YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት 81ኛ መደበኛ ስብሰባውን በቪዲዮ ኮንፍረንስ ያካሄደ ሲሆን በሁለት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

#PMOEthiopia
@Yenetube @Fikerassefa
የተለያዩ የሴራ ፅንሰሀሳብ ተንታኞች ኖቬል ኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ የአምስተኛው ትውልድ(5G) ገመድ አልባ ኔትዎርክ ነው ያስከተለው ሲሉ ሰምተው ይሆናል።

የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ(AFP) Factcheck ክፍል ግን ባለሙያዎችን አነጋግሬያለው ይህ ነገር ሀሰት ነው ብሏል።

በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዝርዝር ማስፈንጠሪያውን ከፍተው ማንበብ ይችላሉ👇👇👇

https://factcheck.afp.com/experts-dismiss-claims-5g-wireless-technology-created-novel-coronavirus?fbclid=IwAR2ivTzcC-nf2izM3Yh6gErSmVnz1XCp7MFbSnbLf5qWrOMWtERS0iFVyX4

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በባሕር ዳር የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሰኞ እንደሚጀመር የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ @Yenetube @Fikerassefa
በተጨማሪም የ #COVID19 ምርመራ ደብረ ብርሀን ላይ ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ከአማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ ትዊተር ገፅ ላይ ተመልክተናል።

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
የኮሮና ክትባት መጀመሪያ በአፍሪካ ሊሞከር ይገባል ያሉትን ፈረንሳያዊ ዶክተሮች ድሮግባና ኤቶ አወገዙ! ሁለት የፈረንሳይ ዶክተሮች በቴሌቪዥን ላይ በነበረ ውይይት የኮሮናቫይረስ የሙከራ ክትባት መጀመሪያ በአፍሪካ ሊሞከር ይገባል ማለታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘትን እያስተናገዱ ሲሆን፤ ታዋቂዎቹ አፍሪካውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ዲዲየር ድሮግባና ሳሙኤል ኤቶም የሰላ ትችታቸውን ሰንዝረዋል። "አፍሪካ መሞከሪያ…
በማህበራዊ ድረገፆች ከፍተኛ ትችት ሁለቱ የደረሰባቸው የፈረንሳይ ዶክተሮች በተወካያቸው አማካኝነት የይቅርታ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ትናንት ባቀረቡት የይቅርታ መልእክትም “ባለፈው ሳምንት ባስተላለፍኩት ሐሳብ የተጎዱትን፣ የተበሳጩትን እና እንደተሰደቡ የተሰማቸውን ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ እፈለጋለሁ” ብለዋል፡፡

@Yenetube @FikerAssefa
‘‘የኮሮና ቫይረስ ከሀገራችን ጠፋ የሚባለውን ዜና ሳልሰማ ከተከራዮቼ የቤት ኪራይ አልቀበልም፡፡’’

ወታደር ልዑል ግርማ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አዮ ጓጉሳ ወረዳ አዘና ከተማ ነዋሪው ወታደር ልዑል ግርማ 27 ዶርሞችን አከራይተው ነው የሚተዳደሩት፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን ከሰሙ በኋላ ግን የገቢ ምንጫቸው የሆኑትን 27 ዶርሞች ወረረሽኙ እስኪጠፋ ተከራዮች በነፃ እንዲኖሩበት ሰጥተዋል፡፡

‘‘በውትድርና የሀገሬን ዳር ድንበር ለ12 ዓመታት አስከብሬያለሁ፤ አሁን ግን ወታደር የማይከላከለው ወረርሽኝ መጣ፤ ስለዚህ በወር ከ8 ሺህ ብር በላይ አከራይቼ የማገኘውን የግል ቤቴን ተከራዮቼ በነፃ እንዲኖሩ ፈቅጂያለሁ’’ ብለዋል፡፡

‘‘ለእኔ በወር 1 ሺህ 258 ብር የጡረታ ስላለኝ በዚሁ እኖራለሁ፤ የኮሮና ቫይረስ ከሀገራችን ጠፋ የሚባለውን ዜና ሳልሰማ ከተከራዮቼ የቤት ኪራይ አልቀበልም’’ ብለዋል፡፡

‘‘ያደረግሁት ነገር ትንሽ ነው፤ ይልቁንስ ሌሎች አካራዮች በዚህ ጊዜ ተከራዮች ጋር በመመካከር ይህን ወረረሽኙን በጋራ መከላከል አለባቸው’’ ብለዋል፡፡

ምንጭ:- AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ያደረጉ 470 ሰዎች ነጻ መሆናቸው ተረጋገጠ!

ለቫይረሱ ተጋላጭ ተብለው ከአዲስ አበባና ከአዳማ ናሙናቸው ከተሰበሰበ 641 ሰዎች 470 ሰዎች ነጻ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት የምርመራ ሥራውን በማስፋት ከአዲስ አበባና ከአዳማ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ 641 ሰዎች ናሙና ተውስዷል።እነዚህ ሰዎች በስራ ባህሪያቸው ለቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መሆናቸውን ጠቁመው ነገር ግን በቫይረሱ የተጠረጠሩ አለመሆናቸው አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት ከኢሚግሬሽን፣ ከአየር መንገድ በተለይ የበረራ ሰራተኞች፣ ከጤና ተቋማት ሆቴሎች፣ ከአውብቶብስ ሹፌሮች፣ ከፈጣን ምላሽ ቡድን አባላት፣ ከአስጎብኚዎች፣ ከፋርማሲ ባለሙያዎችና ከሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ናሙና መወሰዱን ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ከአዲስ አበባና ከአዳማ በድምሩ 641 ሰዎች የምርመራ ናሙና የተወሰደ መሆኑን ገልጸው 444ቱ ከአዲስ አበባ 197ቱ ደግሞ ከአዳማ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከእነዚህ ውስጥ 314 ከአዲስ አበባ 156 ደግሞ ከአዳማ የተወሰዱት ናሙናዎች ምርመራቸው ተጠናቆ በድምሩ 470 ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል።171 ደግሞ ምርመራቸው በሂደት ላይ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ለኢዜአ ገልጸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
በአለም ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ60,000 በልጧል።
@Yenetube @Fikerassefa
የአየር መንገድ ሠራተኛ የመቀነስ እርምጃ ተቃውሞ ገጥሞታል!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ገቢው መቀነሱን ያስታወቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ የኮንትራት ሠራተኞችን ቀንሷል፤ የአየር መንገድ የሠራተኞች መሠረታዊ ማህበር በበኩሉ እርምጃውን ተቃውሞታል፡፡የሠራተኛ ማህበሩ ሊቀ መንበር ‹‹የአየር መንገዱን ስም አጥፍተዋል፣ ሰራተኞችን በቡድን አደራጅተዋል›› በሚል ምክንያት ከስራቸው እንደተባረሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዘገባው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው ዝርዝሩን 👇👇
https://telegra.ph/Compalints-on-Ethiopian-Airlines-04-04
የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታ

- በአሁን ሰዐት ማቆያ ያሉ ታማሚዎች :- 32

-ፅኑ ህሙማን : - 1

- ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ :- 4

-የተያዙ ሰዎች ድምር :- 38

- በበሽታው ተይዞ የሞተ :- 0

ማስታወሻ :- ሁለት ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ሌላ አራት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ዛሬ አስታወቀ። በቫይረሱ የተያዙት ግለሰቦች ሦስቱ ኬንያዊ ሲሆኑ፤ ሌላኛው ፓኪስታናዊ እንደሆነ ተነግሯል። ይህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 126 አድርሶታል። ኬንያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በወረርሽኙ የተጠረጠሩ 372 ሰዎች ላይ ምርመራ አድርጋለች።

- BBC Amharic
@Yenetube @FikerAssefa
ኩዌት የመጀመሪያ ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሞተ ተመዘገበ። የ46 አመት ጎልማሳ ሲሆን ህንዳዊ ነዋሪ መሆኑ ተነግሯል ።

@Yenetube @Fikerassefa
በባህርዳር ከተማ የሚገኘውን ኢትዮስታር ሆቴል መንግስት እንዲጠቀምበት መለገሳቸውን የሆቴሉ ባለቤት ገለጹ። 82 የምኝታ ክፍሎች ያሉት ይህ ሆቴል ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ወረርሽኙን በመከላከል ሥራ የተሰማሩ የህክምና ባለሙያዎችን ማስተናገድ ጀምሯል።

- ElU
@Yenetube @Fikerassefa
በአዲስ አበባ የቤት አከራዮች ተከራዮችን ኮሮና ቫይረስ ያስተላልፉብናል በማለት ተከራዮችን እያሰበቱ እንደሆነ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛል።

ከህክምና ባለሙያዎች የደረሰን መረጃ አለ አብራችሁን ቆዩ።

@Yenetube @FikerAssefa
መልክት ከየኔቲዩብ ለአከራዮች

የቤት አከራዮች በተለይም የህክምና ባለሙያዎችን ያከራያችሁ የቤት አከራዮች #በፍፁም_በፍፁም ተከራዮቻችሁን በሞያቸው ምክንያት ምንም መገለል ሊደርስባቸው ሰለማይገባ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠብ እና የራሳችሁን ጥንቃቄ እንድትወስዱ እናሳስባለን።

ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ የቻናላችን ቤተሰቦች በአከራዮቻቸው ከቤት እንዲቀመጡ ይባስ ብሎ የህክምና ባለሙያ መሆናቸው ካወቁ አከራዮች ቤታቸው እንዲለቁ እየተደረጉ እንደሆነ ጠቁመውናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህክምና ባለሙያዎች ላይ እንደዚህ አይነት ተግባር የሚፈፅሙ የቤት አከራዮችን መታገስ እንደሌለበት ለየኔቲዩብ ተናግረዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የጣሊያን የ24 ሰዓት ሪፖርት እንደሚያሳየው 681 ሞትና 4,805 አዲስ ተጠቂ ተመዝግቧል። ይህም አጠቃላይ የሟቾችን ቁጥር 15,362፣ የተጠቁትን ደግሞ 124,632 አድርሶታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል፣ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴዎችን ለመዝጋት (total lockdown) መንግስት አቅም እንደሌለው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጥንቃቄ በመተግበር የተጎጅዎችን ቁጥር ለመቀነስ መንግስት ይሰራል ብለዋል።ብዙ ቤት የሌላቸው እንዲሁም በየቀኑ ካልሰሩ መብላት የማይችሉ ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ መንግስት ፍላጎቶችን ለማሟላት አቅም የለውም ብለዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ምናልባት ችግሩ ከጸና በማለት ለኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ፈተና (challenge) ሰጥተዋል። አንድ ቤተሰብ ለሌላ አንድ ቤተሰብ በቀን አንድ ምግብ ለማቅረብ እንዲዘጋጅ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ፈተናውን ማዕድ ማጋራት ሲሉ ጠርተውታል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል፣ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴዎችን ለመዝጋት (total lockdown) መንግስት አቅም እንደሌለው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጥንቃቄ በመተግበር የተጎጅዎችን ቁጥር ለመቀነስ መንግስት ይሰራል ብለዋል።ብዙ ቤት የሌላቸው እንዲሁም በየቀኑ ካልሰሩ መብላት የማይችሉ ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ መንግስት ፍላጎቶችን ለማሟላት አቅም የለውም ብለዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ምናልባት…
የኮሮና ወረርሽኝ በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደ አሁኑ "ራሱን እያባዛ ከሔደ እና ወደ ማጥቃት ከተሸጋገረ አደጋው ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል" ከዓለም የጤና ድርጅት ለአፍሪካ መሪዎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገረዋል።

የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ወጣቶችም እረፍታቸውን ተጠቅመው ከዚህ ችግር እንዴት መሻገር እንደሚቻል ጥናት፣ ምርምር እና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የጥበብ ሰዎችም የኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ የተለያየ የስነ-ጥበብ ስራ በመስራት በሽታውን ለማሸነፍ የሚቻልበትን የተስፋ መንገድ እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኤርትራ ዛሬ ተጨማሪ 7 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የኤርትራ ጤና ሚንስትር ተናግሯል።

ከሰባቱ 5 ሴቶች ሲሆኑ 2 ደግሞ ወንዶች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 6 እገዳው ከመጣሉ በፊት ወደ ሀገር የገቡ የኤርትራ ዜጎች መሆናቸውም ተነግሯል።አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ብዛትም 29 ደርሷል።

Via Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
#ኤርትራ

የኮሮና ተሕዋሲ በኤርትራ እስር ቤቶች ሊያደርስ የሚችለውን ቀውስ ለመከላከል የአገሪቱ ባለሥልጣናት ሰብዓዊነት ተሰምቷቸው እስረኞችን እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ትናንት 23ኛ የልደት በዓሏን በእስር ያከበረችው ሲሐም አሊ አሕመድን ጨምሮ ንፅህናቸው ባልተጠበቀ እስር ቤቶች የታሰሩ በርካታ ኤርትራውያን በኮሮና የመያዝ ሥጋት አለባቸው ብሏል።

የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው በአገሪቱ እስካሁን 22 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።
በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮሴ ሙቼና «እንደ ሲሐም አሊ መብቶቻቸውን ተግባራዊ በማድረጋቸው የታሰሩ ዜጎችን የኤርትራ ባለሥልጣናት እንዲፈቱ የሚወተውቱ እጅግ የተጨነቁ ቤተሰቦች እና የለውጥ አራማጆችን ተቀላቅለናል» ብለዋል።
«የተጨናነቁ እና ንፅህናቸው ያልተጠበቀ የኤርትራ እስር ቤቶች ሲሐም እና ሌሎች እስረኞች በኮሮና የመያዝ ዕድላቸውን ከፍተኛ ያደርጉታል፤ ጤና እና ሕይወታቸው አደጋ ላይ ይወድቃል» ያሉት ዴፕሮሴ ሙቼና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የታሰሩ፤ ዕድሜያቸው የገፋ እና የጤና ዕክል ያለባቸውን በመልቀቅ በእስር ቤቶች ያሉ ታሳሪዎችን ቁጥር እንዲቀንሱ ጠይቀዋል።

የኮሮና ምርመራ እና ሕክምናን ጨምሮ እስረኞች እንደ ሌላው ዜጋ ሁሉ ተመሳሳይ የጤና አገልግሎት ማግኘታቸውን የኤርትራ ባለሥልጣናት እንዲያረጋግጡ አምነስቲ ጥሪ አቅርቧል።

የኮሮና ወረርሽኝ በመላው ዓለም ሲበረታ ኢትዮጵያ፣ አሜሪካ እና ሕንድን ጨምሮ በርካታ አገራት በሺሕዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ለቀዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa