YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ምክትላቸው ከኃላፊነታቸው ተነሱ!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቀለ ሙለታ እና ምክትላቸው አቶ ብሩክ ከበደ ከትላንት ሰኞ ነሐሴ 18 ጀምሮ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የተቋሙ ምንጮች ገለጹ። በምትካቸው የቀድሞው የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና አቶ ሰጠኝ እንግዳው በኃላፊነት መመደባቸውን የተቋሙ ቦርድ ሊቀመንበር ተናግረዋል።

እንደ ምንጮች ገለጻ ትላንት ለሁለቱም የፋና ኃላፊዎች የስንብት ደብዳቤ ደርሷቸዋል። የዋና ስራ አስፈጻሚው እና ምክትላቸው ከኃላፊነታቸው መነሳት ለሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች በይፋ ባይገለጽም የኤዲቶሪያል ቡድን አባላት ለሆኑ የፋና የስራ ኃላፊዎች ግን ጉዳዩ እንደተገለጸላቸው ምንጮች ጠቁመዋል። የሁለቱን ኃላፊዎች ከቦታቸው መነሳት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁንም አረጋግጠዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ሱዳን አቀኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ
ካርቱም፣ ሱዳን አቅንተዋል።ዶክተር ዐቢይ ከሽግግሩ ወታደራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሀን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር በሁለትዮሽ
ግንኙነት ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሊባኖስ የሚኖሩ 234 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መመለስ የሚያስችላቸውን ፍቃድ አገኙ!

በሊባኖስ የሚኖሩ 234 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መመለስ የሚያስችላቸውን የመውጫ ቪዛ ማግኘታቸው ተገለጸ።በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ቆንሱል ጄኔራል ተመስገን ዑመር የሊባኖስ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች መሥሪያ ቤት የጉዞ ሰነዳቸው ከተጠናቀቀላቸው ዜጎች መካከል ለ234ቱ የመውጫ ቪዛ መስጠቱን ለኢዜአ ገልጸዋል።የመውጫ ቪዛውን ያገኙት በስምንተኛው ዙር በሊባኖስ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው መረጃቸው ለመሥሪያ ቤቱ የተላከ ዜጎች መሆናቸውን ተናግረዋል።የመውጫ ቪዛው በቤይሩት የወደብ ፍንዳታ በደረሰው ጉዳት በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችንም ያካተተ ነው ብለዋል።

የጉዞ ሰነዳቸው ተጠናቆ የመውጫ ቪዛ እንዲሰራላቸው ወደ ሊባኖስ ኢሚግሬሽን ጉዳዮች መሥሪያ ቤት የተላከላቸው ኢትዮጵያዊያንም ሂደቱ እንዳለቀ ቪዛ እንደሚመጣላቸው አቶ ተመስገን አስረድተዋል።ወደ አገራቸው ሲመለሱ የኮሮናቫይረስ ምርመራና ተያያዥ ጉዳዮችን ቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ በጥቂት ቀናት ውስጥ በዝርዝር እንደሚያሳውቅም ጠቁመዋል።የመውጫ ቪዛ የተሰራላቸው ዜጎች የትራንስፖርት ወጪያቸውን በራሳቸው እንደሚሸፍኑም አክለዋል።ቪዛ የተሰራላቸው ዜጎች በእስር ቤቶች፣ በዲፓርቴሽን ማዕከል እንዲሁም በአሰሪዎቻቸው በደል ደርሶባቸው ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ ዜጎችን እንደማያካትት ገልጸዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
69 በመቶ ኢትዮጵያዊያን ሕገ መንግስቱ እንዲሻሻል እንደሚፈልጉ አንድ ጥናት አመለከተ።

አፍሮ ባሮ ሜትር የተሰኘው ትኩረቱን በህግ እና ፌደራሊዝም ጉዳዮች ያደረገው የጥናት እና ምርምር ተቋም ከፍሪደም ሀውስ ጋር በትብብር ያጠናውን ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።ጥናቱን የመንግስት ተወካዮች፣መገናኛ ብዙሃን ፣የህግ እና የፌደራሊዝም ምሁራን በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።ጥናቱ የሕገ መንግስት መሻሻል ጉዳይ፣የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች ብዛት፣አንቀጽ 39 ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የስልጣን ዘመን፣ የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ እና ሌሎች ጉዳዮች በጥናቱ ለተሳተፉ ዜጎች የቀረቡ ጥያቄዎች ናቸው።በዚህ ጥናት ላይ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ 2 ሺህ 400 ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉ ሲሆን ጥናቱ እና ቀለመጠይቁ ከ6 ወር በፊት መካሄዱም ተገልጿል።

የጥናቱ አቅራቢ እና በኢትዮጵያ የአፍሮ ባሮ ሜትር ናሽናል ፓርትነር አቶ ሙሉ ተካ
እንዳሉት በጥናቱ ከተሳተፉ 10 ኢትዮጵያዊን ሰባቱ ማለትም 69 በመቶ የሚሆኑት ህገ መንግሥቱ እንዲሻሻል ይፈልጋሉ ብለዋል።11 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ይህ ሕገ መንግስት ከነአካቴው መወገድ አለበት ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።18 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ህገ መንግሥቱ ባለበት መቀጠል አለበት ማለታቸው ተገልጿል።በፌዴራል መንግስት አሁን ካለው የስራ ቋንቋ ተጨማሪ የፌደራል የስራ ቋንቋ መካተት አለበት ያሉት 73 በመቶ ናቸው ተብሏል።

በጥናቱ ከተሳተፉ 37 በመቶዎቹ በብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማው መሃል ላይ ያለው አርማ እንዲነሳ ሲፈልጉ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማው አሁን ባለበት እንዲቀጥል ይፈልጋሉ ተብሏል።ሌላኛው በጥናቱ ለተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ጊዜ ነበር።በዚህም መሰረት 73 በመቶዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሁለት ምርጫ ጊዜ ብቻ እንዲያገለግሉ ይፈልጋሉ ተብሏል።

የናሙናው መጠን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰራ ወካይነት ያለው ሲሆን ፣ የስህተት ህዳጉ +/- 2 በመቶኛ ና አስተማማኝነት ደረጃው 95 በመቶ መሆኑ የአፍሮ ባሮ ሜትር ጥናት ቡድን አታውቋል።ኢትዮጵያዊያን በፌዴራሊዝም ስምምነት ቢኖራቸው ብሄርን መሰረት ያደረገ ወይስ መልካ ምድርን አቀማመጥ የሚለው ልዩነት ጥናት ተደርጓል።61 በመቶ በሀገሪቱ ከአህዳዊነት ይልቅ ፊዴራሊዝም መንግስት እንዲኖር የመረጡ ሲሆን በጥናቱ ከተሳተፉ 37 በመቶዎቹ ደግሞ ፌዴራሊዝም ከፍፋፋ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገልጿል።እንዲሁም 49 በመቶ ብሄርን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ያስፈልጋል ሲሉ 48 በመቶዎቹ ደግሞ የክልሎች አወቃቀር መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሴት አባላት (የሴቶች ኮከስ) በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን 900 ሺህ ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ።

አባላቱ ከተለያዩ የመንግሥት እና ልማት ድርጅቶች ያገኙትን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ ምግብ እና አልባሳትን በማሰባሰብ ለተፈናቃዮቹ ማድረሳቸውን አስታውቀዋል።በወረዳው ከቀያቸው ተፈናቅለው ለነበሩ አባወራዎች ቤታቸው በአዲስ መልክ ተሰርቶላቸው ወደ ቀያቸው በመመለስ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተፈናቅለው ከነበሩት ጋር በቀጥታ በመገናኘት ለማወቅ መቻላቸውን ወ/ሮ አበባዬ ገልጸዋል።ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እስኪመለሱ ድረስ የተጀመረው ሰብዓዊ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚያደርጉት ክትትል እና ቁጥጥር እንደሚያጤኑትም ጠቁሟል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
በምስራቅ ጎጃም ዞን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት ኢ/ር በለው ሀብታሙ ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከስራ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የከተማውን የፀጥታ ሁኔታ በማስከበር በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ በተተኮሰ ጥይት ተመተው በተወለዱ በ33 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል።ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ በክትትል ላይ ይገኛል።

[Amhara Police Commission]
@YeneTube @FikerAssefa
ውዳሴ ዲያጎንስቲክ 'ጳጉሜን ለጤና' በሚል ለ11ኛ ግዜ ባዘጋጀው መርሀ ግብር ከመንግስት ህክምና ተቋማት ምርመራ ታዞላቸው አቅም ለሌላቸው 1ሺ ለሚደርሱ ታካሚ የህብረተሰብ ክፍሎች የነፃ አገልግሎት ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ታካሚዎቹ ለምዝገባ ሲቀርቡ አቅም እንደሌላቸው የሚያሳይ ወረቀት ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡ከህክምና ተቋማት ለሚመጡ ነፃ የአምቡላንስ አገልግሎት ከማቅረብ በተጨማሪ 18 ለሚሆኑ ሀገር በቀል የእርዳታ ድርጅቶችም አመቱን ሙሉ ነፃ ምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡

የህክምና አገልግሎቱን ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች ከስር ባለውስልክ ቁጥር ማግኘት ይቻላል ብሏል።

0940050505 ወይም 0940040404 ይደውሉ ተብሏል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በቀጣይ ዓመት የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል።የቀጣዩ ዓመት ትምህርት ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ምዝገባ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል ብለዋል።

የበሽታው ሁኔታ እየተስፈፋ ቢሆንም የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ሆኑ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።ወደ መማር ማስተማር ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሠራ ገልጸው፣ ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ እና መሰል አቅርቦቶችን ከባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በግልም ሆነ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳይከሰት ተማሪዎች ማስክ በማድረግ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና እጅን በመታጠብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል።ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በሚል 2012 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ያለፋቸውን ትምህርቶች ማካካሻ ለመስጠት መታሰቡንም ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት ተቃውሞ ለማሰማት የወጡ ጥቂት ሰልፈኞች በአንድ የኤምባሲው ሰራተኛ ላይ ድብደባ እንደፈጸሙና የደምበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ሂደትም እንዲስተጓጎል ማድረጋቸውን ኤምባሲው አስታውቋል።በአሁኑ ሰዓት ጥቃት የደረሰበት የኤምባሲው ሰራተኛ በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሲሆን ጥቃቱን የፈጸሙት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጥቃቱን የፈጸሙት ግለሰቦች ወደ ህግ በሚቀርቡበት አግባብ ዙሪያ ከፖሊስ ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

[በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ]
@YeneTube @FikerAssefa
በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ከበደ ገመቹ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል!

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረውና ሸሽቶ በነበረበት አዳአ ድሬ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሃምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋለው ከበደ ገመቹ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል።በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አረዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ በተጠርጣሪው ላይ በርካታ የምርመራ ስራ ማከናወኑን ለችሎቱ አስረድቷል።በተጠርጣሪ እጅ ላይ የተገኘው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ መመርመሩን ገልጿል።

በተጠርጣሪው ላይ የተደረገ የቴክኒክ ምርመራ ውጤት መምጣቱን ተከትሎ ይህን ሰፊ ትንተና ውጤት ለመተንተን ጊዜ እንደሚያስፈልገው ለችሎቱ ገልጿል።ተጠርጣሪው ከበደ ገመቹ በበኩሉ በአስተርጓሚ ከተያዘ ከአንድ ወር ከ16 ቀን በላይ እንደሆነው ጠቅሶ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የተገደለበት ሽጉጥ የኔ አይደለም ሲል ፍርድ ቤቱ ዋስትና እንዲፈቅድለት ጠይቋል።መርማሪ ፖሊስም ሽጉጡ የተጠርጣሪው መሆኑን ለችሎቱ አብራርቷል፤ በግድያው ወቅት በቦታው እንደነበር ጠቅሷል።ጉዳዩን የተከታተለው ችሎቱ ለፖሊስ የምርመራ ውጤት ትንተና ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል ሲል የ10 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ኔዘርላንድ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ አገር ሆነች!

በ2012 በጀት ዓመት ኔዘርላንድ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀዳሚ መዳረሻ አገር መሆኗ ተገለጸ፡፡ኢትዮጵያ በ2012 በጀት አመት አበባ ፣ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት የኤሌክትሪክ ውጤቶች፣ ጫማ ፣ ቆዳ ማርና ሰም፣ የቅባት እህሎች የአልኮል መጠጦች፣ ጫት፣ ሻይ ብረትና የመሳሰሉትን ወደ ኔዘርላንድስ ልካለች።
ከተላኩት የወጪ ንግዶችም ኢትዮጵያ 320 ሚሊዮን 162 ሺህ የአሜሪካን ዶላር አግኘታለች።ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቡና ጫማ፣ አበባ፣ የቆዳውጤቶችን፣ የቅባት እህሎችን እና ሌሎች ኢትዮጵያ ወደ ውጪ የምትልካቸውም ምርቶች በመቀበል አሜሪካ በሁለተኛነት ስትቀመጥ፤ በተጠቀሰው በጀት አመት 295 ሚሊዮን 809 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ማግኘት ችላለች፡፡ከሶማሊያ 291 ሚሊዮን 855 ሺህ ዶላር፣ ከሳውዲ አረቢያ 214 ሚሊዮን 652 ሺህ፣ ከጀርመን 174 ሚሊዮን 283 ሺህ ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የገመና እና መለከት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲ አድነው ወንድይራድ (አዶኒስ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን በእሁድ መዝናኛ ይተላለፉ የነበሩት የገመና እና መለከት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲ አድነው ወንድይራድ (አዶኒስ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።ብዙም ወደሚዲያ ቀርቦ የመታየት ፍላጎት የሌለው ደራሲ አድነው ወንድይራድ በሙያው አርክቴክት ሲሆን የአና ማስታወሻ መፀሀፍም ለአንባቢያን አድርሷል።ደራሲና አርክቴክት አድነው ወንድይራድ (አዶኒስ) ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የማርኬቲንግና ቢዝነስ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡በ2012 በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ እና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

መምሪያው እንዳስታወቀው አፈፃፀሙ የእቅዱን 102 ነጥብ 2 በመቶ እንዲሁም በገንዘብ ከእቅዱ የ143 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡ከገቢው ውስጥ 6 ቢሊዮን ብሩ የተሰበሰበው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከቀረበ ጅምላ የኃይል ሽያጭ፣ 607 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብሩ ከከፍተኛ የኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች፣ 44 ነጥብ 36 ሚሊዮን ብር ለኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ከቀረበ የኃይል ሽያጭ እንዲሁም 69 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብሩ ኢትዮ ቴሌኮም ከተጠቀመበት የፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ የተሰበሰበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

[EEPCo]
@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ፋውቺ ለክትባት መጣደፉ ቢቀርብን ይሻላል አሉ!

የአሜሪካ ዕውቅ የማኅበረሰብ ጤናና የተላላፊ በሽታዎች ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ‹‹እኔ ተናግሪያለሁ! ይሄ ለክትባት የምንጣደፈው ነገር አላማረኝም›› እያሉ ነው፡፡ይህን የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ የመጪው ምርጫ በለስ እንዲቀናቸው በሙከራ ላይ ያለን ክትባት ያለጊዜው ወደ ሕዝብ በማውጣት ‹ክትባት ደርሷልና ተከተቡ› እንዳይሉ ስጋት መፈጠሩን ተከትሎ ነው፡፡ዶ/ር ፋውቺ በአሜሪካ ህዝብ ከትራምፕ የበለጠ ተሰሚነትና የመታመን ፀጋን ያገኙ ጎምቱ የጤና ባለሞያ ናቸው፡፡ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት አንድን ክትባት የሕክምና ደንብና መርሆችን ሳይከተሉ ወደ ሕዝብ ማውጣት የሌሎች ክትባቶችን ተስፋ ያጨልማል፡፡ትራምፕ አንድን ክትባት ሙሉ ሒደቱን ሳይጨርስና በብዙ ሰዎች ላይ ሙከራ ሳይደረግበት ይፋ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ የሚገኙት ካለፈው ሳምንት ወዲህ ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ለማድረግ የተበረታቱት በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት በኅዳር ከሚደረገው ምርጫ በፊት ለመጨመር በመሻት ነው፡፡አሁን ባለው ሁኔታ ትራምፕ ከጆ ባይደን ያነሰ ቅቡልና እንዳላቸው የሕዝብ ፖለቲካዊ ሙቀት መመተሪያ ዳሰሳ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ባለፈው ቅዳሜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት ከሆነ የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ለመድኃኒት አምራቾች ሥራቸውን እያደናቀፈባቸው ነው፡፡ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚሉት የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ‹ክትባት አምራቾች ትክክለኛውን የመድኃኒት አመራረት ሒደት ተከትለው እንዲሄዱ› በተደጋጋሚ በማሳሰቡ ነው፡፡ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዶናልድ ትራምፕ በኦክስፎድና በአስትራዜኔካ አማካኝነት እየተሞከረ ያለው ክትባት ለአስቸኳይ የሕክምና አገልግሎት በአቋራጭ ለሕዝብ እንዲቀርብ የሚቻልበትን መንገድ እየፈለጉ እንደሆነ ዘግቦ ነበር፡፡እነ ኦክስፎርድ እየሞከሩት ባለው ክትባት ለመሳተፍ 10 ሺ አሜሪካዊያን ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡

ነገር ግን የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን 30ሺህ ፈቃደኞች ካልተሟሉ ይሁንታን አልሰጥም እያለ ነው፡፡የኦክስፎርድ ክትባት አሁን ዓለም ላይ እየተሞከሩ ካሉ በዐሥራዎቹ ከሚገኙ ምርምሮች እጅግ ተስፋ የተጣለበት ነው፡፡ባለፉት ሳምንታት ታዋቂ መድኃኒት ፋብሪካዎች መድኃኒቶቻቸውን በመሞከር ላይ ተጠምደው ቆይተዋል፡፡ከዚህ ቀደም የኤሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የወባ መድኃኒት የሆነው ሀይድሮክሲክሎሮኪዩን ለኮሮና ታማሚዎች ቢሰጥ እንደማይቃወም ተናግሮ ነበር፡፡ከዚያ በኋላ ግን መድኃኒቱ ከጥቅሙ ጉዳት ማመዘኑ በምርመራ በመረጋገጡ እውቅና ነፍጎታል፡፡ዶናልድ ትራምፕ ይህን መድኃኒት ለሳምንታት መውሰዳቸውንና ፍቱን እንደሆነ እንደደረሱበት በተደጋጋሚ ይናገራሉ፡፡ዶ/ር ፋውቺ እንደሚሉት ክትባቶች ትክክለኛውን አካሄድ ካልተከተሉ አደጋ ማስከተላቸው ብቻም ሳይሆን ሰዎች በቀጣይ በሚወጡ መድኃኒቶች እምነት ያጣሉ፣ እንዲመከርባቸው የሚፈቅዱ በጎ ፈቃደኞችንም ማሸሽ ይሆናል፡፡ዶ/ር ፋውቺ ፖለቲካ ሕክምና ውስጥ ገብቶ መፈትፈት የለበትም፡፡ሕክምና የራሱን መንገድ እንዲከተል ሊተው ይገባል የሚል አቋም አላቸው፡፡

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ተጨማሪ 29 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው። 47 ሰዎች አገግመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 2 ሺኅ 101 ናሙናዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ 29 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።ይህንን ተከትሎም አጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሺኅ 946 ከፍ ብሏል።ባለፉት 24 ሰዓታት 49 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 828 ደርሷል። በእለቱ 11 ሰዎች ደገፍሞ በጽኑ የህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ቢሮው አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በነሐሴ የመጀመሪያ አጋማሽ ቀናት ከ256 ሺህ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደረገላቸው ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በተያዘው ወር እየተካሄደ ባለው የማኅበረሰብ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በ15 ቀናት ከ256 ሺህ በላይ ሰዎች ምርመራ እንደተደረገላቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳኑ ዐብደላ ሐምዶክ የኅዳሴ ግድብን ሊጎበኙ ይችላሉ! -ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ

የሱዳን ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ በመጪው ወር  ወደ ኢትዮጵያ ሲያመሩ ታላቁ የኅዳሴ ግድብን ሊጎበኙ እንደሚችሉ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ የሱዳኑ አቻቸው በሚቀጥለው ወር ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ያረጋገጡት በኻርቱም ባደረጉት የአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ከጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።ዐቢይ "በሚቀጥለው ወር ጠቅላይ ምኒስትር ሐምዶክ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የጋራ ፕሮጀክታችን የታላቁ የኅዳሴ ግድብን እንጎበኝ ይሆናል" ብለዋል።ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ ዐቢይ ይፋ ስላደረጉት የአዲስ አበባ እና በምን አልባት የተጠቀሰው የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉብኝት ያሉት ነገር የለም።

"ታሪካዊ" ያሉትን የኢትዮጵያ እና የሱዳን ግንኙነት ያወደሱት ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ "በጋራ ልንሰራ የምንችለው ነገር ለቀጣናው ውሕደት እንደ ባቡር ሞተር ሊያገለግል ይችላል" ሲሉ ተደምጠዋል።"በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ምኒስትር ሐምዶክ እና ከምኒስትሮቻቸው ጋር ውጤታማ ውይይት አድርጊያለሁ" ያሉት ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከአጀንዳዎቹ መካከል እንደሚገኝበት ገልጸዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክም ለኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ "ትልቅ ተስፋ" ባሉት እና እስካሁን 120 ቢሊዮን ብር በወጣበት የጉባው ግድብ ላይ ውይይት መደረጉን አረጋግጠዋል።ጠቅላይ ምኒስትሮቹን ጨምሮ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ካደረጉት ውይይት በኋላ ያወጡት የጋራ መግለጫ "በሶስትዮሽ ድርድሩ ስኬታማ ማጠቃለያ ላይ ለመድረስ የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ሁለቱ ወገኖች አጽንዖት ሰጥተዋል" ብሏል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1545 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 18,778 የላብራቶሪ ምርመራ 1545 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ17 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 709 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 534 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 15,796 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 43,688 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር አቶ ሙሰጠፋ ሙሁመድ ዑመር በር ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ያለው የትምህርት ቤቶች ግንባታ ጎበኙ።በምክትል ርዕስ መሰተዳደሩ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሳለፈነው በ 2012 በጀት አመት መሰረተ ድንጋይ የተቀመጡ የትምህርት ቤቶች የግንባታ አፈፃፀም ሂደት ነው የጎበኙት።

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ዣንጥራር አባይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ተገኝተው የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት አስጀመሩ፡፡ በክፍለከተማው የማዕድ ማጋራት እና ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም ተከናውኗል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ተገኝተው የአቅመደካሞችን ቤት እድሳት አስጀምረዋል፡፡ክፍለ ከተማው በ2012 አ.ም የክረምቱ ወር ለማከናወን ያቀደውን የአቅመደካሞች ቤት ዕድሳት፣ መዓድ ማጋራት እና የአረንጓዴ አሻራ መር መርሃ ግብር በዛሬው እለት አከናውኗል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa