YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የታማሚዎቹ ሁኔታ:

8 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ነው።

➡️ የጅማ ነዋሪ፣ የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ከሊባኖስ የመጣች፣ ዕድሜ 20

➡️ሁለት ሴትና(ዕድሜ 40ና 42) አንድ ወንድ(ዕድሜ 13) የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ በበሽታው ከትተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።

➡️ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ የቆዩ፣ ዕድሜ 73፣ ፆታ ወንድ

➡️ከጅቡቲ የመጡና በለይቶ ማቆያ ያሉ 3 የድሬዳዋ ነዋሪዎች፣ እድሜ 19፣ 20ና 19፣ ሶስቱም ወንዶች ናቸው ።

➡️የ38 አመት ኢኳቶሪያል ጊኒያዊ ከእንግሊዝ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ

@YeneTube @FikerAssefa
ሚሊኒዬም አዳራሽ ለኮሮና ቫይረስ ህክምና ስፍራ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።የማዘጋጀቱ ስራ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እየተከናወነ ሲሆን፣ 1000 አልጋዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ ይገኛል፣ ስራው በያዝነው የፈረኝጆች ወር መጨረሻ ተጠናቆ አገልግሎት ይጀምራል።

@YeneTube @FikerAssefa
አንድ ተጨማሪ ሰው አገግሟል እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ

- ዛሬ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች :- 9

- በለይቶ ማቆያ ህክምና ያሉ ታማሚዎች :- 85

- ፅኑ ህሙማን :- 1

- ከበሽታው ያገገሙ :- 16

- በሽታው ህይወታቸውን ያለፈ ድምር :- 3


@Yenetube @Fikerassefa
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የለይቶ ማቆያን ካምፓስ ጎበኙ!

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከተለየዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ሰዎች የለይቶ ማቆያ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስን ጎበኙ።ካምፓሱ በዋናነት ከውጭ አገሮች መጥተው ለአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ በተዘጋጁ ሆቴሎች ለመቆየት አቅም ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወሳል።

የሚኒስትሯ ጉብኝት በዋናነት በካምፓሱ ውስጥ የሚከናወኑ አገልግሎት አሰጣጦች ምን እንደሚመስሉ ለመገምገም መሆኑ ነው የተገለጸው። በጉብኝታቸውም ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና በጉዳዩ ከሚሰሩ ሌሎች አካላት ጋር ተወያይተዋል።አሁን ላይ በካምፓሱ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 321 ሰዎች ያሉ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 49ኙ ሴቶች ናቸው።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ደብረብርሃን የቀንድ ከብት ገበያ !

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑ እንዲሁም ስለ ኮሮናም ግድ የለቸው በከፍተኛ ጥግግት ግብይት እየተደረገ ይገኛል።

@Yenetube @FikerAssefa
አዲስ አበባ አያት አከባቢ ገበያው ደርቷል 😢 አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በትክክል ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑ ተመልክተናል።
ሀዋሳ በተለምዶ አላሙራ ተብሎ የሚጠራ ቦታ የዶሮ ገበያ ⬆️

- መ ራ ራ ቅ ለራስ ጤንነት ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
ራይድ 50,000 የሰርጂካል ጭንብሎችን ለኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አስረክቧል 

የኮሮናቫረይስ ህክምና ለማገዝ በማሰብ የራይድ ትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ለኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበር 50,000 የሰርጂካል ጨንብሎችን ዛሬ አስረክባለች።
የሰርጂካል ጭንብሎቹ ዋጋ 1.4 ሚልየን ብር ይገመታል ።

የማህበሩ የቦርድ አባል የሆነችው ዶ/ር መስከረም አለቃ በርክክቡ ወቅት አንዳለችው ” የዚህ አይነቱ ድጋፍ የህክምና ባለሙያዎች የህክምና ስራቸውን በጥንቀቄ አንዲሰሩ እና ለበሽታው አንዳይጋለጡ ያግዛል።የጤና ባለሙያዎች ከሚቸገሩበት አንዱ የሰርጂካል ጭንብሎ ማግኘት ነው ይሄን ተረድተው ሌሎችም ድርጅቶችም ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበቸዋል “ብላለች ።

ወይዘሮት ሳምራዊት ፍቅሩ በበኩሏ “ህይወታቸውንና ጊዜያቸውን አየሰው የእኛን ህይወት ለማትረፍ ቀድመው ለሚረዱን ሀኪሞች የዚህ አይነት ድጋፍ ማድረግ ሞራላዊ ግዴታ አለብን ራይድም የዚህ አይነቱን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል” ብላለች።

Via:- fidelpost.com
@Yenetube @Fikerassefa
አትሌት መሰረት ደፋር 500 ሰዎችን የሚያስተናግድ ሕንጻ ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል ፈቀደች!

አትሌት መሰረት ደፋር መገናኛ አካባቢ እያስገነባች ያለውን ባለ 12 ወለል ሕንጻ ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል ለለይቶ ማቆያነት እንዲያገለግል ማስረከቧን አስታወቀች።ሕንጻ የተረከቡት የኮቪድ-19 መከላከል የለይቶ ማቆያ የሚኒስትሮች ኮሚቴ አባላትም ሕንጻው በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ አመልክተዋል። ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኛውን የኮቪድ-19 ወርርሽኝ ለመቋቋም ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም አትሌቷ በዚሁ ጊዜ ተናግራለች።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2.26 ሚሊዮን በላይ ደርሷል

በዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስካሁን ባለው መረጃ 2 ሚሊዮን 269 ሺህ 143 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ አውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

በአውሮፓ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስካሁን 1 ሚሊዮን 115 ሺህ 555 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 97 ሺህ 985 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በዓለም በኮሮና ከተያዙ 2 ሚሊዮን 269 ሺህ 143 ሰዎች ውስጥ እስካሁን 582, 195 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ 155 ሺህ 190 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት በፍጥነት እየተስፋፋባት በምትገኘው አሜሪካ እስካሁን 710 ሺህ 272 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከእነዚህ መካከል 37,175 ሰዎች ሕይወታቸው አልፋል። 63 ሺህ 510 ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

በአፍሪካ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 724 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሕይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 30 ደርሷል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ደግሞ 5 ሺህ 47 ደርሰዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 105 መድረሳቸውን እና ከእነዚህ ውስጥ 16 ሰዎች ማገገማቸውን፣ ሦስት ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።

VIA:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ጣሊያን በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የባሰ የኢኮኖሚ ውድቀት አጋጥሟታል:: ይህ ሁኔታ ጣሊያን ከአውሮፓ ህብረት እንድትወጣ ለሚፈልጉ የቀኝ አክራሪዎች ጉልበት እንደሚሆናቸው ተንታኞች ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኤኤፍፒ

@Yenetube @FikerAssefa
ኬንያ ትልቁን የገበያ ቦታ ለመዝጋት ወሰነች

ኢስሊ በመባል የሚታወቀውና በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚገኘው ትልቁ የግብይት ቦታ የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት በሚል ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጋ ተወሰነ።

በገበያ ቦታው ያሉ ነጋዴዎች የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ያወጣቸውን አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ሳኒታይዘር መጠቀምና ጭንብል ማድረግን የመሳሰሉ በሽታውን የመከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ነው ለመዘጋት የበቃው።

- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የናይጄሪያው ፕሬዝዳነት የቅርብ ረዳት በኮቪድ-19 ምክንያት ሞቱ

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሐሪ የቅርብ ረዳት የነበሩት አባ ኪያሪ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ በኋላ መሞታቸው ተነገረ።

ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ "የኪያሪ ህልፈትን ለሕዝቡ ሲያሳውቅ በጥልቅ ሐዘን" እንደሆነ ጠቅሷል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ማገገሚያ ሊሆን ነው፡፡

Via:- ELU
@YeneTube @FikerAssefa
በኒውዮርክ ዛሬ ኮሮና ቫይረስ ያደረሰው ጉዳት ከሰሞኑ አንፃር ቀንሷል። በግዛቷ በ24 ሰዓት ውስጥ 540 ሰዎች መሞታቸውን ገዥው አንድሬው ኮሞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከኮሮናቫይረስ የዳኑ ሰዎች ቁጥር ከ570 ሺህ በላይ ደረሰ!

በኮሮናቫይረስ እስካሁን ከተያዙት ሰዎች መካካል ከ570 ሺህ የሚበልጡት ከበሽታው መዳናቸውን ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰበ መረጃ አመለከተ።በዚህም መሰረት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ከበሽታው የዳነባት አገር ጀርመን ስትሆን 77 ሺህ 578 ሰዎች ማገገማቸው ተዘግቧል።በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ደግሞ በሽታው የተቀሰባት ቻይና ስትሆን 74 ሺህ 797 ሰዎች ከኮሮናቫይረስ አገግመዋል።ቻይና በሽታውን መስፋፋት በመቆጣጠር በኩል ስኬታማ እንደሆነች ይነግርላታል። በሦስተኛ ደረጃ በርካታ ሰዎች ከወረርሽኙ ያገገሙባት አገር አውሮፓዊቷ ስፔን ስትሆን 59 ሺህ 672 ሰዎች ድነዋል።ስፔን አውሮፓ ውስጥ በበሽታው ክፉኛ ከተጠቁት አገራት መካከል አንዷ ናት።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ በኮሮና ወረርሽኝ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ1000 ማለፉን የአፍሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳለው ወረርሽኙ አፍሪካ ካላት 54 ሃገራት 52ቱን አዳርሷል።ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስም 19,800 ሰዎች በኮሮና ተሕዋሲ ተይዘዋል።ከሟቾቹ መካከል ትናንት ዓርብ ማረፋቸው የተሰማው የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ የቅርብ አማካሪያቸው እና የጽህፈት ቤታቸው ኃላፊ እንደሚገኙበት አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። የባለስልጣኑ ሞት በአፍሪካ ወረርሽኙ ከፍተኛ ባለስልጣን ከገደላቸው ባለስልጣናት መካከል የናይጄሪያው ተጠቃሽ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በቡርኪና ፋሶ ቀደም ሲል የአሜሪካውን አምባሳደር ጨምሮ በርካታ ሚንስትሮች እና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት በተህዋሲው መያዛቸው ተገልጾ ነበር።የዓለም ጤና ድርጅት ትናንት ዓርብ ባወጣው ሪፖርቱ እንዳመለከተው በአፍሪካ በተሕዋሲው የሚያዙ ሰዎች 51 በመቶ ሲጨምር በዚሁ ጠንቅ የሚሞቱ ሰዎች ደግሞ 60 በመቶ አሻቅቧል። የአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል እንዳለው ከሆነ ደግሞ በመመርመሪያ ቁሳቁስ እጥረት እንጂ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች ቁጥር እጅጉን ሊጨምር እንደሚችል ነው።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa