YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሱዳን በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ላለመሳተፍ ወሰነች!

ሱዳን ሚኒስትሮች በህዳሴው ግድብ ላይ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንደማትሳተፍ ገልጻለች፤ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ሚና ድርድሩን እንዲያመቻቹም እንዲሆን ጠይቃለች፡፡የሱዳን መስኖና የውሃ ሃብት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ካርቱም በፊት በነበረው አካሄድ በሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንደማትሳተፍ ወስናለች፡፡ሱዳን ከዚህ አቋም ላይ የደረሰችው የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል እንደ አመቻች ሆነው እንዲያገለግሉ ትፈልጋለች፤ለዚህ ያቀበቸው ምክንያት ያለፉት የድርድር ዙሮች ጥቅም የሌላቸው ሆነው በማግኘቷ መሆኑን ገልጻለች፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 473 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፣ 209 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 589 የላቦራቶሪ ምርመራ 473 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ሺህ 352 ደርሷል።በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት ከበሽታው ያገገሙ 209 ሰዎች ጨምሮ በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 65 ሺህ 534 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 636 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ ማስጠንቀቂያ አለመስጠቱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ አረጋግጠዋል ሲል ራሱ ዶይቼ ቬለ ዘገበ።

ዋና ዳይሬክተሩ በዶይቼ ቬለ ዘገባዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሉት ያሏቸውን ቅሬታዎች ግን በዝርዝር አስረድተዋል።ባለሥልጣኑ የሬውተርስ የአዲስ አበባ ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ፤ ለዶይቼ ቬለ እና ለቢቢሲ ራዲዮ ጣቢያዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ የሚል መረጃ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተሰራጭቶ ነበር። መረጃው የተሰራጨው የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ለሸገር ራዲዮ ጣቢያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ መሠረት በማድረግ ነው።

"ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው ማስጠንቀቀያ የለም። ምን አልባት ቢሯችን ጠርተን ያደረግንው ምክክር እንደዚያ ተደርጎ ተገልጾ ከነበረ ስህተት ነው። የጽሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር ግን ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው የለም" ያሉት ዶክተር ጌታቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በዘገባዎች ላይ ቅሬታዎች እንዳሉት አስረድተዋል።"ወደ አንድ ወገን ማጋደላችሁ ይኼ ነው ሊባል የሚችል አይደለም። በብዙ ቅሬታ አቅራቢዎች ጭምር የተደገፈ ነው።እኛም ደግሞ በሙያዊ ትንታኔ ያንን አይተን ያንን ቅሬታችንን የምናቀርብ ይሆናል። በዚህ አይነት ከቀጠለ ሌሎቹን ተጠያቂ እንዳደረግንው ሁሉ ዶይቼ ቬለ በዚያ መልኩ አይጠየቅም ማለት አይቻልም" ሲሉ ተቋማቸው ያለውን ቅሬታ ዶክተር ጌታቸው አስረድተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ በሚል የተጠረጠሩ 93 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።

የህወሓት ቡድን በትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ጥቃት እንዳይፈፀም ጠበቅ ያለ ጥበቃ እየደረገ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተናገሯል።በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫዎችና ሰብስቴሽኖች፣ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ጥበቃው መጠናከሩን ኮሚሽኑ በመግለጫው ተነግሯል።በቦሌና በየክልሉ በሚገኙ ኤርፖርቶች፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በውሃ ግድቦች፣ በነዳጅ ዲፖዎች፣ ፋብሪካዎችና ድልድዮችም ፣በስደተኛ ካምፖች፣ በሳተላይት ጣቢያዎች ፣ በማዕድን ማውጫዎች እንዲሁም በሌሎች ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉትን ጥቃቶች አስቀድሞ ለማክሸፍ ጥብቅ ክትትልና ቋሚ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከዚሁ ከፍተኛ ጥበቃና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ በወንጀል የጠረጠሩ 93 የህወሃትና የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።በተደረገ ፍተሻና አሰሳ እንዲሁም በህብረተሰቡ ጥቆማም 30 የመከላከያና የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ 47 የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ 43 የተለያዩ ሽጉጦች፣ 1 ሺ 376 የተለያዩ ጥይቶች ፣ 7 ቦምቦች፣ 2 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 102 ድምፅ አልባ መሳሪያዎች መያዛቸውን ሰምተናል።በተጨማሪም 8 የእጅ ራዲዮ መገናኛ፣ የተለያዩ የቴሌኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች፣ 534,870 ብር እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎች መያዛቸው ተነግሯል።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ፍቅር...

👉ለመላው የቴዎድሮስ ካስሁን(ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎች "ወደ ፍቅር" የተሰኘው ማህበራችን በየ 3 ወር ልዩነት የደም ልገሳ መርሀ ግብር እንዳለው ይታወቃል ስለሆነም በመጪው እሁድ #ህዳር_13 #በብሔራዊ_የደም_ባንክ አገልግሎት ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው ቅጥር ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 03:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራማችን ይጀምራል ስለሆነም መላው #የቴዲ_አፍሮ ወዳጆች በዚህ ቀን ህይወት ለማዳን ተጋብዛችኋል።

👉ለበለጠ መረጃ ከስር ባሉት ስልክ ቁጥሮች መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
0947646445/0913668491

💚💛ፍቅር ያሸንፋል!!!
በትግራይ የተከፈቱ የትኛውም የባንክ አካውንቶች ለጊዜው መንቀሳቀስ አንዳይችሉ ብሔራዊ ባንክ አዟል!

አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ አንደዘገበው በትግራይ የተከፈቱ የትኛውም የባንክ አካውንቶች ለጊዜው መንቀሳቀስ አንዳይችሉ ብሔራዊ ባንክ አዟል።በዚህም መሰረት ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ገንዘብ ማውጣት አይችሉም።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማ ደረጃ 49 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው 5 አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በዛሬው ዕለት በይፋ አሰጀምሯል።

የፕሮጀክቶቹ ማስጀመሪያ ላይ፣ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና አፈጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ እንዲሁም የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የካቢኔ አባላት ተገኝተዋል።ዛሬ ከተጀመሩት ፕሮጀክቶች መካከል 4ቱ በኮዬ ፈጬ እና ቱሉዲምቱ የጋራ መኖሪያ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን ሌላው ከሲኤምሲ ወደ ጎሮ የሚወስድ የመንገድ ፕሮጀክት ነው።የመንገድ ፕሮጀክቶቹ በ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ 49 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ እና ከ15 እስከ 40 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ ገልጸዋል።ፕሮጀክቶቹ በአንድ ዓመት ከ7 ወር እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ሥራ እንደሚጀምሩ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአንድ ሳምንት ብቻ 51 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ከዚህ ውስጥ ከ31 ሚየን ብር በላይ የሚገመተው ወደ ሀገር ሲገባ ሲሆን ከ20 ሚሊየን  ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ነው ተብሏል፡፡በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የቁም እንስሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ ጌጣጌጥ፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና አደንዛዥ ዕፅ ይገኙበታል፡፡በከፍተኛ መጠን ከተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ በሞያሌ ቅርንጫፍ ስር በሚገኙ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ነጌሌ ቦረና፣ ቡሌሆራ መስመር አድንዛዥ ዕፅ፣ በሀዋሳ ቅርንጫፍ ስር በሚገኙ ጢጢቻ፣ ጪጩ፣ ኮንሶ፣አዳባ፣ ዲላ መስመር ዘጠኝ ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ስጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ ናቸው፡፡

እንዲሁም በሞያሌ ቅርንጫፍ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ እንዲሁም በድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀረር፤ ድሬደዋ፣ ለጋር፣ ቢዮቆቤና ደወሌ መስመር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ  የሚገመት የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሲጋራ፣ ኮስሞቲክስ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡እንዲሁም በባህርዳር ቅርንጫፍ ሰራቫ፣ ሻውራ፣ መተማ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች 30 የብሬይን ጥይት፣ 166 የክላሽ ጥይት፣ 2 ሺህ 771 የአሜሪካን ዶለር በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ የሚጀምር ከከባድ ተሽከርካሪዎች የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የሰዓት ገደብ ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የሰዓት ገደቡን ያሳለፈው በአስተዳደሩ እየተከሰተ ካለው የትራፊክ መጨናነቅና በዚህም ሳቢያ እየተፈጠረ ያለውን የመንገዶች መዘጋትና መጉላላት ለመቀነስና ለማስቀረት አስቦ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

ገደቡ ከነገ ጀምሮ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስን ያግዳል ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የፈቀደው ከምሽት 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!!

የመከላከያ ሠራዊት ከአዲግራት ወደ መቀሌ በሚወስደው መንገድ የምትገኘውን እዳጋ ሐሙስ ከተማን ተቆጣጥሯል። የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቀሌን ለመያዝ እየገሠገሠ ነው።

[የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ]
@YeneTube @FikerAssefa
“መቀሌን በታንክ ለመክበብ ከሚያስችል ውጊያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን”-መከላከያ

በተለያዩ ግንባሮች ከህወሓት ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት ጋር እየተዋጋ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ያለው የመከላከያ ሰራዊት በራያ ግምባር ከከተማዋ በ70 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ትናንት ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ በራያ ግንባር የሚደረገው ዘመቻ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል ያሉት የግንባሩ የሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ የተራራ ውጊያዎችን ጨርሰን ቁልቁል ከምንወርድበት የውጊያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

“ከእንግዲህ ያለው ውጊያ የታንክ ነው” ያሉት አስተባባሪው ሰራዊቱ “መቀሌን በታንክ ለመክበብ” ከሚያስችል ውጊያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ጊዜው “መቀሌ ያለው ህዝባችን ከከባድ መሳሪያ ጥቃት ራሱን እንዲታደግ ጥሪ የሚተላለፍበት ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

እንደ አስተባባሪው ገለጻ ከሆነ “ከዚያ በኋላ ምህረት የለም”፡፡

ህብረተሰቡም በውስጡ የተደበቀውን ኃይል “የግድ ማራቅ፣ ውጣልኝ አታስጨርሰኝ” ማለት ይጠበቅበታል፡፡

“ሰራዊቱ እስካሁን ተዋጊውን የህወሓት ኃይል በመለየት እና የህዝቡን ደህንነት በመጠበቅ በጥንቃቄ ላይ የተመሰረተ ማጥቃት ነበር ሲያካሂድ የነበረው“ ያሉት ኮሎኔል ደጀኔ በመቀሌ ግን እንደዛ ሊሆን እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡

[EBC & Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሠፈራ ጣቢያ ለጥፋት አላማ ሊውል የነበረ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አካባቢ ዲቪዥን የሠፈራ ጣቢያ ለጥፋት አላማ ሊውል የነበረ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን በሰሜን እዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብ/ጄኔራል ሙሏለም አድማሱ አስታወቁ።
በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎች፦
-207 ክላሽ፣
-9 ሺህ 80 ጥይት፣
- 26 አርባ ጎራሽ፣
- 18 አስር ጎራሽ፣
- የተለያዩ ሽጉጦች ማካሮፍ 26፣
- ስታር 5፣
- fort five 4፣
- Breta 1፣ Map 2 እንዲሁም 108 የተለያዩ የቦምብ አይነቶች ናቸው። ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ የህወሀት የቀድሞ ታጋዮች እና ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች እንዲሠፍሩ ሲደረግበት በቆየው የመኖሪያ ጣቢያ በተደረገ ኦፕሬሽን ያለምንም የተኩስ ልውውጥ በልዩ ወታደራዊ ጥበብ መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴር ጄነራሉ ገልፀዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጥያ መንገድ የገጠመውን የህወሓት ኃይል ድል አድርጓል።በዚሁ መገንጠያ ላይ የሠራዊቱን ግሥጋሴ ለመግታት በኮሎኔል ጸጋዬ ማርክስና በኮሎኔል ሸሪፎ የሚመራው የጽንፈኛው ቡድን አንድ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።የመከላከያ ዘመቻ ዋና መመሪያ ማምሻውን እንዳስታወቀው የመከላከያ ሠራዊታችን ክፍለ ጦሩን ሙሉ በሙሉ ከደመሰሰ በኋላ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 433 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4,495 የላብራቶሪ ምርመራ 433 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,647 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 157 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 65,691 አድርሶታል፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 105,785 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የተጀመረው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሁለተኛ ምእራፍ መጠናቀቁ እና የ'ጁንታው' አባላት በቀጣይ 72 ሰዓታት ውስጥ እጃቸው በሰላም እንዲሰጡ ጥሪ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠ/ሚር አብይ በትግራይ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው የህግ ማስከበር ዘመቻ ሁለተኛው ምዕራፍ መጠናቀቁን አስመልክተው የሰጡት መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
በማይጸብሪ ተቆርጦ የቀረው የህዋሀት ቡድን በመከላከል ስራ ላይ በነበረው የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በጋራ ባደረገው ውጊያ ድል ተደርጎ እየሸሸ መሆኑ ተገለጸ፡፡

'ጁንታው' የህዋሃት ቡድን ለዓመታት ሲያዘጋጀው የነበረው ምሽግ ዛሬ ጠዋት ላይ ከአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ ጦር ማይላሀም የሚባለውን አካባቢ ለቆ እየሸሸ መሆኑን የአማራ ልዩ ኃይል ጋፋት ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ምግበ ገ/ ሚካኤል ገልጸዋል።እንደ ኮሎኔል ምግበ ገለጻ 'ጁንታውን' በማይጸምሪ ግንባር ለመደርመስ ሲዘጋጁ እንደቆዩ ገልጸው በዛሬው እለት ጠዋት 12:30 ውጊያ በመክፈት ለተከታታይ ሶስት ሰዓታት በተደረገ የዘመቻ ስራ ማይላሀም ላይ የነበረውን ምሽግ ለቆ እንዲወጣ መደረጉን አመላክተዋል።አሁን ላይ የ'ጁንታው' ቡድን እየሸሸና መሳሪያዎችን በየቦታው እየጣለ እየሄደ እንደሆነም ጠቁመዋል።በቦታው የተገኘው የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅትም 'ጁንታው' የህዋሃት ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተራራ ምሽጎችን ለማየት ችሏል።

የ'ጁንታው' ቡድን በማይጸምሪና አካባቢው አሁን ላይ ተስፋ መቁረጥ እየታዬበት ስለሆነ እየሸሸ እንደሚገኝና የአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ
አባላት ማይጸብሪን ለመቆጣጠር እየገሰገሱ መሆነቸውን ኮሎኔል ምግበ ገልጸዋል።'ጁንታው' በዚህ አውደ ውጊያ ከባድ መሳሪያዎችን መጠቀሙን የገለጹት ኮሎኔሉ ልዩ ኃይሉና ሚሊሻው ባደረጉት ውጊያ ድል ማድረጉን ገልጸዋል።'ህገወጥ ቡድኑ' አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ስለደረሰበት የቆሰሉ የራሱ አባላትን ወደ ገደል እየሰደዳቸውና እየረሸናቸው እንደሚገኝ ኮሎኔል ምግበ ተናግረዋል፡፡የተማረኩ የ'ጁንታው' አባላት ወደ ህክምና ቦታ በማድረስ እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሆነም ገልጸዋል።ኮሎኔል ምግበ የአዲዓርቃይና አካባቢው ማኅበረሰብ እያደረገላቸው ባለው ድጋፍ መደሰታቸውንም ገልጸዋል።

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
videotogif_2020.11.17_05.08.23.gif
1.2 MB
📌አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው ትሪትመንት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ👉🏼 አላድግም ብሎ ለቀረ
👉🏼 ራሰ በርሃ ለሆነ
👉🏼 ወደራሰ በርሃነት የተጠጋ  ለሳሳ ፀጉር
👉🏼 ወደውስተጥ ለገባ ፀጉር
👉🏼 ፐረም ወይም ጄል ለጨረሰው ፀጉር
👉🏼ላሽ ለበላው #ፂም #ፀጉር
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን ☞@Brandlife1
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] {Wireless Wifi router}+ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡➡️ ☎️+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
ባህር ዳር ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ በሮኬት መመታቷን የቻናላችን ቤተሰቦች አረጋግጠውልናል።

12:20 አከባቢ ላይ መተኮሰን ጨምረው ገልፀዋል።

@YeneTube @Fikerassefa