YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አሜሪካ በሁለት ወራት ውስጥ ዝቅተኛ የተባለውን የሞት ቁጥር መዘገበች

በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ 450 ሞት የመዘገበች ሲሆን ይህ ቁጥር በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የተመዘገበ ዝቅተኛው ቁጥር ነው ተብሏል፡፡
በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት ግንባር ቀደም በሆነችው አሜሪካ፤ እስካሁን 110ሺህ 990 ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን 2 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በአዉሮጳ በኮቪድ 19 እጅግ ብዙ  ሕዝብ በሞተባት ብሪታንያ በታየዉ ተቃዉሞ በ 17 ተኛዉ ክፍለ ዘመን የባርያ ንግድ በማካሄድ በሃገሪቱ በርካታ ሕንፃና የተለያዩ መሰረተ ልሞቶችን ያስገነባዉ ግለሰብ የዘመናት ሃዉልት  በተቃዉሞ ሰልፈኞች ከአደባባይ ተገርስሶ ወድቆአል።


በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአዉሮጳ ሃገራት ከተሞች ዘረኝነት እና የፖሊስ የግፍ ርምጃን በማዉገዝ ከፍተኛ  የተቃዉሞ ሰልፎች ተካሄዱ። የኮሮና ስርጭትን ለመግታት ሃገራት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ገደብ በጣሉበት በአሁኑ ወቅት በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአደባባይ ወጥተዉ ዘረኝነትን እና የፖሊስ ጥቃትን በአንድ ድምፅ ማዉገዛቸዉ ይበል ቢባልም የኮሮና ተኅዋሲ ዳግም እንዳይስፋፋ ስጋት አሳድሮአል።

በአዉሮጳ በኮቪድ 19 እጅግ ብዙ  ሕዝብ በሞተባት ብሪታንያ በታየዉ ተቃዉሞ በ 17 ተኛዉ ክፍለ ዘመን የባርያ ንግድ በማካሄድ በሃገሪቱ በርካታ ሕንፃና የተለያዩ መሰረተ ልሞቶችን ያስገነባዉ ግለሰብ የዘመናት ሃዉልት  በተቃዉሞ ሰልፈኞች ከአደባባይ ተገርስሶ ወድቆአል። አዜብ ታደሰ በብሪታንያ ስለነበረዉ ተቃዉሞ ከወኪላችን ድልነሳዉ ጌታነህ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች። 

Via:-Dw
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ላይ የጀመሩትን የሶስትዮሽ ውይይት ሊቀጥሉ ነው።

በሱዳን ጋባዥነት ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 2፤ 2012 በኢንተርኔት የቪዲዮ ኮንፈረንስ  አማካኝነት እንዲካሄድ ቀጠሮ በተያዘለት በዚህ ውይይት የአሜሪካ፣ የደቡብ አፍሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ታዛቢዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።በውይይቱ ላይ በህዳሴው ግድብ ድርድር እስካሁንም እልባት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች በአጀንዳነት እንደሚቀርቡ የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) ምሽቱን ዘግቧል። ሶስቱ ሀገራት ከታዛቢዎች ሚና ጋር በተያያዙ የአካሄድ ጉዳዩችም ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዜና ወኪሉ በዘገባው ጠቅሷል። 

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በአሜሪካ ከሁለት ወራት በኋላ ዝቅተኛው ከኮሮና ጋር የተያያዘ ሞት ተመዘገበ።

450 ሰው በኮሮና ምክንያት በ24 ሰአት ውስጥ የሞተ ሲሆን በአሜሪካ ከሁለት ወራት በኋላ በቀን ውስጥ የተመዘገበ ዝቅተኛው ሞት ነው ተብሏል፡፡አሜሪካ 110 ሺህ 990 ሰው በኮሮና ምክንያት በማጣት ክፉኛ የተመታችው ሀገር ነች፡፡ 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ሰውም ተጠቅቷል፡፡በሚያዚያ አጋማሽ በቀን 3 ሺህ ሞት መመዝገብ ጀምሮ ነበር፡፡ባለፉት ሁለት ሳምንታት ግን የሞት መጠኑ ከ 1 ሺህ ዝቅ ማለት ጀምሯል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ፍርድ የቀረበው ፖሊስ 1.25 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ዋስ ተጠየቀ!

በሚኒያፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ ከመሬት ላይ አጣብቆ አንገቱን በጉልበቱ ለዘጠኝ ደቂቃ የተጫነው ነጭ ፖሊስ የሰው ህይወት በማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርቧል። በወቅቱም 1.25 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ዋስ እንዲያቀርብ ተጠይቋል።አቃቤ ሕግ እንደጠቀሰው ወንጀሉ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር እንዲሁም በበርካታ ግዛቶች የተነሳው ተቃውሞና ቁጣን ተከትሎም ነው ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ዋስ እንዲያቀርብ የተጠየቀው።ዴሪክ ቾቪን በሁለተኛ ደረጃ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ክስ የሚቀርብበት ሲሆን ሦስቱ ፖሊሶች ደግሞ በግድያ ወንጀል በመተባባር ይከሰሳሉ።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የእንቅስቃሴ ገደብ አዋጅ በአውሮፓ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት መታደጉን አንድ ጥናት አመላከተ!

የዕንቅስቃሴ ገደቡ የሟቾችን ቁጥር የቀነሰላቸው 11 የአውሮፓ ሀገራት መሆናቸውን የለንደን ዩኒቨርስቲ የምርምር ቡድን አስታውቋል።አገራቱም የአውሮፓ ሀገራት አውስትራሊያ፣ ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ፍራንስ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ኖርዌይ፣ ስፔን፣ ሲውድን፣ ሲውዘርላንድ እና አሜሪካ ናቸው።በመሆኑም በነዚህ ሀገራት የእንቅስቃሴ አዋጅ መታወጁ እና ዜጎች በቤታቸው መቆየታቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት መታደጉን በጥናቱ ተመላክቷል።በጥናቱ እንደተገለፀው የእንቅስቃሴ ገደቡ በኮሮና ቫይረስ የሞቱትን ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ቀንሶታል።ዜጎች በቤታቸው ባይቀመጡና የተለመደው እንቅስቃሴ ቢተገበር የማቾች ቁጥር አሁን ካለበት በብዙ እጥፍ ሊሆን እንደሚችልም በጥናታቸው ጠቁመዋል፡፡በአስራአንዱ የአውሮፓ ሀገራ እስካሁን አንድ መቶ ሰላሳ ሺ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸውን ጥናቱ አካቷል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በትራንስፖርት ዘርፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋትን ለመከላከል ግብረ-ሀይሉ ማስተካከያ አደረገ!

ከ03/10/2012 ዓ.ም ግብረ ሀይሉ በከተማዋ በሚገኙ የባጃጆ፣ ዳማስ /ሱዙኪ/፣ ኪዊት እና የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረጉ ተጨማሪ ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት፡-

1. ባጃጆች የግልም ሆኑ የከተማ ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪ ሳይጨምር 1 ሰው ብቻ ጭነው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ፣

2. ኪዊት /Quit/ የግልም ሆነ የከተማ ታክስ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪን ሳይጨምር 1 ሰው ብቻ ጭነው የሚንቀሳቀሱ መሆኑ፣

3. ዳማስ /ሱዙኪ/ የግልም ሆነ የከተማ ታክሲ አገለግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪ ሳይጨምር 3 ሰው ብቻ ጭነው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው እና

4. የግል የቤት ተሽከርካሪዎች 2 ሰው ብቻ ጭነው ከፊት /ጋቢና/ ሰዉ ሳይዙ እንዲንቀሳቀሱ የተወሰነ ሲሆን በሌሎቹ እዚህ ባልተጠቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ከዚህ በፊት የተወሰኑ ክልከላዎች ተግባራዊ እየተደረጉ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል፡፡

የግል ተሽከርካሪዎችን ሳይጨምር ክፍያን በሚመለከት ከዚህ በፊት ሙሉ ጭነው የሚያስከፍሉትን አሁን በሚሳፈሩ ተሳፋሪዎች ልክ በመጋራት የሚሸፈን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ይህንን ክልከላ በሚተላለፋ አካላት ላይ ባለፈው በግብረ-ሀይሉ ተወስኖ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ቅጣት ተፈጻሚ እንደሚደረግ እና ህብረተሰቡ ለደህንነቱ ሲባል የሚወጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ተጠይቋል፡፡

ምንጭ፡ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በራያ ቆቦ ወረዳ አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!!

ግንቦት 23/2012 ዓ.ም ህግ በማስከበር ላይ የነበሩ የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ በነበሩት አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅመው መሰወራቸውን ይታወሳል።ሆኖም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ከነዋሪዎች ጋር ተቀናጅተው በመስራት በ01/10/2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል። ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የፀጥታ ኃይሉና የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ተመስገን ቢረሳው ምስጋና አቅርበዋል። መረጃውን ያደረሰን ከሰሜን ወሎ ፖሊስ መምሪያ ኮማንደር ሲሳይ ሽፈራውን ጠቅሶ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑትን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለመሸለም ያሳለፈው ውሳኔ ትክክለኛነት ላይ ዛሬም ፅኑ እምነት እንዳለው ገለፀ።

ኮሚቴው አንዳንድ አካላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የሰጠውን የኖቤል የሰላም ሽልማት “ለመሻር ዳግም እያጤነ ነው” ሲሉ ላናፈሱት ወሬ “ማረጋገጫዬን እሰጣለሁ በፊትም ሆነ አሁን ሽልማቱ መሰጠቱን ዳግም ለማጤን አላሰብኩም ወደፊትም ለማጤን ፍላጎት የለኝም” ብሏል።ዛሬ በይፋ ባወጣው ደብዳቤ ይህ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ሽልማት ከተበረከተ በኋላ መሻርን ፈፅሞ እንደማይፈቅድ አስታውቋል።የኖቤል ሽልማት መሰጠት ከተጀመረ ከአሮፓውያኑ 1901 ጀምሮም የአንድም ተሸላሚ ሽልማት አለመሻሩንም ነው ያመለከተው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ላቦራቶሪ ሥራ አስጀምሯል።በሁለት የመመርመሪያ ማሽኖች በተጀመረው ምርመራ እያንዳንዳቸው በአንዴ የ96 ሰዎች ውጤት የመስጠት አቅም አላቸው ተብሏል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
130 ኢትዮጵያውያን ከኩዌት ተመለሱ

130 ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ከኩዌት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፈያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባውን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች እና ሌሎች የመንግስት ተወካዮች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከኩዌት የተመለሱት ኢትዮጵያውያኑ በተዘገጀው የለይቶ ማቆያ ቦታ ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ቤተሰቦቸቸው የሚቀላቀሉ ይሆናል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 190 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4599 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2336 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 32 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 5 ሰዎች ሁኔታ

➡️በጤና ተቋም የነበሩ የ85 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በህክምና ላይ የነበረ የ42 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት የ40 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባት የ32 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

➡️ በህክምና ላይ የነበረ የ40 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 32 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 190 ሰዎች ሲሆኑ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(135) ሴት(55) ናቸው!

➡️ዕድሜያቸው ከ1-89 አመት የሆኑ

➡️ተጨማሪ 18 ሰዎች (11 ከአዲስ አበባ፣5 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሌ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 379 ነው።

➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(153)፣ ከኦሮሚያ ክልል(16)፣ከአማራ ክልል(10)፣ ከሀረሪ ክልል(3)፣ ከደቡብ ክልል(3)፣ ከሶማሌ ክልል(3) ፣ ከትግራይ ክልል(2)በኮሮና የተያዙ በድምር 190 ሰዎች ናቸው።

➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2336 ደርሷል።

➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 32 ነው።

➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 5 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 32 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በጤና ሚንስትር ሰኔ 2 በተገለጸው ሪፖርት መሰረት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጡት ሰዎች ውስጥ 3 በደ/ብ/ብ/ህ ክልል የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ በተደረገ ምርመራ የኮረና ቫይረስ የተገኘባቸው በመሆኑ በአጠቃላይ ይህንን ጨምሮ እስካሁን በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱ ተረጋግጧል።

-በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
የጠገዴ ወረዳ ፍርድ ቤት ሰው በማገት ወንጀል በተሰማራው ግለሰብ ላይ የ13 ዓመት ፅኑ እስራት መወሰኑ ተገለፀ ።

የወንጀለኛው ስም የሻንበል አለበት ፣ዕድሜ 30 ስራ ገበሬ የመኖሪያ አድራሻ ደግሞ ትግራይ ክልል ደቃ አባ ቀበሌ ሲሆን የጠገዴ ወረዳ ከሆነው ዳውጨና ቀበሌ ማይ አርቃይ ጎጥ ነዋሪ የሆነን አጣናው ዳጃውን የተባለ ተማሪ ሀምሌ 9/2007 ዓ/ም ከጥዋቱ 3 ሰዓት አካባቢ ከእርሻ ቦታ ሳለ በማስፈራራት አስሮ ወስዶ 46 ሽ ብር ተቀብሏል።የጠገዴ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ወንጀል የፈፀመውን ግለሰብ ሲከታተል ቆይቶ መጋቢት 1/2012 ዓ/ም ከትግራይ ክልል ከተማንጉስ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል ።የጠገዴ ወረዳ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍልም ምርመራውን ሲያጣራ ቆይቶ ለጠገዴ ወረዳ ፍርድ ቤት ክሱን ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግንቦት 27/2012 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ወንጀለኛው በፈፀመው የሰው መጥለፍ ወንጀል የ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ አድርጓል ።

ምንጭ: የጠገዴ ወረዳ መ/ኮ
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ በ 24 ሰዓታት ውስጥ አንድ መቶ ሃምሳ ሶስት (153) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፤የ5 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል።

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ ሶስት (153) ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ስምንት (1778) ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በ ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ የአምስት (5) ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በክፍለ ከተማ፦
አዲስ ከተማ 12፤
ልደታ 0፤
ጉለሌ 11፤
ኮልፌ ቀራንዮ 6፤
ቦሌ 73፤
አራዳ 13፤
የካ 12፤
ንፋስ ስልክ ላፍቶ 9፤
አቃቂ ቃሊቲ 14፤
ቂርቆስ 3 መሆኑን የከተማው ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በትላንትናው እለት አስራ አንድ (11) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ዳግም ተሾሙ

አል ዐይን አማርኛ እንደዘገበው ከሆነ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሃገራት በአምባሳደርነት ያገለገሉት ዲና ሙፍቲ የኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙዋል፡፡አምባሳደር ዲና በቅርቡ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ከተጠሩት 13 አምባሳደሮች መካከል አንዱ ሲሆኑ እስከተጠሩበት ጊዜ ድረስ በግብጽ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከአሁን ቀደምም ሚኒስቴሩን በቃል አቀባይነት ማገልገላቸው የሚታወስ ነው።

Via All ain/Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa