YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል የሽምግልና ፍላጎት እንደሌለ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ! በትግራይ ያለው ውጊያ በንግግር እንዲፈታ በቀጠና፣ አህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ መሪዎች የማሸማገል ጥያቄ ቢያቀርቡም፤ በኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ በህወሓት በኩል የሽምግልና ፍላጎት እንደሌለ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ተናገሩ። የህወሓት አመራሮች ውጊያውን…
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ዐስታወቀች።

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሕወሓት አመራር መካከል ትግራይ ውስጥ ያለው ግጭት የሚያበቃውም በኹለቱ ኃይላት መኾኑን አሜሪካ ገለጠች።የሰላማዊ ሰዎች ደኅንነት መጠበቊ ወሳኝ እንደኾነ፤ በዋናነትም የዜጎቿን ደኅንነት ለማስጠበቅ በመንቀሳቀስ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሳለች።ትናንት ማምሻውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናዥ እና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሚካኤል ራይኖር ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ኹኔታ በስልክ ኮንፈረንስ ለጋዜጠኞች በሰጡት ልዩ ማብራሪያ ወቅት ነበር ይኽንኑ የተናገሩት።

በማብራሪያው ወቅትም፦ «የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ግጭቱ ፍጻሜ እንዲያገኝ፤ ሰላም እንዲሰፍን፤ ሰላማዊ ሰዎች መጠበቃቸውን ለማሳሰብ የተቻለውን ጥረት ያደርጋል» ያሉት ቲቦር ናዥ፦ «ግጭቱን ማስቆም ያለበት ግን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አይደለም» ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል። «ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ፤ ሕወሓት ጥቅምት 24 ቀን ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ላይ የመጀመሪያውን ጥቃት ከሰነዘረበት ጊዜ አንስቶም በግልም፣ በይፋም እጅግ እንዳሳሰበን አጽንዖት ሰጥተንበታል» ሲሉም አክለዋል። ሰላማዊ ሰዎች ሆነ ተብሎ ዒላማ ውስጥ እንዲገቡና ጥቃት እንዲፈጸምባቸው መደረጉን አስመልክተው የወጠ ዘገባዎች አሁንም በጥልቅ ያሳስቡናል። በማይ ካድራ ለተፈጸመው ጭፍጨፋ ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀርቡም በድጋሚ ጠይቀዋል። የማይ ካድራውን ጭፍጨፋም አውግዘዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ከተማዪቱን ለቀው በሚያፈገፍጉ የሕወሓት ወታደሮች እና ሚሊሺያዎች እንደኾነ ያመላክታል» ያሉት ቲቦር ናዥ፦«የሰብአዊ መብት ጥሰቶች» በመላ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አሳስበዋል።
ጥፋተኛ ኾነው የተገኙትም በሕግ አግባብ እንዲጠየቊ ጥሪ አስለላልፈዋል።

በተለይ አንዳንድ የውጭ ሃገራት ተንታኞች እና ጋዜጠኞች በተደጋጋሚ እንደሚገልጡት በትግራይ የተጀመረው ወታደራዊ ዘመቻ ቃጣናው ላይ ተጽእኖ ይኖረው እንደኾነም የተጠየቊት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናዥ ስለኢትዮጵያ ጥንታዊ መንግሥትነት እና ነፃ ሀገር መኾን በማብራራት የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ሚናን ጠቅሰዋል። «ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያ የቃጣናው አነቃቂ ኾናለች» ብለዋል።«ከመቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ የኹለት ሺህ ዓመት የመንግሥት ታሪክ ያላት ናት።ከሰሃራ በታችም ፈጽሞ ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ ሀገር ናት» ሲሉም ተናግረዋል።

ሕወሓት ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ሚሳይሎችን አስወንጭፎ ግጭቱን ቃጣናዊ ለማድረግ ቢሞክርም ኤርትራ ከግጭት ራሷን መቆጠቧን ቲቦር ናዥ አወድሰዋል።«ከሕወሓት አመራር ዓላማዎች መካከል አንዱ ግጭቱን ቃጣናዊ ለማድረግ መሞከር ነበር» ያሉት ረዳት ሚንሥትሩ፦«በትግራይ አጠቃላይ ሕዝብ ዘንድ የጀብደንነት ነበልባልን ለመለኮስ» የተሞከረ መኾኑንም ጠቅሰዋል።ቲቦር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት መንግሥት ዋነኛ ግቡ በመቶ ሺህ የሚቆጠር አባል ካለው ሕወሓት ውስጥ አመራሩ ላይ መኾኑን አጽንዖት መስጠቱን አስምረውበታል።

አምባሳደር ሚካኤል ራይኖር በበኩላቸው ቲቦር ናዥ በተናገሩት እንደሚስማሙ ገልጠዋል።የሕወሓት ፍላጎትን በተመለከተ፦ «ፍላጎታቸውን በትክክል ማወቅ ባይቻልም ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድን አስወግዶ ላለፉት 27 ዓመታት የበላይ ወደ ኾኑበት የኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድ ለመመለስ ያለመ ይመስላል» ያሉት ቲቦር ናዥ፦ የህወሃት ስልት ተቃራኒ ነገር እንዳስከተለ ጠቅሰዋል። የሕወሓት ድርጊት፦ «ቢያንስ አሁን ጠቅላይ ሚንሥትሩን በመደገፍ ኢትዮጵያውያንን እንደ ሀገር ያሰባሰበ ይመስላል» ብለዋል። ኹኔታው፦ «የኢትዮጵያ ብሔራዊነትን በእውነቱ አስደንግጧል» ሲሉም አክለዋል። አምባሳደር ሚካኤል ራይኖር በኹኑ ወቅት «የክልል እና የፌዴራል መንግሥታት እንዲሁም መጠነ ሰፊ ሕዝብ በመንገስት ዙሪያ መሰባሰቡንም» ተናግረዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ግድያው አሁንም እንዳልቆመ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በመተከል ዞን ከግድያ የተረፉ ዜጎችን የፌዴራል ፖሊስ በጸጥታ ጉዳይ ላይ እንዳወያያቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል፡፡ በወይይቱም በግድያው ምክንያት ትተውት የመጡት ሃብት እና ንብረት የተዘረፈ በመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውንና አሁንም የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከነበሩበት ቀበሌ መፈናቀላቸውንና ቤት ንብረታቸው መውደሙን በውይይቱ እንዳነሱ ለአብመድ በስልክ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ችግር ላይ መውደቃቸውን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የጸጥታው ጉዳይ መፍትሄ የሚያገኝ ከሆነ በጊዜያዊ መጠለያ ቢሆን ወደ ቀያቸው ተመልሰው የመኖር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡የጥቃቱን አለመቆምና ለተፈናቃዮች እየተደረገላቸው ያለውን ድጋፍ ለመጠየቅ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ደህንነት ቢሮ እንዲሁም የምግብ ዋስትና እና አደጋ መከላከል ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎች በተደጋጋሚ ስልክ ቢደውልም ሊያነሱ አልቻሉም፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
‹‹የልደቱ አያሌው የጤንነታቸው ሁኔታ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል›› አዳነ ታደሰ

ልደቱ አያሌው ዛሬ ኅዳር 11/2013 በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ችሎት መቅረባቸው ይታወሳል።ፍርድ ቤቱም ዐቃቤ ሕግ ክሱን እንዲያሻሽል በማዘዝ፤ ክሱ ግልፅ ባልሆነበት እውነታ የዋስትና መብት ላይ ብይን አልሰጥም ማለቱን የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝዳንት አዳነ ታደሰ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

‹ከታሰርኩ አራት ወር ሆኖኛል፤ የእስከዛሬው የፍርድ ቤት ሂደት የሚያሳየው ዐቃቤ ሕግ ዋና ዓላማው እኔን በወንጀል ከሶ የማስቀጣት ሳይሆን በተራዘመ የፍርድ ሂደት እኔን ማሰቃየት ነው› ልደቱ ቅሬታቸውን መግለጻቸውንም አዳነ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
የጤንነታቸው ሁኔታ ከአዲስ ማለዳ ለቀረበላቸው ጥያቄም አሁን ጤንነታቸው እንደተሻሻለ እና በጥሩ ጤንነት ላይ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በ10ሺ ብር ዋስ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ተለቋል።

ባለፈው ማክሰኞ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቀበት በእስር እንዲቆይ እንተደረገ መዘገባችን ይታወሳል። ዛሬ በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በዋስ እንዲለቀቅ ተወስኖ የነበረውን ውሳኔ እንደገና በማፅደቅ፣ ጋዜጠኛ በቃሉ ከማረሚያ ቤቱ ወጥተዋል።

Via:- አውሎ ሚዲያ
@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር ዜና‼️

የመከላከያ ሠራዊት አክሱምን አድዋንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጥሯል ተባለ!

በምዕራብ ግንባር የ'ሕወሐት ጁንታን' ኃይል እያጠቃ ያለው የመከላከያ ሠራዊት፣ ከሽሬ በኋላ ሰለህለሃ ላይ የመሸገ የሕወሐት ኃይል ገጥሞት ነበር። ሰለህለሃ ላይ የመሸገው የ'ጁንታው ኃይል' መንገዱን በዶዘር ቆርጦና አስፓልቱን አበላሽቶ በቦታው ከባድ መከላከል አድርጓል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የ'ጁንታውን' ተከላካይ ኃይል ሠብሮ በመግባት አክሱምን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።
ከአክሱም ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የጁንታው ኃይል ለመከላከል ቢሞክርም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ድል ሆኗል።

መከላከያ እንቲጮንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጥሮ ወደ አዲግራት ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል።አያሌ የ'ጁንታው' ተዋጊዎች እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ከድተው ከ'ጁንታው' ጋር ሆነው ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮችም ይገኙበታል።

[የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 452 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,488 የላብራቶሪ ምርመራ 452 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,620 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 342 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 65,325 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 104,879 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የተመድ ረድዔት ድርጅቶች በቀጣዮቹ 6 ወራት የግጭት ቀጠና ከሆነው ትግራይ ክልል 200 ሺህ ያህል ስደተኞች ሱዳን ይገባሉ የሚል ዕቅድ ይዘው እየሰሩ እንደሆነ ለዐለማቀፍ ዜና አውታሮች ተናግረዋል፡፡ እስካሁን በሱዳን የተጠለሉት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ቁጥር ከ33 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡ ሕጻናት በሚበዙባቸው አዲሶቹ ስደተኛ ጣቢያዎች ተላላፊ በሽታ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋትም ተፈጥሯል፡፡ ተመድ ለስደተኞቹ አስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ እና ለመጠለያ ግንባታ፣ 50 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ባስቸኳይ ያስፈልገኛል ብሏል፡፡

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ሰጥቶት የነበረውን የዘገባ ፈቃድ ሰረዘ፡፡ ባለስልጣኑ በሃገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ “በተሳሳተ መንገድ ዓለም እንዲያውቀው እና በመንግስት ላይ ጫና እንዲበረታ በሚያደርጉ” ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡እርምጃውን በማስመልከት ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መረጃን የሰጡት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር…
ሮይተርስ በኢትዮጵያ እንዳይሰራ አልከለከልኩም ሲል የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የኢትዮጵያ ወኪል ዘጋቢውን እንጂ የተቋሙን የዘገባ ስራዎች ፍቃድ አለመሰረዙንም አስታውቋል፡፡“የሚመለከታቸውን አካላት አካቶ በሚዛናዊነት ከመስራት ይልቅ የአንድ ወገን መረጃዎችን ብቻ የመጠቀም ችግሮች እንዳሉ ለወኪል ዘጋቢዋ ደጋግመን ብናስታውቅም አላረመችም” ያሉት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዷለም “ለተቋሙ በማሳወቅ የወኪል ዘጋቢነቷን ፈቃድ አገድን እንጂ ከሮይተርስ ጋር ያለን ግንኙነት አልተቋረጠም የዘገባ ፍቃዱንም አላገድንም”ሲሉ ለአል ዐይን አማርኘ ተናግረዋል፡፡ከአሁን በኋላ “እንደ ወኪል ጋዜጠኛ ሆና ልትሰራ የምትችልበት” አግባብና እንቅስቃሴ እንደሌለ እና የሚሰጣት መረጃ እንደማይኖርም ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ያስታወቁት፡፡

“ሮይተርስ ሌላ ጋዜጠኛ እንዲልክ ለዋና መስሪያ ቤቱ አሳውቀናል”ም ብለዋል አቶ ወንድወሰን፡፡የቋሚ የሚዲያ ወኪል (ጋዜጠኛ) መታወቂያዋ በባለስልጣኑ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡እንድታርም ተደጋግሞ ስለተነገራት ነገር ምንነት አል ዐይን አማርኛ ላቀረበላቸው ጥያቄም “ምንም ዓይነት የኢንተርኔትም ሆነ የኮሙኒኬሽን ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ ከመቀሌ መረጃ አግኝተው ይሰራሉ ሲሰሩ ግን አዲስ አበባ ከሚገኘው የመንግስት አካል ‘ባላንስ’ አድርገው አይደለም ” አይደለም ሲሉ በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡‘ባላንስ’ አለማድረጉ “ወደ አንድ አካል ጣት መቀሰር የአንድን አካል ፕሮፓጋንዳ ማራገብ” እንደሚሆንና ከጋዜጠኝነት ሙያ መርሆዎች እንደሚያፈነግጥም ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

Via @alainamharic
@YeneTube @FikerAssefa
ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኀብረት ሊቀ መንበር የሆኑትን የሲሪል ራማፎሳን ልዑካን ተቀብለው በግል ይወያያሉ።ሆኖም፣ የፌደራል መንግሥትን እና በህወሓት የሚገኙ ወንጀለኞችን ለማሸማገል ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ዜና ሀሰት መሆኑን እናረጋግጣለን።ድርድርን አስመልክቶ የፌደራል መንግሥት ያለው አቋም ፈጽሞ ያልተለወጠ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ግጭትን ሊያስነሱ የሚችሉ ቃላት ተለይተው ሊታተሙ ነው!

የመብቶችና የዴሞክራሲ እድገት ማዕከል(CARD) እና ዴስቲኒ ኢትዮጵያ peace teach Lab ከተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር ለግጭት አስተዋጽኦ ያላቸውን ቃላት በመሰብሰብ ከአንድ ወር በኋላ በድረ ገፅ መዝገበቃላት እንደሚያሳትም የማዕከሉ ሃላፊ በፍቃዱ ሀይሉ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

እነዚህ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ቃላት የወል ማንነትን መሰረት ያደረጉ ሲሆኑ የተሰበሰቡበት መንገድ ደግሞ የዳሰሳ ጥናቶችን በማድረግና ፌስቡክ የማህበራዊ ትስስር ድረገፅን በመጠቀም በተደጋጋሚ የሚፃፉ ቃላትን የሚሰበሰብበትን ሰው ሰራሽ እውቀት(Artificial intelligence) የተባለ መንገድ በመጠቀም መሆኑን አቶ በፍቃዱ ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለሲሪል ራማፎዛ ገለፃ አደረጉ!

የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎዛ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት ያላትን ከፍተኛ ቦታ መናሻ በማድረግ ነው ፕሬዘዳንቷ ለህብረቱ ሊቀመንበርና ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ህግ የማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ማብራርያ የሰጧቸው ተብሏል።

ሁለቱ ፕሬዘዳንቶች ከዚህ ቀደም ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ የስልክ ውይይት አድርገው የነበረ ሲሆን ገፅ ለገፅ የተደረገው ውይይትም ነባራዊ እውነታውን ይበልጥ ለማስረዳት እድል የፈጠረ እንደነበር ተገልጿል።የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲል ራማፎዛ በፕሬዘዳንቷ ከተደረገላቸው ገለፃ በኋላ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እንደሚከታተሉት ማስታወቃቸውን ኢ.ቢ.ሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ህዳር ሲታጠን

ከ102 ዓመት በፊት በ1911 ዓም. ነበር መነሻው ከወደ አሜሪካ እንደሆነ የሚነገርለት የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ የሚሊዮኖችን ህይወት በመቅጠፍ አለምን ያቃወሰው፡፡

ሳይንሳዊ መጠሪያው H1N1 የተባለው ቫይረስ ስፓኒሽ ፍሉ የሚል ተቀፅላ ስም ተሰጥቶታል፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ ደግሞ የገባበት ወቅት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት በቀናት ውስጥ ብቻ የቀጠፈው በህዳር ወር ነበርና የህዳር በሽታ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ሳል እና ከፍተኛ ትኩሳት ይዞ የመጣውን ይህን ወረርሽ ለማጥፋትም ህዳር 12 ቀን 1911 ዓም ሀገሬው ከየቤቱ ቆሻሻ እያወጣ እንዲያቃጥል በአዋጅ ተነገረ፡፡

ምንም እንኳን ቆሻሻን ማቃጠል ለአየር ንበርት አሉታዊ አስተዋፅዎ ያለው ቢሆንም በጊዜው ወረርሽኙን ያጠፋው ህዳር መታጠኑ ነው ተብሎ ስለሚታመን ዛሬም በአዲስ አበባ እና አንዳንድ የክልል አካባቢዎች ከመቶ አመታት በኋላ ህዳር 12 ቆሻሻ ይቃጠላል፤ ህዳር ይታጠናል፡፡

Via @addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
#ሰበር_ዜና

የመከላከያ ሰራዊት አዲግራትን ከሕወሓት ጁንታ ነፃ ወጣች።

በአሁን ሰዓት ወደ መቐለ እያመራ መሆኑ ታውቋል።

Via:- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ
@Yenetube @Fikerassefa
ጠ/ሚ አብይ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስለሚገኘው ኦፐሬሽን፣ ስለ ሰብዓዊ ድጋፎች፣ የክልሉን ነዋሪዎች ደህንነት ስለማስጠበቅ ያስተላለፉት መልዕክት:

<<ሕግ ማስከበር ተልዕኮው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያስመዘገበው ድል የሚደነቅ ነው። ሠራዊታችን ትናንት ምሽት በአዲግራት ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ዛሬ ደግሞ አዲግራትን ከሕወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ አውጥቷል።

የፌደራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው ከተማዎችና አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች፣ በጸጥታ ኃይሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ወደ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው መመለስ ጀምረዋል። ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን፣ ሰብአዊና ማኅበራዊ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን መንገድ እናመቻቻለን።

የሰብአዊ ድጋፍ ክንውኖችን ለመከታተል በፌደራል መንግሥት የተዋቀረው ከፍተኛ ኮሚቴ፣ ተመጣጣኝ እና ወቅታዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስችል መረጃን እንዲያሰባስቡ ተጨባጭ ሁኔታውን የሚያጣሩ ልዑካንን ወደ ስፍራው ልኳል። በተጨማሪም፣ ይህ ኮሚቴ ባለፉት ቀናት መኖሪያቸውን ጥለው የተሰደዱትን ዜጎች ሁሉ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መሥራቱን ይቀጥላል።

የፌደራል መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ አጠቃላይ ደኅንነት እና ጤንነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ስለ ሆነ፣ በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲሰፍን እና ዜጎቻችን ከጉዳት እና እጦት ነፃ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን።>>

@YeneTube @FikerAssefa
ተማሪዎች ሰርቪስ እንዲጠቀሙ አስገዳጅ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው!

በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን የትራፊክ መጨናነቅ ከማስቀረት አንፃር የተማሪዎች መጓጓዣ ሰርቪስን እንዲጠቀሙ የሚይደርግ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

ከፌዴራል የትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ረቂቅ መመሪያው እንዲወጣ እየተሰራ የገለፁት የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ጅሬኛ ሄርጳ ትምህርት ሲጀመር በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቅረፍ አንፃር ከፍተኛ ሚና አለው ተብሎ የቀረበ ሃሳብ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ግድያው አሁንም እንዳልቆመ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በመተከል ዞን ከግድያ የተረፉ ዜጎችን የፌዴራል ፖሊስ በጸጥታ ጉዳይ ላይ እንዳወያያቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል፡፡ በወይይቱም በግድያው ምክንያት ትተውት የመጡት ሃብት እና ንብረት የተዘረፈ በመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውንና አሁንም የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከነበሩበት ቀበሌ መፈናቀላቸውንና ቤት ንብረታቸው…
በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምግብ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ተናገሩ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሳምቦሰሪ፣ አልባሳን፣ ጋፋሪ፣ ሙዘን፣ ቆርቃ፣ ያምፕ፣ አዲስ ዓለም እና በሌሎችም ቀበሌዎች ንጹኀን አማራዎች ሞትና መፈናቀል ደርሶባቸዋል፡፡ከሞት የተረፉትና ግድያውን ሸሽተው በድባጤ ወረዳ ጋሊሳ ቀበሌ እና በድባጤ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለዋል፤ በምግብ፣ በአልባሳት እና መጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ታረቀኝ ተሲሳ ለተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንዳሉት ከኅዳር 5/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በድባጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ 1 ሺህ 200 ተፈናቃዮች 180 ኩንታል እህል እና 20 ኩንታል የህፃናት አልሚ ምግብ እንዲሁም ሦስት ቦንዳ ልብስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡በድባጤ ቀበሌ ለሚገኙት ትላንት ምሽት 5፡00 ጀምሮ 233 ኩንታል እህል፣ 50 ኩንታል የህፃናት አልሚ ምግብ እና አምስት ቦንዳ አልባሳት በጉዞ ላይ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

ከዕለታዊ ድጋፍ በተጨማሪ ተፈናቃዮቹን በዘላቂነት ለማቋቋም ቀጣናው በኮማንድ ፖስት እየተመራ እንደሆነ ኮሚሽነር ታረቀኝ አንስተዋል፡፡ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል፤ መልሶ የማቋቋም ሥራም ይስራል ብለዋል፡፡በአካባቢው ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡የአካባቢው ነዋሪዎችም የትህነግ ዘራፊ ቡድን ያሰረጸውን የመጠፋፋት ፕሮፓጋንዳ ወደ ጎን በመተው ለዘመናት አብረው ከኖሩ ህዝቦች ጋር ተሳስበው መኖር እንዳለባቸው አመላክተዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
በግብርና፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም በፕላስቲክ፣ ህትመት እና ፓኬጂንግ የስራ ዘርፍ ላይ ተሰማርተዉ የሚገኙ ከሆነ ፕራና ኢቨንትስ በአህጉራችን የመጅመሪያ የሆነውን የበይነመረብ ንግድ ትርኢት እነሆ ይሎታል!
በኢንዱስትሪዉ ዉስጥ መሪ በሆኑት አምራቾችና ባለ ድርሻ አካልት መካከል ዋጋ ያላቸዉን የንግድ ግንኙነቶችን ለመፍጠርና ለማጠናከር ሲባል በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሲዘጋጁ የነበሩ ንግድትርዒቶችን በአንድ ጠንካራ የበይነመረብ መድረክ በማሰባሰብ “ቨርቹዋል አፍሪካ አግሮፉድ እና የፕላስቲክ ህትመት እና ማሸጊያ” በሚል መጠሪያ ከህዳር 14–17፣ 2013 ዓ.ም. የንግድትርዒት ተዘጋጅቷል፡፡
ከአለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ይገናኙ! ይመዝገቡ! በነጻ ይጎብኙ! www.virtual-africa.net
ተሳትፈዉ ምርትዎን ማስተዋወቅ ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያግኙን፡ sales@pranaevents.net
ንግድ ትርዒቱን መጎብኘት ከፈለጉ ደግሞ በዚህ ይመዝገቡ፡ https://registration.virtual-africa.net/
የሀገር ልጅ፣ የማር እጅ’ በሚል የድጋፍ ጥሪ በቀጣይ ሳምንት ኅዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ለትግራይ ሕዝብ ድጋፍ ማሰባሰብ ሊካሄድ ነው።

ጥበብብ ለሀገር በሚል በተዋቀረ የአርቲስቶች ኮሚቴ አዘጋጅነት የሚካሄደው ድጋፍ ማሰባሰብ መርሐ ግብር በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን መሆኑ ታውቋል።በመርሐ ግብሩ ላይ አንጋፋ እና ወጣት አርቲስቶች የሚሳተፉ መሆኑንም ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ሕግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰደ ባለበት የትግራይ ክልል ለሕዝቡ የምግብ፣ አልባሳት እና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለመሰብሰብ መታቀዱም ተገልጿል።በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ ትልልቅ የግል እና የመንግሥት ተቋማት፣ ከአትሌቶች እና ከፋብሪካዎች ድጋፍ ለማሰባሰብ መታሰቡ ተጠቁሟል።

[አሐዱ ሬዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa
በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቆመ!

በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየፈጸመ በመሸሽ ላይ የሚገኘው የሕወሓት ህገወጥ ቡድን በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተጠቆመ።

የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው የአክሱም ከተማ የተገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ በ526 ሚሊዮን 860 ሺህ 200 ብር ወጪ የተገነባ መሆኑን፣ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለአገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሰፊ እንደነበር ተገልጿል።

የአየር ማረፊያው መጎዳት የአክሱም ሐውልትን ከጉዳት ለመታደግ የሚደረገውን የጥገና ስራ እንደሚያስተጓጉልና በርካታ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት 15 ቀናት ውስጥ ከ93 በላይ ሰዎችን የህወሀት እና ኦነግ ሸኔ የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ጦርነቱን አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሳለን ብሎ ሀገር የመናድ ጦርነት የለኮሰው ወንበዴው፣ አሸባሪውና የማፊያዎች ስብስብ የሆነው የህወሀት ጁንታ ቡድን ከዕለት ዕለት ወታደራዊ ሽንፈትና ክሽፈት እየተከናነበ ይገኛል ብሏል።ጽንፈኛው ቡድን በከፈተው በዚህ ባልተጠበቀ ጥቃት እንደመከላከያ ሰራዊታችን ሁሉ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ22 በላይ የልማት አውታሮችን ከየትኛውም ጥቃት ሲጠብቁ አመታትን ባስቆጠሩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ አባላት መኖሪያ ካምፖች ላይ ጥቃት በማድረስ በርካታ አባላት ላይ የግድያና የአፈና ወንጀል መፈጸሙን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ተናግረዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በከፍተኛ ቁጭትና ወኔ በመነሳሳት በመሃል ሀገር ያለውን የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ለማድረግ ቀን ከሌት በትጋት ሙያዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።

ይህ የጥፋት ቡድን አባላትና ተላላኪዎቻቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፣ በቦሌና በየክልሉ በሚገኙ ኤርፖርቶች፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በሀይል ሰብስቴሽኖች፣ በውሃ ግድቦች፣ በነዳጅ ዲፖዎች፣ በፋብሪካዎች፣ በድልድዮች፣ በስደተኛ ካምፖች፣ በሳተላይት ጣቢያዎች፣ በማዕድን ማውጫዎች፣ በቤተመንግስትና በክልል ም/ቤቶች፣ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች፣ በልማት ድርጅቶች፣ በዋና ዋና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች፣ በምድር ባቡር ፕሮጀክቶች፣ በቢሮዎችና መኖሪያ ካምፖች፣ በፌዴራል ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት አውታሮችና ጠረፍና የጠረፍ ከተሞች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉትን ጥቃቶች አስቀድሞ ለማክሸፍ ጥብቅ ክትትልና ቋሚ ጥበቃ በማድረግ ላይ ይገኛሉም ብሏል፡፡

ከዚህም ባለፈ በግዳጅ የነበሩት የፌዴራል ፖሊስ አባላት የከሃዲው ህወሀት ቡድንን ጥቃት በመከላከል በአንዳንድ ግንባሮች ከጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሆን በግንባር እየተፋለሙ ይገኛሉም ተብሏል።

ሌሎች ደግሞ በሰሜን ቀጠና፣ በምዕራብ ቀጠና በኦሮሚያ ወለጋ ዞኖች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና መተከል ዞን እና አካባቢው፣ በደቡብ ቀጠና በሚዛን ቴፒ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በወላይታ ሶዶ እና ኮንሶ፣ ከነገሌ ቦረና እስከ ሞያሌ፣ በምስራቅ ቀጠና ከአዋሽ እስከ ጋላፊ እንዲሁም በሁሉም የሀገራችን ድንበሮች ከክልሎች የፀጥታ ሀይልና በየቦታው ካለው የመከላከያ ሰራዊታችን ጋር ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠርና የህዝብን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ የህግ የበላይነት እንዲከበር ሌት ተቀን በትጋት እየሰሩ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ከተለያዩ ክልሎች ፖሊስ በዚህ ወንጀል የጠረጠራቸውን ከ93 በላይ የህወሀት ቡድን አባላትና የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላትን በህግ ቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሆነ ተገልጿል።

በተደረገ ብርበራ፣ ፍተሻና አሰሳ እንዲሁም በህብረተሰቡ ጥቆማ፡- 30 የመከላከያና የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ 47 የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ 43 የተለያዩ ሽጉጦች፣ 1 ሺህ 376 የተለያዩ ጥይቶች ፣ 7 ቦምቦች፣ 2 የጦር ሜዳ መነፅር፣ 102 ድምፅ አልባ መሳሪያ፣ 8 የእጅ ራዲዮ መገናኛ፣ ለእኩይ ተግባራቸው ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ የቴሌኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎች፣ 534 ሺህ 870 የኢትዮጵያ ብር እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎች መያዝ ተችሏል፡፡

ይህ የተገኘው ውጤት ሰላም ወዳዱ የሀገሪቱ ዜጋ እና በየክልሉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ከፖሊስ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በመስራታቸው የተገኘ ስኬት በመሆኑ ይህንኑ ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል ለሰላምና ደህንነታችን መረጋገጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት እያሳሰብን በቀጣይ ለሚደረጉ የህግ ማስከበር ተግባራት የተለመደውን ድጋፍና ትብብራችሁን እንጠይቃለን ብሏል፡፡አጠራጣሪ ነገሮች ሲኖሩ መረጃ ለመስጠት በስልክ ቁጥሮች፦
987፣ 816 እንዲሁም በ0115-51 80 00 ደውላችሁ አሳውቁኝ ተብላችኋል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa