YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦ አፍሪካ⬆️

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ የቻናላችን ቤተሰቦች ነግረውናል።

@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተጨማሪ ቪዲዮ ግርማዊነቶ 🙏

ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት 2012 በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። በነገራችን ላይ ቴዲ አፍሮ ከ15 አመታት በኃላ ነው መስቀል አደባባይ ላይ ኮንሰርት ያቀረበው።

💚💛❤️ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር 💚💛❤️

--Video መላካችሁን ቀጥሉ YeneTube--
@YeneTube @Fikerassefa
ስፖርት!

ሰለሞን ቱፋ በመጪው ክረምት በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በወርልድ ቴኳንዶ ኢትዮጵያን የሚወክልበትን ውጤት አግኝቷል።

ዛሬ አመሻሽ ላይ በተደረገ የማጣሪያ ውድድር የሴኔጋል አቻውን በብቃት አሸንፎ ነው ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በወርልድ ቴኳንዶ ኢትዮጵያን እንደሚወክል ያረጋገጠው።

ምንጭ:EOC-Tokyo 2020
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ለባህርዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ 10 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል።

ባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ዛሬ ማታ በኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ አድርጓል በቀጥታም በአማራ ቴሌቨዥን ተላልፏል።

በአጠቃላይም 45 ሚሊዮን ብር ቃል መግባቱን ተመልክተናል።
@YeneTube @Fikerassefa
‹የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ላይ ከፖለቲካ ሴራ እስከ ተዋጊ ጦር በመላክ ወደ ውጊያ እንድንገባ እየተፈታተነን ነው›› ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሕወሓት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

https://ethiopianreporter.com/article/18159
የኢራኑ ቴረሀን ዩንቨርስቲ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተማር አቁማል ምክንያተም በኢራን የኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ መጠን መስፋፋት ጋር የተያያዘ መሆኑ ተነግራል።

ስለ ኮሮና ቫይረስ ብቻ የምንዘግብበትን Special Channel ተቀላቀሉ⬇️

@Coronavirusliveupdate
@Coronavirusliveupdate

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Corona Virus Updates
Italy's prime minister announced all sports events in Lombardy and Veneto tomorrow will be cancelled.

Atalanta - Sassuolo
Hellas - Cagliari
Inter - Sampdoria Are the games affected
ጾሙ ምዕመናን ከጥላቻ፣ ፍትህን ከማጉደል፣ ከበደልና ዛቻ የሚቆጠቡበት ሊሆን ይገባል-ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

በመጪው ወርሃ ጾም ምዕመናን ከጥላቻ ፣ ፍትህን ከማጉደል፣ ሰውን ከመበደልና ከዛቻ እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳሰበች። የቤተክርስቲያኗ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ነገ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚጀመረውን የአብይ ጾም አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አልሸባብ ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ መፈፀሙን የአሜሪካ አፍሪካ ኮማንዶ አስታውቋል ።
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ዴሚክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) መንግስት በህዳሴ ግድብ ድርድሩ ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ወደ መስጠት አዝማሚያ ከሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ሊጠራ እንደሚችል አስጠንቅቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️⬆️በዛሬው እለት ሞሮጎሮ፣ ሩቩማ እንዲሁም ንጆምቤ በሚባሉ የታንዛኒያ ግዛቶች ከሚገኙ 5 እስር ቤቶች ተፈትተው 77 ዜጎቻችን ዳሬ ሰላም ከተማ ደርሰዋል። ሌሊቱን ከዳሬሰላም ተነስተው ነገ የካቲት 16 ቀን 2012 ከጠዋት በ1፡30 ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

ዘመድ እና ቤተሰቦቻቸው እንዲቀበሏቸው መረጃውን እንድናስተላልፍላቸው በጠየቁን መሰረት የስም ዝርዝራቸውን እንደሚከተለው አቅርበናል ብሏል በዳሬሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ።

#ሼር_በማድረግ_ይተባበሩ
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና

በአምቦ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመደገፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በተወረወረ ቦምቡ ጉዳት ደረሰ


ዛሬ፣ እሁድ፣ ጠዋት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና ለፓርቲያቸው ድጋፋቸውን ለመስጠት ሠልፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በተወረወረ ቦምብ ቢያንስ 29 ሠዎች መቁሰላቸውን የአምቦ ከተማ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ኃላፊው አቶ ሂንሰርሙ ደለሳ እንዳሉት ቦንቡ የተወረወረው ለድጋፍ ሰልፍ በወጡ ፈረሰኞች ላይ ነው።

ጉዳት ካጋጠማቸው መካከል የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ከሆሰፒታል የወጡ እንዳሉ ሁሉ የተለያዩ የጉዳት መጠን ያስተናገዱ መኖራቸውን አቶ ሂንሰርሙ ተናግረዋል።

ከወንጀሉ ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ኃላፊው "በጫካ ውስጥ ታጥቆ የሚንቀሳቀስው ኃይል ወንጀሉን ሳይፈፅም እንደማይቀር እንጠረጥራለን" ብለዋል።
በጥቃቱ በርካታ ፈረሶችም መጎዳታቸውን ቢቢሲ ከአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ባገኘው መረጃ ለማወቅ ችሏል።

ምንጭ:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa
14 ህገ ወጥ 14 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ በቁጥጥር ስር ዋለ!

በኢሉ አባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 14 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ፡፡የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለፁት የጦር መሳሪያው የተያዘው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አማ 21199 በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ ነው። መሳሪያዎቹ ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ተኩል አካባቢ በቡሬ ከተማ በተደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪው ውስጠኛ አካል በላሜራ በተበየደ ቦታ ውስጥ ተደብቀው ተገኝተዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቀረበ!

ትናንት በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ መላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ ላከናወኑት የፀጥታ ስራ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን አቀረበ።ሰላም ወዳዱ የከተማዋ ነዋሪ ዝግጅቱ ከመጀመሩ ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ለፀጥታ ሀይሉ ያሳየው ትብብር እጅጉን የሚያስመሰግን ነው ያለው ኮሚሽኑ በቀጣይም በከተማችን በሚደረጉ ዝግጅቶች አጋርነቱን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።ዝግጅቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራርና አባላት ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

ምንጭ:- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@YeneTube @FikerAssefa
ወልቂጤ ከተማ አንበጣ መንጋ ተከስቷል። የአካባቢው ማህበረሰብ በጥንቃቄ የአንበጣ መንጋውን የማባረር ስራ እየሰሩ ይገኛል።

@Yenetube @Fikerassefa
ቦንብን ያፈነዱት ቁጥጥር ስር ውለዋል...

ዛሬ በአምቦ ከተማ ለዶክተር አብይ አህመድና ለለውጥ አመራሩ የድጋፍ ሰልፍ ሲካሄድ የቦንድ ጥቃት ያደረሱ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ፡፡


የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ዲሪሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቦምብ ጥቃቱ የደረሰው ወደ አምቦ እየገቡ በነበሩ ፈረሰኞች ሲሆን፤ከ10 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ተጎጅዎች በአምቦ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡

ጥቃት ያደረሱት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለጹት ከንቲባው፣ጉዳዩን ፖሊስ በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን መግለጫ እንደሚሰጥበት አስታውቀዋል።
t.me/Yenetube

የከተማዋ አስተዳደርም ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው፤ ምንም እንኳን ይህ አደጋ ቢያጋጥም የድጋፍ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አመልክተዋል፡፡

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerasssefa
ዕለታዊ ዜና በዩቲዩብ ቻናላችን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለኝ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያላደረጋችህ አድርጉ ⬇️

https://www.youtube.com/channel/UCUYai_rLTnhWlfUayTOsC1Q?sub_confirmation=1
በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርሳል ተባለ!

በዘንድሮው ዓመት በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀስቅሶ የነበረውን ረብሻ ተከትሎ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች እየደረሰ መሆኑ ተጠቆመ።በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ፤ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆኖ መስራት ፈታኝ እየሆነ የመጣና በተለይም የፀጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ፕሬዚዳንቶቹ የተለያዩ ማስፈራሪያዎችና ዛቻ ስለሚደርስባቸው በስጋት ውስጥ ሆነው እየሰሩ ነው።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተማሪዎችን በሐይማኖትና በብሔር በማጋጨት የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮችን ለማጥቃት የሚደረግ ሙከራ መኖሩን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ላይም በየጊዜው ዛቻና ማስፈራሪያዎች ይደርሳል ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa