን ድጋፍ ለማስቀጠል ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታውቋል፡፡

ማኅበሩ ባለፉት 3 ወራት በሀገሪቱ ግጭቶች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች 5 ቡድኖችን መድቦ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት 2 ሚሊዮን 5 መቶ 34 ሺህ 297 ዜጎች የምግብና ምግብነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች፤ የአልባሳት እንዲሁም የስነ-ልቦና እርዳታዎች እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል፡፡በግጭቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች እየቀረበ ያለውን ድጋፍ ለማስቀጠል 9 ቢሊዮን 48 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ማኅበሩ ከሚያደርጋቸው የድጋፍ ስራዎች በተጨማሪ ዜጎችን ለማቋቋም በዚህ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የሰብዓዊ ድርጅቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።ማኅበሩ በግጭት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከ11 ሚሊዮን 600 ሺ ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን፣ መድኃኒቶችና ሌሎች ድጋፎችን አድርጌ አለሁ ብሏል።

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባው የብርሐን ደባርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እና የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ትምህርት ቤቱ ተመርቋል።የቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማሳደግ በሚያደረገዉ ጥረት በጽሕፈት ቤቱ ግንባታቸው ከተጠናቅቁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ይገኛል።

ትምህርት ቤቱ በውስጡ የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን ያካተተ ሲሆን ለግንባታዉ 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበት አብመድ ዘግቧል።ጽሕፈት ቤቱ በዛሬዉ እለት ያስመረቀዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታቸዉ ተጠናቆ ከተመረቁት ስድስተኛው ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርብ ቀን በሁሉም ክልሎች እንደሚያስመርቅም ታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa