YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ 1200 የሚጠጉ የምግብ ባንኮች ተቋቁመዋል።

የምግብ ባንኮቹ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ችግር የሚገጥማቸው ዜጎችን ለመደገፍ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ።ኢ/ር ታከለ በመስጠት ላይ ባሉት መግለጫቸው ነዋሪዎች በየአካባቢው በተዘጋጁት የምግብ ባንኮች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ለኢትዮጵያ ገበያ ሊቀርቡ ጅቡቲ ወደብ ላይ ደርሰው ከነበሩ የምግብ ሸቀጥ እና ዘይቶች ውስጥ የጅቡቲ መንግስት የተወሰኑት እዚያው በሀገሩ ገበያ ላይ እንዲቀርቡ ማዘዙን ሸገር ኤፍ ኤም ሰምቻለው ብሏል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ የነበሩ መኮረኒ እና ፓስታ የመሳሰሉ የምግብ ሸቀጦች የጅቡቲ መንግስት የምግብ እጥረት በሀገሩ ሊኖር ይችላል በሚል እዚያው ለሽያጭ እንዲውሉ ማዘዙ ታውቋል፡፡መረጃውን ለማጣራት ሸገር በጅቡቲ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ሀላፊ የሆኑት አቶ አሊ አብደላ ጋር ደውሏል፡፡እሳቸውም ጉዳዩ በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ደረጃ ንግግር እየተደረገበት መሆኑን በመጠቆም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ምንጭ: ሸገር ኤፍ ኤም
@YeneTube @FikerAssefa
"የኮሮና ቫይረስን ለመመከት" ከ300 ሺ በላይ አባላቱን ማሰማራቱን የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
#69

4 ሰዎች ዛሬ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገው ተጨማሪ ምርመራ 345 ተመርምረው 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል።

@Yenetube @Fikerassefa
የታማሚዎቹ ሁኔታ :-

ታማሚ 1 :- እድሜ 33 : ዜግነት ኢትዮጵያ ሴት ስትሆን ከአሜሪካ የመጣች ናት በለይቶ ማቆያ ያለች

ታማሚ 2 :- እድሜ 30 : ዜግነት ኢትዮጵያ ሴት ስትሆን ከዱባይ የመጣች ናት በለይቶ ማቆያ ያለች

ታማሚ 3 :- እድሜ 29 : ዜግነት ኢትዮጵያ ወንድ ሲሆን ከዱባይ የመጣ ነው በለይቶ ማቆያ ያለች

ታማሚ 4 :-እድሜ 42 : ዜግነት ኢትዮጵያ የጉዞ ታሪክ የለውም
@Yenetube @Fikerassefa
10 ሰው አገግሟል!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ስድስት ግለሰቦች ከኮሮና ቫይረስ አገግመዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 10 ደርሷል።
@Yenetube @FikerAssefa
ሀዋሳ የሚገኘው ኬር አውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል (በአራት ኮኮብ ሆቴል) በሀዋሳ ከተማ ላይ ኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ለአንድ መቶ የህክምና ባለሙያዎች ለአንድ ወር የምሳ አገልግሎት እንደሚሰጥ እንዲሁም በሻሸመኔ ከተማ በንግድ ሱቃቸው ተከራይተው ለሚሰሩ ደንበኞች የአንድ ወር የቤት ኪራይ ነፃ ያደረጉ መሆኑን በተለይም ለየኔቲዩብ ተናግሯል።

@Yenetube @Fikerassefa
በኬንያ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ኬንያ ውስጥ ታስረው የነበሩ 19 ዜጎች ከአገሪቱ የኢሚግሬሽን ባለስልጣን ጋር በመተባብር ዛሬ ሚያዝያ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ሞያሌ አድርሷል።

ከ16-25 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ዜጎች የተያዙት ኬንያን አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲሞክሩ ያለጉዞ ሰነድ በመገኘታቸው ነው ።በኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም የፍልሰት ድርጅት (IOM) ጤንነታቸውን ጠብቆ ለቤተሰባቸው ለማብቃት የኮሮና ለይቶ መቆያ ገብተዋል።ቀደም ሲል በተመሳሳይ ለይቶ ማቆያ የነበሩ 64 ዜጎቻችን ጤናቸው ተረጋግጦ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተሸኝተዋል።

ምንጭ: በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁለተኛ ሞት ዛሬ አስተናግዳለች። የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መሰረት በ24 ሰአት ውስጥ ተጨማሪ 37 ኬዞች የተመዘገቡ ሲሆን በአጠቃላይ የተያዙት ቁጥር 187 እንደደረሰ ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የኮሮና ቫይረስን መመርመር የሚያስችል ላብራቶሪ በክልሉ ፕሬዝደንት ተመርቆ ተከፈተ።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማወስፈፀሚያ ደንብ ይፋ ሆነ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ ደንቡን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚኒስተሮች ምክር ቤት የወጣው ረቂቅ አዋጅ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅጽደቁ ይታወቃል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዋጁን ማስፈፀሚያ ደንብ አጠቃላይ ይዘት በሚመለከት ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምንጭ:ኢ.ፕ.ድ
@YeneTube @FikerAssefa
ማስፈፀሚያ ደንቡ አጠቃላይ አራት ዋና ዋና ከፍሎች ያሉት ሲሆን ይሄውም ክልከላን የሚያስቀምጥ፣ ግደታዎችን የሚጥል፣ የአስፈፃሚ አካላትን ክንውን እንዲሁም ልዩ ለዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

ክልከላን በሚመለከት:

➡️ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

➡️ከአራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን እንዳለበት አቃቤ ህጓ አብራርተዋል።

➡️ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር መኖሩን ጠቁመዋል።

➡️ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

➡️በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ መሆኑን አስረድትዋል።

➡️በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

➡️የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስውጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

➡️ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም መከልከሉን ወይዘሮ አዳነች አብራርትዋል።


➡️በዚህ ደንብ መሰረት ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

➡️ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ የህፃናትም ይሁን የሌሎች መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም የእጅ መጨባበጥ ሰላምታ የተከለከለ መሆኑን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

➡️በትራንስፖርት ዘርፍም አገር አቋራጭ ካለው ወንበር ከ50 በመቶ በላይ ተሳፋሪ መጫን የተከለከለ ነው፡፡


Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር የሚወስደዉ መንገድ ላይ የሚገኘዉ ባለ 9 ወለል ፎቅ ህንጻ ወንጌላዊት ታደሰ ህንጻ ባለቤት ወ/ሮ ገነት ታደሰ ለህንፃዉ ተከራዮች በሙሉ የአንድ ወር የቢሮ ክራይ ነፃ ማድረጋቸዉን አስታውቀዋል ፡፡

Via:- መንግስቱ ሀ/ማሪያም // Yenetube
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የምግብ አቅርቦቶችን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ለገሱ።

ባለፈው ሳምንት እያንዳንዱ ቤተሰብ ከሌላቸው ጋር “ማዕድ እንዲጋራ” ባቀረቡት ጥሪ መሠረት፣ በራሳቸው በኩል ለመስተዳድር የምግብ አቅርቦቶችን አስረክበዋል፡፡

ያስረከቡት የደረቅ ምግብ ዓይነት የከተማ መስተዳድሩ ‘እጅግ ተጋላጭ እና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች’ ብሎ ለለያቸው፣ ብዙ የቤተሰብ አባል ላሏቸው 1‚000 ቤተሰቦች የሚበቃ ነው፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ባለሀብቶች ድጋፋቸውን ቀጥለዋል !!

አቶ ጋሜ ጋቲሶ የተባሉ ባለሀብት ሀዋሳ ከተማ እምብርት ላይ የሚገኘው ህንፃቸውን ( ዳሽን ህንፃ ፊት ለፊት ላይ ) የንግድ ሱቃቸውን ተከራይተው ለሚሰሩ ድርጅቶች ከመጋቢት እስከ ግንቦት ወር ድረስ ከኪራይ ነፃ አድርገዋል።


በተጨማሪ በለሀብቱ : -

-200 ሺ ብር ለሲዳማ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል።

-100 ሺ ብር ሀዋሳ ከተማ በአስተዳደር አስረክበዋል።

- 20 ሺ ብር አዳሬ ክፍለ ከተማ በስጦታ ሰተዋል።

@Yenetube @FikerAssefa
ዋና ካምፓሱን ሀዋሳ ያደረገው ዩኒክ ስታር ኮሌጅ ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን እንዲሁም 400 ሺ ብር በስጦታ አበርክቷል።

#ዩኒክ_ስታር ኮሌጅ 4 ካንፓሶቹን ለለይቶ ማቆያ እንዲውል አድርገዋል።

ካንፓሶቹ :-

- ሱሙዳ ካምፓስ ( ሀዋሳ )

- አለታጩኮ ካምፓስ ( ጩኮ )

-በንሳ ዳዬ ካምፓስ ( በንሳ )

-ሀርቤጎና ካምፓስ ( ሀርቤጎና )

ለለይቶ ማቆያ እንዲውል ለሲዳማ ህዝብ አስተዳደርና ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አስረክቧል።

በተጨማሪም ለሲዳማ ህዝብ አስተዳደርና ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች ከ100 በላይ ታንከሮችን እና 5000 በላይ ጓንቶች ጨምሮ ህብረተሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ የሚረዱ
50,000 ፍላየሮች :
10,000 ባነሮችን እና
5,000 ስቲከሮችን አሳትመው አስረክበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪዎች ባሉበት ሆነ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበትን የትምህርት ስርዐት መዘርጋታቸውን ለየኔቲዩብ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa