#DrLia_Tadess
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙርያ እንደ ሀገር እየተደረገ ባለው ዝግጅት እና የምላሽ አሰጣጥ ሂደት እንዲሁም ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከጤና ባለሙያዎቻችን ጋር ለመነጋገር እሁድ ሚያዝያ 4, 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10-11 ሰአት በፌስቡክ የቀጥታ ውይይት አደርጋለሁ::
በቀጥታ ውይይቱ ላይ እንዲነሱ የምትፈልጏቸውን ሀሳቦች ከታች በሚገኘው የአስተያየት መስጫ ቦታ ላይ እንድታስቀምጡ እየጠየኩኝ ነገ እንድንገናኝ እጋብዛለሁ።
⬇️
https://t.co/t8y2XISb71
@YeneTube @Fikerassefa

የኢትዮዽያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱስ በነቀምቴ ከተማ አደባባዮችና መንገዶች የኮረና ወረርሽኝን በተመለከት ፀሎትና ትምህርት አካሄደች።
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያወጣው መግለጫ
⬇️⬇️
https://telegra.ph/PP-Amhara-Branch-press-release-04-11

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!
➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።
➡️13,145 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
➡️700 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።
➡️2171 ሰዎች አገግመዋል።
ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።
➡️13,145 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
➡️700 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።
➡️2171 ሰዎች አገግመዋል።
ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሞቱ ሰዎች ብዛት አሜሪካና ጣሊያን በቀዳሚነት የሚነሱ ሲሆን የየሀገራቱ ሪፖርት በሚወጣበት ጊዜ በደቂቃዎች ልዩነት በሟቾች ቁጥር እየተፈራረቁ እየመሩ ይገኛሉ ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት የተጣሉ ግዴታዎች ይፋ ሆነዋ
የኮሮናቫይረስ ቨወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈፀሚያ ደንብ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አጽድቋል።
በዚሁ ደንብ መሰረትም የተጣሉ ግዴታዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።
1. ማንኛውም ኮቪድ-19 እንዳለበት የተጠረጠረ ሰው ወይም ወደ ሀገር የሚገባ አለማቀፍ መንገደኛ ኳራንታይን የመደረግና የኮቪድ-19 ምርመራ የማድረግ ግዴታ አለበት፤
2. ወደ ሀገር የገባ አለማቀፍ መንገደኛ ኳራንታይን በሚደረግበት ጊዜ የራሱን ወጪ የመሸፈን ሀላፊነት ያለበት ሲሆን፣ መንገደኛው የመክፈል አቅም የሌለው ከሆነ መንግስት ለዚሁ አላማ ባዘጋጀው ቦታ እንዲቆይ ይደረጋል፣
3. በኮቪድ-19 መያዙ የተረጋገጠ ማንኛውም ሰው መንግስት በሚያዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ክፍል የመቆየት ግዴታ አለበት፤
4. በጉዞ ወቅት ኮቪድ-19 አለበት ተብሎ የሚጠረጠር መንገደኛ ሲኖር የማጓጓዣ አንቀሳቃሹ በአቅራቢያው ላለው ወይም ለሚያርፍበት የመግቢያና መውጫ ኬላ ሀላፊ ወይም የኮቪድ19 ምርመራ ለሚያደርግ ቡድን የማሳወቅ ሀላፊነት አለበት፤
5. የኮቪድ-19 ያለበት ወይም አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወይም ለፖሊስ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
6. የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ ግዴታ አለበት፤
7 በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 6 የተመለከተው የአፍና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ለዚሁ አላማ ተብሎ በፋብሪካ በተሰራ፣ በቤት ውስጥ ከተለያዩ ጨርቃጨርቆች በተዘጋጀ ወይም በማናቸውም አይነት ልብሶች ሊፈጸም ይችላል፡፡
8. ማንኛውም አገልግሎት የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን ማዘጋጀትና ተገልጋዮች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፣
9. ማናቸውም አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋማቱ የሚሄዱ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግ ሀላፊነት አለባቸው፤
10.የመንግስት የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና የግል የሚዲያ ተቋማት ኮቪድ-19ኝና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች፣ የዜና ትንተናዎች ወይም ፕሮግራሞች ሳይጋነኑ ወይም ሳይቃለሉ ተገቢው መረጃ ወደ ሕዝቡ የማድረስ እና አላግባብ የሆነ ድንጋጤና ሽብርን የማይፈጥሩ መሆን አለባቸው፣
11.ማንኛውም በፌዴራልም ሆነ በክልል የሚገኙ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት በተቋሙ ስር ለሚገኙ ሰራተኞች ስለቫይረሱ አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች ላይ ቢያንስ እጅ ለመታጠብ የሚያስችል ውሃና ሳሙና ማዘጋጀት ፣ በተቻለ መጠን ሌሎች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
12.ማንኛውም በፌዴራልም ሆነ በክልል የሚገኙ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት በተቋሙ ስር የሚገኙ ሰራተኞች በአንድ ክፍል ውስጥ፣ በአንድ መስሪያ ቦታ ወይም በአንድ ትራንስፖርት ውስጥ ተጨናንቀውና አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በማያስችል መልኩ እንዳይሰሩ ለማድረግ አስፈላጊውን ፈረቃ ማመቻቸት፤ ሰራተኞቹ ቤታቸው ሆነው የሚሰሩበትን ሁኔታ ወይም እረፍት በመውሰድ ስራ ቦታ እንዳይመጡ የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤
13.ማንኘውም የፌዴራልም ሆነ የክልል የመንግስት ተቋምና በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚተዳደሩ ሰራተኞችን የሚስተዳድር የግል ድርጅት ሰራተኞቹ ወደ ስራ ቦታ ለመሄድ ትራንስፖርት መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ በስራ ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤
14.ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ማረሚያ ቤት ተጠርጣሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤
15 ማንኛውም የቤት፣ የሆቴል፣ የአፓርታማ፣ የተሽከርካሪ፣ የአዳራሽ ወይም የማንኛውም ንብረት ባለቤት መንግስት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ ንብረቱን ለዚህ አላማ አገልግሎት ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል ሲወሰንና ሲጠየቅ ንብረቱን ለእለት ከእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ካልሆነ በሰተቀር ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት፤
16.ማንኛውም አምራች ወይም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት፣ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ አግለግሎት እንዲሰጥ፣ አገልግሎቱን እንዲያሰፋ፣ ምርት እንዲያመርት፣ የሚያመርተውን ምርት መጠን እንዲጨምር፣ አዲስ ምርት አይነት እንዲያመርት ወይም ምርቱን መንግስት በሚወስነው ተመጣጣኝ ዋጋ ለመንግስት፣ ለሾማቾች ወይም ለህብረት ስራ ማህበራት እንዲሸጥ በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ማድረግ አለበት።
17.ሆቴሎች ለደንበኞቻቸው አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ የእጅ መታጠቢያ ውሀና ሳሙና የማቅረብ ሀላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ የሆቴሉ ተጠቃሚዎችም እጃቸውን መታጠባቸውንና አስፈላጊውን ንፅህና አጠባበቅ ስርአት ተግባራዊ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ እንዲሁም ደንበኞች ከተጠቀሙ በኋላ የተገለገሉባቸውን ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮችና ሌሎች እቃዎች የማከም ግዴታ አለባቸው፣
18.ማንኛውም በስራ ላይ ያለ፣ ጡረታ የወጣ ወይም በትምህርት ላይ ያለ የጤና ወይም የሌላ ሙያ ባለቤት ወይም ማንኛውም ዜጋ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በመንግስት ጥሪ ሲደረግለት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
Via: -EPA
@Yenetube @Fikerassefa

በአሜሪካ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ20,000 በልጧል። ይህም አሜሪካን በቫይረሱ ብዙ ህይወት ያለፈባት ሀገር ያደርጋታል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ የምግብ ሸቀጦች ላይ የተጣለ እገዳ አለመኖሩን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተናግሯል!
አሁን ተከሰተ የተባለው ችግር መነሻ ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጉዳዮች ባለመሟላታቸው የተነሳ እንደሆነም ኤምባሲው ተናግሯል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጅቡቲ የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር ተነጋግሮ ችግሩ በአስቸካይ እንደሚፈታ ያረጋገጡ መሆኑን እና የወጪ ገቢ ምርቶች በተሳለጠ መልኩ እንዲከናወን እየተሰራ መሆኑንም ለማረጋገጥ በኤምባሲው የመረጃ መረብ ላይ ሰፍሯል፡፡
ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ሸቀጦችን አስመልክቶ አንዳንድ የሚድያ አካላት እያሰራጩ ያሉት የተሳሳተ መረጃ መስተካከል እንደሚገባው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማስገንዘቡን ተናግሯል። በሚድያዎቹም የጅቡቲ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ የምግብ ሸቆጦችን እንዳገደ ተደርጎ የተገለጸበት አግባብ ከእውነታ የራቀ መሆኑንና በጅቡቲ ነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ በኢትዪጵያ በኩል ተገዝቶ የተከማቸ ምንም ዓይነት የምግብ ሸቀጥ አለመኖሩን ኤምባሲው ተናግሯል።
የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት ጋር በተያያዘ በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር ላይ ያለውን አጠቃላይ የወጪና ገቢ ምርቶች እንቅስቃሴ የምግብ ሸቀጥንም ጨምሮ በበረታ መንገድ እንዲከናወን በጅቡቲ መንግስት በኩል ትብብር እየተደረገ መሆኑን ኤምባሲው መናገሩን ሸገር ከ ኤምባሲው ሰምቻለው ብሏል።
ምንጭ: ሸገር ኤፍ ኤም

ዩናይትድ ስቴት በ24 ሰዓት ውስጥ 31,079 ኮቪድ19 ኬዝ እና 1,845 ሞት ተመዝግቧል።
በዩናይትድ ስቴት በአጠቃላይ 533,475 ኮቪዲ19 ኬዝ ሲኖር እስከዛሬ 20,548 ሰዎች መተውባታል።
@Yenetube @Fikerassefa
በዩናይትድ ስቴት በአጠቃላይ 533,475 ኮቪዲ19 ኬዝ ሲኖር እስከዛሬ 20,548 ሰዎች መተውባታል።
@Yenetube @Fikerassefa
ኮሮና ቫይረስ ፓኪስታን :-
- 254 አዲስ ኬዝ በ24 ሰዐት ውስጥ
- 5,038 ኬዝ በአጠቃላይ
-86 ሞት
-37 ፅኑ ህመም ታማሚ
- ከ60 ሺ በላይ ሰዎች ተመርምረዋል
ኮሮና ቫይረስ ህንድ :-
- 909 አዲስ ኬዝ በ24 ሰዐት ውስጥ
- 8,356 ኬዝ በአጠቃላይ
-273 ሞት
- ከ600 መቶ ሺ ሰዎች በላይ ተመርምረዋል
@Yenetube @Fikerassefa
- 254 አዲስ ኬዝ በ24 ሰዐት ውስጥ
- 5,038 ኬዝ በአጠቃላይ
-86 ሞት
-37 ፅኑ ህመም ታማሚ
- ከ60 ሺ በላይ ሰዎች ተመርምረዋል
ኮሮና ቫይረስ ህንድ :-
- 909 አዲስ ኬዝ በ24 ሰዐት ውስጥ
- 8,356 ኬዝ በአጠቃላይ
-273 ሞት
- ከ600 መቶ ሺ ሰዎች በላይ ተመርምረዋል
@Yenetube @Fikerassefa
ፖሊስ በኮሮና ምክንያት ሥራ ካቆሙ የሺሻና የመጠጥ ቤቶች ተግዳሮት እያጋጠመው እንደሆነ አስታወቀ!
ሺሻ ሲያጨሱባቸውና ሲቅሙባቸው የነበሩ ቤቶች ከፊት ለፊቱ ‹‹ታሽጓል›› የሚል ማስጠንቀቂያ የተለጠፈባቸው ቢሆንም፣ እነሱ በኋላ በር በኩል ከፍተው በማስገባት እንዲያውም ከበፊቱ በበለጠ ብዙ ተጠቃሚዎች እንደሚስተናገዱ እንደ ተደረሰባቸው ታውቋል፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ እንደገለጹት፣ ለምሳሌ ያህል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሜሪካ ግቢ አካባቢ በሦስት የቀበሌ ቤቶች ውስጥ 431 ሰዎች ሺሻ ሲያጨሱና ጫት ሲቅሙ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው በአንድ ቤት ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች መከማቸታቸውን ነው ብለዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በአጋጣሚ በቫይረሱ የተጠቁ ቢሆኑና ወጥተው ቢበክሉ፣ ምን ያህል ወገኖች በወረርሽኙ ሊጠቁ እንደሚችሉ ለማወቅ ነብይ መሆን እንደማያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ምንም እንኳን ሰዎቹ በቁጥጥር ሥር ቢውሉም ማሰር እንደማይቻል የተናገሩት ኃላፊው፣ የንግድ ቤቶቹን ባለቤቶች ለጊዜው በማሰርና ወረርሽኙን በተመለከተ የመንግሥትን መመርያ መጣስ አግባብ እንዳልሆነ በመምከር መለቀቃቸውን አስረድተዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በሌላ ደረቅ ወንጀል የታሰሩ ግለሰቦች በመኖራቸውና መንግሥት ከእስር እየፈታ ባለበት ሁኔታ፣ እነዚህን ሰዎች ማሰሩ ተገቢ ነው የሚል እምነት ስላልነበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Via Reporter

በሩስያ በ24 ሰዓት ውስጥ 2,186 ኮቪድ19 ኬዝ እና 24 ሞት ተመዝግቧል።
በሩስያ በአጠቃላይ 15,770 ኮቪዲ19 ኬዝ እስከዛሬ 130 ሰዎች ሞተውባታል።
@Yenetube @Fikerassefa
በሩስያ በአጠቃላይ 15,770 ኮቪዲ19 ኬዝ እስከዛሬ 130 ሰዎች ሞተውባታል።
@Yenetube @Fikerassefa
የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ ሰዎች ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ዓለም እንዲሁም በኢትዮጵያ ለምትገኙና የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ዛሬ የምታከብሩ ክርስቲያኖች ሁሉ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ ብለዋል።
"በኮቪድ19 ወረርሽኝ የተነሣ በአካል መራራቅ ቢያጋጥምም፣ በመንፈስ አንድ ሆናችሁ ይህን በዓል ስታከብሩ፣ ብርታት እና መጽናናት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክታቸውን ያስተላለፉት።
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ዓለም እንዲሁም በኢትዮጵያ ለምትገኙና የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ዛሬ የምታከብሩ ክርስቲያኖች ሁሉ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ ብለዋል።
"በኮቪድ19 ወረርሽኝ የተነሣ በአካል መራራቅ ቢያጋጥምም፣ በመንፈስ አንድ ሆናችሁ ይህን በዓል ስታከብሩ፣ ብርታት እና መጽናናት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክታቸውን ያስተላለፉት።
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!
➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።
➡️13,686 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
➡️744 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።
➡️2283 ሰዎች አገግመዋል።
ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።
➡️13,686 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
➡️744 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።
➡️2283 ሰዎች አገግመዋል።
ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
የቀብሪ ደሃር የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተመረቀ!
በቀብሪ ደሃር የተገነባው የባለ 132/33 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በይፋ ተመርቆ ስራ ጀመረ።የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን የመረቁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ናቸው።
Via ETV

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በደቡብ ክልል በህዝብ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ማሻሻያ ተደረገበት።
https://telegra.ph/SNNPRs-04-12
https://telegra.ph/SNNPRs-04-12
Telegraph
SNNPRs
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በደቡብ ክልል በህዝብ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ማሻሻያ ተደረገበት!! በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልየተቋቋመው ግብረ ሀይል የህብረተሰቡን ተጋላጭነት ለመከላከል የበህዝብ…
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 286 ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 286 ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
የታማሚዎቹ ሁኔታ:-
- የመጀመሪያዋ የ24 ዓመት እድሜ ያላትና ከአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውሳኔ በፊት ከዱባይ የተመለሰች መሆኗን መግለጫው አመላክቷል።
- ሁለተኛዋም ግለሰብ የ35 ዓመት እድሜ ያላትና ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በተመሳሳይ ሁኔታ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች ናት።