የኦሮሚያ ክልል መንግስት ብስለት ከጎደለው መግለጫው እንዲታቀብ ኦነግ አሳሰበ።
ባለፈው ሳምንት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ”ሕዝቡ ከአገር ጥቅም በተቃራኒ ከቆሙት አካላት ሊጠነቀቅ ይገባል” ሲል በሰጠው መግለጫ በግብፅ የሚደገፍ ቡድንና ወያኔ ከሀገር ጥቅም በተቃራኒ የቆሙ ናቸው ማለቱ ይታወሳል፡፡በክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ሶስተኛውከሀገር ጥቅም በተቃራኒ የቆሙት ቡድኖች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸው ያሉ ሲሆን ምርጫ መራዘሙን መነሻ ምክንያት በማድረግ በአቋራጭ ስልጣን የሚፈልጉ አካላት ናቸው” ብለው ነበር።የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ፓርቲያችን በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት ነው።በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም ጋር በጋራ መግባባት ይሰራል፤ መንግስት የገለፀው የፖለቲካ ድርጅት አይነት አይደለንም፣ እስከምናውቀውም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንዲህ አይነት ድርጅት የለም ብለዋል፡፡
ለሚዲያ ፍጆታ ሊያውለው ፈልጎት ከሆነ ከመንግስት የማይጠበቅ ነው ያሉ ሲሆን በትክክል የትኛውን የፖለቲካ ድርጅት ከሀገር ጥቅም ተቃራኒ የቆመ እንደሆነ አለመናገር ውዥንብር መንዛት ይባላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡የኦሮሞ ህዝብ የብሔር ፣የኢኮኖሚ፣የባህል ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ታግሏል፤ እነዚህ ጥያቄዎቹ አሁንም አልተመለሱለትም፤ ከለውጡ በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋር በተመሳሳይ እስራትን ግድያን፣መፈናቀልን ጨምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰቱም ቀጥሏል፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አልተቻለም ፣ ህገ ወጥነት ሰፍኗል ፣ ህግና ስርአትን ማስጠበቅ አልተቻለም ፣ ህዝቡ ከፍተኛ ቅሬታ ላይ ነው ብለዋል አቶ ቀጀላ፡፡ይሄን የሚያወሳስቡት በመንግስት መዋቅር ላይ ያሉት ናቸው፣ ይሄን መለወጥ ካልተቻለ፣ ራስ ምታት ነው በብዙ ዕጥፍ ጨምሮ በቀጣይ የሚጠብቀን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ቀጀላ ከግጭትና ከቁልቁለት መንገድ የሚታደገን ሁላችንም ፓርቲዎች ያስቀመጥነውን ሀሳብ በጠረጴዛ ላይ በማስቀመጥ ተወያይቶ የተግባባንበትን አማካይ ውሳኔ ማስቀጠል ነው ብለዋል፡፡እናንተ የራሳችሁ ጉዳይ የኔ መንገድ ብቻ ነው የሚተገበረው ብሎ የማይተረጎም ህገ መንግስት ለመተርጎም ማገላበጥ ከቀድሞዎቹ ስርአቶች አለመማር ነውም ብለዋል፡፡ፓርላማው ስልጣኑ መቀጠል የለበትም፣ በአምስት አመት ስልጣኑ ያልቃል የሚለውን ህገ መንግስት ስድስት አመት በማድረግ ተረጎምነው ሊሉ ነው ወይ ሲሉ የሚያነሱት አቶ ቀጀላ መንግስት ብስለት ከጎደላቸው መግለጫዎቹና ተግባራቱ እንዲታረም አሳስበዋል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

በኮሮና ቫይረስ መያዙ ሳይታወቅ ሕይወቱ ያለፈ ሰው የቀብር ሥነ ሥርዓት የፈጸሙና ንክኪ ያላቸው 45 ግሰዎች ወደለይቶ ማቆያ መግባታቸውን የእንሳሮ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ የሆነ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ ወደ ማቆያ ሳይገባ ናሙና ሰጥቶ ነበር፡፡ ናሙና እንደሰጠ በድንገት ውጤቱ ሳይታወቅ ሕይወቱ አልፏል፡፡ የግለሰቡ ሕይወት እንዳለፈም አስከሬኑ ወደ ትውልድ ቀየዉ ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ተልኳል፡፡ይህ የሆነው ባለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም ነበር፡፡ እስከዚው ቀን ድረስ ውጤቱ ስላልታወቀ ዘመድ አዝማድ ተሰብስቦ አስከሬኑን በመያዝ ወደ እንሳሮ ወረዳ አቅንቶ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እሑድ ግንቦት 30/2012 ዓ.ም ተከውኗል፡፡ በዚሁ ዕለት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሠረት ግለሰቡ የኮሮና ቫይረስ እንደነበረበት አረጋግጧል፡፡የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ መረጃው እንደደረሰዉ ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ሰዎች ጋር በመሆን የቀብር ሥርዓቱ በተፈጸመበት እንሳሮ ወረዳ አቅንቶ ከግለሰቡ ጋር ቀጥታ ንክኪ የነበራቸውን ግለሰቦች እየለየ መሆኑን የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ጸዳሉ ሰሙ ንጉሥ ተናግረዋል፡፡
የእንሳሮ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሲስተር በቀለች ሞገስ ደግሞ የቀጥታ ንክኪ ይኖራቸዋል በሚል ጥርጣሬ 45 ሰዎች በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ በወረዳው ሦስት ቀበሌዎች ላይ ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱና ባሉበት ሆነው ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነም ታውቋል፡፡ከሟች ጋር የቀጥታ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብው ከተጠረጠሩ ግለሰቦች ውጭም እነዚህ ግለሰቦች የነበራቸው የንክኪና ግንኙነት ታሪክም እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ድረስ በሰሜን ሸዋ ዞን ደረጃ 182 ግለሰቦች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡በእንሳሮ ወረዳ በለይቶ ማቆ እንዲቀመጡ የተደረጉት ግለሰቦች ናሙና ከዛሬ ጀምሮ መመርመር እንደሚጀምርም ታውቋል፡፡
#አብመድ

የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፔየሪ ንኩሩንዚዛ አረፉ፡፡
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ፔየሪ ንኩሩንዚዛ በ55 ዓመታቸው ከልብ ሕመም ጋር በተያያዘ አርፈዋል፡፡ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የጤና እክል ገጥሟቸው ሆስፒታል የገቡት ፕሬዝዳንቱ ጤንነታቸው ተሻሽሎ እንደነበርና ከትናንት ጀምሮ ግን ሕመማቸው ጸንቶ ማረፋቸውን መንግሥት አስታውቋል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም አዲሱ ገበያ በተባለ አካባቢ በደረሰ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ፤ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
አደጋው የደረሰው ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲስ ገበያ አደባባይ አካባቢ ከሱሉልታ ከተማ የከብቶች መኖ ሳር ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ኮድ 3-19791 ኢት ተሽከርካሪ የተነሣ መሆኑም ተገልጿል። ተሽከርካሪው ከመንገድ ጠርዝ ግንብ ጋር በመጋጨቱ ተገልብጦ የአሽከርካሪው ሕይወት ሲያልፍ፣ ሁለት እግረኞች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአሽከርካሪው ረዳት ከመኪናው ዘልሎ በመውረዱ ሕይወቱን ከአደጋው መትረፉን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የጉለሌ፣የካ እና የአራዳ ክፍለ ከተሞች የቀጠና 2 የትራፊክ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ሙሉጌታ ቢተው ገልጸዋል።
Via ETV

የደቡብ ክልልን በአራት የሚከፍለው አወቃቀር ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲተላለፍ ዛሬ ተወሰነ!
➡️ የወላይታ ጉዳይ ወደፊት ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሏል
➡️ ጌዲኦ “ልዩ ዞን” እንዲሆን ከውሳኔ ላይ ተደርሷል
➡️የጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ደራሼ፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና ኮንሶ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲጠቃለሉ በዛሬው ስብሰባ ከውሳኔ ላይ መደረሱ ተነግሯል።
➡️በተለምዶ “ምዕራብ ዞን” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያሉ ሸካ፣ ቤንች፣ ማጂ፣ ከፋ እና ዳውሮ ዞኖች በአንድ ክልል ስር እንዲሆኑ በምክረ ሀሳቡ ላይ ቀርቧል ተብሏል።
➡️ማዕከላዊ ዞን” በመባል በሚታወቀው አካባቢ ያሉት የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታ፣ ሀላባ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ በጋራ ሆነው ሁለተኛ ክልል እንዲመሰርቱ በምክረ ሀሳቡ መቀመጡ ታውቋል።
ለEthiopia Insider ዝርዝር ዘገባ👇👇👇
https://telegra.ph/The-Fate-of-SNNPR-06-09

Forwarded from HEY Online Market
Playstation 4PRO (Slim)
With 2 controllers
1000 GB storage
With FIFA 2019 CD
Price 23,999 Birr
Contact us :
0953964175
0925927457 @eBRO4
0910695100
@heyonlinemarket
With 2 controllers
1000 GB storage
With FIFA 2019 CD
Price 23,999 Birr
Contact us :
0953964175
0925927457 @eBRO4
0910695100
@heyonlinemarket
Forwarded from Kídus
⚜️SHEBA - ሺባ⚜️
📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን
ጥራት ያለው ጌጣጌጥ 💎በተመጣጣኝ ዋጋ ከኩባንያችን (ሺባ) ይግዙ ይህንን::
⚠️(ሺባ) የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እያከበርን ስለሆነ ‼️ነፃ ‼️ሰዐት ለማግኘት ከዌብ ሳይታችን ላይ ማንኛዉንም እቃ ይግዙ፡
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
Website - www.shebasluxury.com
Telegram - https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ
Contact Admin @ki_d_us
📞 በ 0941158969 ይደውሉልን
🚚 ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን🏍

Forwarded from YeneTube
EmpowerMed የተሰኘ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ዘርፍ በእጅጉ የመደገፍ ብሎም የመዋቅር ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ያልሆነ ግብረሠናይ ድርጅት ነው። መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው ይህ ግብረሠናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፉን በመክፈት እየሰራ ይገኛል። በቅርቡ በተቀሰቀሰው COVID-19 ወረርሽኝን ምክንያት ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ለመርዳት ፕሮግራም በመቅረፅ ማገዝ ይፈልጋል። በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል ያላችሁ የህክምና ተማሪዎች ማለትም Medical, Nursing, Midwifery ወዘተ እና የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች በሙሉ ከድርጅታችን ጋር ህብረት መፍጠር የምትፈልጉ በሙሉ በተገለፀው ዌብሣይት እና የ ፌስቡክ ገፃችን ላይ በመግባት መመዝገብ እና ህብረት መፍጠር ትችላላችሁ ።
የድርጅቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ facebook.com/empowermed.ngo ነው።
የድርጅቱ ዌ ብ ሳ ይ ት
http://EmpowerMed.ngo
ነው።

Forwarded from Fiker Assefa
#ዘ_አልኬሚስት
#4ተኛው_እትም_በገበያ_ላይ_ዋለ
ከ150 ሚሊዮን ኮፒዎች በላይ በመሸጥ ጊነስ ቡክ ላይ ለመስፈር የበቃ፣ ከ80 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ፣ 115 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የተቀዳጀ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፍ የሆነው ዘ-አልኬሚስት #አማርኛው_እነሆ_ለ4ተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ዋለ!!!
#ስለዚህ_ድንቅ_መጽሐፍ_ከተሰጡ አስተያየቶች
“ስለ አስማት፣ ህልም እና በሌሎች ቦታዎች ተግተን ስልምንፈልገው፣ ነገር ግን ከበራችን ደጃፍ ስላለው ሃብት የሚያወራ ውብ መጽሐፍ”
#ማዶና (ዘፋኝ)
“ከምርጥ መጽሐፎቼ አንዱ”
#ዊል_ስሚዝ (ተዋናይ)
Join T.me/teklutilahun

Forwarded from Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን
#የጭን_ቁስል
#27ኛ_ዕትም_በገበያ_ላይ
ሕጻናት ዐምባ ውስጥ ያደገችው እንስት ማን እንደሆነችና ከየት እንደተገኘች አታውቅም፡፡ ዐምባው ወደ ሌላ ተቋም ሲቀየር ህይወቷ አደጋ ላይ ወደቀ…
እናም በገጠማት እጅግ መራርና አንገሽጋሽ የሕይወት ትግል እግዚአብሔርን የምታስፈራራ፣ ሞት ታግሎ ታግሎ ሊጥላት ያልቻለች ነፍስ ሆና የሁላችንንም ጓዳ እያስፈተሸች ማንም ትንፍሽ ሊል የማይደፍረውን ገመና ገላልጣ ታሳየናለች…
***
#ለደራሲው_ሥራ_ከተሰጡ_አስተያየቶች
ታሪኩ አጓጊ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ምእራፍ ወይም ክፍል የሚተረኩት ታሪኮች ስሜት ይዘው የሚነጉዱ ናቸው፡፡ ልብ ያንጠለጥላሉ፡፡ ቀጥሎስ? ከዚያ በኋላስ? መጨረሻውስ እያልን ነው የምናነበው፡፡ #አዲስ_አድማስ_ጋዜጣ
መጽሐፉ በሚመስጥ መልኩ ተጀምሮ፣ በሚመስጥ መልኩ የሚያልቅ ነው፡፡ #ኤፍ_ኤም_97.1
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
join T.me/teklutilahun

⬆️ "ሰው ለመርዳት የማይታክተውን ወንድማችንን እንርዳው!"
(ኤልያስ መሰረት)
ጤና ይስጥልኝ። ዶ/ር መስከረም አበባው እባላለሁ። በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጠቅላላ
ሀኪም ነኝ። ባለቤቴ ዶ/ር ንጉስ ሸጋው አውለውም ጠቅላላ ሀኪም ሲሆን ከባህር ዳር 43 ኪ.ሜ በምትገኝ አደት ሆስፒታል ተቀጥሮ ይሰራል።
ሁለታችንም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የ2010 ዓ.ም ተመራቂዎች ስንሆን በጓደኝነት ለጥቂት
አመታት ቆይተን የነበረ ሲሆን፣ ከተጋባን ደግሞ የተወሰኑ ወራትን አስቆጥረናል። "ሁሉ ነገሬ" ብዬ የምጠራው ባለቤቴ ዶ/ር ንጉስ ሸጋው ይህን ሰሞን መለስተኛ የጤና
መታወክ ይታይበት ነበር።
ከሥስት ቀናት በፊት ባለቤቴ ባደረገው ምርመራ መሰረት Acute myeloid leukaemia (AML) በሚባል የደም ካንሰር አይነት እንዳለበት ተነግሮናል።
ሁሉ ነገሬ ንጉስ አሁን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የደም ካንሰር ህክምና ክፍል ተኝቶ
ህክምናውን በመከታተል ላይ ይገኛል።
ከባለቤቴ ሀኪም ጋር ባደረኩት ምክክር የመቅኔ ንቅለ ተከላ ወይንም hematopoietic stem cell የሚባል ህክምና በውጭ ሀገር ማድረግ
እንዳለብን ገልፆልናል።
ነገር ግን ያለብን የኢኮኖሚ ውስንነት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተጣምሮ ነገሮችን ከባድ
አድርጎብናል። አጥብቄ እርዳታችሁን እፈልጋለሁ። ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለቤተሰባችን
አጣብቂኝ በሆነ በዚህ ጊዜ በገንዘብ ፣ በሀሳብም ሆነ በፀሎት የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋልን
እጠይቃለሁ።
በእንደዚ አይነት በሽታዎች ህመምተኛው የሚያስፈልገውን ህክምና የሚያገኝበት ፍጥነት
በጣም ወሳኝ ነው። በዚህ ወረርሽን ጊዜ በውጭ ሀገር ለህክምና የሚቀበለውን ሆስፒታል
ወይም በፍጥነት ፓስፖርት እንዴት ማግኘት እንደምችል ገና አላውቅም።
ባለቤቴ ሁሉ ነገሬ ነው። አባቴን በለጋነት እድሜ ገና በ13 አመቴ ነው በህክምና አገልግሎት
አለመኖር ምክንያት ያጣሁት። ንጉስ ይህን ህክምና ካላገኘ እኔ ባለቤቴንም አጣለሁ፤
ኢትዮጵያም አንድ የህክምና ዶክተር ታጣለች። ስለዚህ እባካችሁን እርዱን!
ይህ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋራ የባንክ አካውንታችን ነው:
ዶ/ር ንጉስ ሸጋው እና/ወይም ዶ/ር መስከረም አበባው 1000323020349
GoFund me:
https://gf.me/u/x7vthz
ለበለጠ መረጃ በ +251923065854 ዶ/ር መስከረምን ማግኘት ይችላሉ።
ስለ እርዳታችሁ አስቀድሜ አመሰግናለሁ።

gofundme.com
Blood cancer medical support for Dr Negusse, organized by Hana Azene
"All for one and one for all; we leave no one behind."
.
Hello everyone. I am … Hana Azene needs your support for Blood cancer medical support for Dr Negusse

⬆️
በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባንክ ደጃፍ ላይ ተይዞ ለጅቡቲ የፀጥታ ሀይሎች ተላልፎ የተሰጠው የቀድሞው የጅቡቲ አየር ሀይል አብራሪ ሀገሩ ከተወሰደ በሁላ የደረሰበትን ድብደባ የሚያሳይ ቪድዮ በመውጣቱ ጅቡቲ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ እየበረታ ነው!
ሌ/ት ፉአድ ዩሱፍ አሊ ከጅቡቲ ጠፍቶ ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው መጋቢት 2012ዓ/ም ነበር። እርሱ እንደሚለው ለመጥፋቱ ምክንያቱ የደሞዝ አለማግኘት ነበር።
ከዛ ግን አዲስ አበባ ውስጥ ዳሀብሺል ከተባለ የሀዋላ አገልግሎት ገንዘብ ሊያወጣ ሲል በኢትዮጵያ የፀጥታ ሀይሎች ተይዞ ከዛም ለጅቡቲ የፀጥታ ሀይሎች ተላልፎ ተሰጥቷል። የጅቡቲ የፀጥታ ሀይሎችም በልዩ አውሮፕላን ወደ ጅቡቲ ወስደውት ነበር።
ከዛ ግን ለብዙ ሳምንታት ደብዛው ከጠፋ በሁዋላ ሰሞኑን የደረሰበትን ድብደባ የሚያሳይ ቪድዮ ከእስር ቤት ሾልኮ ወጥቷል፣ ይህም ጅቡቲ ውስጥ ቁጣ ቀስቅሷል።
"ይህ ቪድዮ ሾልኮ ወጥቶ ከታየ በህይወት አልተርፍም፣ መሞቴ ግን ብዙ አያስጨንቀኝም" የሚለው ሊ/ት ፉአድ ሰውነቱ ላይ በድብደባ የደረሰበትን ጉዳት እና የታሰረበትን ቆሻሻ ስፍራ በቪድዮው ላይ ያሳያል።
የቪድዮው መውጣትን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የጅቡቲ ዜጎች ግለሰቡ ይፈታ ብለው ሰልፍ ወጥተዋል። ሰልፉ በተለይ በጅቡቲ ሁለተኛዋ ከተማ አሊ ሳቢህ ውስጥ ብሷል ተብሏል።
የጅቡቲ መንግስት በበኩሉ ግለሰቡ የተያዘው "በሀገር መክዳት ወንጀል ነው" ያለ ሲሆን ሰልፍ የወጡት ሰዎችም ዝርፊያ እየፈፀሙ እንደሆነ ጠቅሶ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
በኢትዮጵያ ካሉት የጅቡቲ አምባሳደር እና ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሞክሬ አልተሳካም፣ በኢትዮጵያ በኩልም ምንም አልተባለም።
"ምናልባት ኢትዮጵያ ይህንን ፓይለት ለጅቡቲ አሳልፋ የሰጠችው ከ15 አመት በፊት በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ጠፍተው ጅቡቲ የገቡ የአየር ሀይል ፓይለቶችን ጅቡቲ ለኢትዮጵያ አሳልፋ ሰጥታ ስለነበር ሊሆን ይችላል" ያሉኝ አንድ የምስራቅ አፍሪካ ተንታኝ ናቸው።
የደረሰኝ መረጃ እንደሚያመለክተው ሊ/ት ፉአድ 37 አመቱ ሲሆን የሰባት ልጆች አባት ነው። የጅቡቲ አየር ሀይልን የተቀላቀለው ከ14 አመት በፊት ሲሆን በሩስያ እና ደቡብ አፍሪካ ትምህርት ተከታትሏል።
Via:- @eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa

አንተኒ ፋውቺ ለወረርሽኙ ክትባት እንደሚገኝ ተናገሩ!
የትራምፕ የጤና ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ዶክተር አንተኒ ፋውቺ “ከሁሉ በላይ የሚያስጨንቀኝ ነው” ያሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ “ገና አላበቃም” ያሉ ሲሆን፤ ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋት በጣም ቢያሳስባቸውም፤ ክትባት እንደሚገኝለት ግን እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
Via:- BBC

የሕዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ሁለተኛ ቀን ውይይት ከሰዓታት በኋላ ይጀመራል
ድርድሩ የደቡብ አፍሪካ፣አውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ታዛቢዎች በተገኙበት እንደሚከሄድ ተገልጿል።የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ትናንት ተካሂዷል።ድርድሩ በበይነ-መረብ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ታዛቢዎች በተገኙበት በውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ተካሂዷል።በዚህ ድርድር ላይ በደቡብ አፍሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በታዛቢነት ተገኝተዋል ተብሏል።በዚህ ስብሰባ ሀገራቱ የድርድር ስነ-ስርዓትን ታዛቢዎችን፣ ስለ ድርድሩ አካሄድ እና ዋናዋና የድርድር ያልተቋጩ ጉዳዮችን በተመለከተ ተነጋግረዋል።
እያንዳንዱ ሀገር ዋናዋና የድርድር ጉዳዮች ናቸው ያሏቸውን ሃሳቦች በዝርዝር አቅርበዋል።በዚህም መሰረት በቀጣይ ቀናት ተከታታይ ውይይቶችን ለማድረግ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።ይሁን እንጂ የታዛቢዎቹ ሚና ምን ይሁን የሚለውን በተመለከተ በሀገራቱ መካከል መግባባት ላይ ያልተደረሰ ሲሆን ስብሰባው በዛሬው ዕለትም የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።የሶስቱ ሀገራት ድርድር የግድቡ የመጀመሪያ ሙሌት እና ዓመታዊ አለቃቅ ላይ ብቻ የተወሰነ ሲሆን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ልዩነቶችን በድርድር ለመፍታት ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ዝግጁ መሆኗም ተገልጿል።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጃዋር መሀመድን አስጠነቀቀ!
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጃዋር መሀመድ የክልልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማደፍረስ በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ-ገፆች ከሚለጥፋቸው የተዛቡ መረጃዎች እንዲታቀብ በማስጠንቀቅ እስከአሁንም በለቀቃቸው ከእውነታ የራቁ መረጃዎች በህግ የሚጠየቅ መሆኑን አስታውቋል፡፡ፖሊስ ኮሚሽኑ በትናንትናው እለት ሰኔ2/2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የኦሮሚያ ፖሊስ ወንጀልን ከመከላከል፣ የክልልሉን ሰላም እና ፀጥታ ከማስከበር እንዲሁም ህግ እና ስርዓትን ከማስከበር የዘለለ ተግባር የለውም፡፡
በዚህም መሠረት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ልዩ ኃይሉን በማደራጀት የሕዝቡን ሰላም እና የክልልሉን ፀጥታ በማስጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን የክልልሉን ሰላም እና መረጋጋት የማይሹ አንዳንድ ግለሰቦች እና ቡድኖች የህዝብ መከታ የሆነውን ኃይል ሥም በማጠልሸት የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድለግ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡በዚህም መሰረት ከአሁን በኋላ ማንኛውም ግለሰብ ወይንም ቡድን የኦርሚያ ልዩ ኃይልን መልካም ስም እና ዝና ዝና እንዲያጎድፍ እንዲሁም ለፖለቲካ ትርፍ እንዲጠቀምበት አንፈቅድም፡፡
ከዲንሾ ጋር ተያይዞ የሚሰራጨው ተራ አሉባልታም ሊገታ ይገባዋል፡፡ መነሻው የግለሰቦች ፀብ ሲሆን ጉዳዩ በህግ ተይዞ በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡ቢሆንም ግን እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ ግለሰቦች በተለይም ጃዋር መሀመድ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የተዛባ መረጃን በመለጠፍ ብዙዎችን የማሳሳት ተግባሩን የቀጠለ ሲሆን በእንግሊዘኛ የለጠፈውን እንዲሁም ሌሎች ተጨባጭ መረጃዎችን በማያያዝ በህግ አግባብ የምንጠይቅ መሆኑን እንገልፃለን ማለቱን ከፖሊስ ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Via Addis Maleda

ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭት በሃገሪቱ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ የሚል የውሳኔ ሀሳብ ቀረበ!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጀምሯል።የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን ከማራዘም ጋር በተያያዘ የቀረበለትን የህገ መንግስት ትርጓሜ ጥያቄ ከአተረጓጎም ፣ መርህ ፣ ዘዴና አላማ ይዘት ጋር ገምግሞ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ የውሳኔ ሃሳብ ማሳለፉን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት
1. የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሃገሪቱ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ ፣
2. ተገቢ የሚመለከታቸው አካላት የቫይረሱን ስርጭትና ጉዳት ገምግመው መቀነሱን ወይንም ጉዳት ማድረሱን ማቆሙን ማረጋገጥ ሲችሉ ሃገራዊው ምርጫ ከ9 ወር እስከ 1 አመት ማካሄድ እንደሚቻል የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል። ኮሚቴው ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ የፌደሬሽን ምክር ቤት በማድመጥ እና በውሳኔው ላይ በመወያየት ላይ ይገኛል። ምክር ቤቱም ውሳኔውን መርምሮ በምክር ቤቱ አሰራር መሰረት የሚያጸድቅ ይሆናል።
#FBC

በኢትዮጵያ የስደተኛ ካምፕ የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ መገኘቱን @ASTelegramChannel ዘግቧል።ታማሚዋ የ16 አመት ኤርትራዊት ስደተኛ ስትሆን በአዲ-ሀሩሽ የስደተኞች ካምፕ የነበረችና ባለፈው ወር ወደ አንድ ገዳም ደርሳ እንደተመለሰች የህመም ምልክት እንደታየባት በኋላም ቫይረሱ እንደተገኘባት ታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ምርጫ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ!
ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ውይይት የውሳኔ ሃሳቡን ተቀብሎ በ114 ድጋፍ፣ በአራት ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ አጽድቋል።ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ለማራዘም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቦ ውይይት ተደርጎበታል።የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሺኙ ስጋት ሆኖ እስካለበት ድረስ የሁሉም ምክር ቤቶች ስልጣን እንዲቀጥል፤ እንዲሁም ወረርሽኙ ስጋት አለመሆኑ አለም ዓቀፍ የጤና ተቋማት ካላረጋገጡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንኑ ካጸደቀ በኋላ ከ9 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ምርጫ ይካሄድ የሚለው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው ውሳኔ ያሳለፈው።
ምንጭ:ኢዜአ