የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተቀናጀ የከተማ ውበት፣ አረንጓዴ ልማት እና በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ እንዲሁም በሌሎች የስራ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሴቶች እና ወጣቶች እያስመረቀ ነው።
ከተማ አስተዳደሩ ለ28 ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶች አዲስ የስራ እድል ለመፍጠር ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሁሉም የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልጿል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

የፋይዘር/ባዮኤንቴክ ክትባት በሁለቱ አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች ላይ ከታየው ለውጥ አንጻርም በሽታውን ለመከላከል እንደሚችል የቤተ ሙከራ ጥናቶች አመለከቱ።
ሆኖም ይህ በአዲሱ የቫይረሱ ዓይነቶች ውስጥ ከሚገኙት ከብዙ ለውጦች ውስጥ አንዱ ይህ ነው።
ጥናቱ ተቀባይነት ቢያገኝም ክትባቱ እንዴት እንደሚሰራ የሚያመለክት የተሟላ ሳይንሳዊ ማስረጃ ተደርጎ እየተወሰደ አይደለም።
በዩናይትድ ኪንግደም እና በደቡብ አፍሪካ አዳዲስ የቫይረሱ ዓይነቶች ተገኝተዋል።
ሁለቱም የቫይረሱ ዓይነቶች በፍጥነት እየተስፋፉ ሲሆን ለእነዚህ ዝርያዎች ምን ዓይነት የመከላከያ ክትባቶች ሊሰጥ ይችላል የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
በኮቪድ-19 የሚከሰት ሞትን ይቀንሳሉ የተባሉ ሁለት መድኃኒቶች ተገኙ
በአንድ ሰው ምክንያት የአውስትራሊያዋ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች
የሞደርና ክትባት በዩናይትድ ኪንግደም ፈቃድ በማግኘት ሦስተኛው ሆነ
በብዙዎች አመለካከት ክትባቶቹ አሁንም እንደሚሡሩ ቢሆንም ተመራማሪዎች ማረጋገጫ ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
በቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ጥናት በሁለቱም አዲስ ዓይነት ዝርያዎች ውስጥ በሚገኘው ኤን501ዋይ በሚባለው ልውጥ ዝርያ ላይ አተኩሯል።
'መልካም ዜና'
ተመራማሪዎቹ ሁለት የቫይረሱን ዓይነቶች ፈጥረዋል። እነዚህን ቫይረሶች በክሊኒካዊ ሙከራዎች ከተሳተፉ 20 ታካሚዎች በተወሰዱ የደም ናሙናዎች ላይ ምርመራው ተደርጓል።
በውጤቶቹም ክትባት የወሰዱት ሰዎች በሽታ የመከላከል ሥርዓት አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ለይቶ ማውጣት መቻላቸውን አሳይቷል።
ከኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ራቪ ጉፕታ "የተመረጠው አዲስ ዝርያ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከሚገኙ ከስምንቱ አንዱ ብቻ ነው። በእውነቱ ይህ ብቻውን ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል ተብሎ አይታሰብም ነበር" ብለዋል።
የለንደን የሃይጂን እና ትሮፒካል ሜዲሲን ትምህርት ቤት ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቴፈን ኢቫን በበኩላቸው "ተቃራኒው ውጤት ተገኝቶ ቢሆን ኖሮ ... ያ መጥፎ እና በጣም አሳሳቢ በሆነ ነበር" ብለዋል።
"አዎ ይህ ጥሩ ዜና ነው። ነገር ግን የፋይዘር ወይም ሌሎች ክትባቶች በእርግጠኝነት መከላከያ እንደሚሰጡን ገና ሙሉ መተማመን ላይ አልደረስንም" ሲሉ ገልጸዋል።
Via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa

ቻይና 11 ሚሊዮን ሰው በሚኖርባት ከተማ ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች
ቻይና በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ በምትገኘውና የ11 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ በሆነችው ሺጂያዡዋንግ ከተማ ውስጥ ከ100 በላይ አዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ስላገኘች የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች።
በዚህም ነዋሪዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዳይወጡ የተከለከሉ ሲሆን ትምህርት ቤቶችም ተዘግተዋል።
ነዋሪዎች ተመርምረው ውጤታቸውን ማወቅ እንዲችሉ በከተማዋ ከ500 በላይ የመመርመሪያ ቦታዎች ተከፍተዋል።
በከተማዋ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር በቻይና ለተከታታይ አምስት ወራት ከተመዘገበው አሃዝ ውስጥ ከፍተኛው ነው። ቻይና የወረርሽኙ ምልክት በታየባቸው አካባቢዎች ፈጣንና ጠንካራ እርምጃ መውሰድ ስለቻለች የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር ችላለች።
ምንም እንኳን በአንጻራዊነት ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም፣ በአገሪቱ በአንድ ስፍራ ላይ ሰብሰብ ያሉ ሰዎች በበሽታው ተይዘው በመገኘታቸው፣ መንግሥት የጅምላ መርመራ በማድረግ ህሙማኑን መለየት ችሏል።
@Yenetube @Fikerassefa

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግምቱ ከ97 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣና ንብረትነቱ የኢትዮ-ቴሌኮም የሆነ የተሠረቀ የስልክ መስመር ገመድ ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገለፀ።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ በግ ተራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።ርዝመቱ 63 ሜትር የሆነ እና ግምቱ ከ97 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ንብረትነቱ የኢትዮ ቴሌኮም የሆነ ኬብል ሰርቀው ቤታቸው እንዳስቀመጡት ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ 3 ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር አውሎ በምርመራ እየተጠራ እንደሚገኝ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች መርማሪ ዋና ሳጅን አሸብር አለሙ ተናግረዋል።
[AMN]

በህንድ ሆስፒታል በተቀሰቀሰ እሳት የ10 ጨቅላ ህፃናት ህይወት አለፈ!
በህንድ ማሃራሽታራ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታሎ በዛሬው እለት በተቀሰቀሰ እሳት በወሊድ ክፍል ውስጥ የነበሩ 10 ጨቅላ ህፃናት ህይወት አልፏል።በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ህፃናት እድሜያቸው ከቀናት እስከ 3 ወር ድረስ ያሉ መሆናቸውን የሆስፒታሉ ዶክተር ፓራሞድ ካሀንዴት ተናግረዋል።
የአደጋው መነሻ ምክንያት ያልታወቀ ሲሆን አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ግን ከአራስና የጨቅላ ህፃናት እሳቱ መነሳቱን ይናገራሉ።የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ባደረጉት ብርቱ ርብርብ ግን የሰባት ጨቅላ ህፃናትን ህይወት መታደግ ችለዋል።የህንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ራውል ጋንዲን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት የተሰማቸውን ሀዘን እየገለፁ ይገኛል።
[ብስራት ሬድዮ]

ከኢንዶኔዢያ ጃካርታ የተነሳ ከ50 በላይ ሰዎችን የጫነ ቦይንግ 737 የመንገደኞች አውሮፕላን በ10,000 ጫማ ከፍታ ባህር ላይ መብረር ከጀመረ በኋላ ደብዛው መጥፋቱን ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ጄነራል ብርሃኑ የጅቡቲ ከፍተኛ ወታደራዊ ሽልማት ተበረከተላቸው!
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ጅቡቲ ተገኝተው የሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ሽልማት እንደተበረከተላቸው በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ አምባሳደሩ “በሰሜን ኢትዮጵያ የተመዘገበውን የህግ ማሰከበር ዘመቻ ድል ጅቡቲዎች ከጄነራል ብርሃኑ ጁላ ጋር እያከበሩ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡
የቪዲዮ ሊንክ
https://www.youtube.com/watch?v=ppWtfv9-32g
[Al-ain]

በነገው ዕለት የታላቁ የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሚሽን ጠይቋል፡፡
ፖሊስ የሚያደርገውን የፀጥታ ዝግጅት በቀና መንፈስ በመተባበር የሚታወቀው መላው የመዲናዋ ነዋሪ እና የውድድሩ ተሳታፊዎች ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በዕለቱ መነሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የሚጀመረው ወድድር በአዲስ አበባ ስታዲዮም ሜክሲኮ አደባባይ በልደታ ቤተክርስቲያን በማድረግ በዛጉዌ ህንፃ በመታጠፍ-በጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ በፍልውሃ በመድረግ በካዛንቺስ በኡራኤል ቤተክርስቲያን የአትላስ መንገድ በመያዝ አክሱም ህንፃ አጠገብ መድረሻውን እንደሚያደርግ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር
-ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበልህንፃ
-ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍልጦር
-ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ
-ከሳር ቤት ወደሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
-ከካርል አደባባይ ወደከፍተኛ ፍ/ቤትየሚወስደውመንገድ ልደታ ፀበል
-ከጦርኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ ሜክሲኮ ለሚመጡ ጆስሐንሰን
– ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬበረንዳ
ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)
-ከቸርቸር ወደ አምባሳደር ፣ ሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ ቴድሮስአደባባይ
-ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደባባይ- ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ
-ከቦሌ መድኃኒያለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ
ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ በተጨማሪም ከውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተወዳዳሪዎቹ ወደሚያልፉባቸው መንገዶች መውጣት በጥብቅ የተከለከለ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በተጨማሪም ወድድሩ በሚካሄድባቸው መንገዶች ከማለዳው 11 ሰዓት ከ 30 ጀምሮ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አሳውቋል።

ወላይታ ዲቻ ዋና እና ምክትል አሰልጣኞቹን አሰናበተ!
ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ዋና አስልጣኙንና እና ምክትል አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡የወላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳሙኤል ፎላ በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ ሳሙኤል ከስድስት ጨዋታዎች አንድ ብቻ በማሸነፉ በዋና እና በምክትል አሰልጣኝ እንድሁም ስራ አስከያጁ መሰናበታቸውን ገልጸዋል።የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ህዝባዊ ክለብ በመሆኑ ከወላይታ ህዝብ ህልውና ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ከፋይናንስ ምንጭ ጋር ተያይዘው ተጨማሪ ምንጭ የማመንጨት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡በአጭር ቀናት ውስጥ የአስልጣኝ ቅጥር እንዲፈጽም ክለቡ ማስታወቂያ ማውጣቱም ተገልጿል። በአጠቃላይ 123 ሰራተኞች ያሉት ዲቻ ክለብ ዓመታዊ ወጪ 62 ሚልየን ብር እንደደረሰም ነው የጠቀሱት።
(ኤፍቢሲ)

YeneTube
👆👆 ከሰሞኑ በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሃት አመራሮች በምስል (ኢዜአ) @YeneTube @FikerAssefa
አቦይ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉ የሕወሓት አመራሮች ከነበሩበት ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ አቦይ ስብሃት በአስቸጋሪ ሰርጥ ውስጥ ከተደበቁበት መያዛቸው ይታወቃል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ግጭት የኤርትራዊያን ስደተኞች መጠለያ የሆኑት ሒጻጽ እና ሽመልባ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከሳተላይት ምስሎች ማረጋገጡን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ በሽመልባ ባለፉት ጥቂት ቀናት አንድ ትምህርት ቤት እና የዐለም ምግብ ድርጅት መጋዘን ተቃጥለዋል፤ በሒጻጽ ጣቢያ ደሞ በርካታ አገልግሎት መስጫዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል- ብሏል ዘገባው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ከቀናት በፊት ነውጠኛ የትራምፕ ደጋጊዎች ዋሽንግተንን ሲያምሱ ካፒቶል ሂል የሚገኘውን የናንሲ ፔሎሲን ቢሮ ሰብሮ በመግባት እግሩን ጠረንጴዛዋ ላይ በመስቀል ሲታይ የነበረው ሪቻርድ ባርኔት ዛሬ ማለዳ ከመኖሪያ ቤቱ ታድኖ ተይዞ ታስሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
በአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልዲያ የባቡር ፕሮጀክት ላይ የሚፈጸመው ስርቆት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ!
በሁለት ምዕራፎች ተከፍሎ በ1.7 ቢሊዮን ዶላር እየተገነባ ባለው የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልዲያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ላይ እየተፈጸመ ያለው ስርቆት፣ ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ ኃላፊ አስታወቁ፡፡ግንባታው ተጠናቆ በኤሌክትሪክ ኃይል ምክንያት ወደ ሥራ ባልገባው የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍም ሆነ 80 በመቶ በተጠናቀቀው ሁለተኛው ምዕራፍ ላይ በውድ ገንዘብ የተገዙ የተለያዩ ቁሳቁሶች፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ዝርፊያ እየተፈጸመበት መሆኑን የገለጹት የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልዲያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልከሪም መሐመድ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡
ለፕሮጀክቱ ሥራ ተብለው የተገጠሙት ስልኮች፣ ለግንኙነት ሥራ የሚያገለግሉ አፕል ካውንተሮች፣ የኤሌክትሪክ መስመርና ከአዋሽ ኮምቦልቻ በመሬት ውስጥ ለውስጥ የተገጠሙት የፋይበር ኬብሎች በአካባቢው አርሶ አደሮችና ሌሎች ግለሰቦች ለቤት መገልገያነት እየተዘረፉ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡ በተናጠል እስከ ሦስትና አራት ሚሊዮን ብር የሚያወጡት እነዚህ መገልገያዎች ለዝርፊያ መጋለጣቸው፣ ነገ ፕሮጀክቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝቶ ወደ ሥራ ቢገባም ከባድ ችግር ሊፈጥርበት ይችላል ብለው፣ አሁን ለፕሮጀክቱ የተገጠሙትን ቁሳቁሶች መጠበቅ ፈተና እንደሆነባቸው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡
የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልዲያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት በብዙ ፈተና ውስጥ እያለፈ ያለ ፕሮጀክት መሆኑን የሚናገሩት አብዱልከሪም (ኢንጂነር)፣ ከስርቆቱ ባልተናነሰ ለሥራ የተገጠሙና መሬት ላይ ያሉ ማሽኖች ወደ ሥራ ባለመግባታቸው፣ የመበላሸት ዕድል ያጋጥማቸዋል የሚል ሥጋት እንዳደረባቸውም ገልጸዋል፡፡ የመጀመሪያውና ትልቁ ምዕራፍ ከተጠናቀቀ 18 ወራት እንደተቆጠሩ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል አለማግኘት ሳቢያ ፕሮጀክቱን ከገነባው ሥራ ተቋራጭ ጋር ርክክብ እንዳልተፈጸመና ይህም ፕሮጀክቱን ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳርገው ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡
‹‹ያፒ መርከዚ የተባለው የፕሮጀክቱ ተቋራጭ የምዕራፍ አንድ ሥራ አጠናቆ እንድንረከበው ቢጠይቀንም፣ ፕሮጀክቱን እስከ ስድስት ወራት በሚደርስ የሙከራና የፍተሻ ጊዜ ካላረጋገጥን መረከብ አንችልም፡፡ በመሆኑም ተቋራጩ ከኃይል ጋር የተያያዘው ሥራ ኃላፊነቱ አለመሆኑን በመግለጽ በተደጋጋሚ ቅሬታ እያቀረበ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም እስካሁን ድረስ ንብረቶችን የሰው ኃይል ቀጥሮ እያስጠበቀ የሚገኘው ተቋራጩ እንደ መሆኑ፣ ይኼን ኃላፊነት ከላዩ ላይ ማውረድ ይፈልጋል ሲሉ አክለዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ሁለተኛው ምዕራፍም እንዲሁ ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር አለበት ተብሏል፡፡ ለፕሮጀክቱ ቅድሚያ ካሳ ተከፍሏቸው የተነሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ከአዲሱ አዋጅ ጋር በማያያዝ የካሳ ክፍያ አንሶናል የሚል ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ ሲሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡ከኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ፈትቶ ወደ ሥራ ለማስገባት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የደረሰ ችግሩን ለመፍታት እንቅስቃሴ እንደነበረ ያስታወቁት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል አቅርቦቱን አስተካክሎ ወደ ሥራ ለማስገባት ለአንድ የቻይና ኩባንያ በጨረታ ቢሰጥም ኩባንያው አለማስረከቡን፣ በዓመት ውስጥ ይከናወናል የተባለው ሥራ እንዳልተጀመረ፣ የሚመለከታቸው አካላትም ለችግሮቹ እልባት እንዲሰጡ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ ዋና ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል፡፡
Via Reporter

በመተከል ዞን የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት በአመለካከት ላይ ሰፊ ሥራ መስራት እንደሚያስፈልግ የአካባቢው ነዋሪዎች አሳሰቡ።
በፌዴራል መንግስት ተቋቁሞ የሕግ የበላይነት በማስከበር ላይ የሚገኘው ግብረ ኃይል ከመተከል ዞን ምሑራን ጋር ተወያይቷል።በዞኑ ለተፈጠረው ችግር ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸውን ያነሱት ምሑራኑ በዋናነት ግን የወጣቱ አመለካከት በጥፋት ሃይሎች መመረዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለዚህ ደግሞ በማኅበራዊ ድረ ገፆች፣ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃንና በአመራሮች ሳይቀር አንድን ወገን የሚደግፉ፣ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ብሄርን ከብሄር የሚያጋጩ መልዕክቶች አሁንም ድረስ እየተላለፉ መሆኑን ጠቁመዋል።
በነበረው ሁኔታ በተለያዩ አካላት የጥፋት መልዕክቶች ሲተላለፉና የማኅበረሰቡ አመለካከት ሲመረዝ ሃላፊነቱን የተወጣ አካል አለመኖሩንም አንስተዋል።
ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በመተከል ዞን የሚኖሩና መላው ኢትዮጵያዊያን እንደ ኢትዮጵያዊ ማሰብ እንዳለባቸው አመልክተዋል።
በዞኑ አንድ ዜጋ ሲጎዳ በብሄሩ ሳይሆን ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያዝን ማኅበረሰብ ካልተፈጠረና ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን በአንድ ላይ የሚታገል ማኅበረሰብ ካልተፈጠረ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚመዝንና በእኩል የሚያይ ዜጋ የመፍጠር ጉዳይ የሁሉም ሃላፊነት መሆኑንም ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ በተለይ መገናኛ ብዙኀን፣ የሠብዓዊ መብት ተቋማትና ተሟጋቾች እንዲሁም ሌሎች ገለልተኛ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት ሲገባቸው “ዘንግተውታል” ነው ያሉት ምሁራኑ።በዚህ ረገድ በተለይ መገናኛ ብዙሃን፣ የሠብዓዊ መብት ተቋማትና ተሟጋቾች እንዲሁም ሌሎች ገለልተኛ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት ሲገባቸው “ዘንግተውታል” ነው ያሉት ምሑራኑ።
በተለይ የመተከልን ሠላም ማጣት በተመለከተ አንዳንድ የማኅበራዊ አንቂዎች፣ ኀላፊነት የጎደላቸው አመራሮችና መገናኛ ብዙሃን ወገንተኛና አድሏዊ የሆኑ ችግሩን የሚያባብሱ መመረጃዎችን እያሰራጩ መሆኑን ተናግረዋል።
በዞኑ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ አመላካችና ሚዛናዊ ስራ ነው የሚያስፈልገው ነው ያሉት ምሁራኑ መንግስት ከዚህ የወጡ አካሄዶችን እያየ የእርምት እርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል።
ውይይቱን የመሩት የኮማንድ ፖስቱን የፀጥታ ሃይል በበላይነት የሚመሩት ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ለኢዜአ እንደተናገሩት ችግሩ ሆን ተብሎና ለ30 ዓመታት ታስቦበት የተሰራ መሆኑን ግብረ ሃይሉ ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር ባካሄዳቸው ውይይቶች መገንዘቡን ተናግረዋል።

በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሀብታሟ ይመር ስጦታው ለተባለች ኢትዮጵያዊት የግማሽ ሚሊዮን ብር የጉዳት ካሣ በዛሬው ዕለት እንዲከፈላት ማድረጉን አስታወቀ።
ግለሰቧ ጠፍታ በምትሠራበት ቤት እያለች መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም በአሠሪዋ ልጅ በሽጉጥ ተመትታ ጉዳት ደርሶባት እንደነበር ኤምባሲው ገልጿል።በዚህም ምክንያት በፈርዋንያ በተባለ ሆስፒታል ሕክምና ስትከታተል የነበረ ሲሆን፣ ለደረሰባት ጉዳት ካሣ እንዲከፈላት ኤምባሲው ከፖሊስ ጋር በመሆን ጉዳዩን በጎ ፈቃደኛ ጠበቃ አቁሞ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን አመልክቷል።በዚህም መሠረት ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ የአገሪቱ ፍርድ ቤት ለተጎጂዋ 4000 የኩዌት ዲናር (512 ሺህ ብር) እንዲከፈል ውሳኔ ማሳለፉን ጠቅሷል።ተጎጂዋ ወደ ሀገሯ እስክትመለስ ድረስ በመንግሥት መጠለያ እንድትቆይ መደረጉንም በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ሱዳን የባለሙያዎቹ የተጨማሪ ሃላፊነት ቢጋር ካልተዘጋጀ በቀር ውይይት መካሄድ አይችልም የሚል አቋም መያዟ ተገለጸ!
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነ መረብ ስብሰባ አካሂደዋል።ስብሰባው በደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት ተካሂዷል።ሚኒስትሮቹ የሕዳሴ ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል። ስብሰባው ባሳለፍነው ሳምንት እንዲካሄድ ስምምነት ተደርሶበት የነበረውን የሦስትዮሽ ስብሰባ ላይ ሱዳን ባለመገኘቷ ምክንያት ከቀረ በኋላ የተካሄደ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ኅብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ድርድሩን ለማስቀጠል ይረዳል በሚል አገራቱ ለሦስት ቀናት ለአፍሪካ ኅብረት ባለሞያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ እንዲያካሂዱ፣ በማስከተል የሦስትዮሽ ስብሰባ እንዲካሄድ እና ውጤቱ ለሊቀመንበሯ እንዲገልጽ ሐሳብ አቅርበዋል።ኢትዮጵያ እና ግብጽ ይህንን ተቀብለው ለመቀጠል የተስማሙ ሲሆን፣ ሱዳን ሐሳቡን ባለመቀበሏ ስብሰባው በዚሁ መጠናቀቁን ሚኒስቴሩ ገልጿል።ኢትዮጵያ የሱዳን ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲቻል በግድብ ደህንንነት፣ በመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በሌሎች ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መፍትሔ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ተጨማሪ የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ ከመከላከያ የከዱ አመራሮችም እርምጃ እንደተወሰደባቸው መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-
1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የህወሓት ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበሩ
2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ህወሓትን የተቀላቀሉ
3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች
4ኛ - ሁለት መስመራዊ መኮንኖች
5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ህወሓት የተቀላቀሉ ናቸው።
በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰራዊቱ ማምሻውን ገልጿል።
እነዚህም ፦
1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩ
2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩ
3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበሩ
4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበሩ
5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበሩ
6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበሩ
በተጨማሪም ሁለት ከሀገር መከላከያ ከድተው ህወሓትን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ ናቸው።
[ENA]