YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በአዲስ መልክ ተዋቀረ፡፡

የፕሬዝዳንቱ ፅ/ቤት በአዲስ መልክ ማዋቀሩን ተከትሎ የፕሬዚዳንቱ አማካሪዎች ቁጥር ወደ 9 መቀነሱ ተሰምቷል፡፡በአዲሱ አወቃቅር የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ አቶ መሐመድ አሚን አማካሪዎቹን ፣ የፕሮቶኮሉን ቡድን እና የፕሬዚዳንቱን ደህንነት የሚጠብቀውን ቡድን የሚያስተባበር ሲሆን በተጨማሪም አጠቃላይ የቢሮ ስራዎችን የሚመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ፡-

1. አቶ ጀማል ዲሪዬ ካሊፍ- የሕግ እና የሰብአዊ መብት አማካሪ
2. አቶ አብዱላሂ ሁሴን - የሚዲያ አማካሪ
3. አቶ ባዲል ሂስ ሞሀመድ - የደህንነት አማካሪ
4. አቶ አብዲ አሊ ጃማ- የኢኮኖሚ አማካሪ
5. አቶ አህመድ አብዲ ጉርሀን - የነዳጅ እና ጋዝ ጉዳዮች አማካሪ
6. አቶ ዩሱፍ ሀሰን ጋቢቢ- የአቅም ግንባታ አማካሪ
7. ዶ/ር ታጁዲን ሞሀመድ የሰብአዊ እርዳታና የልማት ትብብር አማካሪ
8. አቶ መሀመድ ዳኢብ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ በመሆን መሾማቸው ታውቋል፡፡

Via Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከቻይና ጋር በኮቪዲ19 ዙርያ የተለዋወጡትን መረጃዋች እንዲያቀርቡ ተጠየቁ

ከሶስት ቀን በፊት የተፃፈውና የ20 የአሜሪካን ኮንግረስ አባላት ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ አንደሚያሳየው የአለም ጤና ድርጅት ሀላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከባለፈው ነሀሴ ጀምሮ ኮቪዲ19 ጨምሮ ህብረተሰብ ጤናን በተመለከተ ከቻይና ጋር የተለዋወጡትን ደብዳቤዎችና ሪፓርቶች ሌሎችንም መረጃዎች አንዲያቀርቡ የኮንግረስ አባላቱ ጠይቀዋል ።
ከታይዋን ጋርም በቫይረሱ ዙርያ የተፃፃፉትን ሪፖርቶቹንና ደብዳቤዎችንም እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ከተጠየቁት ሪፖርቶች መሀል በቻይና ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ የሞቱ ፣የተጠቁ ሰዎችን የሚያሳይ ሪፖርት ይገኝበታል።
የኮንግረስ አባላቱ በደብዳቤው እንዳሰፈሩት ቻይና በሽታውን አቅላ ስትመለከት የአለም ጤና ድርጅትም ተገቢውን ትኩርት ሳይሰጥ ቫይረሱ በአለም ተሰራጭቶ ብዙ ሰው ሊገል ችሏል ብለዋል።

በተጨማሪም የአለም ጤና ድርጅት በቻይና ሪፖርት ተንተርሶ ቫይረሱ ከሰው ሰው መተላለፉን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አላገኘሁም በማለት በጥር መጀመርያ ወር ላይ በቲዊተር ያሰፈረ ሲሆን “ወረርሽኝ” ብሎ የተናገረውም በ19 ሀገራት የ 1,000 ሰው ሞት እና 10,000 ሰው በቫይረሱ ከተጠቃ በኋላ ነው ብሎ ሲገልፅ ይሄም ቫይረሱ “ወረርሽኝ “አስቀድሞ እንዳይባል የቻይና ተፅእኖ ነበረበት ብሏል። በዚህ ወቅትም የቻይናን ሪፖርት በማመን ድርጅቱ ” ቻይና በሽታውን ለመቆጣጠር አስደናቂ ስራ ሰርታለች ” በማለት አሞካሽቷል ።

ከዚህ በተጨማሪም ታይዋን አስቀድማ ቫይረሱ ከሰው ሰው ይተላለፋል የሚል ሪፖርት ስታደርግ የአለም ጤና ደርጅት ችላ ብሏል ሲል ደብዳቤው ወንጅሏል።

ዶ/ር ቴድሮስ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰጡት ምላሽ ” ኮሮናን ፖለቲካ ከማድረግ ይልቅ ተገቢውን ጥንቃቄ እና የህክምና ስራ መስራት ለሁላችንም ይበጃል ” ሲሉ ተደምጠዋል።

Via:- @tesfaget55

@Yenetube @Fikerassefa
አራት መቶ የሚሆኑ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) በግዢ ሂደት ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ከያዛቸው ሰዎች 20 በመቶ የሚሆኑት ኦክስጅን አምስት በመቶ የሚሆኑት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጋቸው መረጃዎች እንደሚያመላከቱ ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በደቡብ አፍሪካ ኮሮና ቫይረስ ኬዝ 2173 ደርሷል እንዲሁም ዛሬ በ24 ሰዐት ውስጥ 145 ኬዝ ሪፓርት ተደርጓል።
@Yenetube @fikerassefa
⬆️
የቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የቅንጅት አመራር የነበሩት አቶ ተመስገን ዘውዴ ዛሬ አርፈዋል!

ከቤተሰቦቻቸው የደረሰኝ መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ተመስገን ለበርካታ ግዜ አልጋ ላይ ሆነው ህክምና ሲከታተሉ ነበር።

ነፍስ ይማር!

ይህ ከታች ያለው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የዛሬ አመት ያወጣው ግለ-ታሪካቸው ነው።

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልላዊ መንግስት ሳውላ ዞን በቡልቂ በሚባል አካባቢ ከዛሬ 70 ዓመት በፊት ተወለዱ። እስከ ስምንተኛ ክፍል እዛው ሳውላ ከተማ የተማሩ ሲሆን ስምንተኛ ክፍል ከጨረሱ በኋላ ግን ወደ ንግድ ስራ ትምህርት ቤት መጥተው በፅህፈት ስራ አራት አመት ሰለጠኑ። ትምህርት ቤቱ እዛው እንዲሰሩ በአስተማሪነት ስለቀጠራቸው አራት አመት አገልግለዋል። በቆይታቸውም ትምህርት ቤቱ በገባላቸው ቃል መሰረት ወደ ህንድ አገር ለመሄድ የትምህርት እድል በመጠባበቅ ላይ ሳሉ ወደ አሜሪካ የመሄድ እድሉን ያገኛሉ። በዳላስ አካባቢ በአንድ የንግድ ኮሌጅ ውስጥ በንግድ ስራ አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ማግኘት ችለዋል። ከዚያ በኋላም ለ22 ዓመት በአሜሪካ አገር በስራ እና በትዳር ልጅ ወልደው ኖረዋል።

ይሁንና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵውያን ወደ አገራቸው መጥተው እንዲሰሩ ባቀረቡት ጥሪ ያለምንም ማቅማማት ይቀበላሉ። ወደ አገራቸው ተመልሰው ለመስራት ጉጉት ያድርባቸውና ስራቸውንና የሞቀ ትዳራቸውን እዛው አሜሪካ ጥለው እትብታቸው ወደ ተቀበረባት እናት አገራቸው ተመለሱ። ዳሩ ግን ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ እርሳቸውም እንደጠበቁት ለመስራት የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳር ሆኖ አላገኙትም።

ይህ ሁኔታም አገራቸውን ጥለው ከመሄድ ይልቅ እዚሁ ሆነው ህዝብን ከጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ ይወስናሉ። በዚያ መሰረትም በ1997ዓ.ም ቅንጅት ውስጥ ገብተው በመወዳደር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው ለአምስት አመት አገልግለዋል።

በምክር ቤት በነበራቸው ቆይታም በርካታ ህዝብ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለሰን በድፍረት በመሞገትና በመከራከር ያውቃቸዋል። ለአገራቸው ባላቸው ልዩ ፍቅር የተነሳ አሜሪካዊቷን ሚስታቸውንና ልጃቸውን ትተው ቢመጡም ከሁለተኛዋ ኢትዮጵያዊት ሚስታቸው ሁለት ልጆች ወልደው ከብረዋል።

Via: - አዲስ ዘመን (EPA) / Eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa
ፋና ቴሌቪዥን ለዲያቆን ዳንኤል ጥያቄ መልስ ሰቷል ማለት ይቻላል። ከትላንት በስትያ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፋና ለምን የፀሎት ሰዓቱን ገፋ በማለት ጠይቆ ነበር ከመሽ ፋና ቴሌቭዥን ምላሽ ሰቷል።

#Fanatelevision

በትናንትናው ምሽት በነበረን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን መደበኛ ፕሮግራም በኛ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በተፈጠረ የፕሮግራም መገፋፋት ዘግይተን በመጀመራችን ከፍ ያለ ይቅርታ እንጠይቃለን።

@Yenetube @Fikerassefa
ደቡብ ኮርያ ለአሜሪካ 600,000 ኮሮና ቫይረስ ለመመርመር የሚያስችሉ መሳሪያዎች ልካለች።
@YeneTube @Fikerassefa
ከኤኮ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮቪዲ 19 ነፃ ተብለው የሚወጡ ሰዎች መገለል አየደረሰባቸው ነው።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ኪዳኔ ሰለሞን በስልክ ከነገሩኝ ;

" ኮሮናቫይረስ አለባቸው ከተባሉ ታማሚዎች ጋር ንክኪ ነበራቸው ብለን ያሰብናቸውን እዚህ መለያ ክፍል አምጥተን እንመረምራለን ።ከሌለባቸው ወደ ቤት እንሰዳቸዋለን ።አየደረሰን ባለው ሪፖርት አዚህ ብቻ ተመርምረው ስለሄዱ በቤታቸውና በአካባቢያቸው መገለል እየደረሰባቸው ነው።ይሄ አግባብ አይደለም ።የዚህ አይነቱ ነገር በሰው ልጅ ላይ መጥፎ የስነልቦና ጉዳት ያስከትላል። ሊታረም ይገባል" ብለውኛል።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
ከኤኮ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮቪዲ 19 ነፃ ተብለው የሚወጡ ሰዎች መገለል አየደረሰባቸው ነው።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ኪዳኔ ሰለሞን በስልክ ከነገሩኝ ;

"ኮሮናቫይረስ አለባቸው ከተባሉ ታማሚዎች ጋር ንክኪ ነበራቸው ብለን ያሰብናቸውን እዚህ መለያ ክፍል አምጥተን እንመረምራለን። ከሌለባቸው ወደ ቤት እንሰዳቸዋለን።

እየደረሰን ባለው ሪፖርት አዚህ ብቻ ተመርምረው ስለሄዱ በቤታቸውና በአካባቢያቸው መገለል እየደረሰባቸው ነው። ይሄ አግባብ አይደለም። የዚህ አይነቱ ነገር በሰው ልጅ ላይ መጥፎ የስነልቦና ጉዳት ያስከትላል። ሊታረም ይገባል" ብለውኛል ሲል ተስፋዬ ጌትነት በገፁ አስፍሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስን በማስመልከት ከጅቡቲ በብዛት እንዲወጡ እየተደረጉ ካሉ ዜጎች ውስጥ የተዋሰኑ ትናንት ምሽት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል!

ድሬዳዋ ውስጥ ጉዳዩን ከሚያውቁ ሰዎች እንዲሁም ከሁለት ስደት ተመላሾች የደረሰኝ መረጃ እንደሚያመለክተው እነዚህ ዜጎች ወደመጡበት ስፍራ ሊመለሱ ቢፈልጉም አንዳንድ ክልሎች "ዝግጁ አይደለንም" በሚል ሊቀበሉ አልቻሉም ወይም አልፈለጉም።

ፎቶው ዜጎቹን ጭነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ምሽት ያመጡ አውቶቡሶችን ያሳያል።

Via:- Eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa
የድሬዳዋ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ

ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ስድስት ሰዎች ተጠርጥረው ናሙናቸው የተላከ ሲሆን ሁሉም ከቫይረሱ ነጻ እንደሆኑ ተረጋግጧል ።

Via Dire Mass Media
@YeneTube @FikerAssefa
#Update

ሶማሌላንድ ተጨማሪ ሶስት ኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሪፓርት ተደርጓል ሁለቱ ሀርጌሳ ሲሆን እንዱ ባራማ ከተማ መሆናቸው የሱማሌላንድ ጤና ሚኒስትር አስታውቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር አለመደበቋን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡ ነገር ግን ቁጥሩ አሁን ያለው ብቻ ነው ብሎ በእርግጠኝነት መናገር እንደማይቻልም ገልጸዋል፡፡

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና ኮሮና ቫይረስ ድጋሚ ኬዝ እየተመዘገበ ነው። በ24 ሰዓት ውስጥ 108 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሪፓርት አድርጋለች።

@Yenetube @Fikerassefa
በአፍሪካ በቫይረሱ ሞቱ ሰዎች ቁጥር 747 ደረሰ

በ52 የአፍሪካ ሀገራት መገኘቱ የተረጋገጠው ኮሮና ቫይረስ እስካሁን 747 ሰዎችን ለሞት መዳረጉን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል አስታውቋል።

Via:- Africa CDC
@Yenetube @Fikerassefa
የኢፌዲሪ አየር ኃይል 17 የአል-ሻባብ የፈንጅ ቡድን አባላትን መደምሰሱን አስታወቀ

አባላቱ የተደመሡት ከዶሎ የተለያዩ ወታደራዊ ቁሣቁሶችን ጭኖ ወደ ባይደዋ በተንቀሣቀሠ የወገን ኮንቮይ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር አስበው የነበረ በመሆኑ ነው ተብሏል።

Via:- አል አይን
@Yenetube @FikerAssefa
ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ቁጥሯን ልትጨምር ነዉ!

ኬንያ በቀጣዮቹ 2 ወይም 3 ሳምንታት ዉስጥ 7000 ዜጎቿ ላይ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ልታደርግ አቅዳለች፡፡ ምርመራዉን ለማደረግ የሚያስችሉ መሳሪያዎችን «ሮች ዲያግኖቲክ» ከተባለ በዮርዳኖስ ሀገር ከሚገኝ የህክምና መሳሪያዎች አምራች ድርጅት ማግኘቷን ካፒታል ኤፍ ኤምን ጠቅሶ ኦል አፍሪካ አስነብቧል፡፡

Via Asham TV
@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ አፍሪካ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ለ600,000 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ እንዳቀደች የጤና ሚንስትሯ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዝዌሊ ምኪህዜ eNCA ለተባለው የሀገር ውስጥ የቴሌቭዥን ጣቢያ እንደተናገሩት በርከት ያሉ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ለመረከብ እየጠበቅን ነው ከዛም በሚቀጥሉት ሳምንታት ሰፋ ያለ ምርመራ እናካሂዳለን ብለዋል።ሀገሪቱ እስካሁን 80,000 ገደማ ለሚሆኑ ሰዎች ምርመራ አድርጋለች።

ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ጀመረ

የደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የኮሮናቫይረስ ምርመራ በይፋ ጀምሯል፡፡በቀን 96 ሰዎችን መመርመር የሚያስችል የላቦራቶሪ አገልግሎት መጀመሩን በማስመልከት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ኢኒስትቱዩቱ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa