YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዶ/ር ሊያ ታደሰ :-

- በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የተመረመሩ ሰዎች 3863 ሰዎች መሆናቸው መግለጫው ያመለክታል።

- በ24 ሰዐት ውስጥ 286 ሰዎች ተመርምረዋል ከዛም ውስጥ 2 ሰው በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጠዋል።

- በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው 56 ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው።

- በኮቪድ-19 ሶስት ሰዎች ሞተዋል

- ሁለት ሰዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

- አስር ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል

@Yenetube @Fikerassefa
ኬንያ ውስጥ ዛሬ ስድስት አዲስ ተጠቂና አንድ ሞት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመዝግቧል። ይህንንም ተከትሎ የሟቾች ቁጥር ስምንት ሲድርስ የተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ መቶ ዘጠና ሰባት ነው፣ ያገገሙት ደግሞ ሃያ አምስት ናቸው።

ምንጭ:MoHK
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ዙሪያ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እየሰጡት ያለውን ማብራሪያ በቀጥታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ Facebook አካውንት በመግባት ያገኛሉ።

Link ⬇️
https://www.facebook.com/liatadsmoh/

@YeneTube @Fikerassefa
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኮሮና አገግመው ከሆስፒታል ወጡ

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮና ቫይረስ ህመም አገግመው ከሆስፒታል ወጡ።

የ55 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በወረርሽኙ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ለንደን በሚገኝ ሆስፒታል ለ10 ቀናት ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተዋል።

በሆስፒታሉ ለ3 ቀናት በፅኑ ህሙማን ክፍል የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሆስፒታል ቢወጡም ከከተማ ወጣ ብለው እንደሚያገግሙ የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Via:- BBC /EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ለሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ሊገባላቸው እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ!

በኢትዮጵያ የኮሮና ህሙማንን በቅርብ ለሚከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ሊገባላቸው እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ውይይት በተለይ የኮሮና ህሙማንን በቅርበት ለሚከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ለመግባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀዋል።የሕክምና ባለሙያዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል የመኖሪያ ቤት፣ ስልጠና እና የመከላከያ አልባሳትን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚንስትሯ የገለፁት።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ:-⬆️⬆️

"ህግና ሰላም በማሰከበር ሂደት አጉል ህዘበኝነትን ለማትረፍ በሚንቀሳቀሱና መሃል ሰፋሪ በሆኑ አንዳንድ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሀይል አመራሮች ላይ መንግሰት እርምጃ እንደሚወስድ እንገልጻለን፡፡"

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የአለም የጤና ድርጅት በደቡብ ሱዳን ደቡባዊ ክፍል የብጫ ወባ መከሰቱን ይፋ አድርጓል።

ምንጭ: CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
ለምስራቁ አገሪቱ ክፍል ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በሁለት ሰዓት ልዩነት 384 ናሙና መመርመር የሚችል ላብራቶሪ ማዕከል ተመረቀ።

በሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሀረር ካምፓስ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሣሪያው በተለይ በሀረሪ ክልል እና በአካባቢው በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችን በመመርመር በውጤቱበመመስረት አፋጣኝ ላይም በአፋጣኝ የመከላከል እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዩስፍ ላብራቶሪው አገልግሎት መስጠት በጀመረበት ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ቫይሱን ለመከላከል በአካባቢው ለሚገኙ ማህበረሰብና ተቋማት በግንዛቤ የማስጨበጥ፣ የድጋፍ እና የቴክኖሎጂ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

Via Harari Communication
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል የትራንስፖርት እገዳው ማሻሻያ ተደረገበት!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በደቡብ ክልል በህዝብ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ማሻሻያ እንደተደረገበት የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።በዚህም መሰረት ከየትኛውም አካባቢ ወደ ክልል የሚንቀሳቀስ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከመጫን አቅሙ ግማሹን በመቀነስ መንቀሳቀስ እንደሚችል ገልጸዋል። እንዲሁም የከተማ አውቶብስ፣ የግል ተሸከርካሪዎች፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሸከርካሪዎችም እንዲሁ ከዚህ በፊት ከሚይዙት ተሳፋሪ በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ተወስኗል ነው ያሉት።

“የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል፣ ባለሶስት እግር ባጃጆችና የከተማ ታክሲ አገልግሎት ቀደም ሲል በክልሉ በግብረ-ሀይሉ የተላለፈው ውስኔ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚሰሩ ይሆናል” ብለዋል።መናኸሪያዎችም ተከፍተው ስራ የሚጀምሩት ለተሳፋሪው የእጅ መታጠቢያ ስፍራና አስፈላጊ ቁሳቁስ መሟላታቸው ሲረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል።በተጨማሪም መንገደኞች ወደ መናኸሪያ ሲገቡና ሲወጡ የሙቀት ልኬት ማከናወን የሚያስችል ልኬታቸው አጠራጣሪ ሲሆን ለይቶ ለማቆያ ስፍራዎች መዘጋጀት እንዳለባቸው ተገልጿል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማልያ ሁለተኛ ሞት ተመዝግቧል።

ሟቹም የhirshabella ስቴት የፍትህ ሚንስትር መሆናቸውን ከቪኦኤ ተመልክተናል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮናቫይረስ መድሃኒት ለማግኘት ምርምር ተጀመረ ማለት ለበሽታው መድሃኒት ተገኘ ማለት አይደለም - ዶክተር ሊያ ታደሰ

የኢትዮጵያን ባህላዊ ጥበብ ከሳይንስ ጋር በማጣመር ለኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) መድሃኒት ለማግኘት የተጀመረው የምርምር ስራ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ምርምሩ በርካታ ጊዜያትን ወስዶ የተለያዩ ሂደቶችን እንደሚያልፍም ነው የተገለጸው።የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከተለያዩ አካላት ለቀረቡላቸውን ጥያቄዎችና በኢትጵጵያ የኮሮናቫይረስ ምላሽ አሰጣጥን በተመለከተ በፌስቡክ ድረ-ገጻቸው በኩል መግለጫ ሰጥተዋል።ሚኒስትሯ መንግስት የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመግታትና ለመከላከል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የጤና ኤክስቴንሽንና ባለሙያዎችንና የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን በመጠቀም ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ነው የገለጹት።ከቫይረሱ ዓለም አቀፋዊ ስርጭት አንጻር ለመከላከይ የሚውሉ ግብዓቶች እጥረት መኖሩን ጠቁመው፤ ''መንግስት ችግሩን ለመፍታት ለቫይረሱ ስርጭት መከላከል የሚውሉ ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ወስኗል'' ብለዋል።
በተጨማሪም አገር ውስጥ ያለውን አቅም ቫይረሱን ለመካከለል በሚያስችሉ ግብዓት ምርቶች ላይ ለማዋል እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም።

''እጥረቱ ቢከሰትም ያለ ምንም መዘናጋት በሚገቡ ግብዓቶች ላይ ጠንካራ የጥራት ቁጥጥር ስራ ይደረጋል'' ነው ያሉት። ከዚህ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን የባህል ጥበብን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማዋሃድ ለቫይረሱ መድሃኒት ለማግኘት የተጀመረው ጥረት እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።ምርምሩ ቀደም ብሎ በኤችአይቪ/ኤድስና በሌሎች ተያያዥ በሽታዎች እንደተጀመረ ጠቁመው፤ ድንገት የኮሮናቫይረስ ከመከሰቱ ጋር ተያይዞ የቫይረሱ ሁኔታ በምርምር ስራው እንዲካተት መደረጉን አብራርተዋል።

በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖሩ የባህልና ዘመናዊ መድሃኒት ተመራማሪዎች በምርምር ስራው እየተሳተፉ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።የምርምር ስራው አንድ ደረጃ በማለፍ አሁን ላይ በእንስሳት ለመሞከር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ነገር ግን የምርምር ስራው በርካታ ጊዜያትን ወስዶ የተለያዩ ሂደቶችን እንደሚያልፍም ነው የተገለጸው።ምርምር ተጀመረ ማለት መድሃኒቱ ተገኘ ማለት አይደለም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።በኢትዮጵያ የተጀመረው ምርምር ቫይረሱን በሚለከት የተለያዩ አገሮች የሚያደርጉት ምርምር አካል መሆኑን በመጠቆም።ህብረተሰቡ ከዚህ አንጻር ያለ ምንም መዘናጋት ቫይረሱን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን እንዲተገብርም ጥሪ አቅርበዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
አራት መቶ የሚሆኑ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) በግዢ ሂደት ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ለሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ሊገባላቸው እንደሆነም ተናግረዋል።የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዙርያ እንደ አገር እየተደረገ ባለው ዝግጅት እና የምላሽ አሰጣጥ ሂደት እንዲሁም ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በፌስቡክ ድረፃገጻቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች ጨምሮ ሌሎች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ ግብአቶችን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ምን እየተሰራ ነው? የሚለው ይገኝበታል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ህብረት ቻይና በሚኖሩ አፍሪካውያን ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዳሳሰበው ገለፀ!

በቅርቡ በጉዋንግዙ የሚኖሩ አፍሪካውያን ኮሮና ቫይረስን ያዛምታሉ በሚል ከሆቴላቸው እንዲሁም ከጋራ መኖሪያ ቤቶቻቸው እንዲወጡ ተደርገዋል።የአፍሪካ ህብረት ከሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት በአፍሪካ ህብረት የቻይና አምባሳደርን አስጠርተው በአፍሪካውያን ላይ እየደረሰ ያለው ዛቻና ጥቃት እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። ሊቀ መንበሩ አክለውም በቻይና የሚገኙ አፍሪካውያን ዲፕሎማቶች የቻይና ባለስልጣናት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በጅማ ከተማ ኪቶ ፉርዲሳ የጋራ መኖርያ ቤቶች የሚኖሩ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በቀበሌዉ ለሚገኙ አረጋዉያንና የኢኮኖሚ አቅማቸዉ ዝቅተኛ ለሆኑ ነዋሪዎች የምግብ እና ቁሳቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

Via:- ELU
@Yenetube @Fikerassefa
በአውሮጳ በኮሮና ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ75,000 በላይ ሆነ። ወረርሽኙ በብርቱ ጉዳት ያደረሰባቸው አራት ሃገራት ከ80 በመቶ በላይ የሞት መጠኑን እንደሚጋሩ መረጃዎች አመልክተዋል። ጣልያን ፣ስጳኝ ፣ፈረንሳይ እና ብሪታንያ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቁ እና ከፍተኛ የሞት መጠን የተመዘገበባቸው ሃገራት መሆናቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። በአውሮጳ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ 910,000 ሰዎች በተሕዋሲው ተጠቅተዋል፤ 75,011 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ጠንቅ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአውሮጳ በወረርሽኙ በብርቱ የተጠቃችው ጣልያን 20,000 ሊደርስ ጥቂት ብቻ የቀረው ሰዎች በዚሁ በሽታ መሞታቸው ታውቋል። በስጳኝ 16,972፣ ፈረንሳይ 13,832፣ እና ብሪታንያ በ9,875 ሰዎች ሞተዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ግብፅ ባለፈው 24 ሰዓት ውስጥ 126 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂና 13 በበሽታው የሞቱ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2065 ሲደርስ 159 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።447 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ስለ ብድር ተቋማት በየኔቲዩብ በኩል በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች:

በሀገራችን ብሎም በከተማችን በርካታ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እንዚህ ተቋማት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነጋዴዎች ብድር በማበደር የንግድ ስራቸወን አንዲያጠናክሩ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንዳላቸው እሙን ነው፡፡

የኮሮና ወረርሽን በሀገራችን ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ በሽታው በሰዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት አንዳለ ሆኖ የሰዎች እንቅስቃሴ በከፊል መቋረጥ አና በሌሎች የሽታው መተላለፊያ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮች መካከለኛና አነስተኛ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ነጋዴዎቹ ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ ጋር የብድር ግንኙነት ያላቸው ነጋዴዎች በዚህ ስራቸው በተቀዛቀዘበት ወቅት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ ነጋዴዎቹን ብድራቸውን እንዲከፍሉ ከፍተኛ ተፅእኖ አና አስገዳጅ ሁኔታዎችን እየጣሉብን ነው ይላሉ ከተለያዩ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የብድር ግንኙነት ያላቸው ነጋዴዎች፡፡

ስራቸን በከፊልና በሙሉ የተቋረጠብን በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ለተበደርነው ብድር የምንከፍለው ቀርቶ እራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን የምናስተዳድርበት በቂ ገቢ እያገኘን አይደለም። ስለሆነም ይላሉ ነጋዴዎች መንግስት ችግራችንን በመረዳት ይህ ወቅት እስኪያልፍና ስራችንን እስክንጀምር ድረስ አበዳሪ ተቋማቱ የብድር መክፈያጊዜ ማራዘሚያ እንዲያደርጉልን ቢደረግ መልካም ነው ይላሉ።

@Yenetube @Fikerassefa