YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤትሰቦች፣ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!

በአሉን ስታከብሩ የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን ባለመዘንጋት ይሁን!

መልካም የፋሲካ በዓል ይሆንልዎ!!!

Hawalle mootichinke kao qaangeemmo ayyaanira keerunni iillishinke!!!

ርሑስ በዓል ፋሲካ ይግበረልና ይግበረልኹም!!!

Ayyaana hiikaa milkii isiniif haa ta'u!!!


@YeneTube
#Drliatadesse መልክት

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በአለማችን እንዲሁም በሃገራችን በተጋረጠው ወረርሽኝ ምክንያት ይህንን በዓል እንደወትሮው ተሰባስበንና በጋራ ማዕድ ተቋድሰን የምናከብረው ሳይሆን እራሳችንን እና ቤተሰባችንን በጤና ለመጠበቅ ሲባል በየቤታችን ሆነን የምናሳልፈው ነው። ይሄን ፈታኝ ጊዜ በጋራ ተጠንቅቀን በማለፍ ቀጣዩን እንደወትሮው እንደምናከብር እምነቴ ነው።

እራሳችንን፣ ቤተሰባችንን እንዲሁም ማህበረሰባችንን የመጠበቅ ሃላፊነት የሁላችንም ነው።

መልካም የትንሳኤ በዓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኮቪድ-19 ህመምተኞች ህክምና መስጫ በሚሌኒየም አዳራሽ የተዘጋጀውን ማዕከል ጎበኙ።

1 ሺ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን ይይዛል የተባለው ማዕከሉ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ህክምና የሚያገኙበት ይሆናል ነው የተባለው።

@Yenetube @Fikerassefa
በጋሞ ዞን በዚህ ሳምንት ውስጥ ባጋጠሙ የአፈር መናድ አደጋዎች የ8 ሰው ህይወት ማለፉን የጋሞ ዞን አስተዳደር የተሰማውን ታላቅ ሀዘን ገልጿል።

ትናንት ምሽት በጋሞ ዞን ገረሴ ወረዳ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ናዳ 5 የቤተሰብ አባላት ህይወት አልፏል፡፡

በተመሳሳይ ቀን በናዳ ምክንያት በአርባምንጭ ዙሪያም የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

በጨንቻ ዙሪያ ወረዳም ሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ናዳ የሁለት ሰው ህይወት አልፏል።

የዞኑ መንግሥት ለተጎጂ ወዳጅ ዘመዶችም መጽናናትን እየተመኘ የዝናቡ ሁኔታ ተጠናክሮ ስለሚቀጥል በአካባቢው የሚገኘው ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በለይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የዞኑ አስተዳደር አሳስቧል።

ናዳ ባስከተለው ጉዳት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም ሰብአዊ ድጋፍ የመስጠቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከዞኑ የመንግሥት ኮምኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 108 ደርሷል። ባለፈው 24 ሰዓት ውስጥ ከተወሰዱ 667 ናሙናዎች ሶስቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 16 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የታማሚዎቹ ሁኔታ:

ሶስቱም ኢትዮጵያውያን እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሲሆኑ

➡️ከአሜሪካ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች፣ ዕድሜ 62

➡️የጉዞ ታሪክ የሌላት፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ካላት በመጣራት ላይ ነው ተብሏል፣ ዕድሜ 52

➡️ከሳውዲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ፣ ዕድሜ 19

@YeneTube @FikerAssefa
ዩኤኢ ተጨማሪ 479 ሰዎች በኮሮና መያዛቸውን አስታወቀች

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጤና ሚኒስቴር በ24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረጉ 23 ሺ ምርመራዎች መካከል 479 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው አስታወቀ፡፡ የተጠቂዎች ቁጥር ወደ 7ሺ ከፍ ብሏል።

Via:- Al ain
@YeneTube @Fikerassefa
ሆቴሎች ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የባንክ ብድር ክፍያ በአንድ ዓመት እንዲራዘምላቸው እየተጠባበቁ ነው!

ሆቴሎች ሠራተኞቻቸውን እንዳያሰናብቱ ቢያንስ እስከ 6 ወራት ደመወዝ እየከፈሉ እንዲያቆዩ፣ መንግሥት በበኩሉ የታክስ ዕፎይታን ጨምሮ የባንክ ዕዳ የክፍያ ጊዜ ማራዘሚያና ሌሎች የድጋፍ ዕርምጃዎችን እያጤነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ምንጭ: ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገር አቋራጭ ስምሪት መስመሮች እና በአውቶቡሶች መውጫ ሰዓት ላይ ሽግሽግ ተደረገ!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማስፈጸም በወጣው የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚወጡ የሀገር አቋራጭ ስምሪት መስመሮች እና የአውቶቡሶች መውጫ ሰዓት ላይ ለውጥ መደረጉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀደም በየዕለቱ ስምሪት ይሰጥባቸው የነበሩ በአማካኝ 232 ልዩ ልዩ የሀገር አቋራጭ መስመሮችን በ60 በመቶ በመቀነስ በየዕለቱ በአማካኝ እስከ 82 መስመሮች ብቻ እንዲወጡ የሚደረግ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም አብዛኛዎቹ ተሸከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ከተርሚናሎች ይወጡ እንደነበረ ሚኒስቴሩ አስታውሶ ከዚህ በኋላ ግን ለተሻለ አፈፃፀም ያመች ዘንድ አውቶቡሶቹ በአራት ተከፍለው በተለያየ ሰዓት እንዲወጡ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል፡፡በዚሁ መሰረት በየዕለቱ 40 ከመቶ የሚሆኑት ተሸከርካሪዎች ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ላይ፤ 30 በመቶ የሚሆኑት ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ፤ 20 በመቶ የሚሆኑት ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ እና 10 በመቶ የሚሆኑት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ከሀገር አቋራጭ አውቶቡስ ተርሚናሎች እንደሚወጡ ተገልጿል፡፡

የመስመሮችን ብዛትና መነሻ ሰዓት ያካተተው እና ከላይ ተያይዞ የቀረበው የአገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ሳምንታዊ ዝርዝር ፕሮግራም ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከፕሮግራሙ ውጪ የማይስተናገዱ መሆኑን ገልጿል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!

➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

➡️21,317 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

➡️1080 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

➡️5203 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
📌ማስታወሻ

ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በተመለከተ;

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት የቤት ተሽከርካሪዎች (ኮድ-2) ፈረቃ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መተግበር እንደሚጀመር መነገሩ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ሲሆን ፥ የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ደግሞ መንቀሳቀስ የሚችሉት ማክሰኞ፣ ሀሙስ እና ቅዳሜ ብቻ ነው።

እሁድ እለት ደግሞ ሁሉም ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀስ ተፈቅዶላቸዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ከስራቸዉ ፀባይ አንፃር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፣ በደንቡ ወይም በአፈፃፀም መመሪያዉ የተገለፁት ጉዳዮች ላይ በቀጥታ የሚሳተፋ ሰዎች ከባለስልጣኑ በሚሰጣቸዉ ልዩ የይለፍ ፈቃድ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል።

Via:- Tsefay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa
በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የሰባት ወጣቶች ህይወት አለፈ!

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ዲቢቢሳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በዮሃንስ ቤተክርስቲያን ለጊዜው በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ሰባት ወጣቶች ሞተው መገኘታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ እንደገለጹት በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ሞተው ከተገኙት ሁሉም እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ሲሆኑ ከሟቾቹ መካከል አንዷ ሴት ናት።ትላንት ከሎሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ሟቾቹ በተገኙበት ወቅት የመብራት አገልግሎት የተቋረጠ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጀነሬተር እንደተለኮሰ ገልጸው አደጋው ከጄኔሬተሩ ጭስ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ እየተጣራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ከአደጋው ጋር በተያያዘ በአካባቢው 11 ግለሰቦች ተጠርጥረው መያዛቸውንና የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።የሟቾቹ አስከሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል መላኩን የገለጹት ኃላፊው በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ሁሉም ቤተ ዕምነቶች ዝግ መሆናቸውንና አማኞችም በቤታቸው አምልኮ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።ክስተቱ እንዴት እንደተፈጠረና ወጣቶቹ እንዴት ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሊገቡ እንደቻሉ እያጣራን ነው ያሉት ኮማንደሩ ጉዳዩን የሚያጣራ ግብረሃይል ተቋቁሞ የማጣራት ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ሁሉም ሰው ርቀቱን ጠብቆ በዓሉን ማክበር አንደሚገባው ያስታወቁት ኮማንደር አስቻለው በቤተክርስቲያኑ የታየው ነገር አስደንጋጭና ትምህርት ሊወሰድበት አንደሚገባም አሳስበዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa