YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኮሮና ቫይረስን (COVID-19) በማስመልከት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ፣ ንግድ ቢሮ እና የትራንስፖርት ቢሮ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ከንግድ ጋር በተያያዘ መግለጫ የሰጡት የንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ መሀመድ በከተማዋ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እና የአቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር የከተማ አስተዳደሩ ግብረ ሃይል አቋቁሞ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል ብለዋል። የምርት እጥረት ከተከሰተም የከተማ አስተዳደሩ ከአርሶ አደሮች ምርቶችን በመረከብ ለተጠቃሚው በቀጥታ እንደሚያቀርብ አቶ አብዱልፈታ ጨምሮ ገልጸዋል፡፡

የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ በከተማ አስተዳደሩ ተመርተው የቀረቡት 200ሺ ሊትር ሳኒታይዘሮች በከነማ የመድሃኒት መደብር ፣ በሸማቾችና በሌሎች መንገዶች ለነዋሪው እየተከፋፈለ ይገኛል ብለዋል፡፡ተጨማሪ ሳኒታይዘሮችን በመመረት ላይ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ለከነማ ፋርማሲዎች የሚከፋፈል ይሆናል።

ከትራንስፖርት ስርአቱ ጋር በተያያዘ መግለጫ የሰጡት የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አከለ መጨናነቅን ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ በርካታ አማራጮችን ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ተጨማሪ አውቶቢሶችን ወደ ስራ በማስገባት ፣ የመንግስት መኪኖች ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ እየደረገ ይገኛል።ታክሲዎች ከተፈቀደው መጠን በላይ እንዳይጭኑ ጠንካራ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን በቀጣይም ህጉን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰዱ የሚቀጥል ይሆናል። ሰልፍ ባለባቸው ቦታዎች ህብረተሰቡ ርቀቱን ጠብቆ እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርዋል፡፡የታክሲ ሹፌሮች ፣ ረዳቶችና በየአከባቢው ያሉ ተራ አስከባሪዎች ህብረተሰቡ በቂ ርቀት ጠብቆ እንዲሠለፍ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ ያቀርባል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመካላከል መንፈሳዊ ጉዞን ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጧን አስታወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መሆኑን አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ጉዞን ለአልተወሰነ ጊዜ ማቋረጧን እና ማንኛውም መንፈሳዊ ጉባኤ በጥንቃቄ እንዲካሄድ ተብሏል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል ቤተክርስቲያቱ መንፈሳዊ ጉዞን ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጧን ተናግረዋል ።

በቅዳሴ ስነ ስርዓት ላይ ምእመናኑ በማህበራዊ ርቀት ሐይማኖታዊ ስነ ስርዓት እንዲያካሂዱ እና በጉባኤ ላይም በተመሳሳይ ርቀትን በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ አሳስበዋል ።

በውጭ ዜጎች ላይ የሚካሄደው ማግለልም ተገቢ ባለመሆኑ ሊወገዝ የሚገባ ተግባር መሆኑን የተናገሩት አቡነ ዮሴፍ ምዕመናን እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይሄንን አግላይ ድርጊት እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
#ተጨማሪ_ሁለት_መቶ_ሺ_ሊትር ይከፋፈላሉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከነማ ፋርማሲዎች በምርት ላይ ያሉ ተጨማሪ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮችን እንደሚከፋፈል አስታወቀ።

በቀጣይ ቀናት ለከነማ ፋርማሲዎች የሚከፋፈለው ሳኒታይዘር ባለፈው የከተማ አስተዳደሩ ካቀረበው 200 ሺህ ሊትር ተጨማሪ እንደሆነ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ አስታውቀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የእርዳታ ጥሪ !

የእህታችንን ህይወት የጓጓችለትን ምርቃቷን ሳታይ እንዳትቀጠፍብን የተማሪነት ድርሻችንን እንወጣ።

ምርቃቷን በጉጉት የምትተብቀው ቤተልሄም ተስፋዬ ዛሬ ጥቁር አንበሳ ተኝታ እህት ወንድሞቼ ህይወቴን ታደጓት እያለች የ እርዳታ ጥሪ ታስተላልፋች። በቻልነው አቅም በየትምህርት ክፍላችን በመልቀቅ የ እህታችንን ህይወት እንታደግ።

ዛሬ ብቻ በ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ 12,921 ብር (አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ አንድ ብር) መሰብሰብ ችሏል። ቀጣይ የታሰቡ ስራዎች በመላው ኢትዮጵያ ማስታወቂያ በመስራት የእህታችንን ህይወት እንታደጋለን።

በ አጠቃላይ ለህክምናው የሚያስፈልጋት ወጪ 50,000$ በ ሃገር ደረጃ 1,645,551 ማለትም አንድ ሚሊየን ስድስት መቶ አርባ አምስት ሺ አምስት መቶ ሃምሳ አንድ ብር ነው። በምንጠቀመው ማህበራዊ ሚዲያዎች በመልቀቅ እህታችን የደረሰባትን ህመም በማስተዋወቅ እንታደጋት።

ቤቲየ ተመርቀሽ ስትስቂ እናይሻለን እሺ እህት አለም። ለወገን ደራሽ ወገን ነው።

የንግድ ባንክ አካውንት

- 1000326460568
@Yenetube @Fikerassefa
#ኢትዮ_ጁቡቲ_አካላዊ_ርቀት

ተሳፋሪዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል እንደሚገባ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለፁ::

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ተሳፋሪዎች ትኬት ሲቆረጡ፣ ሲሳፍሩም ሆነ በመቀመጫቸው ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ የተሳፋሪዎች ጥግግት እንዲቀንስ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ መግለጫ ⬆️

ከመጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:10 ሰዓት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሁሉም መንገደኞች በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀ የለይቶ ማቆያ (quarantine center) ለ14 ቀን እንዲቆዩ ይገደዳሉ።"

በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ
@YeneTube @Fikerassefa
ለእናንተ ነው ምንጮህው እንዳትሰላቹብን አሁን እባካችሁ አካላዊ መራራቅ ተግብሩ !!!

@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ልጅ አዲስ አበባ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ላይ #በማፌዝ ወይንም እውነትም ቫይረሱን #ለማሰራጨት እየሞከረ ነው #የታክሲ_በር እና #መደገፊያዎችን ቫይረሱን ለማሰራጨት ሲሞክር የሚያሳይ ቪዲዮ ነው። በሀገር ደረጃ የመጣብን ጦስ ላይ የሚቀልድ በህግ ሊቀጣ ይገባል።

ልጁን የምታውቁት ወይንም ቪዲዮውን የቀረፀውን ግለሰብ የምታውቁት አድራሻውን ላኩልን ወይንም ለአቅራቢያችን ላሉ ፓሊስ ጣቢያ አሳውቁ።

#Share አድርጉ ማንነቱ እስኪገኝ
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ፈትዋ (ሸሪኣዊ ብያኔ) ሰጠ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ አካል የሆነው የዑለማ ምክር ቤት ለሸገር በላከው መግለጫ፣ "የበሽታው ስርጭት አስጊ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ከጁምዓም ሆነ ከጀመዓ ሶላት መቅረት በሸሪኣው የተፈቀደ" መሆኑን ጠቅሶ፣ "በቤት ውስጥ መስገድ ይቻላል" ብሏል።ምክር ቤቱ በመግለጫው "በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ለጁምዓም ሆነ ለጀመዓ ሶላት፣ እንዲሁም ለሃይማኖታዊ ትምህርት ወደ መስጂድም ሆነ ሕዝብ ወደሚሰበሰብበት ቦታ መምጣት የተከለከለ ነው" ብሏል።የዑለማ ምክር ቤቱ አክሎም፣ "የጤና ጥበቃ ተቋማት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን ምክርና መመሪያ መቀበልና በሥራ ላይ ማዋል ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው" ብሏል።"የመስጂድ ኢማሞች፣ አሊሞችና ዳዒዎች ሙስሊሙ ወደ አላህ እንዲመለስና ምህረትን እንዲለምን፣ ሶደቃ እንዲሰጥና ዱዓ እንዲያደርግ እንዲመክሩ እንጠይቃለን" ብሏል።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
#FactChecking - በረራ ጣልያን አልቆመም

በነገራችን ላይ የኢትዮዽያ አየር መንገድ ወደ ጣልያን ሮም እና ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ የሚያደርጋቸውን በረራዎች አላቆመም። በአውሮዻ የተሰረዙ መዳረሻዎች 4 ብቻ ሲሆኑ ማድሪድ/ስፔን፣ ሚላኖ/ጣልያን፣ ጀኔቫ/ስዊዘርላንድ እና ማርሴ/ፈረንሳይ ብቻ ናቸው።

የሰሜን አሜሪካ፣ የቻይና እንዲሁም የላቲን አሜሪካ ከተሞች በረራቸው ያልተቋረጠ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ካቆመባቸው መዳረሻዎች ከ20 በላይ የሚሆኑት ቀድሞውኑ የተዘጉ ነበሩ።

#ElU
@YeneTube @Fikerassefa
የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ

"የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል ከመጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም ግቢዎች ( ዋናው ግቢ፣ ሽረ ግቢ፣ ጤና ሳይንስ ግቢ እና ዓድዋ ግቢ) ማንኛውም ተማሪ መግባት እና መውጣት እንደማይችል እየገለፅን የነን-ካፌ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ምግብ ቤት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በተለያየ ምክንያት ከግቢው የወጣችሁ ተማሪዎች ከመጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ግቢ መግባት እንደማይቻል አውቃችሁ በያላችሁበት እንድትቆዩ እናሳባለን ።በተጨማሪም በቫይረሱ ዙርያ በየጊዜው በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲያችን የሚሰጡ ማብራርያዎችንና መልእክቶችን እንድትከታተሉ እና በጥብቅ እንድትተገብሩ እናሳስባለን።"

-Aksum University
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ኢንስቲትዩቱ ከሆስፒታሉ ባለሙያዎች እና የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ምርምር ባለሙያዎች አጠቃላይ ኢንፍሉዌንዛን አስመልክቶ ስልጠና በመስጠት በዱብቲ ሆስፒታል የኢንፍሉዌንዛ የቅኝት ማዕከልን ሥራ አስጀመረ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የመጀመሪያ 40 ቀን የአፍሪካ እና የአውሮፓ ግራፍ ስንመለከት እንደ አውሮፓ ሁላ በአፍሪካም በፍጥነት እየተሰራጨ ይገኛል።

እባካችሁ መንግስት ቤት ተቀምጡ እስኪል አትጠብቁ !! በራሳችሁ ወስኑ !!

#JUSTSTAYHOME
@Yenetube @Fikerassefa
ታቅደው የነበሩ ሰዎች የሚበዙባቸው ስብሰባዎች በሙሉ መታገዳቸውን የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፈው መልእክት ታቅደው የነበሩ ሱባኤ፣ ስግደት፣ ጉባኤና ስልጠና እንዲሁም ብዙ ሰዎች የሚሳተፉባቸው ስብሰባዎች በሙሉ መታገዳቸውን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ጉባኤ ለእምነቱ ተከታዮች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚረዳ መልዕክት አስተላላፏል፡፡ጉባኤው ስርጭቱን ለመከላከል በዋነኝነት በዚህ በዐቢይ ፆም ሁሉም የእምነቱ ተከታይ ተግቶ መፀለይ አለበት ብሏል፡፡ከዚህ ጐን ለጐን ቁምስናዎች ተጨማሪ መመሪያ እስከሚተላለፍ ድረስ መደበኛውን የዕለት ተዕለት መስዋዕተ ቅዳሴ ውሱን ቁጥር ባላቸው ምዕመናን ተሳትፎ ብቻ መከናውን አለበት ብሏል ጉባኤው፡፡

የዕለተ ሰንበት እና የበዓላት ቅዳሴዎችን በተመለከተ በተለይ ህዝብ በሚበዛባቸው ቁምሶናዎች ከአንድ በላይ ተደጋጋሚ መስዋዕተ ቅዳሴ ወይንም ለህዝብ ተደራሽ በሆነ መልኩ ከቤተክርስቲያን ውጭ እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡እጅ ለእጅ በመጨባበጥ በመሳሳም እና በመተቃቀፍ የሚከናወኑ የሰላምታ አይነቶች እንዳይደረጉም ጉባኤው ወስኗል፡፡በፍኖተ መስቀል በአርብ ስቅለት ወይም በሌሎች መርሃ ግብሮች ላየ መስቀል የመሣለም ስርዓት እና በማናቸውም ጊዜ የካህናትን እጅ ወይንም መስቀላቸውን መሳለም ክልክል መሆኑንም ጉባኤው ገልጿል፡፡

ማናቸውም አይነት ጉንፋን ብርድ ወይም መሰል ምልክቶች የሚሰማቸው ሁሉ በራሳቸው መልካም ፈቃደ እስከሚሻላቸው ድረስ በቤታቸው እንደቆዩ እና መስዋዕተ ቅዳሜ እንዳይሳተፉ ጉባኤው መክሯል፡፡ጉባኤው ቤተሰክርስቲያኒቷ የጤና ተቋማት የሚያውጡትን መረጃ ለመተግበር ዝግጁ መሆኗንም ገልጿል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የጉንፋን እና የኮሮና ቫይረስ ልዩነቶች ⬆️

@YeneTube @Fikerassefa
የጎንደር ጉዳይ

ለፋኖ ተገቢውን ስልጠና ሰጥተን የክልሉ የፀጥታ አካል ለማድረግ እንፈልጋለን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ።

"በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ግጭት ከአርበኛ መሳፍንት ጋር ሊያያይዙት ይሞክራሉ አርበኛ መሳፍንት አማራን ይገድላል ብየ አላምንም"

ኮምሺነር አበረ አዳሙ ሙሉውን መግለጫ⬇️ https://t.co/7ZTbLEF7S3
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭትን ለመግታት የሆቴል ባለሙያዎች ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለፀ

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ የሆቴል ባለሙያዎች ማህበር የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከጤና ባለሙያዎች ባልተናነሰ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገለፀ።

የግል እና የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ሆቴሎች ዘወትር ከሚያደረጉት በተለየ ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተሻለ የፅዳት ስራዎችን መተግበር ይገባልም ተብሏል።

የሆቴል ሙያ ዘርፍ በእየለቱ ከበርካታ ሰዎች ጋር የሚያገኛኝ እንደመሆኑ መጠን የሆቴል ባለሙያዎች እራሳቸውን ከቫይረሱ እንዲጠብቁ እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚሰጣቸውን የቅድመ መከላከል ስራዎች በተገቢው መልኩ እንዲተገበሩ ነው ማህበሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa